19/09/2026
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር በመጠቀም ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቋረጡ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።
በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ በጎ ፈቃደኞች ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር በማዋል ባደረጉት እንቅስቃሴ 514 ሺህ 905 ብር በመሰብሰብ 600 ደርዘን ደብተር እና 48 ፓኮ እስክሪብቶ በመግዛት ለተማሪዎች ማስረከባቸውን አስተባባሪዎቹ ገልፀዋል።
በርክክቡ ወቅት የተገኙት የታች አርማጭሆ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አስማረ የኋላሸት እንደገለፁት፤ ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር በማዋል የትምህርት ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ የተሰራው ስራ አበረታች ነው።
አክለውም የወላጅ አልባ ቤተሰብ ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳያቋርጡ ይህን በጎ ተግባር ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።
በቁሳቁስ እርክክቡ ወቅት የወረዳው አመራሮች፣ የትምህርት ጽህፈት ቤት አካላት እና የበጎ ፈቃድ አስተባባሪዎች ተገኝተዋል።