Dandii Boru College Dessie Campus

Dandii Boru College Dessie Campus

Share

Dandii Boru College is of privately-owned by higher learning institutions in the country.

Photos from Dandii Boru College Dessie Campus's post 18/06/2026

የዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ የ2ኛ ሴሚስተር የፋይናል ፈተና ፕሮግራም

15/06/2026
Photos from Dandii Boru College Dessie Campus's post 13/06/2026

የ2015 ዓ.ም የነርስ ባች የዛሬው የክፍል እደሳ ውሎ
6/10/2018 ዓ.ም

Photos from Dandii Boru College Dessie Campus's post 10/06/2026

የመልካም አሻራ የመጣል ተሞክሮ እንደቀጠለ ነዉ
የዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ ለሁሉም ሰራተኞች እና ለተማሪ ተወካዮች በ2018 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ የለዉጥ አስተዳደር (Change Management) ስልጠና በመስጠት የአመቱን ስራ መጀመሩ ይታወቃል፡፡ በዚህ ሂደት ዉስጥ ሁሉም ሰራተኛ እና የተማሪ ተወካዮች በኮሌጁ በሚኖራቸዉ ቆይታ ስራን በሚፈለገዉ መጠን፣ጊዜና ጥራት ብቻ ሳይሆን ከኋላ ለሚመጡ ተማሪዎች አሻራ ጥሎ ማለፍ እንዳለባቸዉ አንዱ የስልጠናዉ አካል ነዉ፡፡
..የአመቱን የመጀመሪያ አሻራ የመጣል ስራ የጀመሩት የ2016 ዓ.ም ገቢ የማኔጅምንት ትምህርት ክፍል የሴክሽን 2 ተማሪዎች ሲሆኑ ስራቸዉንም በተሳካ ሁኔታ አቅደዉ፣ፕሮጀክት ቀርጸዉና ፈንድ አሰባስበዉ ሰረተዉ አስመረቀዉ ለኮሌጁ አስረክበዋል፡፡ ይህንን ምርጥ ተሞክሮ የፋርማሲ 2016 ዓ.ም ተማሪዎች ሀሳቡን በማሻሻል እና በመዉሰድ አቅደዉ ለመስራት ሲነቀሳቀሱ የነበሩ ሲሆን ካቀረቧቸዉ ሀሳቦችና ፕሮጅክቶች ዉስጥ አንዱ የኮሌጁን የመግቢያ በር የማሰራት እና የመስተካከል ቢሆንም ስራዉ ከሚወስደዉ ጊዜ አንጻር እና የፕሮጅክቱ ዉስብስብነት እና ሌሎች የመንግስት አካላት ጋር ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ ፕሮጀክታቸዉን አሻሽለዉ እንደ አዲስ ቀይረዉ የክፍላቸውን ኮርኒስ፣ ወለል እና ግድግዳ አድሰው አስረክበዋል።

ይህን ምርጥ ተሞክር በመውሰድ የ2015 ነርስ ባች ተማሪዎች የመማሪያ ክፍላቸውን ማደስ በ 03/10/2018 ዓ.ም ጀምረዋል። ከክፍሉ ተወካዮችና የፕሮጅክቱን አስተባባሪዎች ባነጋገርነዉ መሰረት በአሁኑ ዙር የሚያከናዉኑት የመማሪያ ክፍላቸዉን ግድግዳዉን እና ኮርኒሱን እንዲሁም ሌሎች መሰረተ ልማቶችን እንደ መብራት፣የኢንተርኔት መስመር ዝርጋታ እና እንዲሁም የኮርኒስ እድሳት ለማደረግ በፕሮጀክታቸዉ ለመስራት ያሰቡ መሆኑን የገለጹ መሆኑንና የመማሪያ ክፍላቸዉን የግድግዳ ቁርቆራ ስራና ለጂፕሰም ቻክ ለመስራት የሚያስችሉ ግብአቶችን የማቅረብ ስራዎችን ማጠናቀቃቸዉን አስረድተዉናል፡፡
ምንጭ፡- የ2015 ባች የነርስ ትምህርት ክፍል ተወካዮች እና የፕርጀክቱ አስተባባሪዎች
ዳንዲቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በቴሌግራም_አድራሻችን👇'
=> https://t.me/dandiiborudc
በfacebook_አድራሻችን👇
=> https://fb.me/DBCDC
በዩቲዩብ_አድራሻችን👇
=>https://www.youtube.com/
በኢንስታግራም አድራሻችን፡👇
=>https://www.instagram.com/dandiiborudc/ #
በኤክስ አድራሻችን፡ 👇
=>https://x.com/dandiiborudc
በቲክቶክ አድራሻችን፡ 👇
=>https://www.tiktok.com/

07/06/2026

በአሁኑ ሰዓት በአባይ ቲቪ ምን እየተላለፈ ነው?

