ፍስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ

04/11/2022
ቀን:-18/02/2015 ዓ.ምየፍስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በዛሬው እለት የተለያዩ የልማት ስራዎች ሲያከናውን ውሏል :-1ኛ. የግቢ ውስጥ አረንጓዴ ልማት ስራ የዱራንታ ችግኝ የ...
29/10/2022

ቀን:-18/02/2015 ዓ.ም
የፍስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በዛሬው እለት የተለያዩ የልማት ስራዎች ሲያከናውን ውሏል :-
1ኛ. የግቢ ውስጥ አረንጓዴ ልማት ስራ የዱራንታ ችግኝ የማስተካከልና የማስዋብ ስራ
2ኛ. በክረምት ወቅት ከአንዳቤት ወረዳ ካሉ ጽ/ቤቶች ከተሰበሰቡ የተለያዩ አገልግሎት የማይሰጡ ለተግባር ማሰልጠኛ ማሳያ በሚል በስጦታ መልክ ከተበረከቱት ውስጥ የጥገና ስራ ሲሰራ ውሏል ከነዚህም 1.በዋጋ ደረጃ እስከ 80ሺ ብር የሚያወጣ ካማ ጀኔሬተር አገልግሎት መስጠት ችሏል
2. ሁለት የአምሀ ሞተር ሳይክል እስከ 400 ሺህ ብር ሊያወጣ የሚችል ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ችሏል ለዚህም ከሰራተኛው ተሳትፎ በተጨማሪ አንድ የውጭ ባለሙያ በ4500 ብር ክፍያ ሊሰራ ችሏል ይህ ስራ የሚያበረታታ ስለሆነ ሌሎች ተጨማሪ የጥገና ፕሮግራሞች ይቀጥላሉ። ሙሉጌታ ነኝ ከኮሌጅ

በፍስሀ ይሁን አንዳቤት  ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ "የሚመራበትን ፖሊሲና ስትራቴጅ አላማና ግብ የተገነዘበ አመራርና ባለሙያ እንፈጥራለን ውጤትም እናመጣለን " በሚል መሪቃል ከቀን 14/02/2015...
28/10/2022

በፍስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ "የሚመራበትን ፖሊሲና ስትራቴጅ አላማና ግብ የተገነዘበ አመራርና ባለሙያ እንፈጥራለን ውጤትም እናመጣለን " በሚል መሪቃል ከቀን 14/02/2015-17/02/2015 ዓ.ም ሲካሔድ የነበረው የንቅናቄ መድረክ :-
1. የተጠናከረ የቦርድ አመራር መፍጠረ
2. ጠንካራ የሆነ ማኔጅመንት ካውንስል መደራጀት
3. የለውጥ ተግባራትን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት
4. የመልካም አስተዳደር ችግር ሰለባ አለመሆ
5. የችግሮችን መንስኤ በመለየት ትኩረት ሰጥቶ መስራት
6. ሰብአዊ እና ቁሳዊ ግባት እንዲሟሉ ጥረት ማድረግ እና በአግባቡ መስራት
7.በህብረተሰቡ ዘንድ ታማኒ የሆነ ተቋም መገንባት
8. የአመራር ልምድ መውሰድና መመሪያዎችን ማንበብ እና መተግበር
9. የስልጠና ጥራትን ለማምጣት በመተጋገዝና በትብብር መስራት
10. አመራሩ የለውጥ ተግባርን በተግባር ማሳየት
11.የውስጥ ገቢን ማጠናከር
12.የምርት ማዕከላትን ወደ ተቋም ማምጣት
13. የስልጠና ጥራትና አግባብነትን ተግባራዊ ማድረግ
14. Green TVET ተባራዊ ማድረግ እና ማስቀጠል
15. ችግር ፈች የሆኑ ምርምሮችን መስራት
ለዚህ ውጤት መሳካት በውይይት በቸክሊስት በግብረ መልስ እና በሪፖርት መከታተል በሚሉ በአንዳቤት ስራና ስልጠና ኃላፊ አቶ ሀብቴ አታላይ በተሰጠ የወደፊት የትኩረት አቅጣጫ ተጠናቋል።
ሙሉጌታ ጌቴ ተወካይ ትምህርት ስልጠና ቡድን እና የአይሲቲ ትምህርት ክፍል ተጠሪ
ጥቅምት 18/2015 ዓ.ም

