University of Gondar

University of Gondar The University of Gondar is an esteemed institution of higher learning in Ethiopia, founded in 1954.
(3)

Explore our latest issue!*************We warmly invite you to read Vol. 37, No 3 of the Disability, CBR & Inclusive Deve...
08/09/2026

Explore our latest issue!
*************
We warmly invite you to read Vol. 37, No 3 of the Disability, CBR & Inclusive Development Journal of the University of Gondar, featuring important insights and perspectives advancing disability inclusion and community-based rehabilitation.

https://dcidj.uog.edu.et/index.php/up-j-dcbrid/issue/view/64

የክሊኒካል ኦንኮሎጂ ስፔሻሊቲ ፕሮግራም ውጫዊ የሥርዓተ ትምህርት ግምገማ (External Workshop) ተካሄደ***** በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና አጠቃላይ ስፔሻላ...
07/09/2026

የክሊኒካል ኦንኮሎጂ ስፔሻሊቲ ፕሮግራም ውጫዊ የሥርዓተ ትምህርት ግምገማ (External Workshop) ተካሄደ
*****
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በውስጥ ደዌ ትምህርት ክፍል በኦንኮሎጅ ዩኒት አዘጋጅነት 'የክሊኒካል ኦንኮሎጂ ስፔሻሊቲ' ፕሮግራም ውጫዊ የሥርዓተ ትምህርት ግምገማ ጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም በሆስፒታሉ ግቢ ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጌታው ብርሃን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የሕክምና ዘርፎች በርካታ የስፔሻሊቲ እና ሰብስፔሻሊቲ ፕሮግራሞችን ማስጀመሩን ጠቅሰው በቀጣይም ተመሳሳይ የስፔሻሊቲ እና የሰብስፔሻሊቲ ፕሮግራሞችን በማስፋፋትና በማጠናከር ብቁ የጤና ባለሙያዎችን ለማፍራት ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በፕሮግራሙ የሥርዓተ ትምህርት ግምገማውን በተመለከተ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮ እና አጠ/ስፔ/ሆስፒታል በውስጥ ደዌ ትምህርት ክፍል በኦንኮሎጅ ዩኒት መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ኢዮኤል ነጋሽ እና ዶ/ር መልሰው አበጀ የመወያያ ጽሑፍ ቀርቦ የፕሮግራሙ ዓላማ፣ የትምህርት ይዘት፣ የሥልጠና አተገባበርና የተማሪዎች የሙያ ብቃት ማሳደግ የሚያስችሉ ጉዳዮች ተዳሰዋል።

በውጫዊ ገምጋሚነት ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የተገኙት ዶ/ር አብርሃም አዳሙ የክሊኒካል ኦንኮሎጂ ስፔሻሊቲ ፕሮግራሙን የሥርዓተ ትምህርት ይዘትና አፈጻጸም በተመለከተ ግምገማ አድርገዋል።

በመድረኩ ተሳታፊዎች በፕሮግራሙ የሥርዓተ ትምህርት ይዘትና አፈጻጸም ዙሪያ የተለያዩ ሀሳቦችና ግብዓቶችን አቅርበዋል። በተለይም ፕሮግራሙ ከሀገሪቱ የጤና ሥርዓት ፍላጎትና ከዘመኑ የካንሰር ሕክምና እድገቶች ጋር ተጣጥሞ እንዲቀረጽና ተማሪዎችን ለተግባር ሕክምና የሚያዘጋጅ እንዲሆን የሚያግዙ ምክረ ሀሳቦች ቀርበዋል።

በመጨረሻም በውጫዊ ገምጋሚው በኩል በቀረቡ ምልከታዎችና በተሳታፊዎች በተሰጡ ሀሳቦች መሠረት ለፕሮግራሙ የበለጠ ጥራትና ውጤታማነት ሲባል ማሻሻያዎችን ለማካተት በመስማማት የውጫዊ የሥርዓተ ትምህርት ግምገማ መርሃ ግብር ተጠናቋል።
*****
ለልህቀት እንተጋለን !
የህዝብና ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ
ጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባር በተጠናከረ መልኩ ቀጥሏል****  የጎንደር ዩኒቨርሲቲ  ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በክ...
06/09/2026

