27/05/2023
Inside...Out...
ከውስጥ ወደ ውጭ መኖር!
የሰው ልጅ አምስት የስሜት ህዋሳቱን በመጠቀም፣ ከውጪ ያለን ማንኛውም መረጃ ወደ ውስጡ ሲያስገባ ከውጪ ወደ ውስጥ ይኖራል። ፈጣሪ አምስቱን የስሜት ህዋሳት የሰጠን፣ የውጪውን ዓለም በመመልከት አስፈላጊ የሆነ መረጃ እንድንሰበስብና እንድንማር ነው። የሰው ልጅ የተሸወደው ግን፣ እነዚህን አምስቱን የስሜት ህዋሳት በመጠቀም ከውጪ ወደ ውስጥ መኖር በመጀመሩ ነው። ከውጪ ወደ ውስጥ የሚኖር ሰው፣ በውጪ ደስ የሚያሰኝ ነገር ካየ፣ በውስጡ ደስ ይለዋል። ደስ የማያሰኘውን ነገር ከተመለከት ደግሞ፣ ይደብረዋል።
አንድ ሰው በትክክል ማሰብ ሲጀምር፣ ከውስጥ ወደ ውጪ ነው የሚኖረው። ይህ ማለት ደግሞ በውጪው ዓለም ምንም አይነት ነገር ቢፈጠር፣ የውስጡን ሰላምና መረጋጋት እንዲነካበት አይፈቅድም ማለት ነው። ማንኛውም የማያስብና የማሰብ ሂደትን የማይጠቀም ሰው ግን፣ በአምስቱ የስሜት ህዋሶቹ በመጠቀም፣ ከውጪ ወደ ውስጥ በመኖር፣ የውጪው ዓለም መጫወቻ ነው የሚሆነው። ራሳችሁን ጠብቁ።
የሰው ልጅ አምስት የስሜት ህዋሳቱን በመጠቀም፣ ከውጪ ያለን ማንኛውም መረጃ ወደ ውስጡ ሲያስገባ ከውጪ ወደ ውስጥ ይኖራል። ፈጣሪ አምስቱን የስሜት ህዋሳት የሰጠን፣ የውጪውን ዓለም በመመልከት አስፈላጊ የሆነ መረጃ እንድንሰበስብና እንድንማር ነው። የሰው ልጅ የተሸወደው ግን፣ እነዚህን አምስቱን የስሜት ህዋሳት በመጠቀም ከውጪ ወደ ውስጥ መኖር በመጀመሩ ነው። ከውጪ ወደ ውስጥ የሚኖር ሰው፣ በውጪ ደስ የሚያሰኝ ነገር ካየ፣ በውስጡ ደስ ይለዋል። ደስ የማያሰኘውን ነገር ከተመለከት ደግሞ፣ ይደብረዋል።
አንድ ሰው በትክክል ማሰብ ሲጀምር፣ ከውስጥ ወደ ውጪ ነው የሚኖረው። ይህ ማለት ደግሞ በውጪው ዓለም ምንም አይነት ነገር ቢፈጠር፣ የውስጡን ሰላምና መረጋጋት እንዲነካበት አይፈቅድም ማለት ነው። ማንኛውም የማያስብና የማሰብ ሂደትን የማይጠቀም ሰው ግን፣ በአምስቱ የስሜት ህዋሶቹ በመጠቀም፣ ከውጪ ወደ ውስጥ በመኖር፣ የውጪው ዓለም መጫወቻ ነው የሚሆነው።
🏞🏞🏞✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️
https://t.me/+__7twofgS7kzMWE0
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ለበለጠ መረጃ
📞+251919030909
በደቡብ ወሎ መዲና ደሴ ፒያሳ እንገኛለን ።
17/05/2023
"የቆመ ሰው እግሩን እንቅፋት አይመታውም፤ በፍጥነት በተጓዝክ ቁጥር በእንቅፋት የመመታት እድልህ ይጨምራል ቢሆንም ግን የሆነ ቦታ መድረስህ አይቀርም" ይለናል የፈጠራ ባለሙያው ቻርልስ ኬተሪንግ።
አንድ ነገር ስትጀምር ምቹ እስኪሆን አጠብቅ፤ መንገድ ስትጀምር ለምን ሁሉም የትራፊክ መብራት አረንጓዴ አይሆንልኝም አትልም እኮ! ወዳጄ ያሰብከውን ሞክር ባለህበት ቆመህ አትቅር እንቅፋቱ ቢመታህም ተንቀሳቀስ! ምሽታችሁ መልካም ይሁን;;
https://t.me/+__7twofgS7kzMWE0
16/05/2023
ሰላም ለሁሉ ይሁን ብሩህ አዕምሮ የስብዕና ልህቀት ግንባታ ማእከል
🚶♀️🚶♀️🚶♀️🚶♀️🚶♀️🚶♀️🚶♀️🏃🏃🏃🏃🏃
ሰው ለመሆን ብትፈልግ ... 🔑
-----------------------------
፩. ወደፊት የሚሆነውን ነገር ሳትበሳጭ እና ሳትሰለች በትዕግስት ጠብቅ። የማይረባ እና ጥቅም የሌለው ነገር በመከተል ጉልበትህን አታባክን።
፪. የሚጠሉህ ጠላቶችህም ይሁኑ የሚወዱህ ወዳጆችህ በበደሉህና ባሳዘኑህ ጊዜ ቁስሉ ለልብህ አይሰማው።
፫. ሰዎች በጠሉህ ጊዜ ቂም አትያዝባቸው። እንዲሁም ደግሞ ደግነት አታብዛ ወይም በመለማመጥ ራስህን አታዋርደው።
፬. ምኞትን ተመኘው እንጂ የምኞት ባሪያ አትሁን። ሀሳብን አስበው እንጂ ነገርህ ሁሉ ሀሳብ ብቻ ሆኖ አይቅር።