በቀን 15/02/2015 ዓ.ም የፈስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል የቡድን ውይይቶችና የተለያዩ ሰነዶች ቀርበዋል የቀረቡት ሰነዶች  ...
25/10/2022

በቀን 15/02/2015 ዓ.ም የፈስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ውሏል የቡድን ውይይቶችና የተለያዩ ሰነዶች ቀርበዋል የቀረቡት ሰነዶች DAC,IDP, Zoning and የፖሊሲ ምክረ ሀሳቦች ሲሆኑ አቅራቢዎችም የፍስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ተወካይ ትምህርት ስልጠና አቶ ሙሉጌታ ጌቴ እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ዲን አቶ ጌታቸው ወንዴ ናቸው። በውይይቱም በጣም ገንቢና ጥሩ ጥሩ ሀሳቦች ተነስተው በሀሳብ ዳብረው መግባባት ተደርሷል።
ቢሆንም ግን ከሰነድ ወጣ ያለ ቢሆንም አሰራር ላይ ክፍተት ይፈጥራል የተባለ የኮሌጅ አሰልጣኞች በስራ ላይ እያሉ እመርጀንሲ /ጉዳት ቢደርስ ዋስትና የላቸውም ፖሊሲው ይህንን እንዴት ይፈታዋል የሚል በእኛ ያልተመለሰ ጥያቄ ነው።

የፍስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ከሰአትም ቀጥሎ ውሏል። ከሰአት በሗላ በአንዳቤት ወረዳ ስራና ስልጠና ጽ/ት ምክትል ሐላፊ በሆኑት አቶ ሙሉአለም ካሳው የ...
25/10/2022

የፍስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ከሰአትም ቀጥሎ ውሏል። ከሰአት በሗላ በአንዳቤት ወረዳ ስራና ስልጠና ጽ/ት ምክትል ሐላፊ በሆኑት አቶ ሙሉአለም ካሳው የለውጥ አመራርና ምንነት ሰነድ እየተሰጠ ይገኛል። ከፕረዘንቴሽን በሗላ የቡድን ውይይቶች ይቀጥላሉ።

ፍስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የሚመራበትን ፖሊሲ:ሪፎርም አላማና ግብ የተገነዘበ አመራር እና ባለሙያ በመፍጠር የላቀ ውጤት እናስመዘግባለን። በሚ...
25/10/2022

ፍስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የሚመራበትን ፖሊሲ:ሪፎርም አላማና ግብ የተገነዘበ አመራር እና ባለሙያ በመፍጠር የላቀ ውጤት እናስመዘግባለን። በሚል መሪቃል ዛሬ ጥቅምት 14/2015 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ተጀምሯል።
በፕሮግራሙ የተሳተፉ
አመራር መገኘት የነበረበት ወ 8 ሴ- ድ 8
የተገኘ ወ 7 ሴ- ድ 7
አሰልጣኝ መገኘት ያለበት ወ 21 ሴ 5 ድ 26 የተገኘ ወ21 ሴ 5 ድ 26
ድጋፍ ሰጭ መገኘት ያለበት ወ 9 ሴ 8 ድ 17 የተገኘ ወ 9 ሴ 8 ድ17
ስራና ስልጠና ጽ/ት መገኘት ያለበት ወ 17 ሴ8 ድ 25 የተገኘ ወ 17 ሴ 8 ድ 25
ጠቅላላ ወ 54 ሴ 21 ድ 75
ተሳታፊዎች በተገኙበት የአንዳቤት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የቦርድ ሰብሳቢ በአቶ ክብሮም አለምነው የመክፈቻ ንግግርና የስልጠና አላማውን በማስገንዘብ ተጀምሯል። አሁን ፖሊሲና ስትራቴጅ የሚለው ሰነድ በፍስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክ/ሙያ ኮሌጅ ምክትል ዲን ጌታቸው ወንዴ እየተሰጠ ይገኛል።

የፍስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክኒክና ሙያ  ኮለጅ ቤተሰቦች  አመራሮችና ሰራተኞችእንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳቹህ !! በዓሉ በጠነከረ ህብረት ወደ ከፍታ የመንጓዝበት የመስቀል በዓል እ...
26/09/2022

የፍስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክኒክና ሙያ ኮለጅ ቤተሰቦች አመራሮችና ሰራተኞች
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳቹህ !! በዓሉ በጠነከረ ህብረት ወደ ከፍታ የመንጓዝበት የመስቀል በዓል እንዲሆንልን ምኞታችን ነው!! በአሉን ስናከብር በፍቅር በአንድነት በመተሳሰብ ደመራው ከአንድ ጀምሮ በህብረት እየተደመረ እንደሚደምቅ ሁሉ እኛም በህብረት በአንድነት ደምቀን የኢትዮጵያን ከፍታ የምናረጋግጥበት በዓል እንዲሆንልን እንመኛለን።መልካም በዓል!!
መስከረም 16/2015 ዓ.ም
አንዳቤት

14/01/2015 ዓ.ምየአማራ ክልል የስራና ስልጠና ቢሮ የ2014 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀም እና 2015 ዓ.ም የዕቅድ ኦርንቴሽን ከመስከረም 10-14/2015 ዓ.ም  በባህር ዳር ከተማ በአማራ...
24/09/2022

14/01/2015 ዓ.ም
የአማራ ክልል የስራና ስልጠና ቢሮ የ2014 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀም እና 2015 ዓ.ም የዕቅድ ኦርንቴሽን ከመስከረም 10-14/2015 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ በአማራ ሥራ አመራር ኢንስትቲዩሽን ለተተከታታይ 5 ቀን ሲካሄድ ቆይቶ መስከረም 14/2015 ዓ.ም የኢፊድሪ ስራና ክህሎት ሚኒስተር ሚነስተር ዴታ ክቡር አቶ ንጉሱ ጥላሁን በተገኙበት የእውቅናና የሽልማት ስነ ስርዓት በማካሄድ
በስኬት ተጠናቋል ::
የተሸለማችሁ በርቱ ፣ ያልተሽለማችሁ ድክመቴ ምን ነበር በማለት እራሳችሁን በማየት መዘጋጀት ይገባል።
የሚቀጥለው አመት ስኬት የሚጀምረው ዛሬ እጅ ነገ አይደለም ::
____
ክቡር ሚኒስተሩ ያስተላለፉት መልክት የሚከተለው ነበር >>>
__
"የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንደ ክልል፣ የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ እንዲሁም ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የታወጀባቸውን ጦርነት በመመከት የልማት ሥራ እየሠሩ ፈተናን መቋቋም እንደሚቻል አሳይተዋል::"
ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥራና ስልጠና ቢሮ የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ እና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ማስተዋወቂያ ውይይት አካሂዷል፡፡

