Missionary Of God Ministry

Missionary Of God Ministry

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Missionary Of God Ministry, Religious school, Dilla.

" እንዲህም አላቸው። ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።"
(የማርቆስ ወንጌል 16:15)
"15 And he said unto them, Go ye into all the world, and preach the gospel to the whole creation.

15/02/2026

“ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።”
— ሐዋርያት 1፥8

Photos from Missionary Of God Ministry's post 09/02/2026

እግዚአብሔር አምላክ 🔥 እያዘጋጀችሁ ያላችሁ ሰዎች 📚"ሪቫይቫል እሳትና ዝናብ" በምል ርዕስ በዶ/ር መልሳቸው መስፍን የተጻፈውን 📚አስደናቅ መጽሐፍ እንድታነቡ ይመከራል!
"የሁሉ መልስ መንፈስ ቅዱስ!"
....................................................
🌍🔥🌏🔥🌎🔥🌍🔥🌎🔥🌏

24/01/2026

🔥 🌧
"የሪቫይቫል ዝናብ" ታላቅና የሚያረሰርስ ዝናብ ነው። እሳት እሾሁንና እርጋፊውን ሁሉ ከበላው በኋላ "ዝናብ" ሲዘንብበት ምድር ለምለም አረንጓዴ እንደምትሆን ታላቅ የመንፈስ ቅዱስ ዝናብ ሲወርድም እንዲሁ ታላቅ መንፈሳዊ ልምላሜ በቤተክርስቲያንና በምድርም ይሆናል። አዲስ ሣር ይበቅላል፣ ቅንጣቱ ያልሞተበት ጉቶ እንኳን በዝናቡ ሽታ ይለመልማል። ምድር በልምላሜ ትሞላለች።

"ሪቫይቫል" በነብዩ ሆሴዕ እንደተነገረው ጥጋቱን ማረስ ነው። (ሆሴ 10:12)። ጥጋት መሬት ማለት በአንድ ወቅት ሲታረስና ፍሬ ሲሰጥ የነበሬ የተተው፣ የተረሳ፣ በአረም የተዋጠ፣ ለእርሻ የማይመች የሆነ መሬት ነው። "ሪቫይቫል" እንዲህ ዓይነቱን መሬት እንደገና "በእሳትና በዝናብ" በመጎበኘት ምርታማ እንድሆን ያደርገዋል። "እሳቱንና ዝናቡን" ከላይ የሚልከው እግዚአብሔር ነው።

"ሪቫይቫል" የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው። በሪቫይቫል ጊዜ የእግዚአብሔር ኃይል ከሌላው ጊዜ ለየት ባለ መንገድ ይገለጣል። #በሪቫይቫል ወቅት ዝናቡ እሳቱን ሳያጠፋው ወይም ሳይከለክለው ሁለቱም ተስማምተው ለአንድ ግብ ፣ ለእግዚአብሔር ክብር ይሰራሉ። ያን ጊዜ ኃጢአት ይጠላል፣ እግዚአብሔር ዝማሬ ይበዛል፣ መፈራቱም በቤተክርስቲያንና በምድር ሁሉ ይሆናል።

በ"ሪቫይቫል" ወቅት የእግዚአብሔር ጉብኝት ማለት የእግዚአብሔር "መንፈስ" ከሌላው ጊዜ ይልቅ ለየት ባለ ሁኔታ በሕዝቡ መካከል መገኘቱና ሕዝቡም የእርሱን መቅረብ፣ በመካከል መኖሩን በማወቅ በፍርሃትና በጥንቃቄ መመላለሱ ነው። ይህ ሲሆን በጉባዔ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች በመካከላቸው የተገኘና የስብሰባውን መልክ የለወጠ የከበረ ጌታ እንዳለ ይሰማቸዋል። እያንዳንዱ ሰው ይህን ሲረዳ ስለ ራሱ ትንሽነት በማሰብ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ ይሆናል።

#እግዚአብሔር አምላክ "ምድር ላይ መሥራት እስካላቆመ ድረስ" !! "አባት ሆይ" አሁንም በእኛ ዘመን !!!🙏
....................................................
🌍🔥🌏🔥🌎🔥🌍🔥🌎🔥🌏

