Woizero Siheen Polytechnic College

Woizero Siheen Polytechnic College Welcome to the Official page of Woizero Siheen Polytechnic College (Dessie). We will keep y

የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ታሪክ

የወ/ሮ ስኂን ት/ቤት በንጉሥ ሚካኤል ልጅ በወ/ሮ ስኂን ሚካኤል በ1922 ዓ.ም ሳላይሽ በሚገኘው የልጃቸው ጃንጥራር ኃ/ማርያም አስፋው ርስት ላይ በ25,000 ብር ተሠራ፡፡ ይህም በሀገራችን ዘመናዊ የትምህርት ታሪክ ከተመሰረቱት የመጀመሪያ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ ያደርገዋል፡፡ ላለፉት 89 ዓመታት በተለያዩ የዕድገት ደረጃዎች ውስጥ አልፎ አሁን ካለበት የፖሊቴክኒክነት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ በነዚህ ጊዜያት በሀገር አቀፍም ይሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ በሙዚቃው፣ በፖለቲካው እና ኢኮኖሚው ትልቅ ዝናን ያተረፉ ዜጎች የተገኙበት የትምህርት ተቋም ነው፡፡ ከዚህ ቀጥሎ በዘመን ቅደም ተከተል የ

ቀረበው አጭር ጽሑፍ ይህንኑ ታሪክ ያሳያል፡፡

ታሪካዊ ዳራ እና እድገቱ

በ1920 ዓ.ም ወ/ሮ ስኂን ሚካኤል ከራሳቸው 25000 ማሪያ ቴሬዛ (ጠገራ ብር) እና በራሳቸው ርስት ላይ ከህልፈተ-ሕይወታቸው አስቀድመው ለልጃቸው በሰጡት ኑዛዜ መሰረት ከ2 ዓመታት በኋላ በ1922 ዓ.ም ደሴ ከተማ ሳላይሽ አካባቢ በ4 የመማሪያ ክፍሎች ተመሰረተ፤
በ1939 ዓ.ም የተማሪ ቁጥር በመጨመሩ ምክንያት ቁጥራቸው በርከት ያሉ መማሪያ ክፍሎችን የያዘ አዲስ ሕንፃ ተገንብቶ አሁን ወዳለበት ዋናው (ስኂን) ግቢ ተዛወረ፡፡ በዚያን ወቅት ከ1ኛ - 8ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምር ነበር፡፡ አሁን ዋናው ግቢ (ስኂን ግቢ) የሚገኝበት ቦታ ላይ ትምህርት ቤቱ አንዲሰራ የመሰረት ድንጋይ የጣሉት የስኂን ሚካኤል የልጅ ልጅ አልጋወራሽ መርድ አዝማች አስፋወሰን ኃይለስላሴ ናቸው፡፡ በዚህ ወቅት 15 ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች ተሰሩ፡፡
በ1950 ዓ.ም ወደ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከፍ አለ፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ለመስጠት የተቀበላቸው ተማሪዎች ቁጥርም 63 ደርሶ ነበር፡፡
በ1953 ዓ.ም የመጀመሪያዎቹ የ12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ለሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና (ለሎንዶን ጂ.ሲ.ኤ. ፈተና) እንዲቀመጡ ተደረገ፡፡
በ1953 ዓ.ም እቴጌ መነን /የስኂን ሚካኤል ልጅ/ ለተለያዩ የሙያ ሥልጠናዎች የሚያገለግል ሕንፃ ቮኬሽናል ግቢ በ160,000 ብር አስገነቡ፡፡ በዚህ ወቅት በቀለም ትምህርት ዘርፍ ብቻ ተማሪዎችን ማስተማር በቂ ሆኖ ባለመገኘቱ ከቀለም ትምህርት ጐን ለጐን በመምህርነት ሙያ፣ በእርሻና ተግባረዕድ ሙያወች ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡ ይህ ሁኔታ ትምህርት ቤቱን በሀገሪቱ የመጀመሪያው አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሆን አድርጐታል፡፡
1956 ዓ.ም የስኂን ት/ቤት የሙዚቃ ባንድ ተቋቋመ፡፡ ባንዱ ሲቋቋም 40 ተማሪዎች የነበሩ ሲሆን መምህሩም ሚ/ር ሮናልድ ቤል የተባለ አሜሪካዊ ነበር፡፡