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባር በተጠናከረ መልኩ ቀጥሏል
****
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በክረምት ወቅት የሚያከናውነውን የበጎ ፈቃድና ማኅበራዊ ኃላፊነት ተግባር ከቀደሙት ዓመታት በበለጠ አጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።

የዩኒቨርሲቲው የክረምት በጎ ፈቃድ ቡድን በጎንደር ከተማ አስተዳደር መና የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መረዳጃ ማዕከል በመገኘት ለአረጋውያንና ለአዕምሮ ህሙማን የጤና ትምህርትና ምርመራ ከማድረግ ባሻገር የተለያዩ የጤና፣ የማኅበራዊና የቁሳቁስ ድጋፎችን ጳጉሜ 01/2018 ዓ.ም በአካል ተገኝቶ አስረክቧል።

በድጋፉ ሥነ-ሥርዓት ላይ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጌታው ብርሃን፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና አገልግሎትና ትምህርት ጥራት ኢኖቬሽን ኮርፖሬት ዳይሬክተር አብርሃም ታረቀኝ፣ የሕክምና አገልግሎት ኮርፖሬት ም/ዳይሬክተር ዶ/ር ምናርጓቸው አጣናውና ሌሎች የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

በዕለቱም ለአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን በበጎ ፈቃደኛ የጤና ባለሙያዎች የተለያዩ በሽታዎችን ልየታ፣ የቁስል አጠባ፣ የጤና ትምህርትና የምክር አገልግሎት በመስጠት የአረጋውያኑን የጤና ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያግዝ ተግባር አከናውነዋል።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በክረምት ወቅት የሚያከናውነው የበጎ ፈቃድ ተግባር በዚህ ብቻ ያልተወሰነ ሲሆን፣ ከ500 በላይ የአልባሳት ድጋፍ፣ የማዕድ ማጋራትና ለተማሪዎች የትምህርት አጋዥ መጽሐፍት ድጋፍም ተከናውኗል።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጌታው ብርሃን እንደገለጹት የዘንድሮው የክረምት በጎ አድራጎት ተግባር ከቀደሙት ጊዜያት በበለጠ ተጠናክሮ ቀጥሏል ያሉ ሲሆን ተግባሩ በጎንደር ከተማ አስተዳደር በሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች በቀጣይነት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ዶ/ር ጌታው አክለውም፣ የበጎ ፈቃድ ተግባራቱ ለተጠቃሚዎች አስፈላጊውን የጤናና ማኅበራዊ ድጋፍ ከማድረስ ባለፈ በዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብና በአካባቢው ማኅበረሰብ መካከል ያለውን የመተባበርና የመደጋገፍ ባህል ለማጠናከር የላቀ ሚና እንዳለውም ጠቁመዋል።

በመሆኑም የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባሩ በቀጣይም በተለያዩ የጎንደር ከተማ አካባቢዎች በማስፋፋት ተጨማሪ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እደሚሰራ ተገልጿል። በቀጣይ ቀናትም በሚኖረው የደም ልገሳ መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲያችን እና የጎንደር ከተማ ማህበረሰብ ተሳታፊ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
***
ለልህቀት እንተጋለን!
የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ
ጳጉሜን 1/2018 ዓ.ም

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የአራስ ሕፃናት ሕክምናን ለማጠናከር ከፍተኛ የሕክምና መሣሪያ ድጋፍ ተደረገ*****በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒ...
04/09/2026

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የአራስ ሕፃናት ሕክምናን ለማጠናከር ከፍተኛ የሕክምና መሣሪያ ድጋፍ ተደረገ
*****

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአራስ ሕፃናት ሕክምናን ለማጠናከር የሚያስችል ከፍተኛ የሕክምና መሣሪያ ድጋፍ ሰኔ 28/2018 ዓ.ም በሆስፒታሉ ግቢ ተካሂዷል።

በዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሉ የሕፃናት ሕክምና ክፍል፣ በተለይም የአራስ ሕፃናት ጽኑ ህክምና ክፍል (NICU)፣ የአራስ ሕፃናትን ሕይወት ለመታደግና የሕክምና አገልግሎቱን ለማጠናከር የሚያግዙ የሕክምና መሣሪያዎችን ድጋፍ አሜሪካን ሀገር ቦስተን ከሚገኘው ''Vayu Global Health Foundation'' ከተሰኘ ድርጅት የተገኙ ሲሆን ፋውንዴሽኑ በተለይም ለአራስ ሕፃናት የመተንፈሻ ድጋፍ የሚያገለግሉ *40 ''Bubble CPAP''፣ 30 ''Oxygen Blender''* እና *25 ''Patient Monitor* '' አበርክቷል ።

መሣሪያዎቹ በተለይ የመተንፈሻ ችግር ያለባቸውን አራስ ሕፃናት ለመንከባከብ፣ የኦክስጅን ድጋፍ ለመስጠትና የሕፃናትን ጤና በአስተማማኝ ሁኔታ ለመከታተል ወሳኝ ሚና ይኖራቸዋል ብለዋል ዶ/ር ጌታው ብርሃን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈጻሚ።

ከመሣሪያ ድጋፉ በተጨማሪ በ'' *Vayu Global Health Foundation Africa Team''* መሪ በአቶ ኬኔዲ ኦፖንዶ እና የ''Vayu'' ከፍተኛ የአራስ ሕፃናት ሕክምና አማካሪ በዶ/ር ኩለሄ ሐዲስ የአሰልጣኞች ስልጠና (TOT) ለጤና ባለሙያዎች መሰጠቱን የህ/ጤ/ሳ/ኮ እና አጠ/ስፔ/ሆስ የጤና ትምህርትና የህክምና አገልግሎት ኮርፖሬት ዳይሬክተር አቶ ደምስ ሙላቱ ገልጸዋል።

የዚህ ድጋፍ መሠረት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ 'ARAS Foundation እና Vayu Global Health Foundation መካከል በአራስ ሕፃናት ሕይወትን ማዳን፣ የአራስ ሕፃናትን ጤና ማሻሻልና የጤና አገልግሎት አቅምን ማጠናከር ዓላማ ያለው የትብብር ስምምነቱ ከተፈረመ ከአንድ ዓመት በኋላ መሆኑ ተገልጿል።

የ''ARAS Newborn Care'' መሥራች ዶ/ር ምሕረት ከ''Vayu Global Health Foundation'' ጋር በመተባበር ይህንን ከፍተኛ የመሣሪያ ድጋፍ በማስተባበር ጉልህ ሚናን ተጫውተዋል።

በቀጣይም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ከ Vayu Global Health Foundation እና ARAS Foundation በጋራ በምርምር፣ በአራስ ሕፃናት ሕመምና ሞት ቅነሳ፣ በአቅም ግንባታ እና በአራስ ሕፃናት የጤና አገልግሎት ማሻሻያ ላይ በትብብር ለመሥራት ስምምነት አድርገዋል።

የመሣሪያና የአቅም ግንባታ ድጋፉ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የሚሰጠውን የአራስ ሕፃናት ሕክምና አገልግሎት በማጠናከር፣ የሕፃናትን የሕይወት ዕድል ማስፋትና ጤናቸውን በማሻሻል ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል።
*****
ለልህቀት እንተጋለን !
የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ
ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም

የማርኬቲንግ ማኔጅመንት የሦስተኛ ዲግሪ (ፒ.ኤች.ዲ.) የመጨረሻ የካሪክለም ወርክ ሾፕ ግምገማ ተካሄደ፡፡**************በቀን 28/12/ 2018 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማራኪ ግቢ ...
03/09/2026