24/01/2026

🔥 🔥
እንግዲህ "ሪቫይቫል" ወቅት የእግዚአብሔር ጉብኝት ማለት የእግዚአብሔር "መንፈስ" ከሌላው ጊዜ ይልቅ ለየት ባለ ሁኔታ በሕዝቡ መካከል መገኘቱና ሕዝቡም የእርሱን መቅረብ፣ በመካከል መኖሩን በማወቅ በፍርሃትና በጥንቃቄ መመላለሱ ነው። ይህ ሲሆን በጉባዔ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች በመካከላቸው የተገኘና የስብሰባውን መልክ የለወጠ የከበረ ጌታ እንዳለ ይሰማቸዋል። እያንዳንዱ ሰው ይህን ሲረዳ ስለ ራሱ ትንሽነት በማሰብ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ ይሆናል።

📖(ኢሳይያስ 64:1-3)
¹ ሰማዮችን ቀድደህ ምነው ብትወርድ! ተራሮችም ምነው ቢናወጡ!
² እሳት ጭራሮውን እንደሚያቃጥል፥ #እሳትም ውኃውን እንደሚያፈላ፥ ስምህ ለጠላቶችህ ይገለጥ ዘንድ፥ አሕዛብም በፊትህ ይንቀጠቀጡ ዘንድ።
³ ያልተጠባበቅነውን የክብርህን ሥራ ባደረግህ ጊዜ፥ ወረድህ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ። ይላል።

📖(ማቴዎስ 3፥11)
“እኔስ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ #በእሳትም ያጠምቃችኋል፤” ይላል።

📖(ሐዋርያት 2: 1-4)
¹ በዓለ ኀምሳ የተባለውም ቀን በደረሰ ጊዜ፥ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው አብረው ሳሉ፥
² ድንገት እንደሚነጥቅ ዓውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምፅ መጣ፥ ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው።
³ እንደ #እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች ታዩአቸው፤ በያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው።
⁴ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር። ይላል።

ማንም ሊቋቋመው ወይም በፊቱ ሊቆም የማይቻለው #እሳት፣ ማንም ሊያግደው የማይቻለው "ታላቅ እሳት"፣ ያገኘውን ሁሉ እሾሁን፣ ጉቶውን፣ ጋሬጣውን የሚበላ "የሰድድ እሳት"፣ ድንጋዩን የሚያቀልጥ፣ የሚነጥረውን ከዝገቱ ለይቶ የሚያነጥር እሳት ነው። ትጉህ ገበሬ እሾህና ጋሬጣ የበዛበትን መሬት ከዝናብ በፊት በ"እሳት" አቃጥሎ ለዝናብ ወራት እንደሚያዘጋጅ "ሪቫይቫል" ስመጣ በእንዲህ ይመሰላል። በ"ሪቫይቫል" ጊዜ እግዚአብሔር እንደ ታላቅ ምሕረቱና ፍቃዱ "በእሳት" የሚበላውን ማንም ሊቋቋመው በማይችል "ታላቅ እሳት" እየበዛ ዝናቡን ደግሞ ያዘንብበታል።

#እግዚአብሔር አምላክ "ምድር ላይ መሥራት እስካላቆመ ድረስ" !! "አባት ሆይ" አሁንም በእኛ ዘመን !!!🙏
.....................................................
🌍🔥🌏🔥🌎🔥🌍🔥🌎🔥🌏

23/01/2026

🔥 #ሪቫይቫል🔥
#ሪቫይቫል:- የሚለው የእንግሊዝኛው ቃል "ሪ" እና "ቫይቫል" ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ነው። "ሪ" ማለት #እንደገና ማለት ሲሆን "ቫይቫል" ማለት ደግሞ ማለት ነው።
ሕይወት ለነበረው ነገር ግን ያ ሕይወት እየደከመ፣ እየደበዘዘና ወደ ሞት እየተቃረበ ለሄደው ዳግመኛ ማለት ነው። ስለዚህ #ሪቫይቫል ማለት እንደገና ወደ ሕይወት መምጣት ወይም ከሞት መነሣት ማለት ይሆናል።

