Dilla University

Dilla University

Share

Dilla University, often referred as 'University of the Greenland' due to the greenery in and around.

Photos from Dilla University's post 05/06/2026

በዲላ ዩኒቨርሲቲ ዓለምአቀፍ የአከባቢ ቀን በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ተከበረ
============************=============

ዲ.ዩ: ግንቦት 28/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)

በዓለማቀፍ ደረጃ ለ53ኛ ጊዜ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ33ኛ በሀገራችን ደረጃ የሚከበረው "የአካባቢ ቀን" በዲላ ዩኒቨርሲቲ እፅዋት ጥበቃና ኢኮቱሪዝም ማዕከል በተለያዩ መርሃ ግብሮች ተከብሯል።

በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ምድር በተለያዩ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ምክንያቶች የአየር ንብረት ለውጥ እያስተናገደች መሆኑን ገልፀው፣ የሙቀት መጨመር፣ የሰደድ እሳት፣ የጎርፍ አደጋዎች፣ የመሬት መንሸራተት እና የመሳሰሉ ክስተቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ መምጣታቸውን ገልፀዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ አክለውም የአካባቢውን ማህበረሰብና አስተዳደር በማሳተፍ እንዲሁም መንግሥት የጀመረውን የአረንጓዴ ልማት ንቅናቄ በማጠናከር የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስና ለመቋቋም የጋራ ጥረት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ እፅዋት ጥበቃና ኢኮቱሪዝም ማዕከል ዳይሬክተር እሸቱ ይርሳው (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የቀኑ መከበር ህብረተሰቡ ስለአካባቢ ጥበቃ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኝና የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ለማነሳሳት መሆኑን ገልጸዋል።

በመድረኩ ላይ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ መምህርና ተማራማሪ ቴዎድሮስ በቀለ (ዶ/ር) ስለ ዓለም አቀፍ የአካባቢ ቀን አጀማመር፣ የአየር ንብረት ለውጥ መንስኤዎች፣ የለውጡ ዓለም አቀፍ ተፅዕኖዎች እና ተግባራዊ ምላሾችን የዳሰሰ የመነሻ ጽሑፍ አቅርበው ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ ከዲላ ከተማና ከአጎራባች ወረዳዎች የተውጣጡ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች፣ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ተማሪዎች፣ በዲላ ከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የአካባቢ ጥበቃ ክበብ አባላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በመጨረሻም የመድረኩ ተሳታፊዎች በዲላ ዩኒቨርሲቲ እፅዋት ጥበቃና ኢኮቱሪዝም ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

=== # # #===


Photos from Dilla University's post 04/06/2026

ከ47 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበላቸው የማህበረሰብ ተደራሽ ፕሮጀክቶች ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ
===========**********==========

ዲ.ዩ: ግንቦት 27/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)

በዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት እና በማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት የጋራ ትብብር የተዘጋጀ ከ47 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበላቸው የማህበረሰብ ተደራሽ ፕሮጀክቶች የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዶ፣ ፕሮጀክቶቹም በይፋ ወደ ስራ ገብተዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር) በፕሮጀክቶቹ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንግዶችንና ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ተቀብለው፣ ለማህበረሰቡ ጠቃሚ በሆነው በዚህ መርሃ ግብር ላይ በመገኘታቸው ትልቅ ክብርና ደስታ እንደሚሰማቸው ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ በተጨማሪም ይህ መርሃ ግብር ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለማህበረሰብ ልማትና ለዜጎች ኑሮ መሻሻል ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሰው፣ ፕሮጀክቶቹ በተቀመጠላቸው ዓላማ መሠረት ተግባራዊ ሆነው ለማህበረሰቡ ተጨባጭ ለውጥ እንዲያመጡ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብርና በቅንጅት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ አባል ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር፣ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከመማርና ማስተማር ተልዕኮው ባሻገር በማህበረሰብ ጉድኝትና በልማት ሥራዎች ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ ሲያበረክት መቆየቱን ገልጸዋል። በተለይም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ዩኒቨርሲቲው ከማህበረሰቡ ጋር በመቀራረብ ያከናወናቸው ፕሮጀክቶች በአርሶ አደሮች ኑሮ ላይ ተጨባጭ ለውጥ እያመጡ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ዶ/ር ዝናቡ አክለውም፣ ዩኒቨርሲቲው በየዓመቱ የማህበረሰብ ተደራሽ ፕሮጀክቶችን ቁጥር እያሳደገ በመምጣቱ የህብረተሰቡን ሕይወት ለመቀየር የሚያደርገው ጥረት የሚያስመሰግን መሆኑን ገልጸው፣ አዲስ የተጀመሩት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተጠናቀው ውጤታማ እንዲሆኑ የዞኑ አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ዩኒቨርሲቲው ከመማርና ማስተማር ተልዕኮው ባሻገር በምርምርና በማህበረሰብ ተደራሽ ሥራዎች በርካታ ፕሮጀክቶችን በመተግበር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።

