የጊምቢቹ የቀድሞ ተማሪዎችና መምህራን ትዝታዎች

  • Home
  • Ethiopia
  • Gimbichu
  • የጊምቢቹ የቀድሞ ተማሪዎችና መምህራን ትዝታዎች

የጊምቢቹ የቀድሞ ተማሪዎችና መምህራን ትዝታዎች Gimbichu Administration

በማቀዝቀዣ (ፍሪጅ) ውስጥ ፈጽሞ መቀመጥ የሌለባቸው ምግቦች  የትኞቹ ናቸዉ?AMN- ጥር 5/2018 ዓ.ምማቀዝቀዣ (ፍሪጅ) ምግብ ትኩስነቱን እንደያዘ ሳይበላሽ ለማቆየት የሚያገለግል ዘመናዊ ...
13/01/2026

በማቀዝቀዣ (ፍሪጅ) ውስጥ ፈጽሞ መቀመጥ የሌለባቸው ምግቦች የትኞቹ ናቸዉ?

AMN- ጥር 5/2018 ዓ.ም

ማቀዝቀዣ (ፍሪጅ) ምግብ ትኩስነቱን እንደያዘ ሳይበላሽ ለማቆየት የሚያገለግል ዘመናዊ የምግብ ማስቀመጫ ዋና መሳሪያ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡

ዝቅተኛ የሙቀት መጠን፣ ምግቦች ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲቆዩ እንደሚያደርግ የተደረጉ ሙከራዎችም ያረጋግጣሉ፡፡

ነገር ግን ሁሉም ምግቦች ማቀዝቀዣ ውስጥ እንዲቀመጡ ይመከራል ማለት ሳይሆን፣ ከተፈጥሯዊ ባህሪያቸው የተነሳ አንዳንድ ምግቦች ማቀዝቀዣ ውስጥ ሲቀመጡ ቅርፃቸውን፣ ጣዕማቸውን እና የምግብነት ይዘታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ የታይምስ ኦፍ ኢንዲያ እና ሌሎች የጤና መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በእነዚህ የጤና መረጃዎች መሠረትም፣ በፍሪጅ ውስጥ ፈጽሞ መቀመጥ ከሌለባቸው ምግቦች መካከል የተወሰኑትን ከነምክንያቶቻቸው እንደሚከተለው እንመለከታለን፡-

ቲማቲም (Tomatoes): በፍሪጅ ውስጥ ሲቀመጥ የቲማቲም ተፈጥሯዊ ጣዕምና መዓዛ ይጠፋል። ቅዝቃዜው በውስጡ ያሉትን ኢንዛይሞች ስለሚጎዳ ቲማቲሙ እንዲለሰልስና እንዲላላ (mushy) ያደርገዋል።

ድንች (Potatoes): ቅዝቃዜው በድንች ውስጥ ያለውን ስታርች (starch) ወደ ስኳር ይቀይረዋል። ይህ ደግሞ ድንቹ ሲበስል ጣዕሙ እንዲቀየርና እንዲጠቁር ያደርጋል። በተጨማሪም ለጤና ጎጂ የሆኑ ኬሚካሎች እንዲፈጠሩ ሊያደርግ ይችላል።

ቀይ ሽንኩርት (Onions): ሽንኩርት በፍሪጅ ውስጥ ባለው እርጥበት ምክንያት ቶሎ እንዲበሰብስና ሻጋታ እንዲይዘው ያደርጋል። ሽንኩርት አየር በሚያገኝበት ደረቅ ቦታ መቀመጥ አለበት።

ነጭ ሽንኩርት (Garlic): በፍሪጅ ውስጥ ሲቀመጥ የመብቀል (sprout) እድሉ ከፍተኛ ነው። እንዲሁም እንዲለሰልስና እንዲሻግት ያደርገዋል።

ዳቦ (Bread): ብዙ ሰው ዳቦ ቶሎ እንዳይበላሽ ፍሪጅ ውስጥ ያደርጋል፤ ነገር ግን ቅዝቃዜው ዳቦው ቶሎ እንዲደርቅና ጣዕሙን እንዲያጣ ያደርገዋል።