በታሪክም እንደታየው "ሪቫይቫሎች" እግዚአብሔር መንፈሳዊ ውድቀትንና ማሽቆልቆል ን በመገደብ መንፈሳዊ ሕይወት የሚዘራበት፣ እንደገና መታደስ የሚያመጣበት መንገድ ነው። ስለዚህ "ሪቫይቫል" ከእግዚአብሔር ጉብኝትና በመሞት ላይ ያለውን ነገር እንደገና ሕያው መሆንን ያመለክታል።
እግዚአብሔር "ሪቫይቫልን" በመላክ በመዳከም ላይ ያለች ቤተክርስቲያንን ከመውደቅ የሚያድስበትና "በዓለም ላይ የወንጌል ተልዕኮ" የሚፈጽምበት መንገድ ነው። "ሪቫይቫል" እግዚአብሔር የቤተክርስቲያንን ሕያውነት ይጠብቃል፣ መንግሥቱን በየስፍራው ያስፋፋል፣ የአማኞችን ቁጥርም ያሳድጋል።

"ሪቫይቫል" እግዚአብሔር በመንፈሱ አማካይነት ሰዎችን ከኃጢአታቸውና ከቸልተኝነታቸው ወደ እውነተኛ ንስሐ ለመመለስ፣ ከዓላማው ጋር ለማቀራረብና የእርሱን ሥራ ለመፈጸም በሰዎች ሕይወት የምሠራው ነው።
"እውነተኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሪቫይቫል" እግዚአብሔር ከሰው እጅ ውጭ በሆነ ሁኔታ የቤተክርስቲያንን ሁኔታ ፈጽሞ ለመለወጥና ቅዱስ መገኘቱን በሥራና በታላቅ ኃይል ለመግለጥ በሉአላዊነቱ የሚያደርገው መገለጥ ነው። በሰው እቅድና ጥረት የሚመጣ ከሆነ ያ "ሪይቫይል" አይደለም። "ሪቫይቫልን" መግለጽ የማንችለው እግዚአብሔርን መግለጽ ስለማንችለው ነው።

#ሪቫይቫል የሚለው ቃል እንደ ገና ወደ ሕይወት መመለስ ማለት እንደመሆኑ ሪቫይቫል ከመምጣቱ በፊት የሞተ፣ ቸል የተባለ ወይም የተረሳ ነገር መኖሩን ያመለክታል። ለቤተክርስቲያን መቀዝቀዝ ወይም መዳከም ምልክቶች ከሚሆኑት መካከል ጥቂቶቹ:-
1).አምልኮው ልማዳዊና ሥርዓትን መጠበቅ ብቻ እየሆነ መሄድ፣ ሕያውነቱን ማጣት።
2).እግዚአብሔር አለመፈራትና የቅድስና መጉደል መብዛት።
3).በአማኞች ሕይወት ከዓለም ጋር መመሳሰል በስፋት መታየት።
4).ቤተክርስቲያን ወደ ዓለም የመሄድ ጥሪዋን መዘንጋት።
5).እግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል መኖሩና የክብሩ መገኘት እስከማይታወቅ ድረስ መሆን..ወዘተ ናቸው።

በዕድሜ የገፉና የቆዩ ናቸው የሚባሉት ክርስቲያኖች ለእግዚአብሔር ነገር ግድየለሽ ሆነውና በመንፈሳዊ ሕይወት ቀዝቅዘው፣ ወጣቶችም በእምነታቸው ሥር ያልሰደዱና አለማውያን ሆነው፣ በአጠቃላይ ቤተክርስቲያን በመዳከም ላይ ትገኛለች።
"ሪቫይቫል" ቤተክርስቲያንን ወደ ቀድሞ ሕይወቷ፣ ወደ "ሐዋርያት ዘመን" ሕይወትና ልምምድ መመለስ ነው። ባአከባቢም ህብረተሰብ ላይ ደግሞ መንፈሳዊ ለውጥን "መነቃቃትን" ያስከትላል። እግዚአብሔር የሚልከው "መንፈስ ቅዱስ" በመጣ ጊዜ ቤተክርስቲያንን "ያድሳታል፣ እንደገና ሕይወት ይዘራባታል።" #ሪቫይቫል ሲመጣ ወንጌል በኃይል እንድሰበክ በማድረግ ጌታን የማያውቀውን ሕብረተሰብ ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ዳግመኛ እንድወለዱ እንዲሁም ከለላ ጊዜ በላቀ ሁኔታ መልካም ሥራዎች እንድሰሩ ያደርጋል።
#ሪቫይቫል እንግዲህ በቤተክርስቲያን የጀመረው ሕይወት ወደ አከባቢው ሁሉ በመዛመት ይጀምራል፣ ምድሪቱንም ይደርሳል። ስለሆነ የ"ሪቫይቫል" አካሄድ ከውስጥ ወደ ውጭ ነው ማለት ይቻላል። #ሪቫይቫል የሚጀምረው በአማኞች መካከል ሆኖ በውስጥ ያሉት በታላቅ የእግዚአብሔር "ጉብኝት" ከተጎበኙ በኋላ "ውጭ" ወዳሉት ይዛመታል።