Photos from Dandii Boru College Dessie Campus's post 06/06/2026

የዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ የሪሰርች ፐብልኬሽን እና ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት አስተባባሪ ፣ የ4ተኛ አመት የነርስ ተማሪዎች እንዲሁም ከተማሪዎች ዲን ጋር በመሆን በ29/09/2018 ዓ.ም የደም ልገሳ ተካሂዷል። በእለቱም የኮሌጁ ሰራተኞች እንዲሁም ተማሪዎች ደም የመለገስ ጠንካራ ተሳትፎ አድርገዋል።
በዚህም መሰረት ከነርስ ዲፓርትመንት ከ2015 ባች - 27
ከ2016 ባች - 2
ከ2017 ባች - 2
ከ2018 ባች - 5 ተማሪዎች የለገሱ ሲሆን በአጠቃላይ ከነርስ ዲፓርትመንት 36 ተማሪዎች ለግሰዋል።
ከፋርማሲ ዲፓርትመንት
ከ2015 ባች - 1
ከ2016 ባች - 8
ከ2017 ባች - 5
ከ2018 ባች - 2 በአጠቃላይ 16 ተማሪዎች ለግሰዋል።
ከማኔጅመንት ዲፓርትመንት 3 ተማሪዎች ሲለግሱ 2 ተማሪዎች ከ 2016 ባች፤ 1 ተማሪ ከ2017 ባች በጠቅላላ 3 ተማሪዎች ከማኔጅመንት ዲፓርትመንት ለግሰዋል። ከአካውንቲንግ ትምህርት ክፍል ደግሞ 4 ተማሪዎች የደም መለገስ መርሀ ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል። እንዲሁም 4 የኮሌጁ ሰራተኞችም ለግሰዋል።
በአጠቃላይ 64 በጎ ፈቃደኞች የተሳተፉ ሲሆን 64 ዩኒት ደም እንደተሰበሰበም በወቅቱ የነበሩት የጤና ባለሙያዎች ገልጸውልናል። የኮሌጁ አመራርም እንደዚህ አይነት በጎ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው እና በቀጣይ በሚኖረው ፕሮግራም ላይ ሁሉም የኮሌጁ ማህበረሰብ ከዚህ የበለጠ ተሳትፎ እንዲያደርግ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።
ግንቦት 29/2018 ዓ.ም
ዳንዲቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በቴሌግራም_አድራሻችን👇'
=> https://t.me/dandiiborudc
በfacebook_አድራሻችን👇
=> https://fb.me/DBCDC
በዩቲዩብ_አድራሻችን👇
=>https://www.youtube.com/
በኢንስታግራም አድራሻችን፡👇
=>https://www.instagram.com/dandiiborudc/ #
በኤክስ አድራሻችን፡ 👇
=>https://x.com/dandiiborudc
በቲክቶክ አድራሻችን፡ 👇
=>https://www.tiktok.com/

06/06/2026

ዛሬ ማለትም በ29/09/2018 ዓ.ም በዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ በሚካሄደው የደም ልገሳ ፕሮግራም ላይ ደም በመለገስ የሰብአዊነት አሻራዎን ያሳርፉ።
"የደም ልገሳ ድንበር የሌለው ፍቅር ነው።" 🩸🩸🩸
ዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ

05/06/2026

ደም መለገስ ለምን አስፈለገ
ደም መለገስ አስፈላጊ የሆነው ደም በፋብሪካ ሊመረት ስለማይችል እና የሚያስፈልጋቸው ሕሙማን ከለጋሾች በሚሰጥ ደም ብቻ ሕይወታቸውን ማዳን ስለሚቻል ነው።
የደም ልገሳ አስፈላጊነት
በአደጋ የተጎዱ ሰዎችን ሕይወት ለማዳን
በወሊድ ጊዜ ብዙ ደም ያጡ እናቶችን ለመርዳት
ቀዶ ሕክምና ለሚደረግላቸው ሕሙማን
የደም ማነስ እና ሌሎች የደም በሽታዎች ላለባቸው ሰዎች
የካንሰር ሕክምና ለሚወስዱ ሕሙማን