በሶቢላ (Basil): ይህ ቅመም (ቅጠል) በፍሪጅ ውስጥ ሲቀመጥ ቶሎ ይጠወልጋል እንዲሁም በዙሪያው ያሉትን ሌሎች ምግቦች ሽታ የመምጠጥ ባሕርይ አለው። በውኃ የተሞላ ብርጭቆ ውስጥ አድርጎ ውጭ ማስቀመጥ ይመረጣል።

ማር (Honey): ማር በፍሪጅ ውስጥ ሲቀመጥ እንዲረጋና እንዲጠነክር ያደርገዋል። ማር ለረጅም ጊዜ ሳይበላሽ ስለሚቆይ በቤት ሙቀት ውስጥ ማስቀመጥ በቂ መሆኑን መረጃዎቹ ይጠቁማሉ።

በመሆኑም እነዚህ ምግቦች በፍሪጅ ውስጥ ከመቀመጥ ይልቅ አየር በሚያገኙበትና ደረቅ በሆነ የክፍል ሙቀት ውስጥ ቢቀመጡ ለረጅም ጊዜ ትኩስነታቸውንና ጣዕማቸውን ጠብቀው መቆየት ይችላሉ።

AMN

ዜና ሹመትበማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን የሶሮ ወረዳ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥቷል።  1 - አቶ ፈይሳ ኤርቲሮ - የሶሮ ወረ...
12/01/2026

ዜና ሹመት

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን የሶሮ ወረዳ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥቷል።

1 - አቶ ፈይሳ ኤርቲሮ - የሶሮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ

2 - አቶ ሲዳሞ ዱናዕሎ - የሶሮ ወረዳ ምክትል አስተዳዳና ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ

3 - አቶ ግርማ ዮሐንስ - የሶሮ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪና ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ

4 - አቶ ዘለቀ ለንደቦ - የሶሮ ወረዳ ብልጽግና ጽ/ቤት ረዳት የመንግስት ተጠሪ እና ፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ

5 - ወ/ሮ ብዙነሽ ታደለ - የሶሮ ወረዳ ረዳት የመንግስት ተጠሪ እና አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ

ሆነው ተሹመዋል።

🛑 "ትዳር ጦርነት ነው!" ... ታዲያ እንዴት እናሸንፍ?   | ​አንድ ጸሐፊ "ትዳር ጦርነት ነው!" ይላል። ይህ አባባል ከመሬት አልተነሳም፤ ትዳር ውስጥ የሚፈጠሩ ግጭቶች ካልተያዙ ወደ ከ...
12/01/2026

🛑 "ትዳር ጦርነት ነው!" ... ታዲያ እንዴት እናሸንፍ?

| ​አንድ ጸሐፊ "ትዳር ጦርነት ነው!" ይላል። ይህ አባባል ከመሬት አልተነሳም፤ ትዳር ውስጥ የሚፈጠሩ ግጭቶች ካልተያዙ ወደ ከባድ ቀውስ ሊያመሩ ይችላሉ።

​ጸሐፊው ዳዊት ይዘንጋው (ዳይተም) ትዳርዎ ወደ ጦርነት እንዳያመራ ከብዙ በጥቂቱ የሚከተሉትን 7 "የጦርነት ቀጠናዎች" በጥንቃቄ እንድትይዙ ይመክራል፦

​1️⃣ የቤት ውስጥ ስራ (የመጀመሪያው አብሪ ጥይት):

የቤት ውስጥ ስራ አሰልቺ ነው። እርስ በርስ ካልተጋገዛችሁ የመጀመሪያው ተኩስ ይከፈታል። በአቅምዎ ይርዱ!

​2️⃣ ክብር (ከባድ መሳሪያ):

ግጭት ሲኖር ከመጮኽ ይልቅ መደማመጥ ይቅደም። ያለበለዚያ አክብሮት ሲጠፋ "ከባድ መሳሪያ" ይተኮስቦታል!