የማርኬቲንግ ማኔጅመንት የሦስተኛ ዲግሪ (ፒ.ኤች.ዲ.) የመጨረሻ የካሪክለም ወርክ ሾፕ ግምገማ ተካሄደ፡፡
**************
በቀን 28/12/ 2018 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማራኪ ግቢ ነጋድራስ አዳራሽ በቢዝነስ ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት ትምህርት ክፍል የማርኬቲንግ ማኔጅመንት የሦስተኛ ድግሪ (ፒ.ኤች.ዲ.) መስከረም 2019 ዓ.ም ለመጀመር የመጨረሻ የካሪክለም ወርክ ሾፕ ግምገማ ተካሂዷል፡፡

የእለቱን የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ የድኅረ ምረቃና ምርምር ጉዳች ምክትል ዲን ዶ/ር ይበልጣል ዋለ ናቸው፡፡ ዶ/ር ይበልጣል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመጡ የውጭ ገምጋሚዎች፣ ተሳታፊዎች፣ እና ምሁራን እንኳን ደኅና መጣችሁ ብለዋል፡፡ ዶ/ር ይበልጣል አክለውም የዚህ ፕሮግራም መከፈት አሁን በሀገሪቱ እየተነቃቃ ላለው አገር አቀፍ ዲጅታል ማርኬቲንግ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡ ፕሮግራሙም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲነት በሚያደርገው ሽግግር አንድ ተደማሪ ጉልበት ነው ብለዋል፡፡ የቀረበው ሥርዓተ ትምህርት ከዶክትሬት ፕሮግራም የሚጠበቁ መመዘኛዎችን ያሟላ፣ የማርኬቲንግ ማኔጅመንት ዘመናዊ እድገቶችን የሚያንጸባርቅ፣ ዓለም አቀፍ ተገቢነቱን የጠበቀ፣ የኢትዮጵያንና የአፍሪካን አውድ ፍላጎቶች ያሟላ እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ የዚህ ፕሮግራም ምሩቃንም ለአካዳሚያዊ ዕውቀት፣ ለፖሊሲ፣ ለንግድ እና ለማኅበረሰብ እድገት ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ ማበርከት ይችላሉ በማለት የፕሮግራሙን አስፈላጊነት አረጋግጠዋል፡፡

የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ልዩ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር መንግሥቱ ሙሉ በመክፈቻ ንግግራቸው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ልህቀቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳዳገ አሁን ከደረሰበት የምርምርና የራስ ገዝ ሽግግር ላይ ደርሷል ብለዋል፡፡ ስለሆነም የዛሬው ዓይነት ፕሮግራም መከፈት ከዩኒቨርሲቲው ግብ፣ ተልዕኮና ራእይ ጋር የሚሠምር ሲሆን የምርምር ዩኒቨርሲቲነቱ አንድ አቅም መሆን ይችላል ብለዋል፡፡ የማርኬቲንግ ማኔጅመንት አሁን ባለንበት የዲጅታል ዘመን የኢኮኖሚው የጀርባ አጥንት በመሆኑ የቢዝነስ ዕድገትን፣ ዕውቀትን፣ አዋጭ የኢኮኖሚ ልማትን የሚያረጋግጥ በመሆኑ በሦስተኛ ዲግሪ መከፈቱ አስፈላጊና ጊዜውን የዋጀ ነው ብለዋል፡፡ ዶ/ር መንግሥቱ በመጨረሻም የውጭ ገምጋሚ የሆኑት ዶክተር ጌቴ አንዱለምን፣ ዶክተር መስፍን ወርቅነህን፣ ተሳታፊዎችን፣ አዘጋጅ ኮሚቴዎችን ኮሌጁን እና ትምህርት ክፍሉን አመስግነው ፕሮግራሙን አስጀምረዋል፡፡

