Ethio-Italy Polytechnic College-Dire Dawa

Ethio-Italy Polytechnic College-Dire Dawa "ጥራት ያለው ትምህርትና ስልጠና ለሁሉም"

24/08/2026
ለአስተዳደሩ ስራ አጥ ወጣቶች የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ::   ነሃሴ 12.2018 ዓ.ም ድሬዳዋኤስ.ኦ.ኤስ(SOS) ቺልድረን ቪሌጅ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ከኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር...
18/08/2026

ለአስተዳደሩ ስራ አጥ ወጣቶች የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ::

ነሃሴ 12.2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

ኤስ.ኦ.ኤስ(SOS) ቺልድረን ቪሌጅ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ከኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ከአስተዳደሩ ወረዳዎች ለተወጣጡ ስራ አጥ ወጣቶች የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጥቷል::

ኤስ.ኦ.ኤስ(SOS) ቺልድረን ቪሌጅ ከአስተዳደሩ ወረዳዎች ለተወጣጡ ስራ አጥ ወጣቶች የተለያዩ የሙያ ስልጠዎችን በማሰልጠን ከስራ ጋር ለማስተሳሰር ያለመ ፕሮግራም በመንደፍ በኮሌጁ ስልጠና እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን የህይወት ክህሎት ስልጠናውም የዚሁ መርሃ-ግብር አካል መሆኑም ተገልፇል::

ለተከታታይ ሶስት ቀናት በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለስራ አጥ ወጣቶች የተሰጠው የህይወት ክህሎት ስልጠና በኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን በስልጠናውም ወጣቶች የቀጣይ ህይወታቸውን የመምራት ክህሎት፣ችግሮችን የመፍታት ክህሎት እንዲሁም የውሳኔ አሰጣጥ ክህሎቶችን የሚያዳብሩበት ስልጠና ያገኙበት እንደነበርም ተገልፇል::

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr

በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001

በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1

በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የተሰሩ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች በአስተዳደሩ ወጣቶች ተጎበኙ::   ነሃሴ 07.2018 ዓ.ም ድሬዳዋ በዛሬው እለት ከተካሄደው የወጣቶች መድረክ ጎን ለጎን በስ...
13/08/2026

በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የተሰሩ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች በአስተዳደሩ ወጣቶች ተጎበኙ::

ነሃሴ 07.2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

በዛሬው እለት ከተካሄደው የወጣቶች መድረክ ጎን ለጎን በስራና ክህሎት ቢሮ አዘጋጅነት በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የተሰሩ ቴክኖሎጂዎች ለእይታ የቀረቡበት ኤግዚብሽን በኮሌጃችን ለጉብኝት ክፍት ተደርጓል::

በዚህ ለአስተዳደሩ ወጣቶች በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ላይ ንቅናቄ ለመፍጠር በቢሮው በተዘጋጀው የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽን ላይ በኮሌጃችን በተለያዩ ጊዜያት የተሰሩና የተሸጋገሩ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች ለእይታ የቀረቡ ሲሆን ዛሬን ጨምሮ በቀጣይ 3ቀናት ለጎቡኚዎች ክፍት ሆኖ እንደሚቆይም ተገልፇል::

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr

በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001

በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1

በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

13/08/2026
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራርና ሰራተኞች የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተካላ መርሃ-ግብር አካሄዱ::  ነሃሴ 6.2018 ዓ.ም ድሬዳዋየኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በዛ...
12/08/2026

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራርና ሰራተኞች የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተካላ መርሃ-ግብር አካሄዱ::

ነሃሴ 6.2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በዛሬው እለት የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች ማስጀመርያ መርሃ-ግብር እንዲሁም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ፕሮግራም በኮሌጁ ተካሂዷል::

የኮሌጁ አመራና ሰራተኞች በክረምቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘውን የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ምክንያት በማድረግ በኮሌጁ ባካሄዱት የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ የተለያዩ ለምግብነት የሚውሉ የችግኝ አይነቶችን በተቋሙ በተመረጡ ቦታዎች ላይ በመትከል አሻራቸውን አሳርፈዋል::

ከችግኝ ተከላው በተጨማሪ በቀጣይ የክረምት በጎ ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ሲሆን በዚህም የደም ልገሳ፣ የማዕድ ማጋራት እንዲሁም አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ የመሳሰሉ በጎ ተግባራት በኮሌጁ ማሀበረሰብ እንደሚከናወኑም ተገልፇል::

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr

በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001

በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1

በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የስራ ልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄዱ፡፡  ሐምሌ 29.2018 ድሬዳዋየአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፖሊቴክኒክ ...
05/08/2026

የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የስራ ልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄዱ፡፡

ሐምሌ 29.2018 ድሬዳዋ

የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲኖችን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎችን ያካተተ የልዑካን ቡድን በኮሌጃችን ያለውን የስራ እንቅስቃሴ ለመመልከት እንዲሁም ያለውን ተሞክሮ ለመውሰድ የሚያስችላቸውን የስራ ልምድ ልውውጥ በኮልጁ አካሂደዋል::

ልዑካን ቡድኑ በኮሌጃችን በነበረው የልምድ ልውውጥ መርሃ-ግብር ወቅትም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ በተቋም ደረጃ ያስመዘገባቸውን ውጤቶች በዝርዝር የተመለከቱ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ ከምስረታው አንስቶ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ የነበረውን ሂደት እና ያከናወናቸውን ዘርፈ ብዙ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን በኢንጂነር ፋሲል ማዘንጊያ አማካኝነት ሰፋ ያለ ገለፃና ማብራሪያም ተደርጎላቸዋል::

ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ በተደረገላቸው አቀባበልና በተመለከቱት የኮሌጁ እንቅስቃሴ መነሻ በማድረግ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ እያከናወናቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የስራ እንቅስቃሴዎች አስደናቂ መሆናቸውን ገልፀው በዚህም ኮሌጁ ካሳየው ውጤታማ ጉዞ ብዙ ልምዶችን መቅሰም መቻላቸውንም ገልፀዋል::

በተጨማሪም ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የስልጠና ዎርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በነበራቸው የልምምድ ልውውጥ መርሃ-ግብርም የተሳካ ቆይታን በኮሌጃችን ማድረግ ችለዋል::

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr

በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001

በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1

በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

የ2018 የክረምት የክህሎት ስልጠና በኮሌጁ ተጠናክሮ መካሄዱን ቀጥሏል::  ሐምሌ 23. 2018 ዓ.ም ድሬዳዋበኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 "የአንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ" የክረምት ...
30/07/2026

የ2018 የክረምት የክህሎት ስልጠና በኮሌጁ ተጠናክሮ መካሄዱን ቀጥሏል::

ሐምሌ 23. 2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 "የአንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ" የክረምት ስልጠና ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ወጣቶች ለሶስት ቀናት ሲከተታተሉ የቆየውን የህይወት ክህሎት(Life Skill) ስልጠና አጠናቀቁ::

ሰልጣኞቹ የህይወት ክህሎት ስልጠናቸውን እንዳጠናቀቁ በኮሌጁ የሚገኙ ዲፓርትመንቶች እና ስልጠና የሚሰጥባቸውን ወርክሾፖች ተዘዋውረ የተመለከቱ ሲሆን ስለ ሙያ ዘርፎችም ሰፊ ግንዛቤ ተፈጥሮላቸዋል::

የክረምት ክህሎት ሰልጣኞቹ በተፈጠረላቸው ግንዛቤ መነሻነት ሚፈልጉትን የሙያ ስልጠና አይነት የመረጡ ሲሆን ቀጣይ በተቀመጠላቸው መርሀ-ግብር መሰረትም ስልጠናቸውን የሚከታተሉ ይሆናል::

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr

በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001

በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1

በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

በአስተዳደሩ ለሚገኙ ወጣቶች የክረምት ወቅት የሙያ ስልጠና በኮሌጁ መስጠት ተጀመረ::  ሐምሌ 21. 2018 ድሬዳዋ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 የክረምት ወቅት የክህሎት ስልጠና...
28/07/2026

በአስተዳደሩ ለሚገኙ ወጣቶች የክረምት ወቅት የሙያ ስልጠና በኮሌጁ መስጠት ተጀመረ::

ሐምሌ 21. 2018 ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2018 የክረምት ወቅት የክህሎት ስልጠና "አንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ" በሚል በአስተዳደሩ ለሚገኙ ተማሪዎችና ወጣቶች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያዘጋጀውን የክህሎት ስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር አካሂዷል::

በእለቱ ለወጣቶቹ በተዘጋጀው ኦረንቴሽን ላይ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ባስተላለፉት መልዕክት የዚህ የክረምት ወቅት ስልጠና የተዘጋጀበት ዋና አላማ ጊዜው የክህሎት በመሆኑ ወጣቶች የክረምት ጊዜያቸውን ቁምነገር ላይ በማዋል ቢያንስ የአንድ ሙያ ባለቤት እንዲሆኑ ለማስቻል መሆኑን ገልፀው በተለይም የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክረምቱን በኮሌጃችን በሚኖራችሁ ቆይታ ስለ ቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በጥልቀት የምትገነዘቡ በመሆኑ በቀጣይ ምዕራፋችሁ ለሙያ ተኮር ስልጠናዎች ቅድሚያ እንድሰጡ ይረዳችኃልም ብለዋል::

