13/01/2025
Kassu Media ካሱ ሚዲያ
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kassu Media ካሱ ሚዲያ, Educational consultant, Dessie.
13/01/2025
10/08/2024
√√√√√ቀነኒሳ የምንጊዜም ጀግና ነው!!
🇪🇹 36 ጊዜ ሀገር ወክሎ በመሳተፍ የኢትዮጵያ ባለ ሪከርድ ነው።
🇪🇹 36 ጊዜ ሀገር ወክሎ 24 ወርቅ ለሀገሩ አምጥቷል - ይህም ሪከርድ ነው።
🇪🇹 አራት ኦሎምፒክ ተሳትፏል። አብዛኛውን በድል አጠናቋል‼️
🇪🇹 በ42 አመቱ ኦሎምፒክ በመወዳደሩም ሪከርድ ይዟል
🇪🇹 ከቀነኒሳ ቀጥሎ ለሀገር በመሰለፍ
🇪🇹 ቀነኒሳ በቀለ በ25 አመት የሩጫ ዘመኑ 173 ኢንተርናሽናል ውድድሮችን አድርጓል።
➙ 5000 ሜትርን 56 ጊዜ ሮጧል።
➙ 3000 ሜትርን 37 ጊዜ ሮጧል።
➙ ሀገር አቋራጭ 21 ጊዜ በተለያየ ርቀት
➙ 10000 ሜትርን 19 ጊዜ ሮጧል።
➙ ማራትን 13 ጊዜ ሮጧል።
➙ 10 ኪ ሜ ጎዳና 6 ጊዜ ሮጧል።
➙ 2000 ሜትር 5 ጊዜ ሮጧል።
➙ 1500 ሜትር 4 ጊዜ ሮጧል።
➙ 2 ማይል 4 ጊዜ ሮጧል።
➙15 ኪሎ ሜትር ጎዳና 3 ጊዜ ሮጧል።
➙ ግማሽ ማራቶን 2 ጊዜ ሮጧል።
➙ አንድ ማይልን 10 ማይልን እና 25 ኪሎ ሜትርን አንድ አንድ ጊዜ ሮጧቸዋል።
=====
🇪🇹 ቀነኒሳ ካደረጋቸው ከ173 ውድድሮች ውስጥ
➢ 110 ውድድሮችን - ❶ኛ
➢ 21 ውድድሮችን - ❷ኛ
➢ 6 ውድድሮችን - ❸ኛ ሆኖ ጨርሷል።
ከ173 ውድድሮች ውስጥ 137 ውድድሮችን ሜዳሊያዎች ማለት ነው።
🇪🇹 36 ጊዜ ሀገሩን ወክሎ ያገኛቸው ድሎች
🥇 24 ወርቅ 🙏 👌
🥈 5 ብር 🙏 👌
🥉 1 ነሀስ 🙏 👌
➢ ❹ኛ ደረጃ በማግኘት ሁለት ዲፕሎማ
➢ ❶ ውድድር ❾ኛ ደረጃ በ1999
➢ ❷ ውድድሮችን አቋርጧል።
🇪🇹 ሜዳሊያዎቹ ሲዘረዘሩ
📌 በኦሎምፒክ
🥇 ❸ ወርቅ
🥈 ❶ ብር
👉 ❶ ዲፕሎማ ❹ኛ ደረጃ አግኝቶ
📌 በአለም አትሌትክስ ሻንፒዮና
🥇 ❺ ወርቅ
🥉 ❶ ነሀስ
📌 በአለም ሀገር አቋራጭ
🥇⓭ ወርቅ
🥈 ❶ ብር
📌 ወጣቶች ሻንፒዮና
🥈❷ ብር
📌 ኮንትኔታል
🥈 ❶ ብር
📌 በአፍሪካ ሻንፒዮና
🥇 ❸ ወርቅ
👉 ❶ ዲፕሎማ ❹ኛ ደረጃ አግኝቷል።
=====
🇪🇹 ቀነኒሳ የምንጊዜም ጀግና ነው‼️
10/08/2024
በህግ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ዙሪያ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል፡፡
አዲስ አበባ ነሐሴ 4 ቀን 2016ዓ.ም (ን/ቀ/ት/ሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር) ከብሄራዊ የንግድ ተቋማት የፀረ ህገ ወጥ ንግድና ገበያ ማረጋጋት የጋራ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን የህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች በተለይም ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በማድረግና ምርትን በመደበቅ እጥረት እንዲፈጠር በሚያደርጉ ነጋዴዎችና ድርጅቶች ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ ገምግመዋል፡፡
በዚህም በ11ኛ ቀን አፈፃፀም ብቻ ያላግባብ ዋጋ የጨመሩ 1,091 የንግድ ተቋማት የታሸጉ ሲሆን 12 ነጋዴዎች በእስራት ተቀጥተዋል፡፡
በተጨማሪም 37 ምርት የደበቁ የንግድ ተቋማት ሲታሸጉ ወጣ ያለ የህግ ጥሰት ያሳዩና ለህግ ተገዢ ለመሆን ፍቃደኛ ባልሆኑ 2 ነጋዴዎች ላይ የእስራት ቅጣት ተላልፏል፡፡
በአጠቃላይ እስከዛሬ ድረስ በተደረገው ቁጥጥርና ክትትል የህግ ጥሰት ፈጽመው የተገኙ 12,478 የንግድ ተቋማት የታሸጉ ሲሆን 11,371 የንግድ ተቋማት በህግ አግባብ ለመስራት በመስማማታቸው ተከፍተው ወደ ስራ መግባታቸውም ተገልጿል።
