20/06/2026
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት የምስጋና መልዕክት
********************************************
ቢሾፍቱ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2018(ኢመዩ)በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከሰኔ 4 እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ለቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የተሰጠው የመውጫ ፈተና በከፍተኛ ቅንጅት፣ በጠንካራ ዝግጅትና በሙሉ ኃላፊነት መጠናቀቁን በማስመልከት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ኘሬዝዳንት ተስፋዬ ቶሉ(ዶ/ር) የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዩኒቨርሲቲው ከመውጫ ፈተና ጋር በተያያዘ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን መቆዩቱን ያስታወሱት ዶ/ር ተስፋዬ ፣ በፈተናው ወቅትም አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍና ክትትል መደረጉን ገልፀዋል።
ለዚህ ሀገራዊ ኃላፊነት ስኬት የጎላ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የዩኒቨርሲቲው የመውጫ ፈተና ግብረ ኃይል፣ አካዳሚክና አስተዳደራዊ አመራሮች፣ መምህራን፣ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እና የትምህርት ሚኒስቴር የፈተና ማዕከል አስተባባሪዎች፣ የአይሲቲ ባለሙያዎች፣ የፌዴራል ፓሊስ ና የዩኒቨርሲቲው የፀጥታ አባላት፣ የጤና፣ ሎጂስቲክስና ድጋፍ ሰጪ ክፍሎች እንዲሁም በሂደቱ የተሳተፉ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በዩኒቨርሲቲው ስም አመስግነዋል።
የዘንድሮው የመውጫ ፈተና በሥነ-ሥርዓት፣ ግልፅ በሆነ መንገድ መከናወኑ፣ ዩኒቨርሲቲያችን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና ብቁ ወታደር ሙያተኞችን ለማፍራት ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠ እንደሆነ ምክትል ኘሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው አስረድተዋል።
ወደፊትም ዩኒቨርሲቲያችን ከትምህርት ሚኒስቴር ፣ ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት እና ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በተጠናከረ ትብብር በመስራት የትምህርት ጥራትን፣ የፈተና ታማኝነትንና የተቋሙን አካዳሚክ ልቀት ለማጠናከር ያለውን ጥረት በተከታታይ ያጠናክራል ።
በመጨረሻም ፈተናውን ለወሰዳችሁ ተማሪዎች ሁሉ ከልብ እንኳን ደስ አላችሁ፤ የለፋችሁበት ጥረት በተገቢው ውጤት እንዲከበር እመኛለሁ። በሙያችሁ የሀገራችንን ልማትና የመከላከያ ተቋማትን በብቃትና በታማኝነት እንደምታገለግሉ ሙሉ እምነት አለኝ።
ዶ/ር ተስፋዬ ቶሉ
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ
አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት
ለመከላከያ ሰራዊታችን ልህቀት እንተጋለን!
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ
telegram channel
👇👇👇👇
https://t.me/EthiopianDefenceUniversity
📌website 🌍
👇👇👇👇
http://www.etdu.edu.et
📌Facebook
👇👇👇👇
https://www.Facebook.com/ethdefuni
📌tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/
18/06/2026
📢 ማስታወቂያ
**********//**********
አርብ ሰኔ 12 ቀን 2018ዓ.ም በሶስቱም መርሃ ግብሮች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ዝርዝር መረጃዎችን በተመለከተ ከስር በተቀመጠው ሰንጠረዥ ላይ ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ለመከላከያ ሰራዊታችን ልህቀት እንተጋለን!
