Delghi School

Delghi  School This page is dedicated to Delghi Elementary School. We will share memories of the past and wishes fo

የደልጊ ትምህርት ቤት የተቋቋመው በ1952 በአንድ ግለሰብ ቤት ውስጥ ነበር። በ1954 ሁለት ክፍል ያለው ቤት በሕዝብ ትብብር ተሠርቶ ትምህርት ቤቱ ወደዚያ ተዛወረ ። ይህ ቤት በየጊዜው ክፍሎች እየተጨመሩለት ቆይቶ በ1961 አሁን ያለው ትምህርት ቤት በዚያው ቦታ ተሠራ።

25/12/2021

የቀድሞ ተማሪዎቻችን ትምህርቤታችን ለማሻሻል የሁላችሁንም የሀሳብ፣ ይጉልብት እና የቁስ ድጋፍ እንሻለን።

Sites for Free Online Education1. Coursera--https://www.coursera.org/2. edX--https://www.edx.org/3. Khan Academy--https:...
07/09/2020

Sites for Free Online Education

1. Coursera--https://www.coursera.org/
2. edX--https://www.edx.org/
3. Khan Academy--https://www.khanacademy.org/
3. MIT OpenCourseWare--https://ocw.mit.edu/index.htm
4. Stanford Online--https://online.stanford.edu/
5. Codecademy--https://www.codecademy.com/
6. ICT iitr--https://eict.iitr.ac.in/onlinecourse.html
7. NPTEL--https://nptel.ac.in/course.html

Join Coursera for free and learn online. Build skills with courses from top universities like Yale, Michigan, Stanford, and leading companies like Google and IBM. Advance your career with degrees, certificates, Specializations, & MOOCs in data science, computer science, business, and dozens of o...

ለገጻችን ተከታዮችእንደሚታወቀው Delghi School ገጽ የተቋቋመው የት/ቤቱን 50ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለትምህርት ቤቱ ድጋፍ ለማሰባሰብ በሚል አላማ ነዉ፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ...
15/09/2019

ለገጻችን ተከታዮች

እንደሚታወቀው Delghi School ገጽ የተቋቋመው የት/ቤቱን 50ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለትምህርት ቤቱ ድጋፍ ለማሰባሰብ በሚል አላማ ነዉ፡፡
ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በገጻችን ላይ ገጹ ከተቋቋመበት አላማ ውጭ የሆኑ ጹሁፎች እየወጡ ይገኛል፡፡ ለዚህ ይቅርታ እየጠየቅን ፣ ለወደፊቱ እንደማይደገም እናሳዉቃልን!!

31/07/2019

ትዝታ ትዝ ሲል ትዝ የሚል ትዘዝ ይላል፡፡
ዛሬ ከመሸ ከቀድሞ ወዳጀ ጋር ገናኝቸ አሮጌ ዘፈኖችን ስኮመኩም ማን ትዛለህ አትሉኝም?
የእነ ሀዳስ ፣ባንችቆይ ፣ይርገዱ ፣አድባ ፣አንችናሉ መሸታ ቤት ዉል አይልብኝም መሠላችሁ፡፡፡፡፡፡፡፡፡ነገሩ ወዲህ ነው በ1984 እና ተከታዮቹ ከላይ በጠቀስኳቸው መሸታ ቤቶች የነበሩ ሙዚቆች ከዚነት እስከ ፍቅራዲስ በቢጫ መርገገጫዋ አርቲች ቴፕ ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ያጉረመርማሩ ተስፋ(በጊዜው መብራት የሚያበራ የነበር)ሠዐቱን አእንዲረሳ ጋባዡ ብዙ ነበር፡፡
ማን ነበርክ ዘመነ ፣መሴ እግዙኝማ
የቤቴ ግድግዳ
ጣራና ወለሉ
አስቱካ.......

11/07/2019

መጠናል ከተደበቅንበት ጣና ሀይቅ በመዐበሉ ተገፍተን ከአንባዛው ጋር ወደ ፌዝ ቡክ ተቀላቅለናል፡፡
ጠፍተን ስለነበር አፋሊላሂ በሉን የሀምሌ አቦ ልጆች፡፡ድሮ ድሮ ሀምሌ አቦ ሲደርስ አንገፋራ ፣ መንጠቆ ፣ጫፋ ላይ ብስማር የተሠካበት ዱላ ተይዘዞ ጉዞ ወደ ቶካ (የዛሬ ጊዜ ልጆችን)አይመለከትም እናም ሀምሌ ያዘነበውን አሳና አምባዛ ማሯሯጥ የቀናንን ያህል አፍሰን መመለስ ትዝታው ቡዙ ነው ፡፡

