Former Students of Tewodros II High School

Former Students of Tewodros II High School This page is open to former students of Tewodros II High School to share their idea on the issue o

24/03/2022
23/02/2022

የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ኾነ።

የካቲት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ተራዝሞ የቆየው የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ መኾኑን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዝናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ።

በመጀመሪያ ዙር የተሰጠው የ12ኛ ክፍል የሥነዜጋና ሥነምግባር ትምህርት የፈተና ውጤት መሰረዙንም ኤጀንሲው ገልጿል።

ተማሪዎችም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ጠቁሟል።

የፈተና እርማቱ ደኅንነታቸው አስተማማኝ በኾኑና ከንክኪ ነጻ በሆኑ የማረሚያ ማሽኖች አስፈላጊው የደኅንነት ጥበቃ በፌደራል ፖሊስና በደኅንነት ካሜራዎች ታግዞ በጥንቃቄ መከናወኑንም ነው የገለጸው።

ከዚህ በተጨማሪም የፈተናዎች ውጤት በትምህርት ዓይነት፣ በትምህርት ቤትና በተማሪ ደረጃ ሰፊ የውጤት ትንተና በማካሄድ የእያንዳንዱ የትምህርት ዓይነት ውጤት ተገምግሟል ብሏል ኤጀንሲው ባወጣው መግለጫ።

በዚሁ መሰረት በመጀመሪያው ዙር (ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02/2014 ዓ.ም) በተሰጠው የሥነዜጋና ሥነምግባር ፈተና በኹሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ስለታየበት የፈተና ውጤቱ ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ መወዳደሪያነት እንዳያገለግል መወሰኑንም ጠቅሷል።

በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የተገኘው የውጤት ትንተና ሲታይ ምንም ዓይነት ችግር እንደሌለበትም ተገልጿል።

ወደ ከፍተኛ ትምህርት ገብተው ለመማር ብቁ የሚኾኑ ተማሪዎች ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50በመቶ እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ይኾናሉ።

ለምሳሌ በሰባት የትምህርት ዓይነት ተፈትነው ከ600 ለሚያዝላቸው ተማሪዎች አማካይ ውጤት 300 እና በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ሲልም አስረድቷል ኤጀንሲው።

ይህ እንደተጠበቀ ኾኖ በመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት እንደሚገለጽ ጠቁሟል።

ስለኾነም ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።

1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et
2) በትምህርት ሚኒስቴር ድረገፅ፡- result.ethernet.edu.et
3) በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- - በዚህ ማስፈንጠሪያ በመግባትና Exam Result የሚለውን በመጫን በመልዕክት መጻፊያው ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት እና የ ምልክት በመጫን መላክና ውጤታቸው ማየት ይችላሉ።

4) በ9444 የ ኤስ ኤም ኤስ (9444 SMS) ፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

በውጤት ላይ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች result.neaea.gov.et በመግባት እና Compliant የሚለውን በመጫን ቅሬታቸውን በፎርሙ ላይ በመሙላት ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።

በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በኹለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል።

የመጀመሪያው ዙር ከጥቅምት 29 እስከ ኅዳር 02/2014 ዓ.ም ለወንድ 293 ሺህ 865 ሴት 250 ሺህ 703 ድምር 544 ሺህ 568 ተማሪዎች ተሰጥቷል።

ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በመጀመሪያው ዙር ሳይፈተኑ ለቀሩ ለወንድ 27 ሺህ 979 ሴት 26 ሺህ 456 ድምር 54 ሺህ 435 ተማሪዎች ደግሞ ከጥር 24-27/2014 ዓ.ም በኹለተኛው ዙር ፈተና እንዲወስዱ ተደርጓል።

በአጠቃላይ በኹለቱም ዙር ከተመዘገቡት 617 ሺህ 991 ተማሪዎች ውስጥ ወንድ 321 ሺህ 844 ሴት 277 ሺህ 159 ድምር 599 ሺህ 003 (96.9%) ተማሪዎች ፈተናውን መውሰድ ችለዋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

22/02/2022
07/01/2022

ስብሃት ነጋ፣ ጁሐር መሐመድና እስክንድር ነጋን ጨምሮ በርካታ እስረኞች በምህረት ከእሥር እንዲፈቱ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ስብሃት ነጋ፣ ጁሐር መሐመድና እስክንድር ነጋን ጨምሮ በርካታ እስረኞች በምህረት ከእሥር እንዲፈቱ ወስኗል፡፡

በዚህ መሰረትም ÷

1. አቶ ስብሐት ነጋ

2. ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ

3. አቶ ዓባይ ወልዱ

4. አቶ አባዲ ዘሙ

5. ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር

6. ወ/ሮ ኪሮስ ሐጎስ

7. አቶ ጁሐር መሐመድና በእርሱ መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ

8. አቶ እስክንድር ነጋና በእርሱ መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ ከእስር እንዲፈቱ ተወስኗል፡፡

የፅናት ተምሳሌቶቹ።
07/01/2022

የፅናት ተምሳሌቶቹ።

Address

Debre Tabor

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Former Students of Tewodros II High School posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category