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ
telegram channel
👇👇👇👇
https://t.me/EthiopianDefenceUniversity
📌website 🌍
👇👇👇👇
http://www.etdu.edu.et
📌Facebook
👇👇👇👇
https://www.Facebook.com/ethdefuni
📌tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/
16/06/2026
አራተኛ ቀን የመውጫ ፈተና በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ
********************************************
ቢሾፍቱ፣ ሰኔ 09 ፣ 2018(ኢመዩ)ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና አራተኛ ቀን ፈተና በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባወጣው የፈተና መርሐ ግብር መሰረት በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል።
በጠዋቱ መርሃ ግብር የነርሲንግ የትምህርት መስክ ተማሪዎች እንዲሁም በረፋዱ የሁለተኛ ዙር ደግሞ በአግሪካልቸራል ኢኮኖሚክስ ተማሪዎች ተፈትነዋል። በሦስተኛ ዙር ከሰዓት በኋላ ፈተና የተፈጥሮ ሀብት እና የእፅዋት ሳይንስ የትምህርት መስክ ተፈታኞች ፈተናቸውን ወስደዋል።
ሰኔ 10/2018 ዓ.ም በሚሰጠው 5ተኛ ቀን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና የጋዜጠኝነት እና ኮምዩኒኬሽን(ወታደራዊ ጋዜጠኝነት) እንዲሁም የሜዲካል ዶክተሬት ድግሪ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያስፈትናቸው ይሆናል።
ለመከላከያ ሰራዊታችን ልህቀት እንተጋለን!
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ
telegram channel
👇👇👇👇
https://t.me/EthiopianDefenceUniversity
📌website 🌍
👇👇👇👇
http://www.etdu.edu.et
📌Facebook
👇👇👇👇
https://www.Facebook.com/ethdefuni
📌tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/
16/06/2026
ኮሌጁ በSTATA ሶፍትዌር ስልጠና ሰጠ
******************************************
ቢሾፍቱ ፣ ሰኔ 09 ፣ 2018(ኢመዩ) የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ማህበራዊ ጥናት ኮሌጅ ቢሾፍቱ ካምፓስ ለመምህራኑና ተመራማሪዎቹ በSTATA ሶፍትዌር አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናው ማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዋና ዳይሬክተር ኮ/ል መላኩ ደመላሽ እንደገለጹት፣ ስልጠናው ኮሌጁ በምርምር ዘርፍ ያሉበትን ተግዳሮቶች በመለየት እና በተለይም በአሃዛዊ ምርምር የመረጃ አሰባሰብ ፣ አያያዝና ትንተና ሂደቶች የሚታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ የተዘጋጀ የአቅም ግንባታ መርሃ ግብር መሆኑን ገልጸዋል።
ኮሌጁም በምርምር ልህቀት ላይ ያተኮረ ከባለሙያዎችና ከተመራማሪዎች ጋር የቅርብ ትብብር ባህልን እያጎለበተ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አክለዋል።
የስልጠናው ዋና ዓላማ የአካዳሚክ ማህበረሰቡን በቁጥራዊ የምርምር ዘዴዎች (Quantitative Research Methods)፣ በዳታ አያያዝ፣ በስታቲስቲካዊ ትንተና እና በምርምር ውጤቶች ትርጓሜ ዙሪያ ያላቸውን ብቃት ማጎልበት ያለመ መሆኑን ተመላክቷል።
ስልጠናውን የሰጡት ተመራማሪና የጥናት እና ምርምር አማካሪ ዶ/ር ሙሳ ሃሰን ሲሆኑ፣ በማጠቃለያ መድረኩ ላይ በዘመናዊ የምርምር ዓለም የቁጥራዊ ምርምርና የስታትስቲካዊ ትንተና አስፈላጊነት እየጨመረ መምጣቱን ገልጸው፣ ትክክለኛ የዳታ ትንተና በሳይንሳዊ ማስረጃ ላይ የተመሠረቱ ውሳኔዎችንና የልማት ፖሊሲዎችን ለመቅረጽ ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።
በስልጠናው ከተሳተፉት መካከል የኮሌጁ የጋዜጠኝነት እና ኮምዩኒኬሽን ትምህርት ክፍል ኃላፊ መምህር ሙአብ ዘካሪያስ እንደገለጹት፣ ስልጠናው የመምህራንና የተመራማሪዎችን በSTATA ሶፍትዌር በመጠቀም ትልልቅ የመረጃ ስብስቦችን በማደራጀት፣ በመተንተን እና የቁጥራዊ ምርምር ውጤቶችን በሳይንሳዊ መንገድ በመተርጎም ረገድ ያላቸውን አቅም በእጅጉ የሚያጠናከረ እንደሆነ ገልጸዋል።
ለመከላከያ ሰራዊታችን ልህቀት እንተጋለን!
