27/07/2025
በአማራ ክልል የ2017ዓ.ም 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ይፋ ሆነ‼️
*****
ሐምሌ 20/2017(ትምህርት ቢሮ)
በአማራ ክልል በ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና የተፈተናችሁ ተማሪዎች በሙሉ ፈተናው በአጭር ጊዜ ውስጥ በቴክኖሎጅ በመታገዝ እርማቱ ተካሂዶ ይፋ ሆኗል።
ተማሪዎችም ከታች በተቀመጡት በሁለት አማራጮች ውጤታቸውን ማየት የሚችሉ ሲሆን
➊ በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application ) ላይ
1) 👉 ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara.ministry.et/ #/result የሚለውን አድራሻ በመፃፍ
2)👉 በሚመጣው ቅጽ(form) ላይ
የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) በማስገባት
3)👉ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡
❷ በተጨማሪም 👉 በሚለው የቴሌግራም ቦት ላይ በመግባት ተማሪዎች ውጤታቸውን መመልከት የሚችሉ ሲሆን ለመጀመሪያ
👉start የሚለውን ይጫኑ!
👉በመቀጠልም ክፍልዎን ይምረጡ
👉ከዚያም ክልልዎን ይምረጡ
👉በመቀጠል የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምን በማስገባት ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።
ተማሪዎች ማንኛውም ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ካላቸው ማቅረብ ይችላሉ። ቅሬታቸውንም ለማቅረብ
➌በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ላይ ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application ) ላይ
1) 👉 ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara.ministry.et/ #/complaint የሚለውን አድራሻ በመፃፍ
2)👉 በሚመጣው ቅጽ(form) ላይ
የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number)እና
የተማሪውን የመጀመሪያ ስም (First Name)በማስገባት
3)👉 የትምህርት ዓይነት አሳይ(Fetch course) የሚለውን ቁልፍ በመጫን
4)👉 ቅሬታ ማቅረብ የሚፈልጉበትን ይምረጡ
5)👉በመጨረሻም ሪፖርት (Add Complaint) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ።
🎯 ማስታወሻ ፡ በቅድሚያ ቪፒኤን ማጥፋት ይኖርባችኋል፡፡
ሃምሌ 20/2017 ዓ.ም
ትምህርት ቢሮ
#ትምህርትለትውልድ
20/04/2025
🔷👉 በሰንበትም መጨረሻ መጀመሪያው ቀን ሲነጋ መግደላዊት ማርያምና ኹለተኛዪቱ ማርያም መቃብሩን ሊያዩ መጡ።
🔴👉 እንሆም የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ።
🔷👉 መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ። ጠባቂዎቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ እንደ ሞቱም ሆኑ።
🔴👉 መልአኩም መልሶ ሴቶቹን አላቸው፦እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ ዐውቃለሁና እንደ ተናገረ ተነሥቷልና በዚህ የለም የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።
የማቴዎስ ወንጌል ም. 28 ÷ ቁ. 1
❗እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ❗
13/01/2025
ማሳሰቢያ - ሁለት ቀን ብቻ ቀረው!
