Dire Dawa University Institute of Technology, Ethiopia

Dire Dawa University Institute of Technology, Ethiopia This is an official page for Dire Dawa University Institute of Technology. Relating to academic issu

09/09/2025

የእንኳን ደስ አላችው መልክት ከድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም
===================================
ሀገራችን ኢትዮጲያ በተፈጥሮ ፀጋዎቿ የታደለች እንዲሁም በተለያዩ መልክአ ምድሮቿ እና ህብረ ብሔራዊ ህዝቦች ያጌጠች፣ ታሪክ በተለያየ ኩነቶች የሚዘክራት፣ ቅኝ ገዢዎችን አሳፍራ ቅኝ ሳትገዛ የኖረች፣ የመላው አፍሪካውያን የነፃነት ቀንዲል ጥንታዊ የሰው ዘር መገኛ ውብ ሀገር ናት፡፡

ሀገራችን ያላትን ፀጋ ለመቀራመት ቅኝ ገዢዎች ቢያማትሩም የአንድነታችንን ክንድ መቋቋም ተስኗቸው አፍረው ተመልሰዋል፡፡ ፊት ለፊት ገጥመው አንበርክከው ሊመዘብሯት ያልቻሉትን ሀገራችንን ውስጣዊ አንድነታችንን በማዳከም መንግስታት ከልማት ይልቅ የእለት ችግሮቻችን ላይ ተጠመደው እንዲከርሙ በማድረግ ሀገራችን ከልማቱም ከሰላሙም እንዳትሆን ብዙ ለፍተዋል፡፡ ድህነት እና ኋላቀርነት መገለጫችን ሆኖ በአለም መድረክ እስኪነገር ኢትዮጲያ አቀርቅራ ቆይታለች፡፡

ዛሬ ግን ያ የቁዘማ ዘመን ያ በራስ ሀብት እና ፀጋ የመሸማቀቅ ታሪክ ዳግሞ ላይመለስ ተቀይሯል፡፡ ኢትዮጲያዊያን አንድነታቸውን አፅንተው፣ ከእለት ጉርሳቸው ቀንሰው ለዘመናት የህዝባችን ጥያቄ የነበረውን የመልማት ፍላጎት እና የአባይ ወንዝ እንቆቅልሽ በተባበረ ክንድ መላሽ ሰጥተዋል፡፡ ታላቁ የህዳሴ ግድብ የእውነትም በህዝባችን ጥረት እና ድካም እውን ሆኗል።

ውድ ኢትዮጵያዊያን፦ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለኢትዮጲያ የማንሰራራት ምልክት፤ የለውጥ ጉዞ እና የታሪክ እጥፋት ጅማሮ ማብሰሪያ ነው፡፡ ግድቡ ውሃ ብቻ ሳይሆን ሉአላዊነታችን ላይ ለሚቃጡ ትንኮሳዎችም ልጓም የሚያበጅ ኃይል ነው፡፡ ኢትዮጲያዊያን እናቶች በእንጨት ለቀማ የሚደክሙት ድካም፣ የሚያባክኑት ጊዜ እና ጉልበት ከእንግዲህ አይኖርም። በኤሌክትሪክ ሀይል እጥረት ኢንዱስትሪዎቻችን ስራ አይፈቱም፣ በጋራ ተጠቃሚነት እና አብሮ የመልማት መርህ የህዳሴው ግድብ ከሀገራችን አልፎ ለጎረቤት ሀገራትም ጭምር በረከት ይዞ መጥቷል።

ውድ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ፡ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እውን እንዲሆን ገና ከጅምሩ አንስቶ በተለያየ መልኩ ድጋፍ በማድረግ፣ በሀገር አቀፍ ሚዲያዎች ቀርባችሁ የተሳሳተ ትርክቶችን በመሞገት፣ ከእለት ጉርሳችሁ ሳይቀር ቀንሳችሁ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም ህዝባዊ ንቅናቄዎችን ጭምር በማስተባበር ላበረከታችሁት አስተዋፅኦ፣ ላኖራችሁት ታሪካዊ አሻራ በራሴ እና በዩኒቨርሲቲያችን ስም እያመሰገንኩ በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን እላለሁ።

ዶ/ር ኡባህ አደም

Registration Announcement for Second Year and Above Regular Students
06/09/2025

Registration Announcement for Second Year and Above Regular Students

02/09/2025
02/09/2025
19/08/2025

የሐዘን መግለጫ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ሲሳይ ጉግሳ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ነሐሴ 12 ቀን 2017 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ዶ/ር ሲሳይ ጉግሳ በኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ከመምህርነት ጀምሮ የቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን በመሆን ተቋማችንን እና ሀገራቸውን በታላቅ ቅንነት ከማገልገላቸውም በላይ በርካታ ተማሪዎችን እስተምረው ለወግ ማእረግ ያበቁ ምሁር ነበሩ።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት በዛሬው እለት ሁለት እንቁ ምሁራኖቹን በማጣቱ የተሰማው ሀዘን ጥልቅ መሆኑን እየገለፀ ለዶ/ር ሲሳይ ጉግሳ ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ እና ለመላው የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ መፅናናትን ይመኛል።

የሀዘን መግለጫየድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ማሞ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። ዶ/ር ያሬድ ዩኒቨርሲቲያችንን ከመጋቢት 10 2010 እስከ ታህሳስ 30 2012 ዓ/ም ለ...
18/08/2025

የሀዘን መግለጫ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ማሞ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። ዶ/ር ያሬድ ዩኒቨርሲቲያችንን ከመጋቢት 10 2010 እስከ ታህሳስ 30 2012 ዓ/ም ለሁለት አመታት በፕሬዝዳንትነት መርተዋል።

ዶ/ር ያሬድ ዩኒቨርሲቲያችንን በከፍተኛ አመራርነት ከማገልገላቸውም በላይ ህይወታቸው እስካለፈበት ነሐሴ 11 2017 ዓ/ም በመምህረነት እና በከፍተኛ ተመራማሪነት አገልግለዋል።

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት በቀድሞ የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዝዳንት ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለ ዶ/ር ያሬድ ማሞ ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ እንዲሁም ለመላው የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ መፅናናትን ይመኛል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ት/ርት ቤት ለ2018 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች ከታች በተጠቀሰ...
14/08/2025

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ት/ርት ቤት ለ2018 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች ከታች በተጠቀሰው ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም እንድትመዘገቡ እናስታውቃለን።

መመዝገቢያ ሊንክ፡ https://forms.gle/keEnCwXcW6eZ1wPH9

Congratulations!!!
22/06/2025

Congratulations!!!

22/06/2025
ማስታወቂያበነገው ዕለት ሰኔ 5/2017 ዓ/ም  የጠዋት መርሃግብር ከ 2፡30  -  5፡00  የሚሰጠውን የአገር አቀፍ የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና የምትወስዱ ተፈታኞች የመፈተኛ ቦታ እና ዝርዝር...
11/06/2025

ማስታወቂያ

በነገው ዕለት ሰኔ 5/2017 ዓ/ም የጠዋት መርሃግብር ከ 2፡30 - 5፡00 የሚሰጠውን የአገር አቀፍ የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና የምትወስዱ ተፈታኞች የመፈተኛ ቦታ እና ዝርዝር መርሃግብር በማየት ተዘጋጅታችሁ እንድትመጡ ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

Address

Sabian
Dire Dawa
P.O.BOX:1362

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa University Institute of Technology, Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Dire Dawa University Institute of Technology, Ethiopia:

Shortcuts

Share

Category