በባህዳር ከተማ በተካሄደው ውይይት ላይ የተገኙት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን ላለፉት 5 ቀናት የተካሄደው ውይይት ሲጠናቀቅ እንደተናገሩት የክልሉ ሥራ እና ስልጠና ቢሮ ባለፈው ዓመት ሁለት ዓበይት ተግባራትን አከናውኗል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንደ ክልል፣ የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ እንዲሁም ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የታወጀባቸውን ጦርነት እና ውድመት በመመከት ክልሉም የወደሙ ኮሌጆችን ፣ ኢንተርፕራይዞችን እና የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን እያቋቋመ ፣ መልሶ እየገነባ እና ጀግኖችን እያበረታ በበጀት ዓመቱ ከ 900 ሺህ በላይ የሥራ ዕድል እንዲፈጠር ማመቻቸቱ ችግርና ፈተናን ተቋቁሞ ሥራን መሥራት እንደሚቻል ያሳየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተቋሙ ከማሰልጠን በላይ ታታሪነት ፣ ሥራ ፈጣሪነት ፣ ሀገር ወዳድነት ፣ ውጤታማነት እንዲሁም ብቃትን የተላበሰ ብቁ ዜጋ ማሰማራት ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ ከዳቦ መብላት ባሻገር የሀገር ውስጥ ምርትን በመጨመር ከውጭ የምናስገባቸውን ምርቶች መቀነስ እና የውጭ ገበያን ማሳደግ መሠረታዊ ፍላጎትን ከማሟላት በላይ ሀብት የሚፈጥሩ ዜጎችን በማፍራት የዋጋ ንረትን መቀነስ እንዲሁም የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነትን ሰላማዊ ማድረግ ማለትም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እና የሀገር ብልፅግና ዕውን እንዲሆን ትልቅ ኃላፊነት እንደተሰጠው ያስታወሱት ክቡር አቶ ንጉሡ በያዝነው ዓመትም ለ3.7 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል እንዲፈጠር የማመቻቸት ዕቅዱን ከክልሎች ጋር ተባብሮ ለማሳካት መግባባት ላይ መድረሱን ገልፀዋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥራና ሥልጠና ቢሮ ጦርነትን እየመከትን ፣ የወደሙ ኮሌጆችን ፣ ኢንተርፕራይዞችን እና የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን እያቋቋምን ለ1.2 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ለማመቻቸት ታቅዷል ብለዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ተቋሙን እያደራጀ የተሰጠውን ተልዕኮ በመወጣት ከባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር ትብብር በመፍጠር ስኬታማ ሥራ እንዳከናወነ በመግለፅ የተያዘው በጀት ዓመት ይበልጥ ተደጋግፈን አመርቂ ሥራ የምናከናውንበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የክልሉን ጫና በመገንዘብ በተለያየ መልኩ እንደሚደግፍ ቃል መግባቱንም አስታውቀዋል፡፡

የፍስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በ2015 ዓ.ም በተለያዩ ሙያዎች ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል የሚጠበቀው የሰልጣኞች መምጣት ብቻ ነው። ስለሆነም  ነባር መደበኛ የቀን ሰል...
14/09/2022

የፍስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በ2015 ዓ.ም በተለያዩ ሙያዎች ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል የሚጠበቀው የሰልጣኞች መምጣት ብቻ ነው። ስለሆነም ነባር መደበኛ የቀን ሰልጣኞች ከቀን 9/01/2015 እስከ 20/01/2015 ዓ.ም መጣችሁ እንድትመዘገቡ እና በ23/01/2015 ዓ.ም ስልጠና እንድትጀምሩ ተጠርታችኋል።

ቀን፡27/12/2014 ዓ.ም…….እናስተዋውቃችሁየፍስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅበአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር አንዳቤት ወረዳ ከደቡብ ጎንደር ዞን ዋና ከተማ ደብረታቦር 94 ኪ.ሜ ር...
02/09/2022

ቀን፡27/12/2014 ዓ.ም
…….እናስተዋውቃችሁ
የፍስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር አንዳቤት ወረዳ ከደቡብ ጎንደር ዞን ዋና ከተማ ደብረታቦር 94 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ አመሰራረቱን በተመለከተ እንደማንኛውም ኮሌጅ በክልልና በወረዳ መንግስት በጀት አደለም፡፡

ስለሆነም ይህንን ኮሌጅ ስናነሳ የማይረሱ አንድ ታላቅ ሰው አሉ ይህም ሲባል የአካባቢው ተወላጅ የሆኑ ሰው መኖሪያቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ሰው ለትምህርት መስፋፋት በተለይም ለሙያ ተቋማት ከነበራቸው ከፍተኛ ጉጉት የተነሳ በሀገራችን መዲና ( አዲስ አበባ) የነበራቸውን ቤት የቃል ኑዛዜ እኔ ከዚህ አለም በሞት ስለይ G+1 ፎቅ ቤቴን ሽጣችሁ ለአንዳቤት ወረዳ /ከተማ ህዝብ አገልግሎት የሚሆን አንድ የሙያ ት/ቤት በስሜ አሰሩልኝ ብለው በተናዘዙት መሰረት ቀኑ ደርሶ በሞት ሲለዩ ቤታቸው 7.5 ሚሊዮን ብር ተሸጦ ይህ ኮሌጅ በአቶ ዋሲሁን እስከዚያ አስተባባሪነት በወረዳው አመራርና ህብረተሰብ ጭምር የጉልበት ተሳትፎ 6 ወርክ ሾፕ፤ 1 መማሪያ ክላሶችን የያዘ፤አስተዳደር ቢሮና የቤተ-መጽሐፍ አገልግሎት የሚውል በድምሩ 9 ህንጻዎች ተገንብተዋል፡፡ እኒህ ታላቅ ሰው አቶ ፍስሀ ይሁን እስከዚያ ይባላሉ፡፡

