የቀድሞ ኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት እና ቤተሰብ ማህበር በኢትዮጵያ

የቀድሞ ኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት እና ቤተሰብ ማህበር በኢትዮጵያ

Share

የተለያዩ የበራ ስልጠና እና የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት

05/03/2026

48ኛው የካራማራ ድል በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ።

የካራማራ የድል በዓል ኢትዮጵያውያን በውስጥ ችግር ቢሆኑም እንኳን በሀገር ሉዓላዊነት ላይ የሚመጣን ማንኛውንም ዓይነት ጥቃት በጋራ እንደሚመክቱ ለዓለም ያስመሰከሩበት ታላቅ ታሪካዊ ድል መሆኑ ተገልጿል።

48ኛው የካራማራ የድል በዓል የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ከወዳጅ ሀገራት ጋር በመሆን የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ያስከበሩበት የ“ዳግማዊ አድዋ” ተምሳሌት መሆኑም ተገልጿል።

"በካራማራ ያገኘነው ድል በቀይ ባህር ይደገማል" በሚል መሪ ቃል በድል ሀውልት ስር በተከናወነው በዚህ በዓል ላይ የቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር ሌተናል ጀነራል አዲስ ተድላን ጨምሮ የቀድሞ ሰራዊት ጀነራል መኮንኖች፣ የኩባ አምባሳደር የሌሎች ሀገራት ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ሀይሎችና ፖሊስ ማህበራት ህብረት፣ የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ኮሚቴ እና የቀድሞ የህፃናት አምባ ልጆች በጋራ ባዘጋጁት በዚህ በዓል ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ሌተናል ጀነራል አዲስ ተድላ ይህ ድል ሶማሊያ ታላቋን ሶማሊያ ለመመስረት የያዘችውን ቀቢፀ-ተስፋ አክሽፎ የሀገራችንን አልደፈር ባይነት በደምና በአጥንታችሁ ያረጋገጥንበት ነው ብለዋል።

የካራማራ ድል ኢትዮጵያውያን በውስጥ ችግሮች ውስጥ ቢሆኑም እንኳ፣ በሀገር ላይ ለሚመጣ ማንኛውም ዓይነት ጥቃት በጋራ እንደሚመክቱ ለዓለም ያስመሰከሩበት መሆኑንም ገልጸዋል። የኩባ፣ የሶቪየት ህብረትና የየመን መንግስታት የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንዲከበርና አንድነቷ እንዲጠበቅ የከፈሉት ውድ የህይወት መስዋዕትነትም በታሪክ መዝገብ ለዘላለም ተፅፎ እንደሚኖር ተናግረዋል።

ዛሬ ለተከበረው በዓል የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ላደረገው ቀና ትብብር ምስጋና አቅርበው በቀጣይም ይህ በዓል በሀገር አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲከበር ጥሪ አቅርበዋል።

የአባቶቹ ልጅ የሆነው የአሁኑ ትውልድም በልማትና በሀገር ጥቅም ማስከበር ረገድ ዝግጁ በመሆኑ ኩራት እንደሚሰማቸውና ከጎኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በመቀጠልም ንግግር ያደረጉት የኩባ አምባሳደር ሚስ ቪልማ ቶማስ የካራማራ ድል በኢትዮጵያና በኩባ መካከል ያለውን የረጅም ዘመን ወዳጅነት ይበልጥ ያጠናከረ መሆኑን ገልጸዋል።

ሀገራቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ህፃናትን ወደ ኩባ በመውሰድ በሕክምና፣ በኢንጅነሪንግና በተለያዩ የሙያ መስኮች እንዲሰለጥኑ ማድረጋቸው የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገር ማድረጉን አስታውሰዋል።

የዚህ ታላቅ ዓላማ ጠንሳሽ የነበሩትን የፊደል ካስትሮን 100ኛ ዓመት ልደት እያከበርን ባለበት ወቅት የካራማራ ድል 48ኛ ዓመት መከበሩ ለበዓሉ ልዩ ትርጉም ይሰጠዋል ብለዋል። በበዓሉ ማጠቃለያ ላይ በድል ሀውልት ስር የአበባ ጉንጉን የማኖር ስነ-ስርዓት ተከናውኗል።

Photos from የቀድሞ ኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት እና ቤተሰብ ማህበር በኢትዮጵያ's post 03/03/2026

አላችሁ

03/03/2026
16/02/2022
16/01/2022
Want your school to be the top-listed School/college in Debre Zeyit?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


Debre Zeyit