በዛሬው መርሃ ግብርም ከ47.5 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የተያዘላቸው 8 አዳዲስ ፕሮጀክቶች በይፋ መጀመራቸውን ጠቅሰው፣ ከጠቅላላ በጀቱ 20.5 ሚሊዮን ብር (43%) በዩኒቨርሲቲው የሚሸፈን ሲሆን፣ ቀሪው 26.9 ሚሊዮን ብር (57%) በአጋር ተቋማትና በጉድኝት እንደሚሸፈን ገልጸዋል። ይህ ተግባርም ዩኒቨርሲቲው ወደ ተግባር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ የሚያደርገውን የሽግግር ጉዞውን እያሳካ ለመሆኑ ማሳያ እንደሆነ ገልጸዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት አቶ ተካልኝ ታደሰ በአንጻሩ፤ መድረኩ በዩኒቨርሲቲው በማህበረሰብ ጉድኝት አገልግሎት የሚተገበሩ 8 ፕሮጀክቶችን ለማስጀመር እንደሆነ ገልጸው፤ እነዚህ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ሆነው በህብረተሰቡ ዘንድ በሚፈልገው ልክ ውጤት እንዲያመጡ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በመርሃ ግብሩ የቀረቡት 8 ፕሮጀክቶች ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፣ በውይይቱ የተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በፕሮጀክት አቅራቢዎች እና በመድረኩ መሪዎች ተገቢው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲውና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የአጎራባች ወረዳዎች ተወካዮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ተመራማሪዎች፣ የወረዳ ግብርና መምሪያ ኃላፊዎች፣ መምህራን እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

=== # # #===


Photos from Dilla University's post 04/06/2026

የማህበረሰብ ተደራሽ ፕሮጀክቶች ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው
===========***********==========

ዲ.ዩ: ግንቦት 27/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ተደራሽ ፕሮጀክቶች ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በዩኒቨርሲቲው የእጽዋት ጥበቃና ኢኮ ቱሪዝም ማዕከል ላይ እየተካሄደ ይገኛል።

ፕሮጀክቶቹ ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በጉድኝት የሚሰሩ እንደሆነ እና የማህበረሰቡ ተሳትፎም የታከለበት፣ የሚተዋወቁ ፕሮጀክቶችም የሚጠበቀውን ግብ እንዲመቱ የሁሉም ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

በዚህኛው ዙር ስምንት ተደራሽ ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ ከ47 ሚሊዮን ብር በላይ በሚገመት ወጪ ሚሊዬን የጉድኝት ስራዎች እንደሚሰሩና ከዚህ ውስጥ 20.5 ሚሊዬን ብር ያህሉ በዩኒቨርሲቲው እንደሚሸፈን ተገልጿል።

ፕሮጀክቶቹ ወደ መሬት እንዲወርዱ ከሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር ስለሚሰሩ፣ ባለድርሻ አካላትም የሚጠበቅባቸው እንዲወጡ የጋራ ምክክር ለማድረግ ታስቦ መድረኩ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል።

በመድረኩ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር)፣ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር)፣ የዩኒቨርሲቲው እና የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የአጎራባች ወረዳዎች ተወካዮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

=== # # #===


Photos from Dilla University's post 04/06/2026

የአቅም ማሻሻያ ትምህርት የማጠቃለያ ፈተና መሰጠት ጀመረ
===========************============

ዲ.ዩ: ግንቦት 27/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና መውሰድ ጀምረዋል።

ፈተናው በዛሬው ዕለት የጀመረ ሲሆን፣ እስከ ሰኔ 03/2018ዓ.ም ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ዩኒቨርሲቲው ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም ፈተና እንዲሆንላቸው ይመኛል።

=== # # #===


03/06/2026

📍 National remedial Examination Notice


Photos from Dilla University's post 03/06/2026

የአቅም ማሻሻያ የማጠቃለያ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ገለፃ ተደረገ
============**********============

ዲ.ዩ፡ ግንቦት 26/2018 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)

ከነገው ዕለት ጀምሮ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ የአቅም ማሻሻያ ማጠቃለያ ፈተና በተመለከተ ፈተናውን ለሚወስዱ ተማሪዎች ገለፃ ተሰጥቷል።