ደም በመለገስ የሚገኙ ጥቅሞች
ሕይወት ያድናል። ደም የሚያስፈልጋቸውን ሕሙማን ለመርዳት ይጠቅማል።
የሰብአዊነት ስሜትን ያጠናክራል። ሌሎችን በመርዳት የእርካታ ስሜት ይፈጥራል።
የደም ክምችትን ያሳድጋል። በአደጋና በድንገተኛ ሁኔታዎች ደም እንዲገኝ ያግዛል።
የጤና ምርመራ ዕድል ይሰጣል። ከልገሳ በፊት የደም ግፊት፣ የደም ዓይነት እና ሌሎች መሰረታዊ ምርመራዎች ይደረጋሉ። ማህበራዊ አንድነትን ያጠናክራል። ሰዎች እርስ በርሳቸው እንዲረዳዱ ያበረታታል

ደም ለጋሽ ለመሆን የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
ጤናማ እና ደህና መሆን።
ቢያንስ 18 ዓመት ዕድሜ መኖር።
ቢያንስ 50 ኪ.ግ. ክብደት መኖር።
በቂ የደም መጠን (ሄሞግሎቢን) መኖር።
ተላላፊ በሽታ ወይም ከባድ የጤና ችግር አለመኖር።
በቅርብ ጊዜ ደም ከለገሰ የሚፈለገውን የእረፍት ጊዜ ማሟላት።
ደም ለጋሽ ለመሆን ግለሰቡ ጤናማ፣ 18 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ዕድሜ ያለው፣ በቂ ክብደት እና የደም መጠን ያለው መሆን አለበት።

በዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ ሪሰርች ፐብልኬሽን ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እና ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አስተባባሪ አማካኝነት በሚዘጋጀዉ የደም ልገሳ መርሀ ግብር ላይ በ29/09/2018 ዓ.ም ሁሉም የኮሌጁ ማህበረሰብ አሻራችሁን እንድታሳርፉ ስንል እንገልጻለን፡፡

"የደም ልገሳ ስጦታ ነው፤ ሕይወትን የሚያድን ስጦታ።"🩸🩸🩸
ግንቦት 28/2018 ዓ.ም
ዳንዲቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በቴሌግራም_አድራሻችን👇'
=> https://t.me/dandiiborudc
በfacebook_አድራሻችን👇
=> https://fb.me/DBCDC
በዩቲዩብ_አድራሻችን👇
=>https://www.youtube.com/
በኢንስታግራም አድራሻችን፡👇
=>https://www.instagram.com/dandiiborudc/ #
በኤክስ አድራሻችን፡ 👇
=>https://x.com/dandiiborudc
በቲክቶክ አድራሻችን፡ 👇
=>https://www.tiktok.com/

04/06/2026

የደም ልገሳ በኢትዮጵያ መቼ ተጀመረ ?
በኢትዮጵያ የደም ልገሳ (የደም ባንክ አገልግሎት) በይፋ የተጀመረው በ1969 ዓ.ም. ሲሆን፣ በዚያን ጊዜ የብሔራዊ ደም ስርጭት አገልግሎት (National Blood Transfusion Service) በቀይ መስቀል ማህበር ተቋቁሟል።ከዚያም በ2004 ዓ.ም. አስተዳደሩ ወደ ኢትዮጵያ የጤና ሚኒስቴር ተዛውሮ የደም ሰብሳቢነት፣ ምርመራ እና ስርጭት ስራዎችን አሁንም ደረስ እየሰራ ይገኛል፡፡

ይህንን ያዉቃሉ?
በኢትዮጵያ በጎ ፍቃደኛ የደም ለጋሾች መካከል ለብዙ ጊዜ ደም በመለገስ ቀዳሚ ከሆኑት መካከል አንዷ ወይዘሮ አሰጋሽ ጎሳ ናቸው። በኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት የሚሰሩ ነርስ ሲሆኑ እስከ ሰኔ 2017 ዓ.ም ባለው መረጃ ከ120 ጊዜ በላይ ደም ለግሰዋል።ደም መለገስ ከራስ አልፎ የአንድን ሰው ህይወት ለመታደግ ትልቅ አስተዋፅኦ ያለው እና ከፍተኛ የህሊና እርካታ የሚገኝበት በጎ ተግባር መሆኑን ይናገራሉ።
ምንጭ፡-Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/

በአንድ ጊዜ የሚለገስ ደም የሦስት ሰዎችን ህይወት ማዳን እንደሚችል የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል።

"ደም መለገስ የሰብአዊነት ከፍተኛ መገለጫ ነው።"

በዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ ደሴ ካምፓስ በ29/09/2018 ዓ.ም በሚኖረዉ የደም ልገሳ ፕሮግራም ላይ እንድተገኙ እና አሻራችሁን እንድታሳርፉ ተጋብዛችኋል፡፡

Want your school to be the top-listed School/college in Dessie?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


Dandii Boru
Dessie

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 00:00