ዋሪየርስ ካራቴ ዶጆ & ማርሻል-አርት ገፅ/Warriors Karate Dojo & Marshal-art pagr

  • Home
  • Ethiopia
  • Dessie
  • ዋሪየርስ ካራቴ ዶጆ & ማርሻል-አርት ገፅ/Warriors Karate Dojo & Marshal-art pagr

ዋሪየርስ ካራቴ ዶጆ & ማርሻል-አርት ገፅ/Warriors Karate Dojo & Marshal-art pagr #ዋሪየርስ ካራቴ ዶጆ & ማርሻል-አርት ገፅ
Karate Dojo & Marshal-art page

28/08/2026

ሌላ ትኩሳት

28/08/2026
ከዚህ ቀደም ጆኒ ጋር Fight ለማድረግ የቀረቡ ተፋላሚዎች በእልህ እና በስሜት እንዲሁም ዳጎስ ያለ ብር ለማግኘት ሲሉ ያለ ፕሮፌሽናቸው ዘው ብለው በመግባት ሲቀጠቀጡ እና ተመልካቾችን ሲያበ...
28/08/2026

ከዚህ ቀደም ጆኒ ጋር Fight ለማድረግ የቀረቡ ተፋላሚዎች በእልህ እና በስሜት እንዲሁም ዳጎስ ያለ ብር ለማግኘት ሲሉ ያለ ፕሮፌሽናቸው ዘው ብለው በመግባት ሲቀጠቀጡ እና ተመልካቾችን ሲያበሳጩ አይተናል።

የአሁኑ ግን ከወትሮው ይለያል ምክንያቱም ፣ ማስተር ሃሰን ሞሚን እድሜልኩ በዚህ ሞያ ላይ ከፍተኛ ልምድ ያካበተ ሲሆን ፣ ከአፋር ተነስቶ አገራችን ኢትዮጵያን ወክሎ በተለያዩ የአለም ሃገራት ውድድር አድርጎ ብዙ ሜዳልያዎችን ማግኘት የቻለ ብርቱ ወጣት ነው።

ማስተር ሃሰን ሞሚን ልክ እንደ #ሴዶና ለገንዘብ or ለ ዝና ሲል ወደማይችለው MMA fight ለማድረግ የመጣ አንደለም።

ምክንያቱም ማስተር ሃሰን ማለት በገንዘብም ቢሆን አወዳዳሪው አካልም ቢሆን የማስተር ሃሰንን ያክል ግማሽ እንኳን አይናረውም። ለዝናም ፈልጎ ነው እንዳንል ኢንተናሽናል ፋይተር ነው።

ስለዚህ የሱ ዋናው ፍላጎት በ ሴዶ እና በንቃተ ህሊና የተበላሸው የ MMA fight
ክብር ወደ ቦታው ለመመለስ እና ለ ተመልካቾች ደግሞ ጥሩ ፍልሚያ ለማሳየት እንዲሁም ለአገራችን የእስፖርት እድገት የራሱን አሻራ ለማሳረፍ ሲል ብቻ ነው።

ስለዚህ በቀሉ ማለቴ ጆን ጥያቄውን ተቀበይና
ዝግጂትሽን ከወዲሁ ጀምሪ እላለሁ ✅

Abdulfetah Mohammed ✍️

🥋🔥 ሴዶ ማርሻል አርት 🆚 ጆኒ ጂጂትሱ 🔥🥋ይህ ጨዋታ በእውነት አጓጊ ይሆናል! 👊ሴዶ በአቋም፣ በፍጥነትና በጥቃት ቅንጅት ጠንካራ ሆኖ ከቆመ፣ የጆኒ ጠንካራ ጎን ደግሞ ጂጂትሱ፣ መያዝና መሬት...
21/08/2026

🥋🔥 ሴዶ ማርሻል አርት 🆚 ጆኒ ጂጂትሱ 🔥🥋
ይህ ጨዋታ በእውነት አጓጊ ይሆናል! 👊
ሴዶ በአቋም፣ በፍጥነትና በጥቃት ቅንጅት ጠንካራ ሆኖ ከቆመ፣ የጆኒ ጠንካራ ጎን ደግሞ ጂጂትሱ፣ መያዝና መሬት ላይ ጨዋታ ሊሆን ይችላል።
ነገር ግን ጥያቄው ይህ ነው… 🤔
ሴዶ ጨዋታውን በአቋም ላይ ይቆጣጠረዋል? ወይስ ጆኒ ወደ መሬት አውርዶ የራሱን ጨዋታ ይጫወታል? 🔥
🎯 የእርስዎ ግምት ማን ነው?
በኮሜንት ላይ የሚያሸንፈውን ሰው እና ከቻሉ የማሸነፊያ መንገዱን ይጻፉ። 👇
🏆 ትክክለኛውን ግምት ለሰጡ 3 እድለኞች ልዩ ሽልማት ይኖራል! 🎁
🔥 … ማን ነው አሸናፊ?
ሴዶ? 🥋 ወይስ ጆኒ? 👊
via:-/ካርቲ ብላንች ካራቴ ማእከል ደሴ/ cartiblanch karate center dessie

ቴኮንዶ ከሰውነት እንቅስቃሴ ባሻገር፡ የህይወት ጥበብ እና ለሁለንተናዊ የትውልድ ግንባታ የሚሆን ድንቅ ጥበብ ነዉ!!!።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።ውድ የገጼ ተከታዮች እና የቴኮን...
08/07/2026