በ1956 ዓ.ም የ1ዐኛ ክፍልን ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች የ2 ዓመት የሙያ ሥልጠና በተለያዩ መስኮች በመውሰድ ዲኘሎማ ማግኘት ጀመሩ፡፡ ይህ ሁኔታ እስከ 1976 ዓ.ም ቀጠለ፡፡
በ1972 ዓ.ም የት/ቤቱ ስም የካቲት 66 አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት፤ ከዚያም የካቲት 66 የቀለም ቴክኒክና ሙያ ት/ቤት በሚል ተቀይሮ፣ ከዚያም የካቲት 66 የቀለም፣ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት ተባለ፡፡
በ1980 ዓ.ም በ10+3 የቴክኒክና ሙያ መርሀ-ግብር ስልጠና መስጠት ጀመረ
በ1977 ዓ.ም የ1ዐኛ ክፍል ትምህርታቸውን በጥሩ ውጤት ያጠናቀቁ ተማሪዎች በተለያዩ የሙያ መስኮች ለ2ኛ ደረጃ ሠርቲፍኬት ሥልጠና ጀመሩ፡፡ ይህም ሁኔታ እስከ 1980 ዓ.ም ቀጠለ፡፡ ከዚህ በኋላ የሥልጠናው ጊዜ ከ2 ዓመት ወደ 3 ዓመት ከፍ አለ፡፡
በ1984 ዓ.ም የት/ቤቱ ስም ወ/ሮ ስኂን የቀለም ቴክኒክና ሙያ ት/ቤት ተብሎ ተሰየመ፡፡
በ1992 ዓ.ም ሲሰጡ ከነበሩት የሙያ ስልጠና ዓይነቶች በተጨማሪ የኮንስትራክሽን የሥልጠና ዘርፍ ተከፈተ፡፡
በ1993 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ የቴክኒክና ሙያ ተቋም ሆነ፡፡
በ1994 ዓ.ም የት/ቤቱ ስም ወ/ሮ ስኂን ቴክኒክና ሙያ ተቋም በሚል እንዲጠራ ተደርጐ በተለያዩ የሥልጠና ዘርፎች በመደበኛና በማታ መርሃ-ግብር የ1ዐ+1 እና 1ዐ+2 ሥልጠናዎች በመስጠት በሰርቲፍኬት ደረጃ ማስመረቅ ጀመረ፡፡
በ1996 ዓ.ም ተቋሙ ከደሴ ቴክኒክና ሙያ ተቋም ጋር ተቀላቀለ፡፡
በ1996 ዓ.ም ተቋሙ በጤና ኤክስቴንሽን ሙያ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ሴት ሠልጣኞችን ተቀብሎ ማሰልጠን ጀመረ፡፡
የሙያ መስኮቹም 19 ደረሱ፡፡
በ2000 ዓ.ም ተቋሙ ከደሴ ቢዝነስና ሥራ አመራር ኮሌጅ ጋር ተዋህዶ ስሙም ወ/ሮ ስኂን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ በሚል ተቀየረ፡፡
በ2003 ዓ.ም ኮሌጁ ወደ ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አደገ፡፡ በዚሁ ዓመትም በደረጃ 5 ስልጠና መስጠት ጀመረ፤


ስልጠና የሚሰጥባቸው ግቢዎች፡-
1. ስኂን ካምፓስ (ዋናው ግቢ)፡- ኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ፣ ሆቴል ባህልና ቱሪዝም፣ ከተማ ግብርና እና ከተማ አገልግሎት (Urban Agriculture& Municipality)፣ እንዲሁም የጨርቃጨርቃ እና አልባሳት (Garment &Textile) ስልጠና ዘርፎች
2. ቮኬሽናል ካምፓስ (መነን ህንጻ)፡ ብረታ ብረት ምህንድስና (Metal Manufacturing & Engineering) ዘርፍ ማሰልጠኛ
3. ሆጤ ካምፓስ፡ የኮንስትራክሽን ስልጠና ዘርፎች ማሰልጠኛና የማምረቻ ማዕከል (ማምረቻ ዩኒትን) የያዘ
4. መርሆ ካምፓስ (የቀድሞ የአልጋወራሽ ቤተ-መንግስት የነበረና በኋላም ቢዝነስ እና ስራ አመራር ኮሌጅ የተመሰረተበት)፡ አሁን የInformation & Telecommunication ስልጠና ዘርፍ የሚሰጥበት፤ እንዲሁም የመርሆ ቤተ-መንግስት የሚገኝበት
5. ዳውዶ ካምፓስ (የቀድሞው SDC ተቋም)፡- የአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጅ እና የእንጨት ስራ (Furniture) ዘርፎች ማሰልጠኛ ናቸው፡፡


