Dire Dawa Administration Education Bureau, ICT Directorate

Dire Dawa Administration Education Bureau, ICT Directorate ይሂ በድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ዳይሬክቶሬት ይፋዊ የፌስቡክ ቻናል ነዉ
FM 97.4(Educational Media)

ሰኔ 15/በ2016 ዓ.ምየድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2016ዓ ም የ6ኛ ክፍል አስተዳደራዊ ፈተና ለመስጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት እና በፈተና አሰጣጥ ሂደት ላይ ለፈታኝ መምህራን ...
22/06/2024

ሰኔ 15/በ2016 ዓ.ም
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2016ዓ ም የ6ኛ ክፍል አስተዳደራዊ ፈተና ለመስጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት እና በፈተና አሰጣጥ ሂደት ላይ ለፈታኝ መምህራን ፥ ለሱፐርቫይዘር እንዲሁም ለጣቢያ ሀላፊዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ።
~~~
በድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2016 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠዉ የ6ኛ ክፍል አስተዳደራዊ ፈተና የቅድመ ዝግጅትና በፈተና አሰጣጥ ሂደት ላይ ለርዕሰ መምህራን፣ለፈታኝ መምህራን ፥ ሱፐርቫይዘር ፥ ጣቢያ ሀላፊዎች እንዲሁም የክላስተርና የወረዳ ትምህርት ማስተባበሪያ ኋላፊዎች እና ለሌሎችም ባለድርሻ አካላት ኦረንቴሽን ወስደዋል።

በኦረንቴሽኑ ላይ ሰነድ ያቀረቡት የፈተና አስተዳደር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ አስቻለው ሸዋረጋ ስለ አጠቃላይ የፈተና ስርዓት አስተዳደር ግንዛቤ የሚያሲዝ ፅሁፍ አቅርበዋል።

በከተማ አስተዳደሩ በመንግስት እና በግል ት/ቤቶች በመደበኛና በምሽት የሚማሩ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ የተገለጸ ሲሆን በዚህም 7ሺ 527 ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ ተጠቁሟል።

ተማሪዎች በተማሩባቸው ትምህርት ቤቶች ፈተናው እንደሚሰጥ አውቀው በሰዓቱ እንዲገኙ ከመድረኩ አሳውቀዋል።

እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል ካለፈው የ8ኛ ክፍል አስተዳደራዊ ፈተና በተሻለ ለመፈፀም ያስችል ዘንድ ፈተናዉ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ እና በከፍተኛ ዲሲፒሊን በጥንቃቄ እንዲመራ ሃላፊነታቸዉን መወጣት እንዳለባቸዉ በኦረንቴሽኑ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሱልጣን አሊይ አስገንዝበዋል።
ፈተናውም ከሰኔ 18 እስከ ሰኔ 20 ቀን 2016 ዓ/ም ለተከታታይ ሶስት ቀናት እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

22/06/2024

Address

Dire Dawa
Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa Administration Education Bureau, ICT Directorate posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share