ዶክተር ሙሉጌታ ነጋሽ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የማርኬቲንግ ማኔጅመንት ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ሲሆኑ የካሪክለም ዝግጅት ኮሚቴ አስተባባሪ በመሆን የካሪክለሙን ረቂቅ፣ ስለ ፕሮግራሙ ራዕይ፣ ግብ፣ ዓላማ እና አስፈላጊነት ዘርዘር ያለ የጥናት ውጤት አቅርበዋል፡፡
ከዚህ በመቀጠል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮመርስ ኮሌጅ በዘርፉ የላቀ ምርምርና ጥናት ያደረጉ ተመራማሪዎች ዶ/ር ጌቴ አንዱለም እና ዶ/ር መስፍን ወርቅነህ የፕሮግራሙ መከፈት ለዩኒቨርሲቲውም፣ ለኮሌጁ እና ለትምህርት ክፍሉ የአካዳሚክ አቅሙን አንድ ደረጃ የሚያሳድግ እንደሆነ ገልጸው የወርክ ሾፑን ግምገማ አቅርበዋል፡፡ ምሁራኑ ለካሪክለሙ መዳበር ወሳኝ እና ጠቃሚ የሆኑ ምሁራዊ እሳቤዎችን ያቀረቡ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ሥነ ጽሑፋዊ አቀራረብ፣ ሥነ ዘዴ፣ ንድፈ ሃሳብ፣ ዓላማ፣ የፕሮግራም ማፕ፣ የስታፍ ቁጥርና ፕሮፋይል፣ ኅትመትን፣ ፈተናና ምዘና እና መሰል ጠቃሚ ሳይንሳዊ ሀሳቦች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ከላይ በተነሱት እና መሰል ካሪኩለሙን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከተሳታፊ ምሁራን እና ተመራማሪዎች ጥያቄዎች፣ አስተያየቶች እና ምክረ ሃሳቦች ተነስተው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡ በዚህም ለካሪክለሙ ጠቃሚ ግብዓት የተገኘ ሲሆን በመጨረሻም ዶ/ር አሉበል ወርቄ የመዝጊያ ንግግር አድርገዋል፡፡ በንግግራቸውም የዛሬው የማርኬቲንግ ማኔጅመንት የሦስተኛ ድግሪ ወርክ ሾፕ በኮሌጁ ካሉት ሦስት የፒ.ኤች.ዲ ፕሮግራሞች አራተኛ በመሆን የአካዳሚ ጉዟችን ያሳድጋል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም የውጭ ገምጋሚዎችን፣ አዘጋጅ ኮሚቴዎችን እና ተሳታፊ ምሁራንን አመስግነው የእለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል፡፡
**************
ለልህቀት እንተጋለን!
የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ
ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም

03/09/2026
ዜና እረፍት*************በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ የሶስተኛ ዲግሪ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ በአቶ ፍስሀ እሸቴ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማንን ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆ...
03/09/2026

ዜና እረፍት
*************
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ የሶስተኛ ዲግሪ ሁለተኛ ዓመት ተማሪ በአቶ ፍስሀ እሸቴ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማንን ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው መፅናናትን እንመኛለን።
*************
ለልህቀት እንተጋለን!
የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ
ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም

"ሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን  ለአንድ  ሀገር  የኢኮኖሚ  እድገት፣  የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ተወዳዳሪነትና ዘላቂ ልማት ወሳኝ መሰረቶች ናቸው።" የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ሪፈራል ሆስፒታ...
02/09/2026

"ሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ለአንድ ሀገር የኢኮኖሚ እድገት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ተወዳዳሪነትና ዘላቂ ልማት ወሳኝ መሰረቶች ናቸው።" የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ ዶ/ር ጌታው ብርሃን
********************
​የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው አውደ ጥናት ዛሬ ነሐሴ 27 /2018 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው የፕሬዝዳንት ሕንፃ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል።

​በአውደ ጥናቱ ላይ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈጻሚና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ተወካይ ዶ/ር ጌታው ብርሃንን ጨምሮ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰሮች፣ የካውንስል አባላት፣ ተመራማሪዎችና የፈጠራ ስራ ባለቤቶች ተገኝተዋል።