፭. ደስታ እና መከራ ባገኘህ ጊዜ ሁለቱን በመጠንና በርጋታ ተቀበላቸው እንጂ በደስታ ጊዜ ፈንጠዝያ፤ በመከራ ጊዜ መጨነቅን አታብዛ።
፮. ሕይወትህን መስዋዕት ያደረክለት ሥራህ በፈረሰና በተናደ ጊዜ ይህን ክፉ ፈተና ተቀብለህ ተስፋ ሳትቆርጥ የጠፋውን ሁሉ መልሰህ ለማቋቋም ሳታመነታ ተነሳ።
፯. ያለ የሌለህን ገንዘብህን ሁሉ አንድነት አከማችተህ ስትሰራበት ሁሉንም ባንድ ጊዜ ብትከስር አጣሁ፣ ከሰርኩ ብለህ ቃል ሳትተነፍስ አሁንም ሰርተህ ለማትረፍ ከስር ጀምረህ እንደገና አንድ ብለህ ድከም።
፰. ሀሳብህ፣ ጉልበትህ፣ ስሮችህ ታክቷቸው በደከሙ ጊዜ ልብህ ብቻ አልሸነፍም ብሎ እንዲበረታቱና እንዲጠነክሩ ያስገድዳቸው።
፱. ያች የማትመለሰው አንዲትዋ ደቂቃ ትንሽ ናት ብለህ ሳትንቃት ስድሳ ሰኮንድ መሆንዋን አስበህ የሚጠቅም ሥራ ሳትሰራ በከንቱ አታሳልፋት።
ይህን ምክር ተከትለህ የፈጸምህ እንደሆነ መልካሙ ነገር ሁሉ ላንተ ይሆናል።
ግሩም ቀን ይሁንልን!!
🌔🌓🌓🌏🌏🌏🌏🌏🌏🌔🌔🌔
https://t.me/+__7twofgS7kzMWE0
🌔🌔🌔🌔🏞🌅🌔🌔🌔🌔🌔🌔
ለበለጠ መረጃ
📞+251919030909
በደቡብ ወሎ መዲና ደሴ ፒያሳ እንገኛለን ።
21/03/2023
ብሩህ አዕምሮ የከተማ ጽዳትና ዉበት የበጎ አድራጎት ስራ ላይ
ብሩህ አዕምሮ ሁለገብ የህይወት ክህሎት የስልጠና ማዕከል እና ልዩ ልዩ የማስተባበር ስራዎች ድርጅት
ብዙዎች የሰው ልጆች የሚፈልጉት የስኬት ጫፍ ለመድረስ ቢሆንም ባሰቡት ልክ ዓላማቸው
ሲሳካ አይስተዋልም፡፡ከበለጸጉት ሀገራት የሕይወት ተሞክሮ እንደምንረዳው ከመደበኛው
ትምህርት ጎን ለጎን የአመለካከት ለውጥ እና ክህሎት ላይ ትኩረት ያደረገ ተደጋጋሚ
ሥልጠና በመስጠት ትውልዱ በተማረው እውቀት ለስራ ፈጣሪነት የሚተጋ ማድረግ
ችለዋል፡፡እንደ ሃገራችን መነሻነት ማህጸነ ለምለሟ እናት ሃገር ኢትዮጵያ ፍሪዎቿ
ዘመናትን ተሻግረዋል ፡፡ አንድ ወልዳ እንዲበዛላት የዘመን ጅረት እንዳይገድባት በብዙ
ተሰርቷል፡፡እየተሰራ ይገኛል፡፡
አንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገትን በማምጣት የሕዝቦቿን ኑሮ ማሳደግ የምትችለው
በሚኖራት የሰው ኃይል እምቅ አቅም ነው፡፡ዛሬ በሣይንስና ቴክኖሎጂ በልጽገው በአገራቸው
ልማትን በማምጣት የሕዝባቸውን ተጠቃሚነት ያጐለበቱ አገሮች ልምድ የሚያሳየን ይህንኑ
ሐቅ ነው፡፡ በተለይ በቅርብ አመታት ከነበሩበት የድህነት አረንቋ ወጥተው ከፍተኛ የሣይንስና
ቴክኖሎጂ እድገት ላይ የደረሱ የደቡብ ኮሪያ፣ የቻይና፣ የሲንጋፖር፣ የቬትናም፣
የማሌዢያ፣ ወዘተ. አገሮችን ተሞክሮን እንደ አብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ እነዚህ አገሮች
ለትምህርትና ሥልጠና በሰጡት ትኩረት የሰው ኃይል ሀብታቸውን በከፍተኛ ደረጃ
በማልማት ከፍተኛ እድገት በማስመዝገብ የሕዝባቸውን ኑሮ ማሻሻል ችለዋል፡፡ ከዚህ
የምንረዳው ትምህርትና ሥልጠና ብቁና በቂ የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ ከፍተኛ ድርሻ
እንዳለው ነው፡፡
አንድ ሥራ ውጤታማ እንዲሆን ከሚያስችሉ ጉዳዮች ዋናውና ቀዳሚውን ድርሻ
የሚወስደው እቅድ ነው፡፡ በተደራጀና ሙሉዕ በሆነ እቅድ የሚሠራ ሥራ ውጤታማ
ይሆናል፡፡ በመሆኑም የሰው ሀብት ልማትን ውጤታማ ማድረግ የሚቻለው ዛሬ አለም
የደረሰበትን እድገት ደረጃ ከአገር እድገት ጋር ባገናዘ መልኩ የተናበበ ፖሊሲ በማዘጋጀት
እና ይህን መሠረት ባደረገ በተሟላ እቅድ ሲመራ ነው፡፡
ከዚህ አኳያ ዛሬ በሣይንስና ቴክኖሎጂ እድገት ያመጡ አገሮች የሰው ሀብታቸውን
