Dessie Health Science College

Dessie Health Science College Dessie Higher Education health science college was established as a Asfaw Wosen Dressers School in 1964 GC (1957 EC)

ለ2018ዓም ለገባችሁ የዲግሪ ተማሪዎችየመጀመሪያ ዓመት 1ኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና ከ18/12/2018 ዓም ጀምሮ ይሰጣል።ስለሆነም አስላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጉ።
13/08/2026

ለ2018ዓም ለገባችሁ የዲግሪ ተማሪዎች
የመጀመሪያ ዓመት 1ኛ ሴሚስተር ማጠቃለያ ፈተና ከ18/12/2018 ዓም ጀምሮ ይሰጣል።
ስለሆነም አስላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጉ።

ርክክብ ተደረገ30/11/2018 ዓምደሴ።።በ2018 ዓም የበጀት አመት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በክልሉ የሚገኙ የመንግስት በጤናው ሴክተር የማሰሩ ተቋማትን ያማከለ የስራ አፈፃፀም ግም...
07/08/2026

ርክክብ ተደረገ
30/11/2018 ዓም
ደሴ።።
በ2018 ዓም የበጀት አመት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በክልሉ የሚገኙ የመንግስት በጤናው ሴክተር የማሰሩ ተቋማትን ያማከለ የስራ አፈፃፀም ግምገማ በባህር ዳር ከተማ ማካሄዱ ይታዎቃል።በመሆኑም የደሴ ከፍተኛ ትምህርት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በክልሉ ከሚገኙ ኮሌጆች ጋር በተቀመጠው የKPI መመዘኛ መስፈርት 94% አብላጫ ውጤት በማምጣት 1ኛ ስለወጣ ከክልል ጤና ቢሮ የተለያዮ ሽልማቶች ተበርክቶለታል።ስለሆነም በዛሬው ዕለት ይህ ለተቋማችን ከፍተኛ ትርጉም ያለውን ሽልማት የደሴ ከፍተኛ ትምህርት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ ሁሴን መኮንን የኮሌጁን አካዳሚክ ኮሚሽንና ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ከክልል የተሰጡንን ሽልማቶች አስረክበዋል።
ይህ ሽልማት በተወሰኑ ሰዎች ጥረት የተገኘ ሳይሆን ሁሉም የኮሌጁ ሰራተኞች በየደረጃው የሰሩት ስራ ውጤት ነው እንደግለሰብም ከፍተኛ አስተዋፅኦ የነበራቸው ስለነበሩ እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ይህን የተሰጠንን ሽልማት ሳስረክባችሁ ከክልሉ ጤና ቢሮና እና ከክልሉ መንግስት ከሽልማቱ ጋር የተሰጠኝን አደራና ኃላፊነት አብሬ የማስረክብ ስለሆነ በቁርጠኝነት የተሻለ ስራ እንድንሰራ አደራ ጭምር መሆኑን መግለፅ እወዳለሁ።ይህ እንደ ሀገር ቀዳሚ ለመሆን የምናደርገውን ጥረት የመጀመሪያው ምዕራፍ ስለሆነ ሁላችንም ይህንን ሀሳብ በመያዝ ያለመታከት እንድንሰራ የሚያነቃቃን እንጅ የመጨረሻ ግባችን አደለም ነው ያሉት።ይህ ሽልማት የከፍተኛ ትምህርት ተቋምነትን ባገኘን ማግስት መሆኑ፣ከ500 በላይ ተማሪዎቻችንን ባስመረቅን በቀናቶች ልዮነት በደስታ ላይ ደስታ በስኬት ላይ ስኬት ያገኘንበት ወቅት በመሆኑ ደስታችን ድርብርብ ስለሆነ ለየት ያደርገዋል ።
በማስከተል የዋንጫ 🏆 ምስክር ወረቀት፣የክሪስታል፣እና የሞተር ሳይክል ሽልማት ለኮሌጁ ምክትል ዲኖች ለአቶ ፍሬዘር ግርማና ለአቶ ወርቅነህ ቸኮል እና ለማኔጅመንት ካውንስል አባላት አስረክበዋል።
Join us
https://t.me/dessiehsc1
https://www.facebook.com
www.dhsc.edu.et
https://www.linkedin.com/company/dessie-health-science-college/
#0331124415 ዲን ቢሮ
#0331124413 ሬጅስትራር ቢሮ
#0331124448 አካ/ም/ዲን
#0331124414 አስ/ምር/ምክ/ዲን
#0331124416 ግዥና ፋይናንስ ቢሮ
#0331115303 የሰው ኃ/አስተዳ

እንኳን ደስ ያላችሁ ደስ አለን !!!ደሴ ከፍተኛ ትምህርት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዋንጫና ሜዳሊያ  ተሸላሚ ሆነ።20/11/2018 ዓ.ምባህር ዳር።በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት  በአብክመ ጤ...
28/07/2026