ቴኮንዶ ከሰውነት እንቅስቃሴ ባሻገር፡ የህይወት ጥበብ እና ለሁለንተናዊ የትውልድ ግንባታ የሚሆን ድንቅ ጥበብ ነዉ!!!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ውድ የገጼ ተከታዮች እና የቴኮንዶ ቤተሰቦች፤ ሰላምታዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ።

ባለፉት ከ40 ዓመታት በላይ በITF ቴኮንዶ (ITF Taekwon-Do) ዓለም ውስጥ ስመላለስ፣ ስማር እና ሳስተምር አንድ ትልቅ እውነት ተረድቻለሁ። ቴኮንዶ ማለት የመከላከል እና የማጥቃት ስልት ማስተማሪያ ጥበብ ብቻ አይደለም። ቴኮንዶ ሙሉ ሰብዕናን፣ አእምሮን እና መንፈስን የሚቀርጽ ሁለንተናዊ የህይወት መንገድ (Do) ነው።

ዛሬ ይህ ስፖርት በሁሉም የህይወታችን ዘርፍ ላይ ስላለው ዘላቂ ጠቀሜታ ጥቂት ልበላችሁ።

1. የአካል ብቃት እና የጤና ምንጭ

ቴኮንዶ መላውን አካል የሚያንቀሳቅስ ጥበብ ነው። የጡንቻ ጥንካሬን፣ የመተጣጠፍ ብቃትን (Flexibility) እና የሰውነትን ሚዛን በአስደናቂ ሁኔታ ያሻሽላል። እድሜያችን ምንም ይሁን ምን፣ ሰውነታችን ሁልጊዜ ንቁ እና ብቁ ሆኖ እንዲቀጥል ያደርጋል።

2. የአእምሮ ጥንካሬ እና ትኩረት (Mental Focus)

በዘመናችን ትልቁ ፈተና የትኩረት መበታተን ነው። በቴኮንዶ ውስጥ ያሉ ስልቶች፣ ምናባዊ እንቅስቃሴዎች (Tul/Patterns) ልምምዶች እና ቴክኒኮች ከፍተኛ የአእምሮ ንቃትን ይፈልጋሉ። ይህ ልምምድ አእምሮን በአንድ ነገር ላይ ብቻ የመሰብሰብ (Focus) ብቃትን ስለሚገነባ፣ ተማሪዎች በትምህርታቸው፣ ትልልቅ ሰዎች ደግሞ በስራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋል።

3. የስነ-ምግባር እና የዲሲፕሊን ማማ

የITF ቴኮንዶ መሰረታዊ መርሆች (Tenets) አምስት ናቸው፦

ጨዋነት (Courtesy)

ታማኝነት/ቅንነት (Integrity)

ጽናት (Perseverance)

ራስን መግዛት (Self-Control)

የማይበገረኝ መንፈስ (Indomitable Spirit)

እነዚህ መርሆች በዶጃንግ (ልምምድ አዳራሽ) ውስጥ ብቻ የሚቀሩ አይደሉም። እውነተኛ የቴኮንዶ ስልጠና ማህበረሰቡን የሚያከብር፣ ህግና ስርዓትን የሚጠብቅ፣ በፈተናዎች የማይወድቅ እና ስሜቱን መግዛት የሚችል ጠንካራ ዜጋ ይፈጥራል።

4. የውስጥ በራስ መተማመን እና የአእምሮ ሰላም

የሰው ልጅ ራሱን መከላከል እንደሚችል ሲያውቅ ፍርሃት ከውስጡ ይወገዳል። ፍርሃት ሲወገድ ደግሞ በራስ መተማመን እና ሰላም ይሰፍናል። ቴኮንዶ ጠብ አጫሪነትን ሳይሆን፣ ግጭቶችን በጥበብ የመፍታት እና ሰላማዊ የመሆን ጥበብን ያስምራል።

5. ለሁሉም እድሜ እና ጾታ የሚሆን ስጦታ

ቴኮንዶ ድንበር የለውም። ህጻናትን በስነ-ምግባር ያንጻል፣ ወጣቶችን ከመጥፎ ሱሶችና መስመሮች ይጠብቃል፣ ለአዋቂዎች ደግሞ የጭንቀት (Stress) መቀነሻ እና የረጅም እድሜ ጤና ዋስትና ነው።

ማጠቃለያ
በዚህ ከ40 ዓመት በላይ በዘለቀው ጉዞዬ ያየሁት ትልቁ ስኬት ያሰለጠንኳቸው ተማሪዎች ሜዳሊያ ሲያገኙ ብቻ ሳይሆን፣ በህይወታቸው ስኬታማ፣ ጨዋ እና ለአገራቸው የሚጠቅሙ ምርጥ ሰብዕና ያላቸው ሰዎች ሆነው ሲወጡ ነው። ቴኮንዶ የህይወት ዘመን ጉዞ ነው። ዛሬውኑ ይጀምሩት፣ ህይወትዎን ይለውጡበታል!

ሁሉም በዚህ ሁሉንም ህይወት ያለዉን ነገር ሁሉ በሚያለመልመዉ የክረምት ወቅት የለምንም የዕድሜና ፆታ ገደብ በየሚመቻችሁና በሚቀርባቺሁ የማርሻልዓርት ማዕከላት በመግባት ሁለንተናዊ ብቃታቺሁን እንድትገነቡ እመክራለሁ!!!
fans

Address

Dessie

Telephone

+251919961813

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዋሪየርስ ካራቴ ዶጆ & ማርሻል-አርት ገፅ/Warriors Karate Dojo & Marshal-art pagr posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share