የ2ዐ17 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ( የ12 ኛ ክፍል) ፈተና ምዝገባ ማክሰኞ ጥር 6/2017 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ይጠናቀቃል።
ስለሆነም በተለያየ ምክንያት ያልተመዘገባችሁ ካላችሁ በነዚህ ቀሪ ሁለት ቀናት ላይ ብቻ እንዲትመዘገቡ እናሳስባለን።
⚡️ያልተመዘገበ አይፈተንም❗️
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ትምህርት ሚኒስቴር ✅
✅ ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
🔻https://t.me/Tmhrt_Ministers
09/01/2025
በተለያዩ አካባቢዎች በሰማይ ላይ እየነደደ የሚጓዘው ምን ይኾን? በሳይንስና በሃይማኖት
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 ዛሬ ጥር 1/ 2017 ዓ.ም. በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች የታየ በሰማይ እየተቀጣጠለ የሚኼድ በጣም በርካታ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች በውስጥ መሥመር እየተላኩልኝ ነበርና ምልከታዬን ለማስቀመጥ እሞክራለኹ።
💥 ከሰማይ ላይ አብርተው ስለሚታዩ ስለሚወድቁ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አካላት መረዳት ግድ ይላል።
የተፈጥሮ የሕዋ ዐለቶችን አስቀድመን እንመልከት፦
1. አስትሮይድ
2. ሜትዮራይድ
3. ሚትዮር
4. ሜትሮይት
መካከል ያለውን ልዩነት አንድነት መረዳት ያስፈልጋል፡-
1. አስትሮይድ
💥 በዋነኛነት በማርስ እና በጁፒተር መካከል ባለው የአስትሮይድ ቀበቶ ውስጥ የሚገኙት ዐለታማ ሥሪትነት ያላቸው አካላት ናቸው። መጠናቸውን ለመረዳት ለምሳሌ አስትሮይድ ቬስታ መጠኑ 329 ማይል (530 ኪሎ ሜትር) ዲያሜትር ያለው ሲኾን ከታናናሾቹ ውስጥ ከ33 ጫማ (10 ሜትር) በታች የኾኑም ይገኙበታል። የኹሉም አስትሮይድ አጠቃላይ ክብደት ግን ከምድር ጨረቃ ያነሰ ነው።
👉 በዚኹ አጋጣሚ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ዐርብ ሚያዝያ 5/ 2021 ዓ.ም ወይም እንደ ጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠር ኤፕሪል 13/ 2029 አፖፊስ የተባለው አስትሮይድ ከምድር በላይ 30,600 ኪሎ ሜትር (19,000 ማይል) ርቀት ላይ የሚያልፍ ሲኾን ቢሊዮኖች በዐይናቸው ያዩታል። መሬትን የመመታት ዕድሉ 2.7 ፐርሰንት ብቻ ነው። (አንድሮሜዳ ክፍል 2 ገጽ 388 - 394 )
2. ሜትዮራይድ
💥 ሜትዮራይዶች በሕዋ ያሉ ትናንሽ ዐለቶች ሲኾኑ መጠናቸው ከከሸዋ ቅንጣት እስከ 1 ሜትር አካባቢ ይደርሳሉ። አንዳንድ ሜትዮራይድ ዐለቶች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ብረታ ብረት ወይም የድንጋይ እና የብረት ውሕዶች ናቸው። ሜትዮራይድ ብዙ ጊዜ ከአስትሮይድ ወይም ከኮሜት ወይም ከሌሎች ፕላኔቶች ጭምር የሚመጡ ናቸው። በአጠቃላይ ሜትዮራይድ ስንል ገና በሕዋ ላይ ያሉትን ነው።