እንኳን ደስ ያላችሁ ደስ አለን !!!
ደሴ ከፍተኛ ትምህርት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዋንጫና ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነ።
20/11/2018 ዓ.ም
ባህር ዳር።
በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በአብክመ ጤና ቢሮ አመታዊ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 በጀት አመት እቅድ ትውውቅ ዝግጅት ለተከታታይ ሶስት ቀናት በባህር ዳር ተከናውኗል።በዚሁ ዝግጅት ላይ የደሴ ከፍተኛ ትምህርት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በጤና ቢሮው ስር ከሚተዳደሩ የጤና ሳይንስ ኮሌጆች ውስጥ በዓመቱ በአስመዘገበው አፈፃፀም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ አንደኛ በመውጣት የዋንጫና ሜዳሊያ በተጨማሪም አንድ ዘመናዊ ሞተር ሳይክል ተሸላሚ ሆኗል።
በ2018 በጀት ዓመት በአብክመ ጤና ቢሮ አመታዊ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ የደሴ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ አንደኛ ደረጃ ሆኖ አጠናቋል።
በዕለቱ የተሰጠውን ሽልማት የኮሌጃችን ዲን አቶ ሁሴን መኮንን በዝግጅቱ ላይ በመገኘት ተቀብለዋል።
በተጨማሪም የደሴ ከተማ ጤና መምሪያ ፤ደሴ አጠቃላይ ሆስፒታል ፣ ከጤና ጣቢያ ቁርቁር ጤና ጣቢያ፣ ከክ/ከተማ አራዳ ክ/ከተማ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ አንደኛ ሆነው የዋንጫና ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል።
ለዚህ ውጤት በየደረጃ ያሉ አመራሮች፣ጤና ባለሞያዎችና የአስተዳደር ሠራተኞች የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች በቅንጅትና በትብብር በመሥራት የተሳተፉ ፣ህብረተሰቡና ሌሎች ባለድርሻ አካሎችን መምሪያው ምስጋና አቅርቧል።

"እንኳን ደስ አለን"
ደሴ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ
ደሴ
ሐምሌ 20/2018 ዓም

ለዚህ ውጤት መምጣት በየደረጃ ያሉ አመራሮች፣ የአካዳሚክ፣ የቴክኒካል ረዳት እና የአስተዳደር ሠራተኞች የጋራ ጥረት፣ በቅንጅትና በትብብር በመሥራት የተገኘ ስኬት ነውና እንኳን ደስ ያላችሁ እንኳን ደስ አለን።
ደሴ ከፍተኛ ትምህርት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ!

Join us
https://t.me/dessiehsc1
https://www.facebook.com
/www.dhsc.edu.et
https://www.linkedin.com/company/dessie-health-science-college/
#0331124415 ዲን ቢሮ
#0331124413 ሬጅስትራር ቢሮ
#0331124448 አካ/ም/ዲን
#0331124414 አስ/ምር/ምክ/ዲን
#0331124416 ግዥና ፋይናንስ ቢሮ
#0331115303 የሰው ኃ/አስተዳደር

የደሴ ከፍተኛ ትምህርት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ  በዲፕሎማ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን 576 ተማሪዎቹን አስመረቀ።።ሐምሌ 11/2018 ዓ.ምደሴ::ኮሌጃችን በመካከለኛ(ዲፕሎማ) ደረጃ  ላለፋት ሶስት ዓ...
18/07/2026