ወጣቶች በትምህርት ያገኙትንም ሆነ ያላቸውን ሀሳብ ወደ ተግባር ለመቀየር ከየትኛውም ቦታ በተሻለ ቴክኒክና ሙያ ላይ ምቹ ሁኔታ መኖሩን የገለፁት የኮሌጁ ም/ል ዲን እና የትምህርትና ስልጠና ዋና ሀላፊ አቶ ኤሊያስ አህመድ ሲሆኑ አክለውም ወጣቶች በተመቻቸላቸው ወርቃማ እድል ስልጠናውን በአግባቡ በመውሰድ በቆይታቸው ተፈላጊውን ክህሎት ይዘው እንዲወጡ አሳስበዋል::

ቴክኒክና ሙያ ከሌሎች የትምህርት ተቋማት ልዩ የሚያደርገው ወጣቶች የተማሩትን በእጃቸው ነካክተው በተግባር የሚሰለጥኑበትና ሰርተው የሚያሳዩበት ተቋም በመሆኑ ነው ያሉት ደግሞ የኮሌጁ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ኤክስቴሽን አገልግሎት ዋና ሀላፊ እና ም/ል ዲን የሆኑት አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ አያይዘውም የክረምት ሰልጣኞች ከሚወስዷቸው ስልጠናዎች በተጨማሪ ወደ ቢዝነስ ሊቀይሩት የሚችሉት የቢዝነስ ሀሳብ ካላቸው ቢዝነስ ፕላናቸውን በኮሌጁ እንዲሰሩ ከማድረግ በተጨማሪ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትልም የሚደረግ መሆኑን በመድረኩ ገልፀዋል::

የ2018 የአንድ ሙያ ለአንድ ዜጋ የክረምት ስልጠና ላይ ለመሳተፍ ወደ ኮሌጁ የመጡ ወጣቶች በቅድሚያ የህይወት ክህሎት(Life Skill) ስልጠና የሚሰጣቸው ሲሆን የህይወት ክህሎት ስልጠናውም የቀጣይ ህይወታቸውን የመምራት ክህሎት፣ችግሮችን የመፍታት ክህሎት እንዲሁም የውሳኔ አሰጣጥ ክህሎቶችን የሚያዳብሩበት ስልጠና ሲሆን የህይወት ክህሎት ስልጠናውን እንዳጠናቀቁ በቀጣይ በመረጡት የሙያ ዘርፍ ላይ ስልጠናቸውን የሚወስዱ ይሆናል::

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr

በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001

በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1

በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የኮንስትራክሽ ዘርፍ ላይ ያተኮረ የሙያ ክህሎት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል::  ሐምሌ 13 2018 ዓ.ም ድሬዳዋየድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የኮስትራክሽን ኮንትራ...
20/07/2026

በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የኮንስትራክሽ ዘርፍ ላይ ያተኮረ የሙያ ክህሎት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል::

ሐምሌ 13 2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የኮስትራክሽን ኮንትራክተሮች ማህበር ከኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመቀናጀት የሚሰጠው ይህ የክህሎት ስልጠና ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ስልጠና ሲሆን በሁለት የሙያ ዘርፎችም በኮሌጁ እየተካሄደ ይገኛል::

በኮሌጁ እየተሰጠ የሚገኘው የክህሎት ስልጠና ለኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን፣ ለኮሌጅ ሰልጣኝ ተማሪዎች እንዲሁም ሳይት ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ባጠቃላይ ለ50 ተሳታፊዎች ሙሉ ማሰልጠኛ ማቴሪያሎች ተሟልተው የተግባር ስልጠናው በሁለት የሙያ ዘርፎች ማለትም በRefrigeration, Heat Pump Technology and Air Conditioning System እንዲሁም በSolar grid system ሙያዎች እየተሰጠ እንደሚገኝም ተገልፇል::

ይህ ስልጠና በጀርመኑ BAUVERBÄNDE NRW e.V. እና በኢትዮጵያ የግንባታ ዘርፍ ማህበራት እንዲሁም የሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት መካከል በሚደረግ የሙያ ትምህርትና ስልጠና አጋርነት አማካኝነት የተገኘ እንደሆነም ማወቅ ተችሏል::

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr

በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001

በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1

በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

Address

ድሬዳዋ ሳቢያን ከሰኢዶ ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በሚወስደው መንገድ 300 መቶ ሜትር ገባ ብሎ እንገኛለን፡፡
Dire Dawa

Telephone

+251920203994

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio-Italy Polytechnic College-Dire Dawa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Ethio-Italy Polytechnic College-Dire Dawa:

Shortcuts

Share