ከአገራቸው ልማት እንዲሁም አለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ጋር በማስተሳሰርና
በማዘጋጀት በመተግበራቸው ውጤታማ ሊሆኑ ችለዋል፡፡ የውጤታማነታቸው ሚስጢር
የሚያስፈልጋቸውን የሰው ሀይል በፖሊሲ አቅጣጫ በማስቀመጥ፣ ፖሊሲውን ለመተግበር
የሚያስችሉ የረጅምና የአጭር ጊዜ እቅዶችን
በማውጣት በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ሀብት ማልማት መቻላቸው ነው፡፡
በሀገራችን የተጀመረው ልማትና ዕድገት ፈጣንና ተከታታይነቱን ጠብቆ እንዲሄድ በከፍተኛ
ደረጃ የሰለጠነ የሰው ሀይል ያስፈልጋል፡፡
እጅግ አሳሳቢ የሆነ ብክነት የሚታይበት የትምህርት ውስጣዊ ብቃትን በተመለክተ ብሩህ
አዕምሮ ኃ/የተ/ማህበር በማህበራዊም ሆነ በሁለገብ የማህበረሰብ አገልግሎት በህይወት
ክህሎትና ተዛማጅ ስራዎችን ለመስራት በቆራጥ መነሳሳት እየሰራ ይገኛል፡፡
ሥርዓተ-ትምህርት የትምህርት ፍልስፍና እንዲሁም ይህን ተከትሎ በህይወት ክህሎት
ደረጃ የሚቀረፁትን የትምህርት አላማዎችን መሠረት በማድረግ ዜጋን ብቁ አድርጐ
ለመቅረጽ የሚያስችለን የትምህርት ሥርአቱ ቁልፍ መሣሪያ እንደሆን ካምፓኒዉ በሙሉ
ልብ ያምናል ፡፡ስለሆነም እቅዱ በቀን፤ በሳምንት፤በዓመት፤ እንዱህም በሚፈቅደዉ የሂደት
አኳይ በማስተናገድ ይሰራል ነገር ግን እንደጅማሮ በየሁለት ሳምንቱ የማስተማር፣
የምርምር፣ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት የሆኑትን ዘርፎች በመጨመር በትጋት እየሰራ
ነው ፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ከመደበኛው ትምህርት ውጭ የአመለካከት
ለውጥ እና ክህሎት ላይ ትኩረት አድርጎ በተከታታይነት የሚሰራ መንግሥታዊም ሆነ
መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በቂ የሚባል ባለመኖሩ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ እና ከኮሌጅ
እንዲሁም ከተመረቁ በኋላ ሥራ አጥነት፣ ሱሰኝነት እና ተስፋ መቁረጥ እንዳለባቸው
ይታያል፡፡
ተምሮም ሥራ የያዘው ዓለያም በተለያዬ የስራ መስክ የተሰማራው ዜጋ የሚጠበቀውን
ያክል የሥራ ፈጣሪ እና ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ፍሰቶችን ለመቆጣጠር በቂ እንዳልሆነ
ያሳያል፡፡
ይህንን የብዙኃን ችግር የሆነውን የአመለካከት እና የክህሎት ክፍተት ለመሙላት በማሰብ
ብሩህ አእምሮ ኃ/የተ/ማኅበር በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሥነ-ልቦና ለውጥ ለማምጣት
በማለም ሕጋዊ ፈቃድ አግኝቶ በታላቅ ራዕይ የማማከር እና የሥልጠና ሥራውን ጀምሯል፡
ሁሉንም ስራ በብሩህ አእምሮ መከወን (Perform All tasks in one bright mindset)
እንዲቻል ብሩህ ተስፋ ይዞ ተነስቷል፡፡
https://t.me/+__7twofgS7kzMWE0
21/03/2023
ብሩህ አዕምሮ ሁለገብ የህይወት ክህሎትና ልዩ ልዩ የማስተባበር ስራዎች ድርጅት
በአመቱ ከሚከዉናቸዉ ስራዎች መካከል ከሆነው በጎ አድራጎት ስራዎች
በደሴ ከተማ ለተከታታይ 5 ዓመት እየሰራ ያለ አዉራአምባ የበጎ አድራጎት ጥምረት ለተቸገሩት ደራሽ የሆነ በወጣቶች የተቁቋመ ማህበር ጋር ጥምረት በማድረግ እንዲሁም ንጋት የወጣቶች ማህበር ጋር በመሆን በ10/07/2015ዓም ለአቅመ ደካሞችና ለአረጋዉያን የሚሆን የቤት አስቤዛ የማሰባሰብ ስራዎችን ሲሰራ ለማስታወሻ ይሆን ዘንድ ከማህበራዊ ሚዲያ
በዚሁ አጋጣሚ መርዳት የምትችሉ በማንኛዉም ሁሉ ቧንቧ ዉሃ እሪኩም ሸማቾች ማህበር ፊት ለፊት ይገኛል ውይም ልዩ ስሙ ግብርና ተብሎ ከሚጠራዉ ሰፈር
ገንዘብ ግን የማነው?