ኮሌጁ አሁን ያለበት ሁኔታ፡-

ከላይ እንደተገፀው ኮሌጁ በ2000 ዓ.ም ቀደም ሲል የተመሰረቱትን የወ/ሮ ስኂን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋምን፤ የደሴ ቢዝነስና ሥራ አመራር ኮሌጅን እና የደሴ ሙያ ማሰልጠኛ ተቋምን በማዋሃድ የተደራጀ ሲሆን፤ ወደ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅነት ደረጃ ያደገው ደግሞ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ኮሌጁ ያለበትን ሁኔታ ስንመለከት

 ስልጠና የሚሰጠው ከደረጃ 1 እስከ 5 በ0 ዋና ዋና ስልጠና ዘርፎችና ከ56 በሚበልጡ ሙያዎች ሲሆን እያንዳንዱ ሰልጣኝ በየደረጃው ተመዝኖ ብቁ እንዲሆን ይደረጋል፡፡ በ2011 በጀት ዓመት እስከ ሚያዚያ 2011 ዓ.ም ድረስ ባለው ሁኔታ 5975 የሚጠጉ ሰልጣኞችን እያሰለጠነ ይገኛል፡፡
 አዳዲስ የሙያ መስኮች ከመከፈታቸው በፊት የአካባቢውን ገበያ እና ኢንዱስትሪ ፍላጎት የዳሰሳ ጥናት ይደረጋል፤
 ስልጠናው ፕሮጀክትን መሰረት ያደረገ ነው፤
 ከስልጠናው ጎን ለጎን ሰልጣኞች ቁጠባ እንዲቆጥቡ ይደረጋል፤ ከዚያም ቅድመ-ኢንተርፕራይዝ እንዲመሰረቱ እድል ይፈጠርላቸዋል፡፡
 ከ1994 ዓ.ም (ሙሉ በሙሉ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና መስጠት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ) እስካሁን ድረስ ከ45 ሺህ በላይ ዜጎች በበርካታ የሙያ አይነቶች በቀንና በማታ ፕሮግራም ተመርቀው ራሳቸውን ከመቻል አልፈው ለሌሎች ስራ-አጥ ወገኖች የስራ እድል ፈጣሪ መሆን የቻሉ ዜጎችን አስመርቋል፡፡
 ከምረቃ በኋላ ሰልጣኞች ያሉበትን የስራ ሁኔታ በማጥናት ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡
 ለደንበኞች በሚሰጠው አገልግሎት የISO 9001:2008 ስታንዳርዶችን ያሟላ በመሆኑ በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ አማካኝነት የጥራት ስራ አመራር ማረጋገጫ በ2006 ዓ.ም አግኝቷል፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ስታንዳርዱን ማስጠበቁን በኤጄንሲው በኩል ሰርቬይላንስ ኦዲት በየዓመቱ ተካሂዶ ማረጋገጫ ተሰጥቷል፡፡ ይህ የሚያሳየው ደግሞ የኮሌጁ አገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርዶችን ያሟላ መሆኑን ነው፡፡ አሁን ላይ ደግሞ ISO 19011:2015ን አሰራርን የዘረጋ ሲሆን የማረጋገጫ ሰርቲፊኬቱን ለማግኘት በሂደት ላይ ነው፡፡
 ከተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የተሻሉ ተሞክሮዎችን በማስፋት ተግባራዊ አድርጓል፡፡
 የካይዘን ፍልስፍና ወደሀገራችን ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ሁሉም የስልጠና ሾፖችና የስራ ክፍሎች በካይዘን እንዲደራጁ ተደርጓል፡፡
 በተመሳሳይ ሌላኛውና ትልቁ ተልዕኮው ደግሞ የደንበኞቹን እና የአካባቢውን መካከለኛና አነስተኛ ኢንዱስትሪ የቴክኖሎጅ ፍላጎት መሰረት ያደረገ የምርትና ማምረቻ ቴክኖሎጅ በማላመድ እና በፈጠራ በመስራት፤ ብሎም በማሸጋገር ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችንና የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እያደረገ ነው፡፡
 በተለያዩ የስራ መስኮች ለተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በአራቱም የድጋፍ ማዕቀፎች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት በመስጠት የአሰራር፣ የክህሎት፣ የአመለካከት እና የኢኮኖሚ አቅማቸውን ከፍ ከማድረግ አልፎ ወደመካከለኛ የኢንዱስትሪነት እንዲያድጉ የሚያስችል አቅም እየፈጠረ ነው፡፡
 የአሰልጣኝ መምህራንንና የአስተዳደር ሰራተኛውን አቅም ለመገንባት የረጅምና የአጭር ጊዜ ስልጠና ያመቻቻል፡፡ በተጨማሪም ዘመናዊና ደረጃቸውን የጠበቁ የማሰልጠኛ ማሽኖችና ግብዓቶችን በመግዛት፣ ወርክሾፖችን በመገንባት የራሱን አቅም እየገነባ ነው፡፡
 በቀጣይም በሀገር አቀፍ ደረጃ ተመራጭ የቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት የመሆን ዋነኛ ዓላማ አለው፡፡
 ኮሌጁ ከዋና ዋና ተልዕኮዎቹ ጎን ለጎን በተለያዩ ጊዜያት በርካታ ማህበራዊ ድጋፍ እያደረገ ነው፡፡ ከዚህ መካከል በቅርቡ ለክፍለ-ከተሞች ከ300 በላይ የአዳራሽ ወንበሮች፣ በርካታ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩና በአዳዲስ የተተኩ ኮምፒዩተሮች፣ ለአቻ ተቋማት (ኮሌጆች) የጋርመንትና ቴክስታይል ማሽኖች እና ያገለገሉ ኮምፒዩተሮች እንዲሁም አንድ የመስክ መኪና፣ ለአረጋዊያን በየዓመቱ የተደረገ የአልባሳት ድጋፍ፣ ከተለያዩ ቦታዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ከስታፉ እና ከኮሌጁ የተደረገ የፋይናንስ እና የቁሳቁስ ድጋፍ፣ ለ5 ኅፃናት በፀረ-ኤድስ ፈንድ በየወሩ ቋሚ የገንዘብ ድጋፍ እና በየ6 ወሩ ደግሞ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ ከብዙ በጥቂቱ የሚጠቀሱ ባለፉት 4 ዓመታት ብቻ የተደረጉ ድጋፎች ናቸው፡፡