​3️⃣ አለማመስገን (የተቀበረ ፈንጂ):

ለትንሽም ለትልቅም ነገር አድናቆት ይኑርዎት። ምስጋና የሌለው ቤት ውስጥ አንድ ቀን የሚፈነዳ "ፈንጂ" እንደተቀበረ ይቁጠሩት።

​4️⃣ ገንዘብ (ባለስቲክ ሚሳኤል):

ስለ ወጪ እና ገቢ በግልፅ ተነጋገሩ፤ በጋራ አስተዳድሩ። ያለበለዚያ የገንዘብ አለመግባባት እንደ "ባለስቲክ ሚሳኤል" ቤቱን ሊያናጋው ይችላል።

​5️⃣ መቀራረብ እና ወሲብ (ሽምቅ ውጊያ):

ስሜታዊ ቅርበት ማጣት እና የፍላጎት አለመጣጣም ከባድ የጦርነት መነሻ ነው። ለመጣጣም ሞክሩ፤ አለበለዚያ "ሽምቅ ውጊያውን" አይችሉትም።

​6️⃣ ልጆች (ድሮን):
"ልጅ ደረሰ ቤት ፈረሰ" እንዳይሆን፤ የልጆችን ጉዳይ በጋራ እና ያለአድልዎ ይወስኑ። ያለበለዚያ ልጆችዎ "ድሮን" ይሆኑቦታል።

​7️⃣ የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት (የእርስ በርስ ጦርነት):
ለዘመድ እና ለቤተሰብ ጣልቃ ገብነት ድንበር ያብጁ። ካልሆነ "የእርስ በርስ ጦርነት" ይቀሰቀሳል።

​🕊 መልዕክት:
ወደ ጦርነት እንዳይገቡ ተግተው ይጸልዩ። ፍቅር ካለዎት አሸናፊ ነዎት!

ዳዊት ይዘንጋው /ዳይተም/

የፍቅር ጥግ ማሳያዎችመንታዎቹ!ብሩህ ቀን ተመኘን!
10/01/2026

የፍቅር ጥግ ማሳያዎች

መንታዎቹ!

ብሩህ ቀን ተመኘን!

ወ/ሮ አረጋሽ ካሣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስማት የተሳናቸው ስፖርት ፌዴሬሽን ፕረዚዳንት በመሆን ተመርጣለች ።መልካም የስራ ዘመን ይሁንልሽ በርቺ!
09/01/2026

ወ/ሮ አረጋሽ ካሣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስማት የተሳናቸው ስፖርት ፌዴሬሽን ፕረዚዳንት በመሆን ተመርጣለች ።

መልካም የስራ ዘመን ይሁንልሽ በርቺ!

💍 በጭራሽ እንዳያገቡ! (ቢያንስ እነዚህን ሳያሟሉ)(በዳዊት ይዘንጋው /ዳይተም/)   | ​ትዳር በእሳት እንደመጫወት ነው። ተቃጥለው ሌላውን ከማቃጠልዎ በፊት ቆም ብለው ያስቡ። እነዚህ ነገሮ...
09/01/2026

💍 በጭራሽ እንዳያገቡ! (ቢያንስ እነዚህን ሳያሟሉ)

(በዳዊት ይዘንጋው /ዳይተም/)

| ​ትዳር በእሳት እንደመጫወት ነው።

ተቃጥለው ሌላውን ከማቃጠልዎ በፊት ቆም ብለው ያስቡ። እነዚህ ነገሮች ከሌሉዎት ወደ ትዳር አይግቡ፦

​✅ 1. አቅም (በስጋና በመንፈስ) ከሌለዎት፡-

የገንዘብ አቅም ለኑሮ አስፈላጊ ነው፤ የመንፈስ ጥንካሬ ደግሞ ችግሮችን በብልሃት ለማለፍ ወሳኝ ነው። "ጨለማን የሚሽረው ብርሃን ብቻ ነው!"