3. ሚትየር
💥 ከላይ እንዳየነው ሜትዮራይድ ወደ ምድር ከባቢ አየር ወይም ወደ ሌላ ፕላኔት በከፍተኛ ፍጥነት ሲገቡ እና ሲቃጠሉ ሚትዮር ይባላሉ። በሌላ አጠራር “ተወርዋሪ ኮከቦች” ብለን የምንጠራቸው ሲኾን አንዳንድ ጊዜ ሜትየሮች ከቬኑስ የበለጠ ብሩህ ኾነው ሊታዩ ይችላሉ። ያን ጊዜ “የእሳት ኳሶች” ተብለው ይጠራሉ። ብዙ ተወርዋሪ ከዋክብት በአንድ ላይ በሰዓታት ሲታዩ "ሜትየር ሻወር" በመባል ይታወቃሉ።
4. ሜትሮይት
💥 ሳይቃጠል የምድርን ከባቢ አየር ዐልፎ በምድር ላይ የሚያርፍ የሜትሮይድ ቁራጭ መጠሪያ ነው። በሰዓት በዐሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን በመጓዝ በኃይለኛ ግፊት ወድቆ ሲበታተን ብሩህ ነበልባል ይመስላል።
ሜትሮይትስ በሦስት ዋና ዋና ዓይነቶች ይከፈላሉ፡-
1) ድንጋያማ ሜትሮይትስ (በዋነኛነት ከሲልኬት) ማዕድናት የተውጣጡ ናቸው)፣
2) የብረት ሜትሮዮይትስ (በአብዛኛው ከብረት-ኒኬል ውሕዶች የተውጣጡ ናቸው)
3) ድንጋያማ ብረት ሜትሮይትስ (በግምት እኩል መጠን ያላቸው የሲሊኬት ማዕድናት እና ብረት ኒኬል ይዘዋል)
👉 ሜትሮይቶች ሲታዩ የምድር ዐለቶችን ሊመስሉ ይችላሉ፣ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ የሚያብረቀርቅ ሊመስል የሚችል የተቃጠለ ውጫዊ ክፍል አላቸው። ይኸውም በከባቢ አየር ውስጥ በሚያልፉበት ጊዜ የሜትሮይት ውጫዊ ገጽታ ሲቀልጥ የሚፈጠር ነው።
👉በምድር ላይ ከ 50,000 በላይ ሜትሮይትስ ተገኝተዋል.
ከእነዚህ ውስጥ 99.8% የሚሆኑት ከአስትሮይድ የሚመጡ ናቸው።
👉 በየቀኑ 48.5 ቶን የሜትሮይት ቁስ አካል ወደ ምድር ይወድቃል። ይህም በዓመት 17,000 ሚቴዮራይትስ እንደማለት ነው። አብዛኛው ግን በከባቢ አየር ውስጥ ተንኖ ተወርዋሪ ኮከብ ይኾናል።
👉 በቅርብ የተከሰቱ አደገኛ ከሚባሉት የሜትሮይትስ ክስተቶች ውስጥ ኹለቱን በማንሣት ጽሑፌን ልቋጭ፦
1ኛ) በዘመናዊ ታሪክ ውስጥ አንድ ትልቅ ሜትሮይድ ወደ ምድር ከባቢ አየር ውስጥ የገባው እኤአ በ1908 ሲኾን የቱንጉስካ ክስተት በመባል ይታወቃል። ይህ ሜትዮር በሩሲያ በሳይቤሪያ ላይ የተከሰተ ሲኾን ምድሩን ሳይመታ በፊት በአየር ላይ ጥቂት ማይል ርቀት ላይ ፈነዳ።
👉 የፍንዳታው ኃይል በመቶዎች የሚቆጠሩ ማይሎች ስፋት ባለው ክልል ውስጥ ዛፎችን ለማውደም የሚያስችል ኃይለኛ ነበር። ሜትዮሩ 120 ጫማ (37 ሜትር) ስፋት ያለው እና 220 ሚሊዮን ፓውንድ (100 ሚሊዮን ኪሎ ግራም) ይመዝን ነበረ። በአካባቢው በመቶዎች የሚቆጠሩ አጋዘኖች ሲሞቱ ነገር ግን ማንም ሰው በፍንዳታው መሞቱን የሚያሳይ ቀጥተኛ መረጃ የለም።