28/01/2019

ወርሃ ጥር ከወደ ደልጊ
* * *
ሰላም ሰላም ውድ ጓዶች እንደምን አላችሁ እኔ እንደፈለኩት ሳይሆን እኔ እንደሚያስፈልገኝ የሚያኖረኝ የድንግል ማርያም ልጅ እርሱ ክብሩን ይውሰድ አሜን! ዛሬ ወደኋላ በሀሳብ የጎተተኝን ትዝታ ለእናንተም ላጋራችሁ ይህችን ኮሳሳ ብዕሬን አነሳሁ ፥ ኑ ተከተሉኝ
መቼም በዓል ሲደርስ #የሰውልጅ የትም ቢሆን ትዝ የሚለው የተወለደበት ቀዬው፣ የቦረቀበት ሜዳው፣ የወለዱት ቤተሰቦቹ፣ ወግ ባህሉ፣ ክፉናደግ የለየበት ህይወቱ፣ ከምንም በላይ ሲያጠፋ ቆንጥጦ ሲያለማ መርቆ ሲቸገር ረድቶ ያሳደገው ማህበረሰብ መሆኑ የማያሻማ ሃቅ ነው ፤ ይህ ነገር በእኔም ህይወት ይንፀባረቃል ፤ ሆኖም የእኔ ለየት ይላል ብዬ አስባለሁ የእኔ ትዝታ ግን ጥልቅ ነው ለአፍታም አያባራም ሁሌም ትዝ ይለኛል ፡ የሽሮ ነገር ሆኖብኝ የተለያዩ ቦታዎች ተንቀሳቅሼ አይቻለሁ ብዙ ጣፋጭና መራራ ህይወትን መምራት ችያለሁ ብዙ የአኗኗር ዘይቤዎችን ተመልክቻለሁ ብዙ ደጋግ ማህበረሰቦች ጋር የመኖር ዕድሉ ገጥሞኛል ብዙ ወዳጅ ጓደኛም አፍርቻለሁ ፦ ጥር ሲደርስ ግን ሁሌም ትዝታዬ እጅግ ወደምናፍቃት የትውልድ አገሬ #ደልጊ ይወስደኛል፡ ( ስለደልጊ እና አካባቢዋ የምትገልፅ ትንሽ ፅሁፍ በቅርቡ እለጥለፋሁ)) ዛሬ ግን ለትዝታዬ ምክንያት ለፅሁፌ መነሻ ስለሆነው በወርሃ ጥር በ21ኛው ቀን ሰለሚከበረው #አስተርእዮ ማርያም ትንሽ ትዝታ እንጫወታለን ፥
መቼም የዛን ወቅት ክብረ በዓሉን ከመናፈቄ የተነሳ የቀኑና የሌሊቱ ርዝመት ፣ ከቤተሰብ የልብስ እና ጫማ ግዙልኝ ለቅሶ ( ደግሞ ለበርባሶ))፣ በስንት ትግል ሄደን ተለክተን ብር ተከፍሎ የልብስ ቤቱ ወረፋ ስንት ደጅ ጥናት ይጠይቃል( ቡቲክን ማን አውቆት ))፣ የሽመል ቆረጣው ዝግጅት ፣ ለበዓል መዋያ ሰሙኒ ሳንቲም ለመቀበል ስንት አልቅሰህና ስንት የቤተሰብ ግዳጅ ፈፅመህ መሰለህ? አቤት የተከፈለ መስዋእትነት ቤት ይቁጠረው...........
ከስንት ጉጉትና ናፍቆት በኋላ የበዓሉ ዋዜማ ይደርሳል ፡ ታድያ ያን ቀን ቤተከርስቲያን ይታደራል ፡ መቼም ማይረሳኝ ከማር የሚጣፍጠው የአባቶች ትምህርት፣ የሰንበት ተማሪዎች መንፈሳዊ መዝሙር፣ ድራማ ፣ የዲያቆናት ቅኔ ዘረፋና የምዕመናን እልልታ ዛሬም ድረስ በጀሮዬ ያቃጭልብኛል .............
በማግስቱ ረፋድ ላይ ታቦቱ ወደ ጥምቀተ ባህሩ ( ወደ ጣና ሐይቅ) መውረድ ይጀምራል፤ ይሄኔ ቄሱ በቅዳሴ ፣ ዲያቆናቱ በውረባ፣ ሰንበት ተማሪው በዝማሬ ፣ ኮበሌው በሆታ ፣ ሴቶች በእልልታና ህፃናት በጭፈራ ከፊት ሆነው፣ አባቶች በጭብጨባ ከኋላ እየተከተሉ ያጅቡታል ...የፀናፅሉ ድምፅ የዕጣኑና የከርቤው ሽታ ሌላ ነው ፨ #የሴቶቹ የበጥለት ያጌጠ ጥልፍ ቀሚስ ፣ የፀጉራቸው ጋሜናቁንጮ ፣ የእጃቸው አምባር ፣ በሎሚ ተረከዛቸው ያደረጉት አልቦ ፣ በአንገታቸው ያሰሩት ገማዴና ድሪ #የወንዶች የፀጉራቸው ታሬ ፣ ቁምጣና እጀጠባብ ልብሳቸው፣ ሽመል አያያዛቸውና ጭፈራቸውን አልረሳውም ።
የጆሊጁሱ ፣ የከረሜላው ፣
የሸንኮራው ፣ የማስቲካው ፣ የሎሚው እና ቀለም ቀቢው ነጋዴ ስፍር ቁጥር የለውም .. እኔም አንድ ጠርሙስ ጆሊጁሴን በአስር ሳንቲም ጨልጬ ሆዴ ተጎጥሮ ወደ ጭፈራው ስመለስ ከምኔው ታቦቱ ጣና ደርሷል ፡ ቅዳሴው ተጠናቆ ጠበልም ተረጭቶ መመለስ ሲጀምር ስከንፍ ቤት ሄጄ ምሳ ተጣድፌ በልቼ ወደ ጥምቀቱ ስመለስ ታቦቱ ወደ ቤተክርስቲያን ተጠግቶ አገኜዋለሁ ፡ አሁን ከመቸውም በላይ ጭፈራው ይደምቃል ፣ ታቦቱ እንዳይገባ ወጣቱ መንገድ ይዘጋል፣ አቧራ እንደጉድ ይነሳል፣ በየቦታው ከበሮ እየተመታ ሰው እስክስታውን ያስነካዋል፣ ጎረምሳው ኮረዳውን እንደጉድ ያሽኮረምማል ይጀነጅናል ፣ ኮበሌው ክብ ሰርቶ ሳይሳይ / ሽመል ምክቻ // እስኪበቃው ይጠላለዛል፣ ቡጢ ይገጥማል በለስ የቀናው አንስቶ ያፈርጣል የፈረደበት አፈር ልሶ ይነሳል ..........
እንዲህም እንዲያም እያለ ታቦቱ ወደ ቤተክርስቲያን ይገባል ስለት ያለበት ስለቱን አስገብቶ የሀይማኖት አባቶች መልዕክት አስተላልፈውና ፀሎት አድርሰው የበዓሉ ፍፃሜ ይሆናል ።
ታዲያ እንዴት አይናፍቀኝ ጓዶች ???
መልካም በዓል ውዶች!