Photos from Missionary Of God Ministry's post 21/01/2026


ወንጌላዊ ፀጋአብ በቀለ፣በተለይ የጻሐፋቸው መጽሐፍቶች ትኩረታቸውን የሚያደርጉት (ዓለምን በወንጌል መድረስ) ላይ ያተኮሩ ናቸው።
📚የጻሐፋቸው የመጽሐፍቶች ርዕሶች:-
1). ባለራእነት ቅጽ 1።
2). ባለራእነት ቅጽ 2።
3). ተሃድሶ ቅጽ 1።
4). ተሃድሶ ቅጽ 2።
5). ቤተክርስቲያን ከፖለቲካ ውጭ ናትን?።
6). የኢትዮጵያ አብያተክርስቲያናት ህብረት ዓለምን በወንጌል የመድረስ ጥሪ ።
7). ሪቫይቫል።
8). ወንጌል እና ባህል።
....ወዘተ ናቸው።
#ክርስቲያን የሆነ ሁሉ እኝን መጽሐፍቶች አግኝቶ፣ ገስቶ በቤቱ ማንበብ መቻል አለበት ብየ አምናለሁ። በተለይ እግዚአብሔር #ለምሽን(ዓለምን በወንጌል ለመድረስ) እያዘጋጃችው ያላችሁ ሰዎች እኝን መጽሐፍቶች ማንበብ አማራጭ የለሌው ጉዳይ ነው!
.................................................
🌍🔥🌏🔥🌎🔥🌍🔥🌎🔥🌏

Photos from Missionary Of God Ministry's post 11/01/2026

🎯 ☂️
(Spiritual Warfare)
ለሁሉም ክርስቲያን የዲያብሎስን ሽንገላ ለማሸነፍ መንፈሳዊ ውጊያ አውቀን እንደት መዋጋት እንዳለብን የሚያስተምረን 📚 #መጽሔት መንፈሳዊ ውጊያ በምል ርዕስ የተዘጋጀ
#በዶ/ር_ደስታ_ላንገና የተጻፈውን አስገራምህ መጽሔት እንድታነቡ ይመከራል!

Photos from Missionary Of God Ministry's post 30/12/2025

📚
እግዚአብሔር አምላክ #ለሚሽን(ዓለምን በወንጌል ለመድረስ)እያዘጋጃቸው ያላቸው ሰዎች "ወንጌል እና ባሕል" በምል ርዕስ የተዘጋጀውን የጻሐፈውን #አስደናቅ መጽሐፍ እንድታነቡ ይመከራል። በተለይ በተለያዩ ሀገራት፣ ቋንቋና ባሕል ወንጌልን ለዓለም ለማድረስ የሕዝቡን #ባሕልን ማወቅ #ለሚሽን አገልግሎት ዋናውና የመጀመሪያው ጉዳይ ነው።
....................Join Us.....................
🔶 : 🔶
🔶 : Missionary Of God Ministry🔶
🔶 : Missionary Of God Ministry🔶
....................SHARE.....................
🌍🔥🌏🔥🌎🔥🌍🔥🌎🔥🌏

24/12/2025

🔥
✅የአሁኗ ቤተክርስቲያን ውስጥ እጅግ አሳፋሪ፣ #በአሕዛብ ዘንድ የምደረጉ ልማዶች በእኛም ዘንድ የተለመዱ መሆናቸው፣ ወንጌል በአንድ እጅ ይዘው በለላኛው እጅ ደግሞ (ጥንቆላን፣አስማት፣መተት፣ሞራ ገላጭነት፣ጣኦት ማምለክ...ወዘተ) የመሳሰሉትን በክርስትያኖች ዘንድ የተለመደ እየሆነ መቷል። ይህ በክርስትያኖች ዘንድ እጅግ አሳፋር ተግባር ነው። ክርስቲያን ሆኖ ምድራዊ ሀብትን ለማካበት፣ገንዘብን ለማግኘት..ወዘተ #ጦንቃይ ቤት በስውር የምሄዱ አሉና። ይህ በእግዚአብሔር ዘንድም #አጸያፊ ተግባር ነው።