የክትትልና የቁጥጥር ስራው አድማሱን በማስፋት በግንባታ እቃዎች ላይ የቁጥጥርና ክትትል ስራ በተቀናጀ መልኩ የተጀመረ ሲሆን በዚህ ዘርፍ ህገ ወጥ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ 244የሲሚንቶ፣ 62 የብረት፣ 15 የቆርቆሮ፣ 4የሚስማር፣ እንዲሁም 6 የሴራሚክ ንግድ ተቋማት ታሽገዋል፡፡ በተመሳሳይ ለህግ ተገዢ ለመሆን ፍቃደኛ ያልሆኑ 2 የሲሚንቶ ነጋዴዎች በእስር ተቀጥተዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን:-
Email: [email protected]
[email protected]
facebook:-https://www.facebook.com Ethiopian-Ministry-of-Trade-and-Regional-Integration
For trade license : www.etrade.gov.et
website: www.motri.gov.et
telegram channel :https://t.me/motri_gov_et
https://t.me/etrade_gov_et
https://www.youtube.com/
29/07/2024
መረጃ‼️
የብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ሥርዓት በተመለከተ ዛሬ ንጋት ላይ በድረገጹ ባጋራው ባለ 108 ገጽ ዝርዝር መመሪያ ላይ የውጭ ምንዛሬን ማን፤ መቼ፤ እንዴት፤ ለምን... መያዝ፤ መሸጥ እንዲሁም መግዛት እንደሚችል ይዘረዝራል። ቅጣቶችንም ያስቀምጣል።
ከድንጋጌዎቹ መካከልም የሚከተሉት ይገኙበታል👇
- ከኢትዮጵያ ወደ ሌላ ሀገር የሚጓዝ ወይም ከሌላ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ ሰው ከ3,000 የኢትዮጵያ ብር በላይ በጥሬው መያዝ አይችልም።
- ወደ ጅቡቲ ወይም ወደሌላ የጎረቤት ሀገር ወደብ ከተሞች የሚጓዝ ሰው እስከ 10,000 የኢትዮጵያ ብር መያዝ ይችላል።
- በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ሰው ወደ ግዛት ክልሏ ሲገባ በጉዞ ሰነዱ ላይ በስደተኞችና በዜግነት አገልግሎት ማህተም ተረጋግጦ የገባበት ቀን ተብሎ ከሚጠቀሰው ቀን አንስቶ በ30 ቀናት ውስጥ የያዘውን የውጭ ሀገር ገንዘብ ፍቃድ ባላቸው የምንዛሪ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት የመመንዘር ወይም በባንክ በስሙ በተከፈተ የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለበት።
- ሆኖም ግለሰቡ የያዘው ሊመነዘር የሚችል የውጭ ሀገር ገንዘብ ከ10,000 የአሜሪካን ዶላር እኩል ወይም በላይ ከሆነ የውጭ ሀገር ገንዘቡ በውጭ ሀገር ምንዛሪ የባንክ ሂሳብ ገቢ ማድረግ አለበት። ገቢ ሲያደርግም የጉምሩክ ዲክላሬሽን ወይም ወደ ሀገር የገባ የውጭ ሀገር ገንዘብ ማሳወቂያ መግለጫ ሰነድ ማቅረብ አለበት።
- ግለሰቡ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ሀገር ዜጋ ወይም ኢትዮጵያ ውስጥ ማይኖር ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከሆነና ከዘጠና ቀናት በላይ በኢትዮጵያ ውስጥ የመቆየት ሀሳብ ካለው፤ የያዘውን የውጭ ሀገር ገንዘብ በሙሉ በጉዞ ሰነዱ ላይ ከሚጠቀሰው ወደ ሀገር የገባበት ቀን ጀምሮ በዘጠና ቀናት ውስጥ በውጭ ምንዛሪ የባንክ ሂሳቡ ገቢ ማድረግ አለበት።
- ከ10,000 ዶላር በላይ የውጭ ሀገር ገንዘብ ይዞ ከሆነም ገንዘቡን በውጭ ምንዛሪ ሂሳቡ ገቢ ሲያደርግ ወይም በሕጋዊ መልኩ ሲመነዝር የጉምሩክ የውጭ ምንዛሪ ማሳወቂያ ሰነድ ማቅረብ አለበት።