=====________=====
ሁለት ሀሳብ ሆኜ ብዕሬን አነሳው
ጥያቄ ልጠይቅ እየተሰናዳው
ገንዘብ የፈጣሪ ወይስ የሴጣን ነው?
የሚለው ጥያቄ ውስጤ ተመላልሶ
ሰላም እየነሳኝ ከአይምሮዬ ደርሶ
ብዙ ጊዜ አስቤ መፍትሄ መጣልኝ
መልሱን ላድማጭ ብዬ ይሄን ግጥም ፃፍኩኝ🙌
ገንዘብ ግን የማነው??
ገንዘብ የሴጣን ነው ብለው እያወሩኝ
ገንዘብ ስጠኝ ብዬ ፈጣሪን ለመንኩኝ
የሴጣን ነው እያሉ ፈጣሪን መለመን ስህተት ሆነብኝ
ግን ቆም ብዬ አሰብኩ እኔም ግራ ገብቶኝ
ገንዘብ ግን የሴጣን እንዴት ሆነ ብዬ አንድ ሰው ጠየኩኝ
እሱም አንደዚህ አለኝ👐
ሠርተህ ያመጣኸው የልፋትህ ገንዘብ በላብህ የመጣ
አንተን ተገዢ አርጎ አይምሮህን ወርሶ ካመጣብህ ጣጣ
ለሰው ማሰብ ትተህ ለራስህም ሳትሆን
ጨካኝ ህሊና ቢስ አይምሮ የለሽ ስትሆን
ገንዘብ ሞልቶህ ሣለ ሰላም ካልተሰማህ
የሴጣን ገንዘብ ነው አይጠቅምም ይቅርብህ
ብሎ መለሰልኝ የጠየኩት ሰው
ያለኝን ሰምቼ ሄድኩ አመስግኜው😊
ግን ከሄድኩበት መለስ አርጎ ጠራኝ
አንድ ነገር አለ ሳልነግርህ የቀረኝ
አለኝና ጠርቶ ወሬውን ቀጠለ
ገንዘብ የፈጣሪ የሚሆንበትም አንድ አጋጣሚ አለ
ሰርተህ ያመጣኸው የልፋትህ ገንዘብ በላብህ የመጣ
አንተን አለቃ አርጎ እሡ ባርያህ ሆኖ ከችግር ካወጣህ
ከራስህም አልፎ ለሰው ማሰብ ስትችል
አይቶ እንዳላየ ሰው ማለፍ ሳትችል
ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ ካረከው
እሱን ነገር ለምን የፈጣሪ ገንዘብ ነው
አለኝና ሄደ ምክሩን ጨርሶ
ግራ ያጋባኝን ጥያቄ መልሶ
ከዛም እኔ ብልጡ ያለኝን ሰምቼ
እግዜሩን እንዲ አልኩት እጆቼን ዘርግቼ🤲
ያንተን ገንዘብ ስጠኝ መፍትሔ እንዲሆነኝ
ሰው ልርዳበትና ሰው ይደሰትብኝ::
አመሰግናለሁ
ሰዉ እንድንሆን ፈጣሪ ይርዳን
🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄
https://t.me/+__7twofgS7kzMWE0
19/03/2023
ነገ ዛሬ ትናንት
የህይወት ግቦች (goals) ማስቀመጥ የሚሰጠው ጥቅም
በሕይወታችን የት መድረስ እንደምንፈልግ ማወቁ አስፈላጊ ሲሆን፣ ለምን መድረስ እንደፈለግን በውል ማወቅ የበለጠ አስፈላጊ ነው። አንዳንዶቹ ይህን መድረስ ከምንፈልግበት በስተጀርባ ያለውን ምክንያት እውነተኛው ግብ እያሉ ይጠሩታል። የሕይወት አጭር ወይም ረጅም ግብ (goal) ማዘጋጀት ለምን እንደሚጠቅም ባለሙያዎች እንደሚከተለው ያብራራሉ።
ፍላጎታችን እና ምኞታችን ይሟላል – በሕይወታችን አንድ ነገር ላይ መድረስ ለምን እንደምንፈልግ አስቀምጠን ስንቃኝ፣ ያስቀመጥነው ግብ በእውነትም ያንን ውጤት ሊያመጣልን እንደሚችልና እንደማይችል መመርመር እንችላለን። ስለሆነም በስሜታችን ፣ በደስታችን እና በማንነታችን ላይ ለውጥ የሚያመጡ ነገሮች ላይ ብቻ አተኩረን እንድንሰራ ይረዳናል።
በሕይወታችን ምን እንደሚያነሳሱን ብሎም እራሳችንን የበለጠ እንድናውቅ ይረዳናል – ግቡን አስቀምጠን የሚያመጣልንን ደስታ እና ትርፍ ስናመዛዝን በዚያ ሂደት ከሕይወታችን ምን ማግኘት እንደምንፈልግ ብሎም ደስታችን በምን ላይ የተመሰረተ እንደሆነ የበለጠ እናውቃለን። ይህም ለበለጠ የእራስ ማስተዋል እና ግምገማ ጥሩ ዕድል ይፈጥርልናል። ወደ ጥሩ የሕይወት አላማም ለመጉዋዝ ማስተካካያወች እንድናደርግ ይረዳናል።
ለአእምሯችን ጤንነት ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል – የሕይወት ግቦችን ማስቀመጥ እና እንደምንደርስባቸው ለራስ መንገር ለአምሯችን ሰላም መሰማት ትልቅ አስተዋፅኦ አለው። አእምሮአችን፣ ወደ ግባችን ለመድረስ ስንሰራ ደስታን ያገኛል፣ በዚህም የተነሳ ስለወደፊት ሕይወታችን ያለን አመለካከት ከፍ እያለ ይመጣል። በዚህም ትልቅ የአእምሮ ሰላም እናገኛለን።