የዩኒቨርሲቲው ዋና ሬጅስትራር ስራ አስፈፃሚ አስናቀ ይማም (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ በማጠናቀቅ እና ለፈተናው የሚያስፈልገውን ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን በመግለጽ፣ ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው መርሐ ግብር መሠረት ፈተናው ከነገ ግንቦት 27/2018 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

ዶ/ር አስናቀ በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ የኦንላይን መሰረተ ልማት በማዘጋጀት እና አስፈላጊ የሰው ኃይል በመመደብ በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የዲላ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘገዬ ንጉሴ በበኩላቸው፣ ተማሪዎች ፈተናቸውን በመመሪያው መሠረት መፈጸም እንዳለባቸው አሳስበው፣ በፈተና ወቅት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት እና ሌሎች የተከለከሉ እቃዎችን ይዘው መገኘት ክልክል መሆኑን አስገንዝበዋል።

ከነገ ጀምሮ በሚሰጠው ፈተና በዲላ ዩኒቨርሲቲ 1243 የተፈጥሮ ሳይንስ እና 623 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በአጠቃላይ 1,866 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

=== # # #===


Photos from Dilla University's post 29/05/2026

በስራ ፈጠራ ክህሎት ዙሪያ ለቤተመጻሕፍት ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ
============*************============

ዲ.ዩ: ግንቦት 21/2018 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)

የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ከስነ ውጤት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር በስራ ፈጠራ ክህሎት ዙሪያ ለቤተ-መጻሕፍት ሰራተኞች ስልጠና ሰጥቷል።

በስልጠናው መክፈቻ ላይ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ታምራት በየነ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ መንግስት በሀገር ደረጃ እያካሄደ ያለው መጠነ ሰፊ ለውጥ ስራዎች በትምህርት፣ በምርምርና በሌሎች ዘርፎች ላይ የተለያዩ ስራዎች እንዲከናወኑ እያስቻለ መሆኑን ገልጸው፣ በዩኒቨርሲቲውም በርካታ የልማትና የፈጠራ ስራዎች እየተካሄዱ እንደሚገኙ አስረድተዋል።

በቤተመጻሕፍት ሰራተኞች የተጀመረው የስራ ፈጠራ ክህሎት ስልጠና በቀጣይ ለሁሉም የአስተዳደር ሰራተኞችና ለመምህራን እንደሚሰጥ የገለጹት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፣ ስልጠናው ሰራተኞች በስራቸው ውጤታማ እንዲሆኑና ራሳቸውን እንዲያበረታቱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ጠቁመው፣ ይህም ለሰራተኛውና ለተቋሙ ውጤታማነት ትልቅ ፋይዳ ያለው ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

ምክትል ፕሬዘደንቱ በተጨማሪ እንደተናገሩት ሰራተኞች የወሰዱትን ስልጠና በተግባር ላይ እንዲያውሉ ለማስቻል ከዞን፣ ከከተማ፣ ከክልልና ከፌዴራል ተቋማት ጋር በመተባበር የንግድ ፈጠራ ስራዎችን የሚደግፉ አሰራሮች እንደሚመቻቹ ገልፀው፣ ይህም ሰራተኞች የራሳቸውን ኑሮ ከማሻሻል ባለፈ የተቋሙንም ውጤታማነት ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የስነ ውጤት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መምህር አብይ ረጋሳ በበኩላቸው፣ ስልጠናው ተማሪዎችንና የተቋሙን ሰራተኞች በፈጠራ አስተሳሰብ ለማበረታታት ያለመ መሆኑን ገልጸው፣ ሰራተኞች ከመደበኛ የስራ ተግባራቸው በተጨማሪ አዳዲስ የንግድ እድሎችን በመለየት የግል ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ የሚያስችል እውቀትና ክህሎት ለማስጨበጥ እንደሆነ ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ አያይዘውም ስልጠናው ለሁሉም የተቋሙ ማህበረሰብ፣ ለተማሪዎች፣ ለአካዳሚክ እና ለአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች በተለያዩ ይዘቶችና ጊዜያት ላይ እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቤተ መጻሕፍትና ኢንፎርሜሽን አገልግሎት ዳይሬክተር አስናቀ ሙሉዬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ስልጠናው ለሁሉም ሰራተኞች የተዘጋጀና በስራ ፈጠራ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ገልጸው፣ ሁሉም ስልጠናውን በተገቢው ሁኔታ ተግባራዊ ካደረጉ ምርታማ እንደሚሆኑና ኢኮኖሚያቸውን እንደሚያሻሽሉ ተናግረዋል። በተጨማሪም ለሌሎችም የስራ እድል የሚፈጥር በመሆኑ ሰራተኞች ራሳቸውን አነሳስተው ወደ ስራ እንዲገቡ ያበረታታል ብለዋል።