የደሴ ከፍተኛ ትምህርት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዲፕሎማ ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን 576 ተማሪዎቹን አስመረቀ።።
ሐምሌ 11/2018 ዓ.ም
ደሴ::
ኮሌጃችን በመካከለኛ(ዲፕሎማ) ደረጃ ላለፋት ሶስት ዓመታት ሲያሰለጥናቸው የነበሩትን በተለያዩ የጤና ባለሙያ ዘርፍ በዛሬው ዕለት በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ።
በተማሪዎቹ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ መልካሙ ጌትነት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ም/ቢሮ ኃላፊው በስነ-ስርዓቱ ላይ የስራ መመሪያና ንግግር ሲያደርጉ፦
"የደሴ ከፍተኛ ትምህርት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዛሬ ተማሪዎቹን ሲያስመርቅ አብዛኛው ተመራቂ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ እንደሆኑ ተመልክተናል።ይህ የሚያሳየው የኮሌጁ መምህራን ተማሪዎቻቸውን ለማብቃት የታተሩበትን ሁኔታ የሚያሳይ ነው። ተመራቂ ተማሪዎች በቀጣይ ጊዜ በምትወስዱት የስራ ስምሪት በሽታን በመከላከል፣በማከም እና ተገልጋይን በመንከባከብ ውድ የሆነውን የሰው ልጅ ጤና በመጠበቅ የተከበረ ሙያችሁን በተግባር ታሳያላችሁ ብየ አስባለሁ።መማር በኮሌጅ ብቻ የሚያበቃ ባለመሆኑ በስራ ቦታ በልምድም ሆነ በማንበብ አቅማችሁን ማሳደግ ይጠበቅባችኋል።በመቀጠል የኮሌጁ መምህራን፣የማኔጅመንት ካውንስል እና አካዳሚክ ኮሚሽን ተግባር ላይ ያተኮረ ትምህርት በመስጠት በቂ እውቀት፣ክህሎት እና የስራ ፍላጎት ያዳበረ ተመራቂ እንድታቀርቡ ማሳሰብ እወዳለሁ።
የኮሌጁን አቅም በማጠናከር እረገድ ጤና ቢሮው እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ ድጋፍና ክትትሉን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
በመጨረሻም ይኸን ልዩ የምርቃ በዓል ለአዘጋጁ ለአስተባበሩ ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ።
በመጨረሻም ውድ ተመራቂዎችና የተመራቂ ቤተሰቦች ለዚህ በመብቃታች እንኳን ደስ አላችሁ "ብለዋል።
የኮሌጁ ዲን አቶ ሁሴን መኮንን ባስተላለፉት መልዕክት "ይህን የምረቃ ዝግጅት ስናዘጋጅ እንደ ኮሌጅ ከ2012 ዓ.ም ወዲህ የተዘጋጀ በመሆኑ እና የከፍተኛ ትምህርት ኮሌጅነት የደረጃ ማሻሻያ ባደረገበት ማግስት መሆኑ ከፍተኛ መነቃቃት ፈጥሯል ብለዋል::"
በዛሬው ዕለት በፋርማሲ ቴክኖሎጅ፥በክሊኒካል ነርሲንግ፥በሙያ ማሻሻያ ጤና ኤክስቴንሽን፥በሜዲካል ራዲዮሎጅ እና በሜዲካል ላብራቶሪ ቴክኒሻን ሙያዎች 576 የጤና ባለሙያዎች ትመረቃላችሁ።ተመራቂ ተማሪዎቻችን ዕውቀትን በመማሪያ ክፍል፤ ክህሎትን በተግባር ልምምድ ላለፉት ዓመታት ጠንክራችሁ በመቅሰማችሁ እና ለዚህ ውጤት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ። እኛም በጤናው ዘርፍ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራታችን ደስታ ይሰማናል።ውድ ተመራቂዎች ወደ ስራው አለም ስትቀላቀሉ በሙያ ብቃታችሁ ስለምንተማመንባችሁ በየተቋማቱ አንባሳደሮቻችን እንደምትሆኑ አምናለሁ ብለዋል።
በመጨረሻም ውድ ተመራቂዎች የተመራቂ ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ።
በመጨረሻም በዓመቱ ከየትምህርት ክፍሉ ብልጫ ላመጡ ተመራቂዎች ከ1-3ኛ ደረጃ ለወጡ የምስክር ወረቀትና የወርቅ ሜዳሊያ የተሰጠ ሲሆን በዓመቱ ከተመረቁ ሴት ተመራቂዎች እንዲሁም አጠቃላይ የኮሌጁን ከፍተኛ ውጤት 4 ኘጥብ ያስመዘገበችው በፋርማሲ ቴክኖሎጅ ትምህርት ክፍል ተማሪ ማህሌት ዮሴፍ ጌታቸው አንድ የወርቅ ሜዳሊያና ሁለት ዋንጫዎችን በመውሰድ ልዮ ተመራቂ ሆናለች።በማጠቃለያጨየክብር እንግዶች ከኮሌጁ አካዳሚክ ኮሚሽን አባላትና ተመራቂዎች ጋር የመታሰቢያ ፎቶ በመነሳት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
Join us
https://t.me/dessiehsc1
https://www.facebook.com
/www.dhsc.edu.et
https://www.linkedin.com/company/dessie-health-science

part 3
18/07/2026

part 3

18/07/2026
18/07/2026
የኮሌጁ የተማሪዎች ምረቃ እየተከናወነ ነው
18/07/2026

የኮሌጁ የተማሪዎች ምረቃ እየተከናወነ ነው

ለ2018ዓ .ም ተመራቂ ተማሪዎችና አስመራቂ ቤተሰቦች።በ11/11/2018 የሚከናወነው የምረቃ ፕሮግራም በወሎ ባህል አምባ አዳራሽ ስለሆነ በዕለቱ ከጧቱ 2:00 ሰዓት እንድትገኙ እናሳስባለን።...
17/07/2026

ለ2018ዓ .ም ተመራቂ ተማሪዎችና አስመራቂ ቤተሰቦች።
በ11/11/2018 የሚከናወነው የምረቃ ፕሮግራም በወሎ ባህል አምባ አዳራሽ ስለሆነ በዕለቱ ከጧቱ 2:00 ሰዓት እንድትገኙ እናሳስባለን።
ሸር በማድረግ መረጃው እንዲዳረስ አድርጉ።

Address

Located Behind Dessie Comprehensive Hospital, Via The Emergency Entrance
Dessie
1212

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251331124415

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dessie Health Science College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Dessie Health Science College:

Shortcuts

Share