Soro Woreda Education Office -Gimbichu

Soro Woreda Education Office -Gimbichu Soro woreda have 6 secondary schools and 39 primery schools

26/01/2023

Educational Assessment and Examinations Services (EAES) among others has a powers and duties of preparing country wide national examinations based on the country's education curriculum and training policy, Administer and ensure the confidentiality and safety of national exams, Establish and administ...

19/12/2022
15/12/2022

ማስታወቂያ !

ሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና ከታህሳስ 18 እስከ 21/2015 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል፡፡ ስለሆነም ተፈታኞች ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡

የሚፈተኑ ተፈታኞች ከሁሉም ክልል ሲሆኑ እነርሱም፡-
1.የመጀመሪያ ዙር ፈተናን በወሊድ ወይም በእርግዝና ምክንያት ተንቀሳቅሰው ለመፈተን
ያልቻሉ
2. በህግ ጥላ ስር ወይም በማረሚያ ቤት ሆነው በነበረው መፈተኛ ሁኔታ ለመፈተን ያልቻሉ
3. የሀገር መከላከያ ሠራዊት ወይም የፌዴራል ፖሊስ ወይም የክልል ልዩ ኃይል አባል ሆነው
በወቅቱ በግዳጅ ላይ በመሆናቸው ያልተፈተኑ
4. በህመም ወይም ተቀባይነት ባገኘና ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ፈተና ያልተፈተኑ
5. ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው የድልድይ መደርመስ አደጋ ምክንያት ያልተፈተኑ
6. በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ምክንያት አንድ ፈተና እንዲፈተኑ የተወሰነላቸው
7. ተቀባይነት ባገኙ ችግሮች ምክንያት እንዲፈተኑ የተወሰነላቸው

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

14/12/2022
06/12/2022
15/11/2022

"በቀጣይ ዓመታት የመንግስት ትኩረት ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ያሉ ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋት ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ህዳር 6/2015 ዓ.ም ሀዋሳ

በቀጣይ አመታት የመንግስት ትኩረት ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ያሉ ትምህርት ቤቶችን ማስፋት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ገለጹ።

ላለፉት 4 ዓመታት አንድም ዩኒቨርስቲ እንዳልተከፈተ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥም መንግስት አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች የመክፈት ዕቅድ እንደሌለው ገልጸዋል፡፡
በሚቀጥሉት ዓመታት የመንግስት ትኩረት በቅድመ መደበኛ (መዋዕለ ህጻናት) ፣የመጀመሪያ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤቶች ላይ አስተማማኝ መሰረት መጣል እንደሚሆን አብራርተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዩኒቨርስቲዎች በሚጠበቅባቸው ደረጃ ማደግ እና ራሳቸውን ወደ ማስተዳደር መሸጋገር እንዳለባቸው ጠቅሰው፤ ይህንን የጀመሩ ስለመኖራቸውም አንስተዋል፡፡ ጥራት ያለው ትምህርት በዩኒቨርስቲዎች መጀመር እንዳለበት የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ከዩኒቨርስቲዎች ተመርቀው የሚወጡ ዜጎችም ችግር ፈቺ መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

በትምህርቱ ዘርፍ የተጠቀሱት መሰረታዊ ጉዳዮች ሲሟሉ ትክክለኛ የዩኒቨርስቲ ጥያቄ ያለባቸው አካባቢዎች ወደፊት ምላሽ እንደሚያገኙ ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ፡- ትምህርት ሚኒስቴር

የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

15/11/2022
04/10/2022
03/10/2022

Address

Shewa
Gimbichu

Telephone

+251910091875

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Soro Woreda Education Office -Gimbichu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category