- ወደ ውጭ ሀገር የሚጓዝ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ሰው ከተፈቀደላቸው የምንዛሪ አገልግሎት ሰጪዎች የገዛው የውጭ ሀገር ገንዘብ ካለ የገዛበት ደረሰኝ ላይ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ይዞ ማቆየት ይችላል።
- ከኢትዮጵያ ጋር ድንበር ከሚጋሩ የጎረቤት ሀገራት በየብስ መጓጓዣ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ ማንኛውም ሰው በድንበር ላይ ላለ የጉምሩክ ቅርንጫፍ ወይም ጣቢያ ከ500 የአሜሪካ ዶላር ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ወይም ከዛ በላይ ሌላ የውጭ ሀገር ገንዘብ ከያዘ የያዘውን የገንዘብ መጠን የጉምሩክ የውጭ ምንዛሪ ማሳወቂያ መግለጫ ላይ በመሙላት ማሳወቅ ያለበት ሲሆን፤ ይህንኑ ያሳወቀውን የውጭ ሀገር ገንዘብ መጠንም ጉዳዩን ጨርሶ ሲመለስ ይዞ መውጣት ይችላል።
- በብሔራዊ ባንክ ወይም አግባብ ባለው ሕግ ካልተፈቀደለት በስተቀር ማንኛውም ሰው የውጭ ሀገር ገንዘብ በጥሬው በስጦታም ሆነ በእርዳታ ወይም ለግብይት ክፍያ ለሦስተኛ ወገን ማስተላለፍ ወይም መክፈል አይችልም።
- በብሔራዊ ባንክ ፍቃድ በዚህ መመሪያ ወይም በሌላ ሕግ በተፈቀደው መሰረት ካልሆነ በቀር በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የውጭ ምንዛሪ መያዝ አይፈቀድም።
መመሪያው ከዚህ በተጨማሪ በርካታ ዝርዝሮች የያዘ ሲሆን ይህን ማስፈንጠሪያ በመከተል ሙሉውን ማንበብ ይቻላል👇👇 https://nbe.gov.et/fx/
20/06/2023
20/05/2023
የሟቾች ቁጥር 20 ደረሰ!!
የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረው መኪና በደረሰበት አደጋ በአሁኑ ወቅት የሟቾች ቁጥር 20 መድረሱ ተገለፀ። አደጋው የደረሰው መምህራኑ ሻሸመኔ ካምፓስ ለማስተማር ወደ ዶዶላ እየተጓዙ እያሉ ባጋጠማቸዉ የትራፊክ አደጋ ነዉ።
ፈጣሪ ከእንድህ አይነት ነገር ይጠብቀን ለሟች ወዳጅ ዘመድ ሁሉ መጽናናትን ይስጥልን።
02/05/2023
22/04/2023
22/04/2023
የጄኔራል ሰዓረ መኮንን መታሰቢያ ፓርክና ሐውልት ተመረቀ
************
(ኢ.ፕ.ድ)
የቀድሞ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን መታሰቢያ ፓርክና ሐውልት ዛሬ በአዲስ አበባ ተመረቀ።
በምርቃቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ ጀኔራል መኮንኖች፣ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች፣ የጄኔራል ሰዓረ መኮንን ቤተሰቦችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ፤ ሐውልቱ በአዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ በስማቸው በተሰየመ ፓርክ ውስጥ ክብራቸውን በሚመጥን መልኩ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱ ተገልጿል።
የቀድሞ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን አገር ወዳድ የኢትዮጵያ ልጅ እንደነበሩ ተወስቷል።
ጄኔራል ሰዓረ ከግንቦት 2010 ዓ.ም ሕይወታቸው እስካለፈበት ሰኔ 15/2011 ዓ.ም ድረስ የኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም በመሆን ኢትዮጵያን በታላቅ ታማኝነትና ቅንነት አገልግለዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Telephone
Website
Address
Dessie