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ
telegram channel
👇👇👇👇
https://t.me/EthiopianDefenceUniversity
📌website 🌍
👇👇👇👇
http://www.etdu.edu.et
📌Facebook
👇👇👇👇
https://www.Facebook.com/ethdefuni
📌tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/
16/06/2026
📢 ማስታወቂያ
===******===
ሰኔ 10 ቀን 2018ዓ.ም በመጀመሪያው ፣ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ዙር ( ,2 and 3) ላይ የመውጫ ፈተና ተፈታኞች፣ የመፈተኛ ቦታ እና ተያያዥ መረጃዎችን ከስር ከተቀመጠው ሰንጠረዥ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ተፈታኞች ለፈተና ስትመጡ የፋይዳ መታወቂያ ፣ የዩኒቨርሲቲ መታወቂያ እንዲሁም የፈተና መግቢያ ቲኬት ይዛችሁ መምጣታችሁን እርግጠኛ ሁኑ።
ዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ጊዜ የሚያስፈትናቸውን የጋዜጠኝነት እና ኮምዩኒኬሽን እንዲሁም የሜዲካል ዶክተሬት ድግሪ እና ሌሎች ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ መልካም እድል እንዲገጥማችሁ እንመኛለን።
መረጃውን ለተፈታኞች ማጋራታችሁን እርግጠኛ ሁኑ !
ለመከላከያ ሰራዊታችን ልህቀት እንተጋለን!
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ
telegram channel
👇👇👇👇
https://t.me/EthiopianDefenceUniversity
📌website 🌍
👇👇👇👇
http://www.etdu.edu.et
📌Facebook
👇👇👇👇
https://www.Facebook.com/ethdefuni
📌tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/
16/06/2026
🎓 PhD Dissertation Oral Defense Announcement
The Department of Aerospace Engineering, College of Engineering, Ethiopian Defence University, is pleased to announce the PhD Dissertation Oral Defense of Mr. Teshager Degefa Robi, a PhD Candidate in Aerospace Engineering.
Dissertation Title:
Nonlinear Dynamics and Control of Fractional Order Aeroelastic Airfoil Systems with Various Types of Plunge and Pitch Stiffness
📅 Date: 22 June 2026 (Monday)
🕘 Time: 9:00 AM
📍 Venue: Chemistry Hall, College of Engineering, Ethiopian Defence University
Faculty members, researchers, postgraduate students, and interested scholars are cordially invited to attend this important academic event and contribute to the scholarly discussion.
Ethiopian Defence University
College of Engineering
Ethiopian Defence University
WE STRIVE FOR EXCELLENCE OF NATIONAL DEFENCE FORCES
📌telegram channel
👇👇👇👇
https://t.me/EthiopianDefenceUniversity
📌website 🌍
👇👇👇👇
http://www.etdu.edu.et
📌Facebook
👇👇👇👇
https://www.Facebook.com/ethdefuni
📌tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/
16/06/2026
❝From Green Seedlings to National Strength; We Grow What We Defend.❞
Ethiopian Defence University
WE STRIVE FOR EXCELLENCE OF NATIONAL DEFENCE FORCES
📌telegram channel
👇👇👇👇
https://t.me/EthiopianDefenceUniversity
📌website 🌍
👇👇👇👇
http://www.etdu.edu.et
📌Facebook
👇👇👇👇
https://www.Facebook.com/ethdefuni
📌tiktok
👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/