© AlexoZDelgi

13/01/2019

የሠሚ ያለህ?
በድኩላርባ ከተማ የሚገኘው ፕሪፖራቶሪ ት/ቤት ውስጥ የሚገኘው ቤተ መፀሀፍት ከተዘጋ ሁለት ወር የሞላው መሆኑን ሠምተናል፡፡ጉዳዮ ለተማሪወች ከእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ ሁኗል ት/ቤቱ አዲስ እና መፀሀፍ ያልተደራጀ ከመሆኑ በላይ የወረዳው ሲቪል ሰርቢስ በዝርክርክ አሠራሩ ባለሙያ ባለመቅጠሩ ተማሪወች የመልቀቂያ ፈተና ለመውሰድ ለመዘጋጀት እንደቸገራቸው ገልፀውልናል፡፡
በሌላ በኩል ጉዳዮ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻው ሆኖ እያለ የወረዳው አመራሮች ዝምተን መርጠዋል፡፡የጽ/ቤቱ ኃላፊ ለማናገር ወደ እጅ ስልካቸው ብንሞክርም ሊያነሱ አልቻሉም፡፡ስለዚህ ትኩረት ተሠጥቶ ተገቢው እርምት ሊደረግ ይገባል መፀሀፍ ለማሠባሠብም እየተነጋገር መሆኑንም እንገልፃለን፡፡