​መርሐ ግብሩን በንግግር የከፈቱት ዶ/ር ጌታው ብርሃን፣ ሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ለአንድ ሀገር የኢኮኖሚ እድገት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፣ ተወዳዳሪነትና ዘላቂ ልማት ወሳኝ መሰረቶች መሆናቸውን ያነሱ ሲሆን፣ ዲጅታል ሽግግርና ሥራ ፈጠራ የወጣቶችን እውቀት፣ ተሰጥኦና ፈጠራ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ገልፀዋል።

አያይዘውም የፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ትርጉም የሚገለጠው ለዲጂታል ኢኮኖሚው የሚመጥን የሰው ኃይል በማፍራትና የተማሪዎችን የፈጠራ ሀሳቦች ወደ ተግባር በመቀየር ረገድ ዩኒቨርሲቲው ድርሻውን መወጣት ሲችል እንደሆነ አስገንዝበዋል።

​አውደ ጥናቱ በብሔራዊ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን (STI) ፖሊሲና የአፈጻጸም ስትራቴጂ፣ በ"Digital 2030" ስትራቴጂ እና በስታርት አፕ አዋጅ (Startup Proclamation) ዙሪያ ግንዛቤን ለማሳደግና የትብብር እድሎችን ለማጎልበት ያለመ ነው።

​በመድረኩም ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በዶ/ር አበበ ሞላ፣ በብሔራዊ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ዙሪያ ገለፃ የቀረበ ሲሆን፣ በአቶ ታደሰ አምበሴና በዶ/ር በኩረጽዮን ዓለማየሁ በተከታታይ በኢትዮጵያ የስታርት አፕ አዋጅና በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ዙሪያ ሰፊ ገለጻ ቀርቧል።

​በተጨማሪም በዩኒቨርሲቲው የ21 ቀናት የክረምት ሥልጠና (Summer Camp) ካጠናቀቁ የፈጠራ ባለሙያዎች መካከል ወጣት ዮሐንስ ጥላሁን (በአይቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቅ) "አኳ ፍሎው" (Aqua Flow) የተሰኘ ስማርት የውኃ አስተዳደር ሥርዓት የቀረበ ሲሆን፣ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ኢኖቬሽን የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ በሆነው አምበሉ እንዳለው "Etconx AI" የተሰኘ የዲጂታል ኮንስትራክሽን አስተዳደር የፈጠራ ሥራ ቀርቧል።

​በቀረቡት መነሻ ፅሁፎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ፣ ለቀረቡ ጥያቄዎች በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አመራሮችና ባለሙያዎች ምላሽና ማብራሪያ ከተሰጠ በኋላ የክረምት ሥልጠና (Summer Camp) ለወሰዱ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

በመጨረሻም በምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት አማካሪ በዶ/ር ውለታው መኩሪያው የመዝጊያ ንግግር አውደ ጥናቱ ተጠናቋል።
*********************
ለልህቀት እንተጋለን!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
ነሀሴ 27/2018ዓ/ም

University of Gondar, ADG Engineering and Technologies, and City of Gondar Sign “Gondar Triangle Model” Tripartite MoU t...
01/09/2026

University of Gondar, ADG Engineering and Technologies, and City of Gondar Sign “Gondar Triangle Model” Tripartite MoU to Advance Innovation and Development
********************
The University of Gondar, African Development Group (ADG) Engineering and Technologies, and the City of Gondar have signed a tripartite “Gondar Triangle Model” Memorandum of Understanding (MoU) aimed at strengthening collaboration among academia, industry, and the public sector. The MoU was signed by Dr. Asrat Atsedeweyn, the former President of the University of Gondar; Eng. Aynshet Gelagay, representing ADG Engineering and Technologies; and H.E Chalachew Dagnew Kebede, the Mayor of the City of Gondar, participating as a key development and implementation partner.

The agreement, signed on July 13, 2026, establishes a framework for the three partners to work together in areas of mutual interest, including research and innovation, knowledge and technology transfer, capacity building, professional development, consultancy, and the development of practical solutions to local and national challenges.