ዛሬ ብሩህ አዕምሮ ድርጅት መስራች አባላት የአመቱን ግብ በሚያምረው በጦሳ ተራራ እስከ 2040 ዓ.ም ድረስ ፣በሚያስገርም ሁኔታ አስቀምጠው ለሃገር ለሁሉም የሚያስፈልግ ሁለገብ አቅም ግንባታን ''ብሩህ ለሁሉ ሁሉም በብሩህ እንዲሁም እሰከታዬህ ድረስ ሂድ ያልታዬህ ይታይሃል በሚለው ታላቅ አላማ ያለዉን መርህ በመከተል ለሁሉም ተደርሽ ለማድረግ ታላቁን ደስ የሚለዉን መፈክር የሰው ልጅ እና ሚዲያ ባለበት ሁሉ ብሩህን ተደራሽ ማድረግ በማለት እንሆ ሰንቆ ተነሳ መልካም የሰራ ዘመን ለዚህ የቴሌግራም ቻናል ተከታታዮች በሙሉ ብያለሁ በፍቅር ሃሳብና አስተያየት ካላችሁ
በስልክ 0919030909 ብሩህ አዕምሮ ድርጅት ወሎ ደሴ/ወይም
https://t.me/brightmindset
በዚህ ቴሌግራም ማንኛዉንም ጥያቄና አስተያይት በቅንነት መስጠት ይቻላል ጻፉልን ለሌሎችም አድርሱ ታተርፉበታላችሁ (https://t.me/senay1621) ፡፡
15/03/2023
ሰላም ለሁሉ ይሁን እንዴት አደራችሁ ?
ይህ ብሩህ አዕምሮ የስብእና ልህቀት የስልጠና ማእከል የቴሌግራም ቻናል ነው
✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️
በዓለም ላይ 3 አይነት ሰዎች አሉ። እነሱም:-
1. የተቀመጡ ሰዎች
2. የተሰረቁ ሰዎች
3. ባለ ራዕይ ሰዎች
✍️ የተቀመጡ ሰዎች
እነኚህ ሰዎች ሕይወትን በ TV ነው የሚያዩት። ትችትን፣ ነቀፌታን፣ ተግዳሮት የማይፈልጉ፣ አሸናፊነትንም ሆነ ሀላፊነትን አይወዱም ባጠቃላይ (Challenge Life) አይፈልጉም።
✍️ የተሰረቁ ሰዎች
ሌላውን መስሎ መኖር ምኞታቸው ነው። የራሳቸው የሆነ አቋምም ሆነ ማንነት የላቸውም። የተሰረቀ ሰው ራሱን ከሌላ ጋር እያወዳደረ ነው የሚኖረው!
✍️ ባለራዕይ ሰዎች
ነፃ እና ተፈጥሯዊ ሰዎች ናቸው። የበታችነት ስሜት አይሰማቸውም! መተባበር፣ ፍቅር እና ማህበራዊ ተቆርቋሪነት መገለጫቸው ነው። እነዚህ ሰዎች በቅድሚያ፦
🔹 ማህበረሰቡን
🔹 በመቀጠል ቤተሰባቸውን
🔹 በመጨረሻም ራሳቸውን የሚያስከትሉ ናቸው።
"እንዲህ አይነት ሰው ካርታውን ያለ ማጭበርበር የሚጫወት እንጂ የሚያሸንፍ አይደለም!"
(ከማህበራዊ ሚዲያ)
ለተጨማሪ ጽሁፎች ይደርሷችሁ ዘንድ join forward this link
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/bruhsc2015
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+__7twofgS7kzMWE0
05/03/2023
ሰላም ለሁሉ በሁሉ ይሁን
ዛሬ እሁድ በደሴ ወ/ሮ ፖ/ቴ/ኮሌጅ ፒያሳ ግቢ
በምርጥ አሰልጣኝ ስለ ችግሮችን የመቋቋም ክህሎት ለስኬታማ ህይወት
በሚል በሚገርም ሁኒታ እየሰጠ ይገኛል፡፡
የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉን ተጨማሪ መረጃዎችን እናደርሳለን
ሙሉዉን ከሰአታት ቆይታ በኋላ እንለቃለን
https://t.me/bruhsc2015
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+__7twofgS7kzMWE0
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Join group chat on Telegram
04/03/2023
ሰላም ለሁሉ በሁሉ ይሁን ፡፡
✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️
ያልሰማ አለ ?
✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️✍️
የማይቀረበት ታላቅ አቅም ግንባታና የህይወት ክህሎት ስልጠና
inspirational and growth of life skill training for all
👉ሳምንቱን በስራ ሲደክሙ በሰላም ለእረፍት ደርሰዉ እረፍትዎን በሚያምር ሁኔታ ማሳለፍ ይፈልጋሉ?
እንግዲያዉስ እሁድ በ26 / 06 / 2015ዓም ሀገረኛ የእናንተው የሁለገብ የህይወት
ክህሎት የስልጠና ማእከል ጎራ ይበሉ፡፡በደስታ እንጠብቅወታለን፡፡በህይወታችን መማር
ካሉብን እንቁ ትምህርቶች መካከል አንዱ የሰዉን ልጅ ድብቁን አእምሮ ማሰራት እንዲችል
ማድረግና ከተፈጥሮ ጋር በማዛመድ የስኬትን ምስጢር መጎናጽፍ ነዉ፡፡ይህም እድል
በሁሉም ዘርፍ የህይወትን ምስጢራዊ ገጽታ በብሩህ አዕምሮ ኃ/የተ/ማህበር በሙያዉ
ብቁ የህይወት ክህሎት አሰልጣኞች በየጊዜው መድረክ በማዘጋጀት ሁለገብ ትምህርቶችን
ለሁሉም እያስተማረ ይገኛል፡፡እርስዎም የዚህ ተካፍይ እንዲሆኑ በአክብሮት ተጋብዘዋል፡፡
👉ልብ ይበሉ ለሌሎች ማድረስን አይዘንጉ ፡ተደራሽ በማድረግዎ ይደሰቱበታል፡፡
*በንቃተ- -ህሊና የመለወጥ’ በሰዎች ህይወት ላይ ችግሮችን በመቀነስ ወይም ሙሉ
በሙሉ በማስወገድ የሰው ልጅ ወደ ታምራዊ አቅጣጫ የመቀየር ወሳኝ ተግባር ላይም ያተኩራል።
👇👇👇👇👇👇
ልብ ይበሉ
👆👆👆👆👆👆👆
ምርጥ ሃሳቦች እያሉህ ወደ ተግባር ካላወረድካቸው፣እራስህን ከሌሎች ጋር
ካነፃፀርክ፣የማይጠቅምህ ላይ ጊዜህን ካቃጠልክ፣ሰዎች ስለኔ ምን ያስቡ ይሆን ብለህ
ከተጨነክ፣ትላንት ስላሳለፍከው ህይወት ሁሌ የሚቆጭህ ከሆነ፣ነገ ምን እሆናለሁ ብለህ
የምትጨነቅ ከሆነ፣እቅድህ በጣም ከበዛ፣ምንም የማይጠቅም ክርክር ውስጥ
ከገባህ፣ለምትሰራው ነገር ደንታ ቢስ ከሆንክ፤ ህይወትህን በጣም እያባከንክ ነውና ንቃ!
🦻🦻🦻🦻🦻🦻🦻🦻🦻🦻🦻🦻🦻
የስልጠና ቦታ ደቡብ ወሎ ደሴ ከተማ
ወ/ሮ ስኂን ፖ/ቴ/ኮሌጅ ግቢ ዉስጥ
👉 አቅጣጫ መሐል ፒያሳ ወደ መድሃኒያዓለም ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ 100 ሜትር ገባ ብሎ
ከ 3፡30 ጀምሮ
ማሳሳብያ ሲመጡ ማስታወሻ ቢይዙ መልካም ነው
👂👂👂👂👂👂👂👂👂👂👂👂👂👂
ቴሌግራም Join as https://t.me/+__7twofgS7kzMWE0
https://t.me/bruhsc2015
ለበለጠ መረጃ
📞phone +251919030909
አዘጋጅ ብሩህ አዕምሮ ኃ/የተ/ ማህበር
ደሴ
27/02/2023
ሰላም ለሁሉም ይሁን
ይህ ብሩህ አዕምሮ ሁለገብ የስልጠና ማዕከል የቴሌግራም ቻናል ነው
🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄🌄
መንገድ ይፈለግለት!