✅ለቤተክርስቲያን እና (መጋብዎች፣ አስተማረዎች፣ ወንጌላውያን፣ ሐዋርያት፣ ነቢያት፣ ዘማሪዎች፣ ዲያቆናት..ወዘተ) እና ባጠቃላይ #የተሃድሶ ጩኸትና ጥሪ እናስተጋባለን!። ለጋራ ጥቅም ስባል ተሃድሶ ያስፈልገናል ብለን እናምናለን። የዚህ ዘመን ክርስቲያን ሁሉ የአድስ ኪዳን ካህናት አገልጋዮች ነን።

✅እኔ #ነህምያ፣ ዕዝራ፣ዙርባበል #ተሃድሶ እንደት አመጡ??🤔
#አንደኛ:- ሕዝቡ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በአንድ ሃሳብ ሆነው በእውነተኛ ንሳሃ እራሳቸውን አዋርደው፣ ንሳሃ ገቡ።
#ሁለተኛ:- ካህናቱና ለዋዊያኑ እንድቀደሱ አደረጉ
#ሦስተኛ:-ቤተ መቅደሱንና እቃዎችን ቀደሱ።
#አረተኛ:- ሕዝቡ እንድቀደሱ አደረጉ።
#አምስተኛ:- የሕጉ መጽሐፍ ተነበበ፣ አስተማሩ።
#ስድስተኛ:- የተለያዩ አምልኮ ሥርዓቶች አደረጉ።
በዚህ መንገድ #ተሃድሶ አደረጉ።

✅ #ቤተክርስቲያን እና #አገልጋዮች ተሃድሶ ለማምጣት ምን ማድረግ አለብን??🤔

#ቤተክርስቲያን እና #አገልጋዮች በአንድ ሀሳብ፣ በአንድ ልብ ተሃድሶን በቤተክርስቲያን ለማምጣት ጠንካራ ውሳኔ መወሰን፣ እርምጃ በአፋጣኝ መውሰድ መቻል አለባት። የሳተውን አገልጋይ፣ነቢይ፣ ሐዋርያ፣ ሽማግለ፣ ፓስተር፣ አስተማርህ፣ ወንጌላዊ፣ ዘማሪ፣ሕዝቡን ሁሉ ወደ እውነተኛ ንሳሃ መመለስ ይገበናል።

✅በቤተክርስቲያን ያለውን ነገር ሁሉ (መድረኮቻንን፣ ስብከታችንን፣ ትምህርቶቻችንን፣ ትንቢቶቻችንን፣ መዝሙሮቻችንን፣ ፀሎቶቻችንን..ወዘተ) በእግዚአብሔር ቃል መሠረት መመርመር፣መለወጥ፣ማደስ አለብን። በቤተክርስቲያን ላይ መንደድና መቀጣጠል መቻል አለበት።
ይህ የሁሉም ነው። #ዘመናችንን በከንቱ የምንጨርስ በእግዚአብሔር ላይ የምናፈዝ፣ሰዎች ሳኖን እግዚአብሔር አምላክ ለቤተክርስቲያን #ተሃድሶ የምናመጣ ሰዎች ያድርገን።
📖“ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ።”
— ኤፌሶን 5፥16
.............ተፈፀመ🙏...

24/12/2025

🔥
✅70(ሰባው) ዓመት ከተፈፀመ በኋላ እግዚአብሔር በነቢያቱ አፊ እንደተናገረ ቅረታዎችን ሕዝብ እኔ(ዕዝራ፣ ዙሩባበል፣ ኢያሱ፣ መርዶክዮስ፣ አስተር..ወዘተ) ወደ ሀገራቸው፣ኢየሩሳለም ተመለሱ። ነህምያም የኢየሩሳሌም ቅጥር መፈረስ፣ የቤተ መቅደስ መቃጠል ከወድሞቹ ሰምቶ ቅጥሩን ለማደሰ መጣ። ቅጥሩንም አደሱ፣ ቤተ መቅደሱንም ሠሩ። ከዚያ በኃላ እስራኤል ሁሉ ማቅ ለብሰው በእግዚአብሔር ፊት የአባቶቻቸውን ሃጢያታቸውን፣ የሕዝቡን ሁሉ ሃጢያተ ተናዘዙ፣ የሕጉ ቃል ተነበበ፣ የቤተ መቅደስ ሥርዓቶች ተደረጉ። ባጠቃላይ #ተሃድሶ አደረጉ። ተሃድሶ ማለት ይህ ነው።