This initiative was introduced by the former President of the University of Gondar, Dr. Asrat Atsedeweyn , and further advanced through continued discussions and collaboration under the leadership of the current President, Dr. Yechale Kebede. Building on this shared vision, the University of Gondar will contribute its academic expertise, research capacity, and human resources; ADG Engineering and Technologies will bring industry expertise, engineering knowledge, and technological solutions; while the City of Gondar will provide a vital platform for turning innovative ideas into practical solutions for urban and community development.

Through this partnership, new opportunities are also expected to be created for students, researchers, academics, engineers, professionals, and innovators through joint projects, practical training, knowledge exchange, technology-based initiatives, and professional mobility.

Importantly, this tripartite partnership seeks to bridge the gap between knowledge generation, technological innovation, and practical implementation. By bringing academia, industry, and government together, the initiative can help connect research findings and engineering expertise with practical development priorities and tangible benefits for the community.
The partnership also aligns with broader efforts to advance science, technology, engineering, and innovation (STI) and promote sustainable, knowledge-based development.

The signing of the “Gondar Triangle Model” MoU marks more than the beginning of institutional cooperation. It represents a strategic partnership connecting the University of Gondar’s academic and research capacity, ADG Engineering and Technologies’ technical product development and deployment expertise, and the City of Gondar’s development priorities toward fostering innovation and creating meaningful real-world impact.

The University of Gondar, ADG Engineering and Technologies, and the City of Gondar look forward to transforming this strategic partnership into concrete projects, innovative solutions, and sustainable development outcomes that will benefit Gondar and beyond.
******************
Devoted to Excellence!
Public Relations and Communications Executive
September 1, 2026

University of Gondar Delegation Participates in Sustainable Watershed and Resource Management Workshop in Austria*******...
31/08/2026

University of Gondar Delegation Participates in Sustainable Watershed and Resource Management Workshop in Austria
***************
A delegation from the Institute of Technology at the University of Gondar has concluded a two-week scientific workshop at BOKU University in Vienna, Austria. The workshop, which ran from August 3 to August 14, 2026, marks a significant milestone in international academic collaboration for sustainable resource management.

The session is a core component of the SWARM2 project (Sustainable Watershed and Resources Management through shared local wisdom, Advanced Research and Mobility).

Financed by the Austrian OeAD, SWARM2 operates as a joint initiative between BOKU University and the University of Gondar to address critical environmental and water challenges.

This follow-up meeting builds on the momentum of the project's initial kickoff workshop held in April 2026 at the ILRI campus and Capital Hotel in Addis Ababa, Ethiopia. During the April sessions, the joint team laid the groundwork for their collaboration by designing research blueprints, planning joint fieldwork campaigns, meeting with Austrian Development Agency (ADA) representatives, and establishing concrete protocols for soil and water sampling in the Ribb watershed.

While the first workshop focused on logistical planning, the recent two-week event in Vienna centered on deep scientific integration. The Ethiopian delegation engaged directly with BOKU University research partners, evaluated advanced scientific facilities, and accelerated joint research frameworks. The team toured BOKU’s international relations office, the Cluster for Development Research, the hydraulic lab infrastructure, the forest research station, and the specialized erosion research station.

In a practical boost to the partnership's research capabilities, BOKU University has temporarily transferred a specialized scientific instrument to the University of Gondar. The device is designated for exclusive, time-limited use within the technology institute's experimental framework to monitor chlorine concentration in potable water.

The international initiative is organized under the joint leadership of Ass. Prof. Dipl.-Ing. Dr. Stefan Strohmeier from BOKU’s Institute of Soil Physics and Rural Water Management (SoPhy), and Dr. Abebe Worku Mekonnen, Assistant Professor of Civil Engineering and Scientific Director of the Technology Institute at the University of Gondar.
***************
Devoted to Excellence!
Public Relations and Communications Executive
August 31, 2026

Address

Maraki Street
Gondar

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 17:00
Sunday 08:00 - 17:00

Telephone

+251581141232

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when University of Gondar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to University of Gondar:

Shortcuts

Share