2ኛ) እ.ኤ.አ. በ 2013 በቼልያቢንስክ ሩሲያ ሰማይ ላይ ቤትን የሚያህል ሜትሮይድ በሰከንድ ከ11 ማይል (18 ኪሎ ሜትር) በላይ ወደ ከባቢ አየር በመግባት ከመሬት በላይ 14 ማይል (23 ኪሎ ሜትር) ላይ ፈነዳ። ፍንዳታው ወደ 440,000 ቶን የሚገመተውን የቲኤንቲ ኃይል በመልቀቁ ከ200 ስኩዌር ማይል (518 ስኩዌር ኪሎ ሜትር) በላይ መስኮቶችን የሰባበረ እና ሕንፃዎችን ያበላሽ አስደንጋጭ ኹኔታን ፈጠረ። በፍንዳታው ይልቁኑ በመስታወት ስብርባሪ ከ1,600 በላይ ሰዎች ቆስለዋል።
💥 ሌላው በሰማይ እየተቃጠሉ ሲሄዱ ሊታዪ የሚችሉት ሰው ሠራሽ ነገሮች
👉 ከአሁን በኋላ የማይሠሩ በጠፈር ውስጥ ያሉ ሰው ሠራሽ ነገሮች Space debris, space junk, orbital debris በመባል ይታወቃሉ።
ለምሳሌ፡-
👉 የድሮ ሳተላይቶች
👉 የሮኬት ክፍልፋዮች
👉 የፈነዱ ወይም የተጋጩ ተሽከርካሪዎች ወይም የተቆራረጡ ቁርጥራጮች ይገኙበታል።
👉 ከጠፈር ተልእኮ በኋላ የተጣሉ ቁሶች ናቸው።
💥 በግምት ከ10 ሴንቲ ሜትር በላይ ከ36,500 በላይ ቁሶች ሲኖሩ፤ ከ1-10 ሴ.ሜ በላይ 1 ሚሊዮን ቁርጥራጮች እና ከ1 130 ሚሊዮን የሚጠጉ ትናንሽ ቁርጥራጮች ይገኛሉ።
ሊያመጡ የሚችሉት አደጋዎች፡-
1) የሚሠሩ ሳተላይቶችን፣ ዐለም ዐቀፍ የጠፈር ጣቢያ (አይኤስኤስ) ወይም የጠፈር መንኮራኩሮችን በመግጨት ሊጎዳ ይችላል።
👉 አንዳንድ ቁርጥራጮች ወደ ምድር ከባቢ አየር ውስጥ ከገቡ መሬት ላይ አደጋ ሊፈጥሩ ይችላሉ።
👉 ለምሳሌ ሰኞ ታኅሣሥ 21/ 2017 ወይም December 30, 2024, በኬንያ፣ ሙኩኩ መንደር ውስጥ ከሮኬት የመለያያ ቀለበት በመባል የሚታወቅ አንድ ትልቅ ብረታማ ነገር የተከሰከሰ ሲኾን ቀለበቱ በግምት 2.5 ሜትር ዲያሜትር እና 500 ኪሎ ግራም ይመዝናል። እንደ እድል ሆኖ ግን ምንም ጉዳት አልደረሰም።
💥 ሌላው በተለያዩ ሀገራት ታዩ የሚባሉት የማይታወቁ በራሪ አካላት (UFO ወይም UAP) ዙሪያ ብዙ ቪዲዮዎች በYoutube ላይ የሠራሁትን ማየት ይቻላል።
💥 በሃይማኖት መጻሕፍት ስንመለከት በተለይ በዮሐንስ ራእይ ላይ ለቁጣ የሚወድቁ እንደ ችቦ የተቃጠለ የሚመስል እንደሚወድቅ እንዲህ ይጽፋል፦
✍️ “ሦስተኛውም መልአክ ነፋ፤ እንደ ችቦም የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፥ በወንዞችና በውኃም ምንጮች ሲሶ ላይ ወደቀ። የኮከቡም ስም እሬቶ ይባላል። የውሃውም ሲሶ መራራ ሆነ መራራም ስለተደረገ በውሃው ጠንቅ ብዙ ሰዎች ሞቱ።”
— ራእይ 8፥10-11
✍️ “ሁለተኛውም መልአክ ነፋ፤ በእሳት የሚቃጠል ታላቅ ተራራን የሚመስል ነገር በባሕር ተጣለ፤ የባሕርም ሲሶው ደም ሆነ”
— ራእይ 8፥8
💥 ስለዚኽ አንባቢዎች የራሳችሁን ምልከታ በአስተያየት መስጫው ላይ ማስቀመጥ ትችላላችኹ።
(ስለ ሥነ ፈለክ ለመረዳት አንድሮሜዳ ክፍል 1፤ አንድሮሜዳ ክፍል 2፤ ማዛሮት መጽሐፍን ያንብቡ)
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
07/01/2025
ልደተ ክርስቶስ
የሰው ልጅ ነጻ ፈቃዱን ተጠቅሞ አትብላ የተባለውን ዕፀ በለስን በልቶ በራሱ ላይ ሞትን ዐወጀ ከእግዚአብሔር ተለየ (ዘፍ. ፪፣፲፯) ቸርነት የባሕርየ የሆነ እግዚአብሔር ግን ሰውን ሞቶ እንዲቀር አላደረገውም። በከልጅ ልጁ ተወልዶ እንደሚያድነው ቃል ኪዳን ሰጠው። እግዚአብሔር ይህንን ቃል ኪዳን በየዘመኑ ለተነሡ ሰዎች በተለያዩ ነቢያት አስነገረ።
“ ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ እምርላሃለሁ፣ይቅርታም አድርግልሃለሁ “(ቀሌም.፫፥፲፱፣ኢሳ.: ኢሳ.፱፣፮) እንዲል ጊዜው በደረሰ ጊዜም ከሦስቱ አካላት እግዚአብሔር አንዱ ወልድ ከድንግል ማርያም ተወለደ። “ነገር ግን ቀጠሮው በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ልጁን ላከ ከሴትም ተወለደ” እንዲል (ማቴ. ፩፣፳፩-፳፫፣ሉቃ. ፪፣፮-፯፣ዮሐ. ፩፣፲፬ ፣ገላ. ፬፣፮)
የጌታችን ሁለቱ ልደታት
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ልደታት አሉት።እኒህም ቀዳማዊ ልደትና ደኃራዊ ልደት ይባላሉ።
ቀዳማዊ ልደት
አብ ወልድን በዘመን ሳይበልጠው የወልድ ቃልነት የመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነት ሳይለየው ወልድን ወለደው መንፈስ ቅዱስን አሠረፀው እንላለን። ይህም ከኅሊና በላይ የሆነ በሰውና በመላእክት አእምሮ ሊመረመር የማይችል ነው። “ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከሆድ ወለድኩህ” (መዝ. ፻፱፣፫) እንዲል። ስለዚህም የአብ ግብሩ ወላዲ ይባላል። የወልድ ግብሩም ደግሞ ተወላዲ ይባላል። በቀዳማዊ ልደቱ እናት የለውም። ቅዱስ ያሬድ በአንቀጸ ብርሃን ድርሰቱ “ከመዝ ነአምን ዘአልቦቱ እም በሰማያት” ብሎ የገለጸው ይህንን ነው። በዚህኛው ልደት ተመትሮ የለበትም። ይህም ማለት አብ ወልድን ሲወልደው ወልድ ከአብ አልተለየም። ዘኢየኀልቅ ልደቱ ያሰኘው ይህ ነው። ወልድ ወልድ ሲባል ይኖራልና።
ደኃራዊ ልደት
ደኃራዊነቱ ለቀዳማዊው ልደት ነው። በኋለኛው ዘመን አዳምን ለማዳን ያለ አባት ከድንግል ማርያም የተወለደው ልደት ነው። ይህ ልደት ያለ ወንድ ዘር፣ያለ ሩካቤ ከድንግል ማርያም የተወለደው ልደት ነው። በክርስቶስ ልደት የሰው ልጆች ተስፋ ተፈጸመ። ስለዚህም እረኞች ከመላእክት ጋር የደስታ ምስጋናን አመሰገኑ። “ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ ሠራዊት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መጡ። ክብር ለእግዚአብሔር በሰማያት ሰላምም በምድር። ለሰው ልጅም በጎ ፈቃድ ሆነ” (ሉቃ. ፪፣፲፫-፲፬ ) እንዲል ለምድር ሰላም ተሰበከላት። ሰላሟ ክርስቶስ መጣ። እሾህ አሜኬላ ይብቀልብህ ፍትወታት እኩያት ይሰልጥኑብህ የተባለ ሰው በክርስቶስ ልደት ግን “በጎ ፈቃድ ሆነለት” ። ድንግል ፈጣሪዋን በሥጋ ወለደችው። (ሃይ. አበ. ፵፯፣፪-፬)
እንዴት ሰው ሆነ
እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሲሆን እግዚአብሔርነቱን ሳይለቅ ያለ መለወጥ ነው። እግዚአብሔር የሚለዋወጥ አምላክ አይደለምና። ሰውም አምላክ ሲሆን ሰውነቱን ለውጦ አይደለም። ሰው አምላክ ሆነ እያልን ስንናገር ስለክርስቶስ ሰውነት እየተናገርን መሆኑን ማስተዋል ይገባል። አምላክ ሰው ሆነ ስንልም በተለየ አካሉ ስለ አካላዊ ቃል ወልድ እየተናገርን መሆኑን መረዳት ይገባል።