26/09/2018

#ትዝታ ዘ ደልጊ!
#እንቆሮቆባሽ! ብያለሁ፡፡
#የመስቀል በዓል ሲመጣ ሁሌም ካለሁበት በሀሳብ ርቄ እሄዳለሁ፡፡ያሳለፍኳቸው የጨዋታ አይነት እና ጓደኞቸ ትዝ ሲሉኝ እስቃለሁ ወይ አይኖቸ ያጤዛሉ፡፡ እነ ይሁን ታፈረ፣አይችሉትም ቀሬ፣አበበ አጥናፍ፣አያሌው ቀሬ፣ይበልጣል ቀሬ፣ምስጋናው ሲኖር፣አዱኛ ሲኖር፣ዬናስ ሹመት፣ዬሴፍ ሹመት፣ርስቱ ዬሀንስ፣አደራጀዉ ብርሀኑ......በስም የረሳኋቸዉ ወዘተ
የመስቀል በዓል ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀደም ብሎ እስከ በዓሉ አጋማሽ በየቤቱ እየሄድን ......
መጣነ ባመቱ አረ እንደምን ሰነበቱ !
ሆያ ሆየ ፤ሆየ ፣መስቀል ሆየ
………….. አሲስቡየ አሲምቦ በሉ…….
ከድንጋይ ላይ ድንጋይ ተ😂ዘላለች ጦጣ....ሆናበባ ሆናበባ
ምንም አለቅሽም ነብሴ ብትወጣ....ሆናበባ ሆናበባ
ኧረ በቃ በቃ...ጉሮሮአችን ነቃ...ሆናበባ ሆናበባ
አበባ ማለቴ አወይ ልጅነቴ ሆናበባ ሆናበባ ........የሚሉ ማህበረ ሰቡ ያፈለቃቸው በእምነት እና ባህል የተላወሱ ሙዚቃወች አሁን ድረስ በጀሮየ ይሰሙኛል፡፡በዚህ ጊዜ እስከ ሁለት ቀን ቤት መሄድ አይታየንም ፈላጊም የለንም ፡፡የነፃነትታችን ቀን ነዉ፡፡ ከዚያው ከዉጭ ይበላል ይጠጣል፡፡ለዚህ ዝግጅት ባዶ ቤት ይፈለጋል፡፡ብዙጊዜ ባዶ ቤት በነፃ በመስጠት የሚያኮሩን #አባሲኖር ናቸው፡፡
በተለይ ለኛ መስቀልን ከሚያደምቁልን ነገሮች ምግብ መጠጡ ሳይሆን ሌሊት የሚደረገው ድብድብ ነው፡፡
የድብድቡ ህግ አንድ ደከም ያለሰው ወይም ለጨዋታ ብቁ ያልሆነ መብራት የሚያጠፋ አና የሚያበራ ይመደባል፡፡ ፎጣ ወይም አቦጀዲ ለላ ተደርጎ ተጠቅልሎ ሁሉም ለድብድብ ቦታ ቦታዉን ወይም ጥግ ጥግ ከያዘ በኋላ መብራት ይጠፋል፡፡ ሁሉም በዚህ ሰፊ ቤት በጨለማ ይደናበሳል፡፡....ይፈላለጋል፡፡ድምፅ ከተሰማ በድምፁ አቅጣጫ ጠላት ሊመጣ ስለሚችል ብትመታም የበለጠ ጥቃት እንዳይደርስብህ ሳቅህ ቢመጣም እንኳ በሆድህ በመዋጥ ፀጥ ማለት አለብህ ፡፡ በተለይ የአዱኛ ምት ጫፉላይ ድንጋይ የተቋጠረበት ነው የሚመስለዉ፡፡ ብዙ ጊዜ ይሁንና እኔ ተጠቃቅሰን አንድ ለይ መሆን እንወዳለን፡፡ ፡፡ችግሩ አንድ ላይ ስንሆን ተንኮል እናስባለን፡፡.....በተለይ ብዙ ጊዜም ተንኮል ሚያመነጨው እሱ ሲሆን ፈፃሚ እኔ ነኝ፡፡አንድ ቀን አይችሉትም ቀሬን በጋራ አቂመነው አጠር ያለ ሽመል አዘጋጅተን እሱን ለመምታት አስበን ስንሰነዝር በመጀመሪያው ሙከሩ ከጥግ የተገኘውን አበበ አጥናፍን ስናጭደው አበበ እውታውን ለቀቀው ፡፡"....ሽመል ገብቷል ....ሽመል መብራት መብራት "አለ፡፡ ይሁን እናኔ በድንጋጤ ሽመሉን ወረወርነው፡፡አበበ ግን ከጥጉ ያገኘው ሀ/ማርያምን ስለነበር በጥርጣሬ ታፋታፋውን ሞጨለፈው፡፡ አይችሉትምን በዘዋሪ ስላገኘነው ይሁን እናኔ የልባችን ደርሶ በሳቅ አነባን፡፡አይረሴ ድርጊት! አይረሴ ክዋኔ! አይረሴ ትዝታ! ....አይ ሆያ ሆየ.....አይልጅነት እንዲህ እየወደቅሁ እየተነሳሁ ያሳለፍኩት ጊዜ ከዚህ በኋላም በቀሪው ሕይወቴ ስወድቅ ስነሳ የምረሳው አይመስለኝም ፡፡

