የድሬደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት

  • Home
  • Ethiopia
  • Dire Dawa
  • የድሬደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት

የድሬደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም

22/08/2026
"ትምህርት ቤቶች ዋና ተግባራቸው ብቁና ውጤታማ ዜጋን ማፍራት ነው" — አቶ ሱልጣን አልይድሬዳዋ — ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከመንግሥታዊ ካልሆኑ የትም...
18/08/2026

"ትምህርት ቤቶች ዋና ተግባራቸው ብቁና ውጤታማ ዜጋን ማፍራት ነው" — አቶ ሱልጣን አልይ

ድሬዳዋ — ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከመንግሥታዊ ካልሆኑ የትምህርት ተቋማት (Non-governmental schools) ባለቤቶችና አመራሮች ጋር በመማር ማስተማር ሂደት፣ በትምህርት ጥራት እና በጊዜ አጠቃቀም ዙሪያ ያተኮረ የምክክር መድረክ አካሄደ።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ትምህርት ቤቶች የነገዋን ሀገር የሚረከቡ ብቁ፣ በእውቀትና በሥነ-ምግባር የታነጹ ዜጋን ማፍራት ዋና ተግባራቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በውይይቱ ወቅት በመንግሥታዊ ካልሆኑ የትምህርት ተቋማት መካከል የሚስተዋሉ የሥርዓተ-ትምህርት ትግበራ ልዩነቶች በሰፊው ተዳስሰዋል። በተለይም የቅድመ-አንደኛ ደረጃ ትምህርት አደረጃጀት፣ የአንደኛ ክፍል የተማሪዎች ቅበላ ዕድሜ፣ ተማሪዎችን ከመመዘን፣ ውጤት ከመመዝገብና የማለፊያ ነጥብ ከመወሰን አኳያ የነበሩ ወጥነት የሌላቸው አሠራሮች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ መንግሥታዊ ባልሆኑ ትምህርት ቤቶች የሚታየውን የትምህርት ካላንደር ልዩነት ለመፍታትና የአንድ ትምህርት ቤት ተማሪ ወደ ሌላ ተቋም የሚያደርገውን ዝውውር ምቹ ለማድረግ፤ ሁሉም ትምህርት ቤቶች በአራት ሩብ ዓመታት የተከፈለ ወጥ ካላንደር እንዲተገብሩ አቅጣጫ ተቀምጧል።

አቶ ሱልጣን ለተነሱት ሀሳቦች በሰጡት ምላሽ የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅና ወጥ የሆነ አሠራር መከተል የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ኃላፊነት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል። ተቋማቱ መንግሥት ያስቀመጣቸውን ደረጃዎችና መመሪያዎች ጠብቀው መንቀሳቀስ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በትምህርት ተቋማቱ መካከል የነበሩት የአሠራር ልዩነቶች እየሰፉ መምጣታቸውን ጠቅሰው፣ ትምህርት ቢሮው ይህንን መሠረታዊ ችግር ለመፍታት ያቀረበው የምክክር መድረክ እጅግ ወቅታዊ መሆኑን ገልጸዋል። ውይይቱ በውስጣቸው ያለውን ልዩነት ለማጥበብና ወጥነት ያለው የትምህርት ሥርዓት ለመዘርጋት ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም ተሳታፊዎቹ በአጽንኦት ጠቁመዋል።

በመጨረሻም አቶ ሱልጣን ከእነዚህ ተቋማት ጋር የሚደረገው የምክክር መድረክ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ለተነሱ ችግሮችም ቢሮው አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

04/08/2026
04/08/2026

በድሬዳዋ አስተዳደር ስር ለምትገኙ ሁሉም መንግስታዊ ያልሆኑ (የግል) ትምህርት ቤቶች በሙሉ የትምህርት ፖሊሲ መሰረት በማድረግ ማንኛውም መንግስታዊ ያልሆነ የትምህርት ተቋም የቅድመ-አንደኛ ደረጃ ትምህርትን ለሶስት (3) ተከታታይ ዓመታት መተግበር እንዳለበት ይታወቃል።

በመሆኑም የክፍል ደረጃዎቹና የተማሪዎች የዕድሜ እርከን ከዚህ በታች በተቀመጠው ስያሜ መሰረት እንዲተገበር እናሳስባለን፡-

- ዕድሜ 4 ዓመት፡ ኬጂ 1 (ደረጃ 1) / KG 1 (Level 1)

- ዕድሜ 5 ዓመት፡ ኬጂ 2 (ደረጃ 2) / KG 2 (Level 2)

- ዕድሜ 6 ዓመት፡ ኬጂ 3 (ደረጃ 3) / KG 3 (Level 3)

ሁሉም ትምህርት ቤቶች ይህንን የክፍል ደረጃ አወቃቀር ጠብቃችሁ ምዝገባ እንድታከናውኑ እናሳስባለን።

29/07/2026
Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Mesfin Bezu, Hagaloo Dooyyoo To, Hana Bayisa, Ased Real
22/07/2026

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Mesfin Bezu, Hagaloo Dooyyoo To, Hana Bayisa, Ased Real

19/07/2026

Address

Dire Dawa
Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የድሬደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category