02/04/2023
አዛውንቱ ከአንድ ወጣት ጋር ይገናኛሉ። ከዚያም ወጣቱ እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል
"አስታወሱኝ?"
"አላስታወስኩህም" አሉት አዛውንቱ ከዚያም ድሮ አስተምረውት እንደነበር ነገራቸው።
አዛውንቱም "እና አሁን ምን ላይ ደረስክ ምን እየሰራህ ነው?"
"አስተማሪ ሆኛለሁ"
"በጣም ደስ ይላል ልክ እንደኔ?"
"አዎ እንደርሶ አስተማሪ ሆንኩ በእርሶ አነሳሽነት"
አዛውንቱ በየትኛው አጋጣሚ አስተማሪ ሊሆን እንደወሰነ ጠየቁት። እሱም የሚከተለውን አጋጣሚ ነገራቸው።
"አንድ ጊዜ የእርሶ ተማሪ የነበረ አንድ ጓደኛዬ የሚያምር አዲስ የእጅ ሰዓት ይዞ መጣ እኔም ሠዓቱን ስለወደድኩት ከኪሱ አውጥቼ ሰረቅኩት...
ትንሽ ቆይቶ ጓደኛዬ ሠዓቱ እንደጠፋ ስለተረዳ ለአስተማሪው ተናገረ(ለእርሶ ማለት ነው) ...
እርሶም "የዚህ ተማሪ ሰዓት አሁን በምንማርበት ወቅት ጠፍቷል...ማንም ይሁን ማን ተሳስቶ የወሰደበት ካለ ይመልስልት!..." አሉ ነገር ግን ልመልስ ፈቃደኛ አልነበርኩም...
ከዛ የመማሪያ ክፍሉን ዘግተው ሁላችንም እንድንቆምና ክብ እንድንሰራ ካደረጉ በኋላ ሰዓቱ እስኪገኝ ድረስ የሁላችንም ኪሶች ፈተሹ...
በፍተሻው ወቅት ሁላችንንም አይናችንን እንድንጨፍን አዘውን ነበር ምክንያቱም ሰዓቷን በደንብ ለመፈለግ እንዲያመችዎ...
እየፈተሹ እየፈተሹ..እኔ ጋ ደርሰው የኔን ኪስ ፈተሹ... ሠዓቱንም አገኙት ነገር ግን እስከመጨረሻው ፍተሻዎትን ቀጠሉ....
ከዛም "አይናችሁን ክፈቱ ሠዓቱ ተገኝቷል" አሉ።
ነገር ግን ለማንም እኔ መሆኔንና ያገኙበትን አጋጣሚ አልተናገሩም በዚያም ዕለት የኔን ክብር ታደጉት ...ያ ቀን ለኔ በጣም አሳፋሪው ቀኔ ነበር...ነገር ግን ያ ቀን ሌባ (መጥፎ ሰው) እንዳልሆን የወሰንኩበት ሆኖ አለፈ...
ያ ሁሉ ሲሆን እርሶ አንድም ነገር አልተናገሩም ነበር... ብቻዬን ጠርተው ሊመክሩኝም አልሞከሩም።
መልእክትዎ ግልፅ ሆኖ ደረሰኝ
አመሠግናለሁ..አንድ እውነተኛ አስተማሪ ምን ማድረግ እንደሚገባው አስተማሩኝ...
"ይሄንን አጋጣሚ ያስታውሱት ይሆን ፕሮፌሰር?"
አዛውንቱም "አዎ አጋጣሚውንም ከተማሪዎቼ ኪስ ፈልጌ ያገኘሁትን የተሰረቀውን ሰዓትም አስታውሰዋለሁ ነገር ግን አንተን አላስታወስኩህም ምክንያቱም እኔም አይኔን ጨፍኜ ስለነበር...'ለሌሎች ክብር ሳይኖርህ ልታርማቸው ከሞከርክ..እንዴት ማስተማር እንዳለብህ አታውቅም ማለት ነው...ይሄ ነው የማስተማር ትርጉሙ።