DDCSS

DDCSS Teaching learning processs

08/12/2021
29/03/2021

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዛሬ ወይም ነገ ይፋ ይሆናል።
_____________________________
የ 2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች ውጤት ዛሬ
ወይም ነገ ይፋ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር
ጌታሁን መኩሪያ ገለጹ።
ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ፈተናው በ 2ሳምንት ውስጥ ታርሞ
መጠናቀቁን እና ይህም ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልፀዋል ።
በመሆኑም ተፈታኞች ውጤታቸውን ከዛሬ ወይም ከነገ ጀምሮ በ8181
እንዲጠባበቁ ጠቁመዋል።
የ2012ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና ከ የካቲት 29 እስከ መጋቢት
2,2013ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል።

26/03/2021

የትምህርት ሚኒስቴር ባልደረባ የነበሩት አቶ መብራቱ ብርሃን በርሄ
ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
*******
የሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ባልደረባ የነበሩት አቶ መብራቱ ብርሃን
በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
አቶ መብራቱ ብርሃን ከ1978 ዓ.ም ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈበት
ዕለት ድረስ በትምህርት ሚኒስቴር በልዩ ልዩ የስራ መስኮች
በባለሙያነትና በሃላፊነት አገልግለዋል፡፡
አቶ መብራቱ ባደረባቸው ድንገተኛ ሕመም ሆስፒታል በሕክምና ሲረዱ
ቆይተው በተወለዱ በ59 ዓመታቸው በትናንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም
በሞት ተለይተዋል፡፡
የአቶ መብራቱ የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬው ዕለት ከቀኑ 10፡00 በቦሌ
ሚካኤል ቤተክርስቲያን ይፈጸማል፡፡
አቶ መብራቱ ብርሃን በሥራቸው ሰው አክባሪ፣ ታታሪና ትጉህ ሰራተኛ
ነበሩ፡፡
አቶ መብራቱ ብርሃን ባለ ትዳርና የአንድ ሴትና የአንድ ወንድ ልጅ አባት
መሆናቸውን ከህይወት ታሪካቸው የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡
የሚኒስቴር መስሪያቤታችን አመራሮችና ሰራተኞች የተሰማንን ጥልቅ
ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን
እንመኛለን፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር

21/03/2021
16/03/2021

የ12ኛ ክፍል ፈተና አልተሰረቀም ሲል የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ!
በዛሬው እለት መግለጫ የሱጠት የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዶ/ር
ጌታሁን መኩሪያ የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና አለመሰረቁን ይፋ
አድርገዋል። ፈተናው ተሰርቆ አንዳንድ ተማሪዎች ቴሌግራም በተሰኘው
መተግበሪያ መልስ ሲለዋወጡ ነበር ቢባልም ፈተናውን ተማሪዋች
እስኪፈተኑ ድረስ የፈተናውን ስብጥር የሚያቀው አንድ ግለሰብ ብቻ
ነው፤ ከአሁን በፊት በአንድ ፈተና አራት ስብጥር የነበረ ቢሆንም
የዘንድሮ ፈተና በ 32ስብጥር በመደረጉ እንዳይሰረቅ ለማረግ ተችላል
ሲሉ ሚኒስትሩ መናገራቸውን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።
የዘንድሮው በፍፁም ሳይሰረቅ እና ኢንተርኔት ሳይቋረጥ መከናወኑን
ያነሱት ሚኒስትሩ በቴሌግራም ላይ መረጃዎችን ሲያሰራጩ የነበሩ
ተማሪዎች ተፈታኝ አለመሆናቸውን ጌታሁን መኩሪያ
ተናግረዋል።ሞባይል ደብቀው የገቡ ተፈታኞች ፈተናውን ስካን አድርገው
ለመላክ የሞከሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።በትግራይ ክልል
ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተሰጥቷል።
ለ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና 358ሺ ተማሪዎች ለፈተና የተቀመጡ
ሲሆን ውጤቱ እንደተለቀቀ ነጥብ የመጣላቸው በተያዘው 2013 ዓመት
ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይመደባሉ ሲሉ ሚኒስትሩ ይፋ
አድርገዋል።በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ ለዚህ ድጋፍ ላደረጉ የፌደራል
ፖሊሰ የክልል መስተዳደር አካላትና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት
ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ አሁን ምስጋና ማቅረባቸውን ብስራት ሰምቷል።
7-7-2013 ዓ.ም ማክሰኞ

14/03/2021

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁ ተገለፀ።

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መጠናቀቁን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫውም ከየካቲት 29 - መጋቢት 02 ,2013ዓ.ም ሲሰጥ የነበረው የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታውቋል።

Send a message to learn more

Address

Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when DDCSS posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category