Fasiledes 2 General Secondary School ፋሲለደስ II አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • Fasiledes 2 General Secondary School ፋሲለደስ II አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

Fasiledes 2 General Secondary School ፋሲለደስ II አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ልዩ ልዩ ትምህርታዊ መረጃዎች ይቀርባሉ።

16/03/2026
22/12/2025
🎉🎉🎉🌼🌼🌼As Ethiopia enters the New Year 2018, we celebrate more than a calendar shift; we mark the completion of the Grand...
09/09/2025

🎉🎉🎉🌼🌼🌼
As Ethiopia enters the New Year 2018, we celebrate more than a calendar shift; we mark the completion of the Grand Ethiopian Renaissance Dam, a dream realized through 14 years of unwavering dedication.

GERD is not just a dam; it’s a symbol of unity, sovereignty, and resilience. Built by the hands of Ethiopians, it stands as proof that progress is possible when we believe in ourselves.

May this New Year be powered by GERD’s light energizing our homes, lifting our hopes, and reminding us that no dream is too distant when we stand together.
🌼🌼🌼🎉🎉🎉

13/05/2025

በ2017ዓ/ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁ ተማሪዎች💫✨

መምህራን በትምህርት ቤቶች ሰላምን  መስበክ ይገባቸዋል።በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የሚገኙ የመንግሥት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን፣ የትምህርት መሪዎች እና የአሥተዳደር ሠራተኞች...
13/05/2025

መምህራን በትምህርት ቤቶች ሰላምን መስበክ ይገባቸዋል።

በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የሚገኙ የመንግሥት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን፣ የትምህርት መሪዎች እና የአሥተዳደር ሠራተኞች "የጥፋት እጆች እና መዘዞቹ" በሚል መሪ መልዕክት እየተወያዩ ነው።

በውይይቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ከፖለቲካ ንክኪ ነጻ የኾኑ ዕውቀት መጋቢ መምህራን እና ተማሪዎች በጥፋት ኀይሎች ታፍነው ተወስደዋል፤ ቆስለዋል፤ ተገድለዋልም ብለዋል።

የጥፋት ኀይሎች በእኩይ ምግባራቸው የአማራን ሕዝብ ወደ ቁልቁለት ጉዞ መርተውታል ያሉት አቶ ጎሹ አሁን ደግሞ ከአማራ ሕዝብ የውስጥም የውጭም ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር ለተጨማሪ ጥፋት እየተሯሯጡ ይገኛሉ ነው ያሉት።

ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አክለውም መምህራን እና የአሥተዳደር ሠራተኞች ለሰላም ዘብ በመቆም ስለሰላም የመስበክ እና ሀገርን የማስቀጠል ታሪካዊ ብሎም ሙያዊ ኀላፊነት አለባቸው ነው ያሉት።

የጥፋት ኀይሎች ከባዕዳን የአማራ ሕዝብ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር አማራን ለማጎሳቆል ብሎም ለማጥፋት የሚያደርጉትን ደባ መምህራን አጥብቀው በማውገዝ መቃወም አለባቸው ብለዋል።

ከተማ አሥተዳደሩ በአንድ እጁ ሰላምን እያሰፈነ እና እያጸና በሌላ እጁ ልማትን በማሳለጥ ባሕር ዳር ከተማ ለነዋሪዎቿ የተመቸች፣ ለጎብኝዎች የምትመረጥ ብሎም በአፍሪካ ተመርጣ የምትጎበኝ ውብ ከተማ ለማድረግ እየተጋ ስለመኾኑም አስገንዝበዋል።

እንደማሳያ በኮሪደር ልማት አበረታች ውጤት ተመዝግቧልም ነው ያሉት።

የከተማ አሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ሙሉዓለም አቤ (ዶ.ር) የጥፋት ኀይሎች በትምህርት ቤቶች ቅጥር ግቢ ቦንብ በማፈንዳት መማር ማስተማሩ እንዲስተጓጎል እድርገው እንደነበርም አስታውሰዋል።

ይሁን እና ትምህርት ከየትኛውም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ነጻ በመኾኑ የጥፋት ኀይሎችን እኩይ ምግባር መምህራን ማውገዝ አለባቸው ነው ያሉት።

በውይይቱ ከፍተኛ የክልሉ እና የከተማ አሥተዳደሩ መሪዎች ተገኝተዋል።

ግንቦት 5/2017

አሚኮ

የ2017 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ  (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት መርሃ ግብር ተገለጸ፡፡ፈተናው ከሰኔ 23/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8/2017...
10/05/2025

የ2017 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት መርሃ ግብር ተገለጸ፡፡

ፈተናው ከሰኔ 23/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም የሚሰጥ ሲሆን በወረቀት የሚፈተኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 21 እና 22/2017 ዓ/ም እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 29 እና 30/2017 ዓ/ም ወደ ሚፈተኑበት ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ይሆናል፡፡ በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተፈታኞች ከመኖሪያ ቤታቸው በየቀኑ እየተመላለሱ በተመደቡበት መፈተኛ ማዕከል የሚፈተኑ ሲሆን ዝርዝር መርሃ ግብሩ በሚከተለው ሠንጠረዥ ተገልጿል፡፡

የፈተናው ይዘት በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያተኮረ በመሆኑ እያንዳንዱ ተፈታኝ በትምህርት ቤቱ የተማረበትን የተማሪ መጽሐፍ መሠረት አድርጎ ተገቢ የሆኑ አጋዥ መጽሐፍትን ለበለጠ እውቀትና መረዳት በመጠቀም እንዲዘጋጅ እናበረታታለን፡፡ በፈተና ወቅት ለፈተና ስርቆትና ኩረጃ የሚውሉ ማንኛውንም ቁሳቁሶች መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ ዝርዝሩ በቀጣይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ግንቦት 01/2017 ዓ/ም

Address

Kebele 15
Gondar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fasiledes 2 General Secondary School ፋሲለደስ II አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category