✅በእስራኤል ታሪክ በንጉስ ሳኦል ዘመን፣ ካህናቱም ሳይቀሩ፣ ሕዝብም በቤተ መቅደስ አጸያፍ ሃጢያት በእግዚአብሔር ፍት ሠሩ፣ ኤልም ዝም አለ፣ ንጉሱም ሳኦልም ሃጢያትን ሠራ እግዚአብሔር ተቆጣ፣ በፊልስጠማዋያን ታቦቱ ተማረከ። የእግዚአብሔር ክብር ከቤተ መቅደሱ ሄደ፣ ተነሳ። ነገር ግን ንጉስ #ዳዊት ወደ ንግስና ወንበር ስመጣ አስቀድሞ "ታቦቱ በሳኦል ዘመን አልተፈለገምና" ብሎ ንጉስ ዳዊት ታቦቱን ከተማረከበት ፣የእግዚአብሔር ክብር፣ መገኘት እንደገና መለሰ። #ተሃድሶ ማለት ይህ ነው። እግዚአብሔር ፊት መፈለክ፣ ክብሩን መመለስ ነው።
✅እንዲሁም ዘመንም እንድሁ የእስራኤል ሕዝብ ጣኦቱን፣ መስገጃዎችን በመሰባበረ፣ በማስወገድ፣ የተዘጉትን ቤተ መቅደሶች በመክፈት፣ ሥርዓቶችን በማደስ፣ የክህነት አገልግሎት በማስጀመር፣ የሕጉን ቃል ማስተማር ሕዝቡን ከስህተት መንገድ ወደ እግዚአብሔር ዞር በማድረግ እውነተኛ #ተሃድሶ አመጡ።

✅ስለዚህ ለእኛም ለአሁና ቤተክርስቲያን ተሃድሶ ያስፈልገናል ብየ በግለ አምናለው። በእኛ ዘመን ላለው አመጽ፣ጥፋት..ወዘተ እውነተኛ ተሃድሶ ያስፈልገናል። የእግዚአብሔር ታቦት የሆነውን ኢየሱስን ወደ ቤተ መቅደሱ፣ ወደ ቦታው መመለስ፣ ክብሩን መፈለግና፣ ማምጣት የእኛ እጣ ፋንታ ጉዳይ ነው። የእኛ መኖር በሱ መኖርና መመለስ ላይ ይወሰናል። አሻፈረኝ፣ ምን አገባኝ፣ የምንል ከሆን ከእግዚአብሔር ቁጣ ፍርድ ማምለጥ የማይቻል ነው።
........ይቀጥላል......

23/12/2025

🔥
✅እግዚአብሔር ሰውን ፈጠረ መልካም እንደሆነ አየ። ያ የመጀመሪያ ሰው አዳም ነበረ ሁለተኛው ሰው ሄዋን ነበረች። ሁለቱም ሀጢያትን ሰሩ ከኤደን ገነት ተባረሩ፣ ኪዚያ ጊዜ አንስቶ የአዳም ልጆች፣ ዘሮች ሀጢያትን መስራት ሥራቸው አደረጉት። እግዚአብሔር ላይ አመጽ በይፋ ተጀመረ። የምገርመው ነገር በዚህ ሕዝብ አመጽ ውስጥ እግዚአብሔርን የምፈራ ጻድቅ ሰው ሐኖክ ነበረ፣ አሁንም የሕዝቡ አመጽ በርትቶ ቀጠለ፣ ሰዶምና ጎመራ ጋር ደረሰ። የሰው ዘር ከጥፋቱ የተነሳ በድን እሳት የምጠፋበት፣ የቀረውም በቁጣ ውሃ ጨርሶ የምጠፋበት ጊዜ ደረሰ።