መልካም መስቀል !!!፡፡

01/09/2018

የደልጊ እና አካባቢ የተቸገሩ ተማሪወችን ለማገዝ ይቻል ዘንድ በአክሊሉ አድማሱ እና በፍሲል ቸኮል ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000256679039 የሆነ ተከፍቷል ስለዚህ ቃል የገባችሁ እንዲሁም ለማገዝ የምትፈልጉ ወገኖቻችን ይህንኑ መጠቀም ትችላላችሁ፡፡

▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸ለወገኖቻችን የእንድረስ ጥሪ!!!ወንድማችን @ፋሲል ቸኮል ታገለ የተቀደሰ አላማ ጀምሯል። @ጣቁሳ ወረዳ/ለተቸገሩ ደራሽ የሚል ፔጅ ፈጥሯል።እነ  ም በዚህ ዙሪያ እየተንቀሳቀሱ ...
31/08/2018

▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸ለወገኖቻችን የእንድረስ ጥሪ!!!

ወንድማችን @ፋሲል ቸኮል ታገለ የተቀደሰ አላማ ጀምሯል። @ጣቁሳ ወረዳ/ለተቸገሩ ደራሽ የሚል ፔጅ ፈጥሯል።
እነ ም በዚህ ዙሪያ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ሰምተናል።

✦እኛም ይህን በመደገፍ የሚከተለውን ብለናል።

★☆★
ለ፪፼፲፩ (2011) ዓ.ም የትምህርት ዘመን በደልጊና አካባቢው ለሚገኙ ት/ቤቶች: መማር እየፈለጉ ቤተሰቦቻቸው አቅም በማጣታቸው ምክንያት ሳይማሩ የሚቀሩ ወይም ተቸግረው የሚማሩ ብዙ ወንድም/እህቶቻችን አሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ ከዚህ ቅን ህዝብ የወጡ ወገናቸውን ማገዝ የሚፈልጉ ነገር ግን አጋጣሚውን ያላገኙ ብዙ ወገኖቻችን አሉ።

እኛም ይህን በማሰብ ለወገን ደራሽ ወገን ነውና ሁላችንም በምንችለው: ማለትም

ደብተር
ስክርቢቶ
እርሳስ
ዩኒፎርምና ሌሎች ቁሳቁሶችን

የሚችል በአካል ገዝቶ ለሚፈልገው እንዲሰጥ: ያልቻለ ደግሞ

1. Birhanu ስልክ 0965132363
2. @ፋሲል ቸኮል ታገለ ስልክ 0911683931

በማግኜት የተቻላችሁን እንድታግዙ ጥሪ እናቀርባለን።

ይህ ሀሳብ ለሁሉም እንዲደርስ Share ያድርጉ።

SHARE!
share!
Share!

ይህ ከስር የምትመለከቱት ካርታ በስኮትላንዳዊው ተጓዥና የጉዞ ጸሀፍት ጄምስ ብሩስ እ.አ.አ ከ1768 - 1773 የአባይን ምንጭ ለማጥናት በመጣበት ጊዜ ምንጩም ጣና ሀይቅ መሆኑን አረጋግጫለሁ...
27/07/2018

ይህ ከስር የምትመለከቱት ካርታ በስኮትላንዳዊው ተጓዥና የጉዞ ጸሀፍት ጄምስ ብሩስ እ.አ.አ ከ1768 - 1773 የአባይን ምንጭ ለማጥናት በመጣበት ጊዜ ምንጩም ጣና ሀይቅ መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሎ የሠራው ካርታ ነው።
ይህ 245 ዓመት በላይ ያስቆጠረው ካርታ የደልጊንና አካባቢዋን (ቸመራ፣ አሪኮ፣ወዘተ) ከያዙ ቀደምት ካርታዎች መካከል ይጠቀሳል። ካርታው ላይም ለማየት እንደሚቻለው በጊዜው የአቢሲኒያ/ኢትዮጵያ ዋና ከተማ ከነበረችው ጎንደር ከተማ ወደ ጎጃምና አገው ምድር ከሚወስዱት ሁለት መንገዶች መካከል በደልጊ በኩል የሚያልፈው ዋናው እንደነበረ ያሳያል።
ምንጭ: Travels to discover the source of blue nile , by games bruce, 1790 published book

Address

North Gondar
Delghi
DELGI

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Delghi School posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category