17/08/2026
በወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የሙያ ብቃት ምዘና በዛሬው ዕለት መሰጠት ተጀምሯልደሴ፡-ነሀሴ 11 /2018ዓ.ም (ወስፖኮ)
17/08/2026

በወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የሙያ ብቃት ምዘና በዛሬው ዕለት መሰጠት ተጀምሯል
ደሴ፡-ነሀሴ 11 /2018ዓ.ም (ወስፖኮ)

የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የባለድርሻ አካላትና የትብብር ሥልጠና ፎረም ምስረታ አካሄደደሴ፡ ሐምሌ 09/2018 ዓ.ም. (ወስፖኮ)ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከደሴ ከተማ አስተዳደር ስራ...
15/08/2026

የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የባለድርሻ አካላትና የትብብር ሥልጠና ፎረም ምስረታ አካሄደ
ደሴ፡ ሐምሌ 09/2018 ዓ.ም. (ወስፖኮ)
ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከደሴ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት መምሪያ ጋር በጋራ በመሆን ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር፣ የግል ዘርፍ ተቋማት፣ የመንግሥት ተቋማት፣ የኢንዱስትሪና ንግድ ድርጅቶች ጋር ያለውን ትስስርና ትብብር በማጠናከር የሥልጠናውን ጥራትና ከሥራ ዓለም ጋር ያለውን ተገቢነት ለማሳደግ የባለድርሻ አካላት የትብብር ሥልጠና ፎረም አቋቋመ።
የፎረሙ ምስረታ ዋና ዓላማ ኮሌጁ ስልጠናን በትብብር በመስጠት የሥልጠናውን ጥራት የተሻለ ለማድረግ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን የተቀናጀ ትብብር ማጠናከር፣ የሙያ ሥልጠናዎች የገበያ ፍላጎትን ያማከሉ እንዲሆኑ ማድረግ፣ ለሰልጣኞች የተግባር ልምምድና የሥራ ዓለም ተሞክሮ የሚያገኙበትን ዕድል ማስፋት እና ከምረቃ በኋላ ወደ ሥራ የመግባትና ሥራ የመፍጠር አቅማቸውን ማሳደግ ነው።
ፎረሙ በEducation and Skills for Employability (EASE) Project ድጋፍ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የኮሌጁን የሥልጠና አሰጣጥ ከሥራ ዓለም ፍላጎትና ከኢንዱስትሪ እውነተኛ ፍላጎት ጋር ለማገናኘት የሚያግዝ የትብብር መድረክ ሆኖ ያገለግላል። በዚህም በኩል የሥልጠና ፕሮግራሞችን በጋራ መገምገም፣ የሥራው ዓለም የሚፈልጋቸውን ክህሎቶች መለየት፣ የተግባር ሥልጠናና የኢንዱስትሪ ልምምድ ዕድሎችን ማስፋት እና የሰልጣኞችን የሥራ ተገቢነት ማሳደግ ይቻላል።
በፎረሙ ውይይት ወቅት የሙያ ሥልጠናን ከሥራ ዓለም ጋር በተግባር ለማገናኘት የሚያስፈልጉ የትብብር መስኮች በስፋት ተነስተዋል። በተለይም ሰልጣኞች በኢንዱስትሪና በተለያዩ የሥራ ቦታዎች የተግባር ልምምድ እንዲያደርጉ፣ የሥራ ዓለም ተቋማት በሥልጠና ሂደት እንዲሳተፉ፣ የሙያ ክህሎትና የሥራ ገበያ ፍላጎት መረጃዎች በመለዋወጥ የሥልጠና ፕሮግራሞች ተገቢነት እንዲጨምር እና ለተመራቂዎች የሥራ ዕድል እንዲፈጠር ትኩረት ተሰጥቷል።
በተጨማሪም ፎረሙ የሰልጣኞችን የተግባር ክህሎት ብቻ ሳይሆን የሥራ ፈጠራ አቅም፣ የሥራ ሥነ-ምግባር፣ የቡድን ሥራ፣ የችግር መፍታት እና የግንኙነት ክህሎት እንዲዳብር የሚያግዙ የጋራ ሥራዎችን ለማከናወን እንደ ዋና የትብብር መድረክ እንዲያገለግል ተጠቁሟል።
በመድረኩ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላትም በቀጣይ ከወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በቅርበትና በቀጣይነት በመሥራት የሙያ ሥልጠናን ከሥራ ዓለም ጋር ለማገናኘት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል። በተለይም ሰልጣኞችን በተግባር ሥልጠና ማሳተፍ፣ የሥራ ዕድልና የሥራ ምደባ ዕድሎችን ማመቻቸት፣ የሥራ ገበያ መረጃ ማጋራት እና የሙያ ሥልጠናውን ጥራት ለማሻሻል በጋራ ለመሥራት ቃል ገብተዋል።
በአጠቃላይ የባለድርሻ አካላት የትብብር ሥልጠና ፎረሙ መመሥረቱ የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን ከሥራ ዓለም ጋር በተግባር የሚያገናኝ ጠንካራ የትብብር ሥርዓት ለመፍጠር ትልቅ እርምጃ ነው። ይህም ለሰልጣኞች የተግባር ልምድና ክህሎት እንዲያገኙ፣ ገበያው የሚፈልገውን ብቃት እንዲያዳብሩ፣ የሥራ ዕድል እንዲያገኙ እና የራሳቸውን ሥራ ለመፍጠር አቅም እንዲኖራቸው የሚያግዝ ሲሆን፣ ኮሌጁም የሥራ ገበያን የሚያሟሉ ብቁ፣ ተወዳዳሪና ምርታማ የሰው ኃይል ለማፍራት የሚያደርገውን ጥረት ያጠናክራል።

15/08/2026
ማስታወቂያ
11/08/2026

ማስታወቂያ

በወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የሕይወት ክህሎት ስልጠና መስጠት ተጀመረደሴ:-01/12/2018ዓ.ም(ወስፖኮ)     ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በEducation and Skills for Em...
07/08/2026

በወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የሕይወት ክህሎት ስልጠና መስጠት ተጀመረ
ደሴ:-01/12/2018ዓ.ም(ወስፖኮ)
ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በEducation and Skills for Employability (EASE) ፕሮጀክት በዓለም ባንክ ድጋፍ ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች Internal Displaced Persons (IDPs): የሕይወት ክህሎት (Life Skill) ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች የመግባቢያ ክህሎት፣ የችግር አፈታት፣ የሥራ ዝግጁነት እና የሕይወት ክህሎቶችን በማጎልበት ሥራ ፈጠሪ እንዲሆኑ እና ራሳቸውን እንዲችሉ ያግዛቸዋል።

ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በቀጣይም ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች (IDPs): ጥራት ያለው የቴክኒክ ክህሎት ስልጠና በመስጠት ለማህበረሰቡ አገልግሎት መስጠቱን ይቀጥላል።

የወ/ሮ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ ISO 9001:2015 የመጀመሪያ ዙር የክትትል ኦዲት (First Surveillance Audit) በስኬት አጠናቀቀ!ደሴ:-ሀምሌ 27/2018 ዓ.ም(ወስፖኮ)...
03/08/2026

የወ/ሮ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ ISO 9001:2015 የመጀመሪያ ዙር የክትትል ኦዲት (First Surveillance Audit) በስኬት አጠናቀቀ!

ደሴ:-ሀምሌ 27/2018 ዓ.ም(ወስፖኮ)

​የወ/ሮ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ የመጀመሪያው የ ISO 9001:2015 የጥራት ስራ አመራር ስርዓት ሰርተፊኬት ባለቤት መሆኑ ይታወቃል ኮሌጁ የዘረጋውን የጥራት አስተዳደር ሥርዓት (Quality Management System) ውጤታማነት እና ቀጣይነት ለማረጋገጥ ከኢትዮጵያ ተሰማሚነትና ምዘና ድርጅት (Ethiopian Conformity Assessment Enterprise) በዘርፉ ኦዲተሮች የተካሄደውን የ ISO 9001:2015 የመጀመሪያ ዙር የክትትል ኦዲት (First Surveillance Audit) በሙሉ ስኬት አጠናቋል።

​ይህ ስኬት ኮሌጃችን የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን እና ለስልጠና ጥራት ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ ለዚህ ውጤት መመዝገብ አስተዋጽኦ ላደረጉት ለኮሌጁ አመራሮች፣ ለኮሌጁ የጥራት አስተዳደር ስርዓት አስተባባሪ (Quality Management System Manager)፣ የውስጥ የጥራት አስተዳደር ስርዓት ኦዲተሮች (Internal Quality Management System Auditors)፣ የማናጅመንት አባላት፣ የዘርፍ አስተባባሪዎች፣ የስራ ቡድን መሪዎች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና አጋር አካላት በሙሉ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና የሰላም የህፃናት መንደር ከባለድርሻ አካላት ጋር ያደረጉት የምክክር መድረክ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ ደሴ:-ሀምሌ 15/2018ዓ.ም(ወስፖኮ) ​እንደሚታወቀው...
22/07/2026

የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እና የሰላም የህፃናት መንደር ከባለድርሻ አካላት ጋር ያደረጉት የምክክር መድረክ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ

ደሴ:-ሀምሌ 15/2018ዓ.ም(ወስፖኮ)

​እንደሚታወቀው የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከሰላም የህፃናት መንድር ጋር በመተባበር በEASE ፕሮጀክት ድጋፍ የዲጂታል ክህሎት ስልጠና (Intermediate Digital Skill in IT System Infrastructure) ለ4 ወራት የሚዘልቅ ስልጠና ለወጣቶች በመስጠት ላይ ይገኛል።

​ሰልጣኞቹ ስልጠናውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ የቀጣይ የትብብር ስልጠናዎችን ከማመቻቸት እና ለሰልጣኞች የሥራ ቅጥር ሁኔታዎችን ከመፍጠር አንፃር ከአጋር ድርጅቶች ጋር ሲመከር የቆየው የውይይት መድረክ በትላንትናው እለት ሰኔ 14/ 2018 ዓ.ም በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
​ይህ ስልጠና እና የምክክር መድረክ ወጣቶች በዘመናዊው ቴክኖሎጂ ራሳቸውን አብቅተው የሥራ ዕድል እንዲያገኙ ትልቅ ፋይዳ ያለው ሲሆን፣ በቀጣይም ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረጉ ትብብሮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

20/07/2026

Address

Dessie
54

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Woizero Siheen Polytechnic College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Woizero Siheen Polytechnic College:

Shortcuts

Share