አብ እና መንፈስቅዱስ ሰው አልሆኑምና። ከዊነ ልብ እና ከዊነ እስትንፋስ ሰው አልሆኑምና። ቃል ሥጋ ሲሆን ሥጋም ቃልን ሆነ። የቃል ገንዘብ የሆነው ሁሉ ለሥጋ ሆነ። የሥጋ ገንዘብ የሆነው ሁሉ የቃል ሆነ። ቅዱስ ቄርሎስ እንደተናገረው። “እንቲኣሁ ለቃል ኮነ ለሥጋ ወእንቲኣሁ ለሥጋ ኮነ ለቃል”። የኢየሱስ ክርስቶስን ልዕልናውን በትሕትናው አወቅን። ስለዚህ ያለ መለወጥ፣ ያለ መቀላቀል፣ ያለ መለየት በተዋሕዶ በተዐቅቦ ሰው ሆነ።
።።።። ።።።።
።።።።። ።።።።።
።።።።። ።።።።።
05/01/2025
ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተላለፈ ማስታወቂያ‼️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
1 - የ 1 2ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ጥር 6 /2017 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ የሚጠናቀቅ ይሆናል። ስለሆነም ምዝገባ ያላጠናቀቃችሁ ከቀነ ገደቡ አስቀድማችሁ እንዲታጠናቅቁ እናሳስባለን።
2- የ2017 የትምህርት ዘመን ፈተናዎች ይዘት የሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ሁኔታ ከ 9 - 12ኛ ክፍሎች እንዲሁም የ 8 ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 7- 8ኛ ክፍሎች የሚሸፍን ይሆናል።
3- እያንዳንዱ ተማሪ በተማረበት የክፍል ደረጀ የተማረውን የተማሪ መጽሐፍን መሠረት አድርጐ ሊዘጋጅ ይገባል። ፈተናዎቹ ተማሪዎቹ የተማሩትን መሠረት አድርገው የሚዘጋጁ ይሆናል።
የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል።
24/09/2024
🇪🇹🇪🇹 እንኳን ወደ 🪐🪐 GPT 🪐🪐
🇪🇹ቻናል በደህና መጡ!!!🇪🇹
✍✍✍✍✍ ከ9 እስከ 12 ክፍል ለተማሪዎች እና ለመ/ራን ለ2017 ዓ.ም የት/ት ዘመን Physics በማዘጋጀት ላይ ነኝ።
✅ Short Notes PPT and PDF
✅ Exam Questions
✅ የPhysics ቤተ ሙከራ ጥያቄ እና physics Lab Simulation
📖📖📖📖✍✍✍✍ በተጨማሪም አድሱን ስርዓተ ትም/ት ከ7ኛ እስከ 8ኛ General science and Mathematics
✅ Short Notes PPT and PDF SB and TG
✅ Exam Questions
✅ የ ቤተ ሙከራ ጥያቄ እና Lab Simulation
Join ያድርጉን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/getnet12/422
https://youtube.com/shorts/ZZ3N8wcRcYA
https://www.facebook.com/profile.php?id=100024312595895
Telegram: Contact @getnet12