👉እኛም እንደ ሁሉም ሰው ይህቺ አለም ወደ እኛ የምትወረውረውና የምታቀብለን ነገር አታጣም፡፡ ያለን ምርጫ ወይ ይህንን እውነታ በመቀበል አልፎ ለመሄድ ከቆረጡት መካከል በመሆን መንገድ መፈለግ ነው፣ ወይም በንጭንጭና በተስፋ መቁረጥ ተሰብሮ መቅረት ነው፡፡
• 👉ገንዘብ ያለውን ሰው የጤና ችግርን ታቀብለዋለች፤ ጤናማ የሆነውን ሰው ደግሞ የገንዘብ ችግር ትወረውርበታለች፡፡
• ፍቅረኛ ያገኘውን ሰው ከፍቅረኛው ጋር አብሮ ለመኖር ያለመቻልን ሁኔታ ትፈጥራለች፤ አብሮ ለመኖር የሚያስችል ሁኔታ ያለውን ሰው ደግሞ በአንድነት ላይ ጣልቃ-የሚገቡ ሰዎችን ትልካለች፡፡
• 👉በተፈጥሮ ሃብት የበለጸገ ሃገር ያለውን ሕዝብ እርስ በርስ መተራመስንና መከፋፈልን ትፈጥርታለች፤ በቂ የተፈጥሮ ሃብት የሌለውን ሃገር ሕዝብ ደግሞ የሌላውን በመቀማት ክፋት የተካነ ታደርገዋለች፡፡
• 👉 በአእምሮ እውቀት የተሳካለትን ሰው የባህሪይ ስነ-ምግባር እንዲጎድለው ታሳምነዋለች፤ የባህሪይ ስነ-ምግባር ያለውን ሰው ደግሞ ሰነፍ ሆኖ እንዲቀር የሚያደርግን ሁኔታ ትፈጥርለታለች፡፡
👉ልክ ነው! ይህች አለም አስቸጋሪ አለም ነች፡፡ ይህች አለም ፍትህ የላትም፡፡ ይህች አለም ጠማማ ነች፡፡ ሆኖም ይህንን ሁሉ ሁኔታ አልፈው ለመልካምነትና ለስኬት የኖሩና አሁንም የሚኖሩ፣ ነገሩ በደንብ የገባቸው ሰዎች ሞልተዋል፡፡
እነዚህን ሰዎች ከሌሎቹ ተስፋ ቆርጠው ከተቀመጡት ሰዎች ለየት የሚያደርጋቸው፣ ይህች አለም ለምታቀብላቸው እንቅፋቶች መንገድ ፈልገው ማለፍ እንደሚችሉ የማመናቸው ጉዳይ ነው፡፡
በሉ! ያላችሁን ነገር ይዛችሁ ገስግሱ! ለጎደላችሁ ነገር ደግሞ መንገድ ፈልጉለት! ይቻላል!
ያወቁትን ማሳወቅ መልካምነት ነው
መልካም ቀን ተመኘሁ
ለተጨማሪ ጽሁፎች ይደርሷችሁ ዘንድ join forward this link
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/bruhsc2015
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+__7twofgS7kzMWE0
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
@!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!መልካም መልካሙን እናስብ !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!የተባረከ ዉሎ ተመኘን !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
26/02/2023
ብሩህ አዕምሮ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጥር 14 ቀን 2015ዓ.ም በወ/ሮ ስኂን አጠቃለይ ፖሊቴክኒክ ተቋም የመሰብሰቢያ አዳራሽ ባዘጋጀው የሕይዎት ክሂሎት አነሳሽ ስልጠና (Life Skill and Inspirational Training) ላይ ተገኝቼ የበርካታ ዓመታት የትምህርትና የሥራ ዓለም የሕይዎት ክሂሎት ልምዴን ለወጣቶች አካፈልኩ፡፡
በርካታ ምሁራን የሕይዎት ክሂሎትን የሚገልጹበት አንድ ወጥ ያልሆነ አውድና ቀመር ቢኖርም እኔ የሕይዎት ክሂሎትን አንድ ሰው በህብረተሰቡ ውስጥ ሲኖር ሊጫወተው የሚገባው ተስማሚና አጥጋቢ ልማታዊ ሁለንተናዊ ሚና ብየ ገልጨዋለሁ፡፡ በሕብረተሰቡ ውስጥ የምንኖር ማናችንም የተወሰነ ተገቢ ሚና ሊኖረን ይገባል፡፡ ይህ ሚናችንም ለእኛም ሆነ ለህብረተሰቡ ተስማሚና አጥጋቢ መሆን ይኖርበታል፡፡ አለበለዚያ የሕይዎት አላማጅ ያልሆነ ከንቱ ነገር ሆኖ ፤ እኛም ከንቱ ሆነን ልንቀር እንችላለን፡፡
ማህበሩ የሚያዘጋጀው መድረክ ቀጣይነት ቢኖረው ለወጣቱ ትውልድ የመልካም ስሜታዊ ብልህነት ግንባታ የጎላ አስተዋጽዖ ይኖረዋል ብየ ስለምገምት የሚመለከታቸው ክፍሎች ትብብርና ድጋፍ ሊሰጡት፤ ወጣቶችም እየተጠራሩ በመድረክ በመገኘት ዕድሉን ቢጠቀሙበት መልካም ነው እላለሁ፡፡
በዕለቱ ሦስት የወሎ ዩኒቨርስቲ ምሁራን የሕይዎት ክሂሎትና የስሜት ብልህነት ማነቃቂያ ትምህርታዊ ገለጻ አቅርበዋል፡፡ መልካም ትምህርታዊ ገለጻ ነበር፡፡ ስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence) በሚል ርዕስ ዝግጅት ያቀረቡ አንድ ምሁር ዶ/ር ኢዮብ ማሞ (2009) የደረሱትን "የስሜት ብልህነት" መጽሐፍ ጠቅሰው ስለዜጎች የስሜት ብልህነት በተጠና አንድ ዓለምአቀፍ ጥናት ከ185 አገራት ኢትዮጵያ 182ኛ ደረጃ መያዟ ተገልጿል፡፡ በእርግጥ ይህ ግፊት በእጅጉ ቆርቁሮን ወደፊት ለአዎንታዊ የስሜት ብልህነት ባለቤትነት በቁጭት እንድንነሳሳ ይገፋፋናል ብየ አስባለሁ፡፡