ከተሳታፊዎች መካከል ወ/ሮ በለጠች ወረታው በሰጡት አስተያየት፣ ስልጠናው ከውድቀት በኋላ ስኬት እንዳለ ግንዛቤ እንዲያገኙ እንዳስቻላቸው ገልጸው፣ ችግሮችን በጽናት በመቋቋም ወደ ስኬት መድረስ እንደሚቻል ጥሩ ግንዛቤ እንዳገኙ ተናግረዋል።

=== # # #===


Photos from Dilla University's post 28/05/2026

Dilla University Hosts Doctoral Research Defense
===========*************===========

DU: May 20, 2018 E.C (P.I.R)

The College of Agriculture and Natural Resources at Dilla University held a doctoral research defense for Tigistu Gezahagn, a lecturer in the Department of Natural Resource Management. The event took place at the university’s Nebaru campus seminar hall, in the presence of internal and external examiners, advisors, faculty members, family, and other stakeholders.

The dissertation, titled “Potential of Indigenous Agroforestry Practice to Climate Change Adaptation and Livelihood Diversification in the Gedeo Zone, Southern Ethiopia Rift Valley Escarpment,” was evaluated by a panel that included Dr. Firezer Alemu, Director of Academic Programs, and Dr. Samson Hailemariam, Dean of the College of Agriculture and Natural Resources, alongside other faculty representatives.

During the defense, it was highlighted that the study scientifically examined traditional agroforestry systems and conservation practices passed down through generations in the Gedeo Zone. The research demonstrated how indigenous knowledge can be harnessed to address challenges such as population growth, human pressure, and climate change, and identified future directions for sustainable resource management.

Evaluators emphasized that the dissertation offers valuable contributions to climate resilience and livelihood diversification and reflects the growing environmental awareness among younger generations.

The ceremony concluded with the candidate's gowning, marking a significant academic achievement for Tigistu Gezahagn and a proud moment for the Dilla University community.

=== # # #===

Photos from Dilla University's post 27/05/2026

የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ለፍሬሽማን እና ሪሜድያል ተማሪዎች ገለፃ አደረገ
============*************============

ዲ.ዩ: ግንቦት 19/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ፍሬሽማን እና ሪሜድያል ፕሮግራም እየተከታተሉ ለሚገኙ ተማሪዎች አጠቃላይ ገለፃ አድርጓል።

በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ልማት እንስቲትዩት ዳይሬክተር የሆኑት ኮለኔል በርሱፈቃድ ነጋሽ (ዶ/ር) እና በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ጉዳይ ዳይሬክተር የሆኑት ኮለኔል አድናን ከማል ለተማሪዎቹ ገለፃ አድርገዋል።

በመድረኩ ላይ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች እና ተማሪዎች በመሳተፍ የጋራ ውይይት አድርገዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ይመኑ ዳካ፣ በመድረኩ ላይ በመገኘት ገለፃ ያደረጉ የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችን አመስግነው፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ ዘርፎች ላይ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ ስለመሆኑ አንስተዋል።

መሠል የልምድ ልውውጥ ስራዎች ወደፊትም ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የጠቆሙት አቶ ይመኑ፣ በተቋማት ላይ የሚሰሩ የምርምር ስራዎች ለሀገር ልማትና እድገት ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፣ ልምዶችን መለዋወጥ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል። በቴክኖሎጂው ላይ የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ የሚሰራቸው ስራዎች ለዲላ ዩኒቨርሲቲም ልምድ የሚሆኑ ስለመሆናቸውም አንስተዋል።

በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ልማት እንስቲትዩት ዳይሬክተር የሆኑት ኮለኔል በርሱፈቃድ ነጋሽ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደተናገሩት፣ ዩኒቨርሲቲው ከምስረታው ጀምሮ ላለፉት በርካታ ዓመታት ለሀገር ትልቅ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ዜጎችን ማፍራቱን ጠቁመው፣ አሁን ላይ ተቋሙን ከአፍሪካ ምርጥ 5 የመከላከያ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ለማድረግ ዓላማ ተይዞ መጠነ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ አብራርተዋል።

መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን የታጠቀ፣ ለተግባር ትምህርት ስርዓቱም የተሟሉ ላብራቶሪዎችን የያዘ ተቋም መሆኑን የገለፁት ኮሎኔል በርሱፍቃድ (ዶ/ር)፣ ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች፣ ሀገር ወዳድ እና መልካም ስነ ምግባር የተላበሱ ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪዎች ገለፃ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ጉዳይ ዳይሬክተር የሆኑት ኮለኔል አድናን ከማል በበኩላቸው፣ ዩኒቨርሲቲው በየዓመቱ በቁጥር ውስን የሆኑ ነገር ግን ልዩ ብቃት ያላቸው ተማሪዎችን በትምህርት ሚኒስቴር መስፈርት መሠረት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡና የተቋሙን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎችን እንደሚቀበል ገልፀው፣ በዩኒቨርሲቲው የሚማሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ተከታትለው እንደጨረሱ በተለያዩ የተቋሙ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የስራ እድል እንደሚያገኙ አብራርተዋል።

የፈጠራ ችሎታ እና ክህሎት ያላቸው ተማሪዎች አስፈላጊውን ሁሉ ግብዓት በማግኘት ለሀገር የሚተርፍ የፈጠራ ውጤታቸው ግቡን እንዲመታ ብሎም መሬት ላይ እንዲወርድ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው የገለፁት ኮሎኔል አድናን፣ አሁን ላይ በዩኒቨርሲቲው በርካታ የፈጠራ ውጤቶች በመሰራት ላይ እንደሚገኙና የተሰሩ የፈጠራ ስራዎችም ገበያውን እንዲቀላቀሉ እየተደረገ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

በዩኒቨርሲቲው ገብተው ህልማቸውን ማሳካት የሚፈልጉ ተማሪዎችም እድሉን እንዲጠቀሙ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በመድረኩ ከተማሪዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን፣ ተሳታፊ ተማሪዎች የተደረገላቸው ገለፃ እጅግ ግልጽ እንነበርና ዩኒቨርሲቲውን ለመቀላቀል ፍላጎት እንዳሳደረባቸው ገልፀዋል።

ገለፃው በዩኒቨርሲቲው ኦዳያኣ እና ሀሴዴላ ጊቢዎች ላይ የተደረገ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ሪሜድያል እና ፍሬሽማን ተማሪዎች ተሳትፈዋል።

=== # # #===


Photos from Dilla University's post 27/05/2026

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የዒድ አል-አድሃ በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ
=========*********========

ዲ.ዩ: ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)

በዲላ ዩኒቨርሲቲ 1447ኛው የዒድ አል-አድሃ በዓል በሁሉም ካምፓሶች ከሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ጋር፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በተማሪዎች ምግብ ቤት በደማቅ ስነ-ስርዓት ተከብሯል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ማቲዎስ ሀብቴ (ዶ/ር) በዝግጅቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮችና ለዩኒቨርሲቲው ሙስሊም ተማሪዎች “እንኳን ለዒድ አል-አድሃ በዓል አደረሳችሁ” በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልፀው፣ ተማሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ርቀው በዓሉን እንደሚያከብሩ በመጠቆም የቤተሰብ ናፍቆት እንዳይሰማቸው ዩኒቨርሲቲው በየዓመቱ በቤተሰባዊ መስተንግዶ በዓሉን እንዲያከብሩ ሁኔታዎችን እያመቻቸ መሆኑን ገልጸዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አገልግሎት ዲን ፍቅረፅዮን ፈቀደ (ዶ/ር) አንደተናገሩት፣ በዓሉ በእጅጉ የተዋበና በቤተሰባዊ መንፈስ የተከበረ መሆኑን ገልጸው፣ ይህ ከመደበኛ ተማሪዎች ጋር በጋራ የሚከበረው የመጨረሻ በዓል በመሆኑ ልዩ የመተሳሰብና የአንድነት መንፈስ እንደታየበት ተናግረው፣ ለዝግጅቱ መሳካት አስተዋጽኦ ያደረጉትን አካላትን አመስግነዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ አማኑኤል አለሙ በበኩሉ፣ በዓሉ ከዚህ ቀደምም ከተማሪዎች ጋር በፍቅርና በአንድነት ሲከበር የቆየ መሆኑን በመግለጽ፣ ዘንድሮም ከተማሪዎች ህብረትና ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በመተባበር ተማሪዎች በሰላምና በደስታ በዓሉን እንዲያከብሩ መደረጉን ገልጿል።

በዓሉ በተለያዩ የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች በደማቅ ስነ ስርዓት ተከብሮ ውሏል።

=== # # #===


Want your school to be the top-listed School/college in Dilla?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


South Ethiopia Region
Dilla
419

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:30
Tuesday 08:00 - 17:30
Wednesday 08:00 - 17:30
Thursday 08:00 - 17:30
Friday 08:00 - 17:30
Saturday 08:00 - 17:30