ፍስሀ ይሁን አንዳቤት ቴ/ሙያ ኮሌጅ ግንባታው ሙሉ በሙሉ ባይጠናቀቅም በ2006 ዓ.ም ሠልጣኞችን ተቀብሎ ማሰልጠን የጀመረ ቢሆንም የአካባቢው ማህበረሰብ ለቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የነበረው አመለካከት ጥሩ ነው የሚባል ባለመሆኑ እና ሰልጣኞች ከቤተሰብ ርቆ የመማር ልምድ በመኖሩ የሰልጣኝ ቁጥሩ አነስተኛ ነበር።
ማህበረሰቡ ለቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ያለውን አረዳድና አመለካከት የተሻለ እንዲሆን ለማድረግ የተደረጉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በቂ በሚባል ደረጃ አለመኖራቸው ለዚህ ውጤት ቀላል የማይባል ሚና ተጫውተዋል፡፡

በሌላ በኩል ለኮሌጁ ግንባታ አሰራር ተገቢ ጥበቃና ቁጥጥር ባለመደረጉ ከተሰሩት ህንጻዎች ውስጥአራቱ መስኮታቸው መስታዎት ያልተገጠመላቸውና ሁሉም በሚባል ደረጃ የፍኒሽግ ስራ ያልተሰራላቸው በመሆናቸው ለስልጠናና ለማሽን ተከላ ስራ ችግር ፈጥሯል።ስለሆነም ይህ አንገብጋቢ ችግር መፍትሔ ያሻዋል እንላለን፡፡በነገራችን ላይ እስካሁን ከኮንትራክተሩ ጋር በክስ ላይ ያለ ተቋም መሆኑንም ማንሳት ወደድን……..

ይሁን እንጅ የተቋሙ ሰራተኞች በነበራቸው ቁርጠኝነትና ለስራ ተነሳሽነት ምክንያት፡-
ማሽን በመሸከም ከቦታቦታ በማንቀሳቀስ የተግባር ስልጠና መስጠት ተችሏል፡፡
በርና መስኮት ያልነበራቸውን መስራት ተችሏል፡፡
ግንባታዎችን በማስተካከል ለማሽኖች ደህንነትና ለስልጠና ጥራት ምቹ ማድረግ ተችሏል።
የግቢው ውበት ሳቢና ማራኪ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል።
በዚህም ጉድለት ወስጥ ሁኖ እስከ አሁን 8 ጊዜ ሰልጣኝ ማስመረቅ ችሏል፡፡

ከላይ የተገለፁት ጥቂቶቹ ስራዎች ቢሆኑም የአካባቢው ማህበረሰብም ሆነ አመራሩ እንዲሁም ልዩ ልዩ የህብረተሰባችን አካላት ወደ ኮሌጃችን እየመጣችሁ አብረን እንድንሰራ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።
በመጨረሻም እስካሁን ለተሰሩ ስራዎች የተቻላችሁን ሁሉ አስተዋፅኦ ላበረከታችሁ የኮሌጃችን ሰራተኞች ምስጋናችን ይድረሳችሁ እያልን ለቀሪ ስራዎች መጠናቀቅ የቦርድ አመራር፤ የኮሌጁ አመራሮች፤ማኔጅመንት፤ ትምህርት ክፍሎች፤የአካባቢው ማህበረሰብ ፤ የኮሌጁ ሰራተኞች እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት በሙሉ በሚቀርብላችሁ አሰራርና አመራር የሙያ፤የጉልበት፤የገንዘብ፤ የመልካም እሳቤ ስራዎች፤ ከመንግስትም ይሁን ከህብረተሰብ የሚጎድሉ ስራወችን ለማሟላት በመልካም ፈቃደኝነት እንድትተባበሩን እንላለን፡

Address

South Gondar
Debre Tabor
ANDABET

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ፍስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to ፍስሀ ይሁን አንዳቤት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ:

Shortcuts

Share

Category