​✅ 2. እውነተኛ ፍቅር ከሌለዎት፡-

ፍቅር የትዳር መሰረት ነው። ያለ ፍቅር ማግባት የራስን፣ የአጋርን እና የልጆችን ተስፋ ማጨለም ነው።

​✅ 3. ይቅር ባይ ካልሆኑ፡-

"ደስተኛ ትዳር የሁለት ጥሩ ይቅር ባይ ጥምረት ነው።" ቂመኛ እና በቀለኛ ከሆኑ ትዳር ለእርስዎ አይደለም።

​✅ 4. ሃላፊነት መውሰድ ካልቻሉ፡-

ትዳር ሀላፊነት ነው። የተቀረፀውም በፈጣሪ ነው። ሚስት ለባሏ፣ ባልም ለሚስቱ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥበት የተቀደሰ ተቋም ነው።

​✅ 5. በሰው ግፊት ወይም በእድሜ ምክንያት፡-

ሰው አይቶ ስራ ይሰራል እንጂ አይቶ አይኖርም! የቤተሰብ ጫና ወደ አላሰቡት አቅጣጫ የሚወስድ "ደቦ" ነው።

​✅ 6. በራስዎና በአጋርዎ ካልተማመኑ፡-

ያለ እምነት የሚገነባ ትዳር፤ ድቡሽት ላይ እንደተገነባ ቤት ነው።

​✅ 7. ልብዎ ሌላ ቦታ ከሆነ፡-

በሌላ ሰው ፍቅር እየዋኙ ወደ ትዳር አይግቡ። "ፍቅር በሁለት አካላት፣ በአንድ ነፍስ ውስጥ የተዋቀረ ነው!"
​ትዳር የህይወት ጉዞ ነው፤ በጥንቃቄ ይጀምሩት!

​ሰላም ለኢትዮጵያ! 🇪🇹

ውድ የጊምቢቹ የቀድሞ ተማሪዎችና መምህራን ትዝታዎች ቤተሰቦች እንኳን ለጌታችን እና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።          🎄🎅መልካም በዓ...
07/01/2026

ውድ የጊምቢቹ የቀድሞ ተማሪዎችና መምህራን ትዝታዎች ቤተሰቦች እንኳን ለጌታችን እና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

🎄🎅መልካም በዓል🎅🎄
✨Merry Christmas✨

4ኛ ዙር የጊምቢቹ ከተማ የህዝብ ቤተመጻሕፍት ግንባታ ገቢ ማሰባሰቢያ ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም የሀዲያ ዞን አስተዳደር ክቡር አቶ ማቲዎስ አኒዮ በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።የሀብት ድጋፍ የሰ...
02/01/2026

4ኛ ዙር የጊምቢቹ ከተማ የህዝብ ቤተመጻሕፍት ግንባታ ገቢ ማሰባሰቢያ ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም የሀዲያ ዞን አስተዳደር ክቡር አቶ ማቲዎስ አኒዮ በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል።
የሀብት ድጋፍ የሰጡ ሰዎች ስም ዝርዝር ፦
፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤፤
1. የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳደር የተከበሩ አቶ ማቲዎስ አኒዮ ......10,000 ብር
2. የሀዲያ ዞን ም/አስተዳደር አቶ ደነቀ ጊቻሞ .....10,000
3. የዞኑ ት/ት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዴታሞ ጡምደዶ ......10,000
4. የጊ/ከ ከንቲባ አቶ አየለ ጋዴ ....5,000
5. አቶ በቀለ ሀብታሙ ................ 5,000
6. ዶ/ር ክባሞ ዴታሞ ................10,000
7. አቶ አማኑኤል ኤርጃቦ................5,000
8. አቶ ኤርሚያስ ዮሐንስ ................5,000
9. አቶ ጥጋቡ አሰፋ .......................5,000

10. አቶ አክሊሉ አማኑኤል ከሙሉ ቤተሰቡ ጋር ............................ 100,000 ብር

11. አቶ ውብሸት ገዛኸኝ ከቤተሰቡ ጋር 4 መስኮት ...... 27,000 ብር እና 20,000 ብር

12. ጋሽ ወ/ማሪያም ገዳቦ......30,000 ብር
13. አቶ እስራኤል ከበደ ..............1,000
14. ቄስ በየነ ኮብሮ .................10,000
15. አቶ ታምሬ ታደሰ .................. 5,000
16. ጋራድ ማቲዎስ ፎርስዶ.........10,000
17. ወጣት ሙሉጌታ ደዳቸው......10,000