አሁንም ከዚያ ሕዝብ መካከል አንድ ጻድቅ ሰው ተገኘ ኖህ ይባላል። የእስራኤል አመጽ አሁንም ቀጠለ ማቆሚያ የለውም እስከ አሁን ድረስም ቀጥሏለል። እግዚአብሔር የምፈሩ ሰዎችም እስከ መጨረሻ ድረስ አይታጡም።(አብርሃም፣ ይህሳቅ፣ ያዕቆብ፣ ዮሰፈ፣ ሙሴ፣ ኢያሱ፣ ኤልያስ፣ ኤልሳኤ፣ እዩ፣ ጌደኦን፣ ሳሙኤል፣ ዳዊት፣ ሕዝቅያስ፣ ኢዮብ፣ ኢዮሳፈጥ፣ ዳንኤል፣ ስድራቅ፣ ምስራቅ፣ አብድናጎ፣ ነህምያ፣ ዕዝራ፣ኢያሱ፣ ዙርባበል፣ መርዶክዮስ፣ ኤርሚያስ፣ ኢሳያሳ፣ ሕዝቀል..ወዘተ) ነበሩት ጌታ።

✅በዚህ ዘመንም እንኳን እግዚአብሔርን የምፈሩ፣የምወዱ፣የምታዘዙ ጥቅት ቅረታዎች አለው እግዚአብሔር። እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን፣ አመጸኞችን ያዋርዳል፣ይቀጣል፣ያጠፋቸዋል። እግዚአብሔር ለምፈሩ ግን የጽድቅ ፀሐይ ትወጣለች።
✅ስለዚህ ከምመጣው ከእግዚአብሔር ቁጣ ለማምለጥ፣ ለመዳን ምን እናድረግ በግልም እንደ ቤተክርስቲያንም??🤔
✅ ያስፈልገናል በግላችንም፣ እንደ ቤተክርስቲያንም ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ እራሳችንን አዋርደን ንሳሃ እንግባ፣ ወደ ቃሉ እንመለስ። እግዚአብሔር ላይ አመጽ መክፈት ለእስራኤልም አልበጀም። ያተረፉት ጥፋትን ብቻ ነው።

✅በእስራኤል ታሪክ ንጉስ ሰሎሞን ከሞተ በኃላ እስራኤል ሕዝብ ለሁለት እንደተካፈለ 10 ነገዶች ሰሜኑን ክፍል ስይዙ 2ቱ የይሁዳና የብንያም ነገዶች ደቡብን ክፍል ያዙ። ኪዚያ በኃላ ለሁለት ክፍል የተከፈለው የእስራኤል ሕዝብ አሁንም እግዚአብሔር ላይ ማመጽ ቀጠሉ፣ ጣኦት ማምለክ፣ ቤተ መቅደስን መዝጋትና መቆለፍ ወደ ጣኦት አምልኮ መግባት።
📖(መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ ምዕ. 36)
14፤ ደግሞም የካህናቱ አለቆች ሁሉ ሕዝቡም እንደ አሕዛብ ያለ ርኵሰት ሁሉ መተላለፍን አበዙ፤ በኢየሩሳሌምም የቀደሰውን የእግዚአብሔርን ቤት አረከሱ።
15፤ የአባቶቻቸውም አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡና ለማደሪያው ስላዘነ ማለዳ ተነሥቶ በመልእክተኞቹ እጅ ወደ እነርሱ ይልክ ነበር።
16፤ እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወጣ ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ይሳለቁ፥ ቃሉንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።
17፤ ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጕልማሶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጕልማሳውንና ቈንጆይቱን ሽማግሌውንና አሮጌውን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።
18፤ የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃ ሁሉ ታላቁንና ታናሹን፥ የእግዚአብሔርንም ቤት መዝገብ፥ የንጉሡንና የአለቆቹን መዝገብ፥ እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ።
19፤ የእግዚአብሔርንም ቤት አቃጠሉ፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር አፈረሱ፥ አዳራሾችዋንም በእሳት አቃጠሉ፥ መልካሙንም ዕቃዋን ሁሉ አጠፉ። ይላል።

✅70 ዓመት ከተፈፀመ በኃላ እግዚአብሔር በነቢያቱ አፊ እንደተናገረ ቅረታዎችን ሕዝብ ጨምሮ እኔ(ዕዝራ፣ ዙሩባበል፣ ኢያሱ፣ መርዶክዮስ፣ አስተር..ወዘተ) ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።
......ይቀጥላል

Want your school to be the top-listed School/college in Dilla?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Address


Dilla