27/12/2022
ሰርጂዮ ራሞስ: "ከአለም ዋንጫ አሸናፊው ጋር ለማውራት መጠበቅ አልቻልኩም።"
"ለአለም ዋንጫው ጉልበቱን ሲቆጥብ ቆይቷል። እናም ተመልክተነዋል። አሁን PSG ቁጭ ብሎ ወደኋላ በመመለስ ሊዮኔል ሜሲ ያሳለፈውን ታሪክ መመልከት አለበት። አሁን ክለቡ PSG የቻምፒየንስ ሊግ ህልሙን እንዲያሳካ ለመርዳት ብቻ ነው እንጂ ለምንም አይነት ሽልማት ብሎ አይጫወትም። የአርጀንቲናን የረጅም ጊዜ ህልም አሳክቷል አሁን የፒኤስጂን የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ የማሸነፍ ህልም ለማሳካት ያለውን አቅም ሁሉ ይሰጣል። ከዚያም በኋላ ጫማውን ለመስቀል አያስብም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ከፍተኛ ገንዘብ ለማግኘት ብሎ ከአውሮፓ ሊጎች የመውጣት ፍላጎት ያለው አይመስለኝም። ወደ ሌላ ሀገር ከመሄድ ይልቅ በቻምፒዮንስ ሊግ እየተጫወተ የእግርኳስ ህይወቱን ቢያጠናቅቅ ደስ እንደሚለው ተናግሯል።"
27/12/2022
ራፋዬል ናዳል: "ሜሲ ሶስተኛውን ግብ ሲያስቆጥር እንባዬ መቶ ነበር። ይህም የሆነው አንድ ታላቅ ተጫዋች ለማሳካት ሲናፍቀው የነበረውን ዋንጫ ለማሳካት ሲታገል ከማየት የመጣ ስሜት ነው።"❤
26/12/2022
'' ሊዮኔል ሜሲ የምንጊዜም የአለም ምርጡ ተጫዋች ነዉ ''
በኳታሩ የአለም ዋንጫ ላይ ሀገሩን ስፔንን ወክሎ መጫወት ችሎ የነበረዉ የአትሌቲኮ ማድሪዱ አማካይ ኮኬ ሊዮኔል ሜሲ የምንጊዜም የአለማችን ምርጡ ተጫዋች መሆኑን ሲናገር የአለም ዋንጫዉም እንደሚገባዉ ገልጿል።
'' ሊዮ የአለም ዋንጫን ማሳካት ብቻ ነበር የቀረዉ ያንንም አድርጎታል ፤ ለዚህ ደግሞ እንኳን ደስ አለህ ማለት አለብን ስለዚህ አሁን ሊዮኔል ሜሲ የምንጊዜም የአለም ምርጡ ተጫዋች መሆኑን ለመመስከር ማመንታት አያስፈልገዉም '' ሲል ሀሳቡን ሰጥቷል።
👉የዩቲዩብ ገፃችን https://youtube.com/
👉የቴሌግራም ፃችን https://t.me/DC4544
97.6 ከልብዎ የቀረበ
26/12/2022
በ37 ዓመታቸው፡-
🇧🇷 ፔሌ መጫወት አቁሟል
🇦🇷 ማራዶና መጫወት አቁሟል
🇧🇷 ሮናልዶ መጫወት አቁሟል
🇫🇷 ዚዳን መጫወት አቁሟል
ነገር ግን ዝላታን ኢቭራሂሞቪች በ41 አመቱ አሁንም ከአውሮፓ 5ቱ ከፍተኛ ታላላቅ ሊጎች ዉስጥ በጣሊያኑ ኤስሚላን እየተጫወተ ይገኛል።
26/12/2022
የርገን ክሎፕ: "በእኔ የህይወት ጊዜዬ አስገራሚው እና ታላቁ ተጫዋች ሊዮኒዪል ሜሲ ነው። እሱን መመልከት ያዝናናል።"
🇦🇷🤝🏻🇩🇪
26/12/2022
Lionel Messi's FC Barcelona trophy cabinet is on another level 🤯
26/12/2022
ሮበርት ሌዋንዶውስኪ ቀጣዩን ባሎንዶር ማሸነፍ ያለበት ሊዮኔል ሜሲ ነው እያለ ነው። ሜሲ ካሸነፈ በእግር ኳስ ህይወቱ 8ኛው ባሎንዶር ይሆናል።
በሌዋ ሀሳብ ትስማማላችሁ?
25/12/2022
የክሪስቲያኖ ሮናልዶ ዝዉዉር ጉዳይ !
ክለብ አልባው ፖርቹጋላዊው ኮከብ ማረፊያ የት ይሆን ?
25/12/2022
ሮበርት ሌዋንዶስኪ "እግር ኳስ ከማቆሜ በፊት ከሊዮኔል ሜሲ ጋር መጫወት እፈልገዋለው"
25/12/2022
ዝላታን ኢብራሂሞቪች
በዚን ጊዜ እያለቀሰ ወይ ተክዞ ያለ ሰው ካገኝህ ያ ሰው በእርግጥ የ ማድሪድ እና ሮናልዶ ደጋፊ ነው። ከ ሜሲ አለም ዋንጫ ማንሳት በሁዋላ አይምሩዋቸው ልክ አደለም የ ሮናልዶ እና ማድሪድ ደጋፊዎች።
22/12/2022
🔵 የአርጀንቲናው ጋዜጣ El Financiero እንዳለው የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ የሊዮኔል ሜሲ ምስል ያረፈበት 1000 ፔሶ የብር ኖቶች ሊያትም ነው ሲል አስነብቧል
🔵 አርጀንቲና ገንዘብ ላይ ምስሉ የታተመለት የመጀመሪያው ተጫዋች በመሆን ለማራዶና ያላደረጉትን ክብር ለሊዮኔል ሜሲ በመስጠት የእግር ኳስ ዘመኑን በስኬት ላይ ስኬት በክብር ላይ ክብር እያጎናፀፉት ይገኛል።
🇧🇷 ብራዚሎች ለፔሌ ይህን አላደረጉም
🇳🇱 ሆላንዶች ለክራይፍ ይህን አላደረጉም
🇵🇹 ፖርቹጋሎች ለሮናልዶ ይህን አላደረጉም
🇮🇹 ጣልያኖች ለፓውሎ ሮሲ ይህን አላደረጉም
🇫🇷 ፈረንሳዮች ለፕላቲኒ ወይም ለዚዳን ይህን አላደረጉም
🇩🇪 ጀርመኖች ለቤከንባወር ወይም ጌርድ ሙለር ይህን አላደረጉም
🏴 እንግሊዞችም ለጆፍ ኸርትስ ፣ ቦቢ ሙር ወይም ቦቢ ቻርልተን ይህን አላደረጉም
🇦🇷 አርጀንቲና ግን ብርቅዬ ልጇን የወረቀት ገንዘብ ላይ አትማ ትውልዱ ሁሉ ሲያየው እሱን ያደነቀ እና እያከበረ አርአያ በማድረግ የነገው ተተኪ ትውልድ ለመሆን እንዲጥሩ ምክንያት ይሆናል
✍ Yisma Mo