18. የጊምቢቹ ከተማ አስተዳደር መዋቅር .......................100,000 ሺህ ብር

19. አቶ እስክንድር ላምቦሬ.......5,000
20. ዳኛ ታምራት ታኮሬ .......... 1,000
21. አቶ ፍቅሬ ዴቴቦ .............. 1,000
22. አቶ ታምራት መሶሬ ........... 5,000
23. ውብሸት ጩፋሞ ...............1,000
24. አቶ ፀጋዬ አየለ....................5,000
25. አቶ መስገን ታምራት ............5,000
26. አባገዳ ተደሰ ጊቾሬ..............5,000
27. አቶ አዲሱ ዘውዴ.................1,000
28. አቶ ደነቀ አቦሴ .................. 3,000
29. አቶ ሠላሙ ወንድሙ.............5,000
30. አቶ በፀጋው ጴጥሮስ ..........10,000
31. የጊምብቹ ከተማ ውኃ አገ/ት...10,000
32. ከበቡሽ ዳዊት ....................... 2,000
33. አቶ ታፈሰ ሚትኩ .....................2,000

34. አበጌ ዶዕለሶ (ከአሜሪካ) ትልቁን መግቢያ በር ለማሰራት፣

35. ወንድሙ ወልዴ ...................... 5,000
36. ታምራት ቲሮሬ ........................... 500
37. ዳኛ ታገሠ አሾሬ ....................... 500
38. አድ/እጃጆ ለንዶሬ...................... 1,000
39. አማረች ኦሴ ............................. 2,000
40. አለምነህ አቦሴ ......................... 3,000
41. ወ/ዊ ተረፈ እልሎ ..................... 1,000
42. ጊ/ከ ቃለሕይወት ቤ/ክ............. 10,000
43. ገ/ዮሐንስ ዳአሞ .......................... 500
44. ወ/ሮ አበባ ገብሬ ........................2,000
45. አቶ ዮሐንስ አቡቴ ......................... 1,000
46. ይስሐቅ ጡሚሶ .......................... 1,000 ናቸው።

በዕለቱ ቃል የተገባውና በአካውንቱ የገባው ብር መጠን 570,500 (አምስት መቶ ሰባ ሺህ አምስት መቶ) ብር መሆኑም ተውቋል።
በዚህ ትውልድን ለመቅረጽ በሚደረገው ርብሪብ አሻራቸውን በማኖር ላደረጋችሀት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሁሉ እግዚአብሔር በዘላለማዊ ክብሩና በባርኮቱ አብዝቶ ይባርካችህ ።

👉 ሌሎች ወገኖቻችን፣ ወዳጆቻችንና አጋሮቻችን በላይብሬሪው አካውንት ቁጥር :- 👇 1000496653096 G/k/yehizb libirary ginbata project 👈👈👈 ላይ ገቢ በማድረግ አሻራችሁን ስለምታኖሩ ከወዲሁ እናመሰግናለን።

እንደጀመርን እንጨርሳለን። ፈጣሪ አምላካችንም ከእኛ ጋር ነው። ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን።

እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካችሁ!

02/01/2026
27/12/2025
ዜና ሹመትየቀድሞ የጊምቢቹ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ታገሠ ተመስገን የሀዲያ ዞን ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። መልካም የስራ ዘመን!
23/12/2025

ዜና ሹመት

የቀድሞ የጊምቢቹ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ታገሠ ተመስገን የሀዲያ ዞን ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

መልካም የስራ ዘመን!

የቤተመጻሕፍት ግንባታ አሁናዊ ሁኔታ!ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም       ጊምቢቹ
16/12/2025

የቤተመጻሕፍት ግንባታ አሁናዊ ሁኔታ!

ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም
ጊምቢቹ

Address

Hadiya Zone Gimbichu Administration
Gimbichu
0020

Telephone

+251905435860

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጊምቢቹ የቀድሞ ተማሪዎችና መምህራን ትዝታዎች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to የጊምቢቹ የቀድሞ ተማሪዎችና መምህራን ትዝታዎች:

Shortcuts

Share

Category