ምንም እንኳ ጥናቱ በወቅቱ ትውልድ የስሜት ብልህነት ላይ ቢመሰረትም እኛ የብሩህ አዕምሮ ባለቤቶች የነበሩ ቀደምቶች የባህርይ ውርስ ያለን ትውልድ ስለሆንን ይህንን ያህል በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የምንገኝ ዜጎች አንሆንም፡፡ በዩኔስኮ የዓለምአቀፍ ቅርስ መዝገብ ላይ የተመዘገቡ የታሪክ፤ የባህልና የኃይማኖት ገጽታዎች መረጃዎች አሉን፡፡ ኢትዮጵያ በዓለም የብልህነት የፈጠራ ውጤት ቁንጮ የሆነውን የሚበሉ እጽዋትና እንስሳት መርጣ ካላመደችና ለዓለም ካበረከተች ጥቂት አገራት፤ በዓለም ላይ የእርሻ ሥራ ከተጀመረባቸው አምስት ቦታዎች (Five Hearths) ተርታ አንዷ ናት፡፡
ኢትዮጵያዊያን ከአገራቸው ታሪካዊ ጠላቶች በየጊዜው የሚሰነዘርባቸውን ጥቃት በብቃት ተከላክለው በመቀልበስ አገሪቱ በታሪክ በሚታወቁ ትውልዶች ስም ተመዝግባ ትታወቃለች፡፡ በአሁኑም ጊዜ በዓለም በሚገኙ የታወቁ የከፍተኛ ትምህርትና ምርምር ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ዜጎችንና የዓለም አቀፍ ውድድር ተወዳድረው የሚያሸንፉ ዜጎችን የምታበረክት አገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ አትንኩኝ ባይ አገር ናት፡፡
ይህ የጥናት ውጤት የአገራችን ታሪካዊ ጠላቶች በየጊዜው የሚፈጥሩልን እኛን አዳክሞ ዝቅ የማድረግ አጀንዳ ቀጣይ ጥረት ሊሆን ይችላል፡፡ የቀደምቶቻችን የስሜት ብልህነት ለአሁኑ ትውልድ የስሜት ብልህነት ደረጃ መሰረቱ ነው፡፡ በእርግጥ ይህ የብልህነት ደረጃ ጥናት ጥቂት ዜጎች ላይ የተደረገ የቅርብ ጊዜ የባህርይ ዳሰሳ ጥናት ውጤት ነው፡፡
ጥናቱ የተካሄደበት ይህ ቅርብ ጊዜ የዜጎች ስሜት ለኢትዮጵያ ብቸኛ በሆነው የብሔር ፖለቲካ የተቃኘበት፤ የዜጎች አዕምሮ በብሔር ፖለቲካ ትርክት አስከፊ ውጤት የላሸቀበት ወቅት በመሆኑ ለዜጎች የስሜት ብልህነት ደረጃ መውረድ ኋላቀሩ የብሔር ፖለቲካ ጉልህ መጥፎ አስተዋጽዖ አላበረከተም ማለት አይቻልም፡፡
ዛሬ የዜጎች አዕምሮ በብሔር ፖለቲካ ንግድ መሲሆቻችን አጉል የፈጠራ ትርክት ተንሸዋሯል፣ ደንዝዟል፡፡ ስለራሳቸው፤ ስለአገራቸውና ሕዝቧ ሊኖራቸው የሚገባው የተስተካከለ የስሜት ብልህነት፤ ብልህ የሆነ ሰው ሊጠብቀው ከሚችል ደረጃ በታች ዘቅጧል፡፡ አገራቸው ስትፈርስ ቆመው የሚመለከቱ፤ የሚጨፍሩና አገሪቱን ለማፍረስ እስከ ሲዖል ድረስ እንወርዳለን የሚሉ ሴረኛና ሸፍጠኛ የፖለቲካ መሪዎችና ደቀመዝሙሮች የበዙባት አገር በዓለም ኢትዮጵያ ብቻ ናት፡፡
ኃይማኖትን እንደ ሳይንስ ግኝት ይዘቱንና ሥነስርዓቱን በየጊዜው ለማሻሻል የሚውተረተሩ፤ ነባር የኃይማኖት እሴቶችን፣ ስሪቶችንና ትውፊቶችን በመከለስ ለወቅታዊ የፖለቲካ ጥቅም ማሳኪያ ለማዋል የሚጥሩ ሆድአደሮች፤ በሕዝብ ጉስቁልናና እልቂት ላይ ረዥም ዕድሜ በድሎት ለመኖር የሚጣጣሩ ኃላፊነት የጎደላቸው ዕኩያን ፖለቲከኞች ጉልበት ያወጡበት አሳዛኝ ወቅት ነው፡፡ ይህ የሆድ አደርነት ሰለባ መሆን ያስከተለው የድድብና ውጤት በስሜት ብልህነት ጥናት ወቅት ሲመዘገብ ለዜጎች የስሜት ብልህነት ደረጃ መውረድ ዓይነተኛ ፍንጭ ይሰጣል፡፡ ከብሔር ፖለቲካ ድድብና ስንወጣ የዜጎች የስሜት ብልህነት ዳግም ያቆጠቁጣል፡፡ ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
👇fro this face book page https://www.facebook.com/adalmohammed.hussien?__cft__[0]=AZUesfb9YNWY1scGGA7n-beld29U-d7zBkt7qz4zmXjPGCKPAKcpPUbDe5JNSMHwpgV9O1JlkPXBMTQpd3fR73ffS1dIrkUjSuy7b0ic464tz7q3ovHsSjd46zTl3aaayIVDk7vfIVL68el3t6VZn6pw&__tn__=-UC%2CP-R
this is BRUH aimiro company telegram channel join
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+__7twofgS7kzMWE0
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