Gondar College of Teacher Education - ጎንደር መምህራን ኮሌጅ

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • Gondar College of Teacher Education - ጎንደር መምህራን ኮሌጅ

Gondar College of Teacher Education - ጎንደር መምህራን ኮሌጅ Gondar College of Teachers’ Education (GCTE) was first established as Teachers’ Training Institu

የክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና ለሚወስዱ መርሱ ቅድመ ኦረንቴሽን ተሰጠ!በጎንደር ቀጠና ለሚገኙ ር/መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች እና መምህራን ለሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና በጎንደር ከተማ ቅ...
31/07/2026

የክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና ለሚወስዱ መርሱ ቅድመ ኦረንቴሽን ተሰጠ!
በጎንደር ቀጠና ለሚገኙ ር/መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች እና መምህራን ለሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና በጎንደር ከተማ ቅድመ አረንቴሽን የተሰጠ ሲሆን በዚህ መድረክ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ክንዱ ዘውዱ እና የጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ዲን አቶ የሻምበል ፀሀይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል::
በዚህ የአቅም ግንባታ ስልጠና ከ 2ሺ በላይ ሰልጣኞች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል:: የተሳታፊዎች የቆይታ ጊዜም እስከ 15 ቀን እንደሚሆን ይታወቃል።
በመክፈቻ ንግግሩ ላይ አቶ ክንዱ ዘውዱ እንደተናገሩት የክልሉ መንግስት እና ትምህርት ቢሮ ለመርሱ አቅም ግንባታ በዚህ ልክ ለተግባሩ ትኩረት መሰጠቱን ብሎም ለስልጠናው ከፍተኛ በጀት በመመደቡ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል:: በተጨማሪም ከባለፈው ዓመት አፈፃፀም በመነሳት አጭር ማብራሪያ አቅርበው በጥንካሬ የነበሩትን ለማስቀጠል እና በእጥረት የነበሩ ጉዳዮችን እንዲስተካከሉ አሳስበዋል።
የጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ዲን አቶ የሻምበል ፀሐይ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን አጠቃላይ በስልጠናው ቴክኒካል ጉዳዮች ዙሪያ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል::
በመጨረሻም ሁሉም ስልጣኝ በየማዕከሉ ስርዓትን ጠብቀው ዋናውን ኦረንቴሽን እና ስልጠናውን እንዲከታተሉ ብሎም ቆይታቸው መልካም እንዲሆን ገልፀዋል::

15/07/2026

NEWS

12/07/2026

GFGFG

12/07/2026
12/07/2026
12/07/2026
ኦሳድ OSSHD ለጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ድጋፍ አደረገ/////////////*******/////////////በማኅበራዊ አገልግሎት፣ ጤናና ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠረው ኦሳድ ከ...
04/07/2026

ኦሳድ OSSHD ለጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ድጋፍ አደረገ
/////////////*******/////////////
በማኅበራዊ አገልግሎት፣ ጤናና ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠረው ኦሳድ ከ386,780.00 ብር የሚያወጣ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ለኮሌጁ 500 ሴት ተማሪዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡
ይህ መንግስታዊ ያልሆነው ድርጅት ለአንድ ተማሪ አንድ ቅባትና ሳሙና እንዲሁም ሦስት ሞዴስ ድጋፍ አድርጓል፡፡ በአጠቃላይ
ሳሙና - 10 ካርቶን በፍሬ 500
ቅባት - 10 ካርቶን በፍሬ 500
ሞዴስ - 62 ካርቶን በፍሬ 1500 የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በዛሬው ዕለት በ26/10/2018 ዓ.ም የኦሳድና የኮሌጁ ተወካዮች በተገኙበት የርክክብ መርሀግብሩ ተከናውኗል፡፡
በርክክብ መረሀግብሩ ላይ የተገኙት የኮሌጁ አካዳሚክ ዲን ዶር. አግማስ አማረ ኦሳድ ለሴት ተማሪዎቻችን ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በቀጣይም በጋራ ለመሥራት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎች በበኩላቸው ኮሌጅ ያለበንን ችግር ተመልክቷ መንግስታዊ ካልሆነው ድርጅት ጋር መልካም ግንኑነት በመፍጠር እገዛ እንዲደረግልን በማድረጉ ሊመሰገን ይገባል በማለት ሐሳባቸውን ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም ኦሳድ ዛሬ ያደረገውን ድጋፍ ወደፊትም እንዲቀጥልበት አሳስበዋል፡፡
“ለትምህርት ጥራት በትጋት እንሰራለን”

Address

Gondar

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 12:00
Sunday 08:00 - 12:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gondar College of Teacher Education - ጎንደር መምህራን ኮሌጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Gondar College of Teacher Education - ጎንደር መምህራን ኮሌጅ:

Shortcuts

Share

Category