East Gojjam Zone Education Department

East Gojjam Zone Education Department We like to communicate and discuss with Education Community.

East Gojjam Education Department is a non profit organization dedicated to coordinate the education process among 18 Woreda's of East Gojjam Administrative Zone.

በ2015 የትም/ዘመን በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሀገር አቀፍ የተፈታኞች ምዝገባን አስመልክቶ ከፈጻሚዎች ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ።የምክክር መድረኩን የከፈቱት የምስ/ጐ/ዞብ ትምህርት መምሪያ ...
01/04/2023

በ2015 የትም/ዘመን በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሀገር አቀፍ የተፈታኞች ምዝገባን አስመልክቶ ከፈጻሚዎች ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ።
የምክክር መድረኩን የከፈቱት የምስ/ጐ/ዞብ ትምህርት መምሪያ ም/ኃላፊ አቶ ደመላሽ ታደሰ እንደገለጹት በዘመኑ ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና የDRS ምዝገባን አስመልክቶ ከአስፈታኝ ት/ቤት ር/መምህራን፣ ከየት/ቤቱ ተመርጠው ለመጡ መዝጋቢዎች እና የወረዳ ፈተና ጉዳይ ባለሙያዎች እና ሌሎች ለሚመለከታቸው አካላት ምዝገባውን አስመልክቶ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ አጽንኦት በተሞላበት ሁኔታ ገልጸዋል።
ኃላፊው አያይዘውም ስራውን በትኩረት አለመፈጸምና ተገቢውን ጥንቃቄ አለማድረግ በተማሪዎች ህይወት ላይ የሚያስከትለውን ተጽእኖ አብራርተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በምክክር መድረኩ የተገኙ ር/መምህራን፣ ለተማሪዎች አስፈላጊውንና የሚቻለውን ድጋፍ ሁሉ እንዲደረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር (ከወላጆች፣ ከወረዳው አስተዳደርና ከት/ጽ/ቤቶች ጋር በመመካከር መርሀ ግብሮች ተዘጋጅተው ከባለፈው በተሻለ መልኩ ፈተናው እስከሚሰጥበት እለት ድረስ የቀረውን ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም ወደ ተግባር እንዲገባም አቶ ደመላሽ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ከዚህም በተጨማሪ የምስ/ጐ/ዞን ትምህርት መምሪያ የፈተና ጉዳዮች ባለሙያ የሆኑት አቶ ደሳለኝ አበበ በዚህ አመት ለሚሰጠው አገር አቀፍ ፈተና በምዝገባ ወቅት ባለፈው አመት የተአእተዋሉ ችግሮችን በማንሳትና ለተሳታፊዎች በማሳየት ችግሮቹ እንዳይደገሙ አሳስበዋል።

04/03/2023
12/02/2023

#ማስታወቂያ የዩኒቨርስቲ ምደባን በሚመለከት

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለመከታተል ላመለከታችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከየካቲት 05/2015 እኩለ ሌሊት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል።

ስለሆነም ተማሪዎች ከታች በተገለጹት አማራጮች የተመደባችሁበትን ተቋም ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ከየካቲት 15/2015 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትቆዩ እናሳስባለን፡፡

የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች

Website: https://result.ethernet.edu.et

SMS: 9444

Telegram bot:

ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችሁ ማንኛውም ጥያቄ

result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Complaint

የሚለውን በመጫን ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ምንም አይነት ጥያቄም ሆነ ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።

በዚሁ አጋጣሚ ተማሪዎች የትምህርት ጥራትን ለማረጋጋጥ የጀመርናቸውን የሪፎርም ሥራዎች እንዲሳኩ የበኩላችሁን እንድትወጡ እያልን በዩኒቨርስቲ ቆይታችሁ ህልማችሁ እንዲሳካና በቀጣይ ጠንካራ አገር ለመገንባት እንደ ህዝብ ለጀመርነው ተግባር ተገቢውን እውቀትና አስተውሎት የምትይዙበት ዘመን እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር

28/01/2023

1. የተማሪዎች አማካይ ውጤት በየትምህርት ዘርፉ፤

አጠቃላይ መረጃ፡- ፈተና የተፈተኑ ብዛት-----908,256 ናቸው፡፡
 አማራ………..30.37%
 ኦሮሚያ…..…27.96%
 ደቡብ………..28.17%
 ሀረሪ…………32.88%
 አዲስ አበባ----38.46%
 ደሬደዋ--------31.42%
 ሲዳማ---------28.34%

2. ከ50% እና በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ብዛት ከተፈተኑ መካከል
(እንደ ሀገር ያለፉ 29909 (3.3%) ናቸው
 አማራ………ከ246,675 መካከል 8,810 ((3.6%)
 ኦሮሚያ…..…327,737 መካከል 6,407 (2.0%)
 ደቡብ………..ከ127,345 መካል 2,533 (2.0%)
 ሀረሪ…………ከ1,849 መካከል 194 (10.5%)
 አዲስ አበባ----ከ47,980 መካከል 9,491 (19.8%)
 ደሬደዋ-------- ከ3,726 መካከል 250 (6.7%)
 ሲዳማ---------ከ53,478 መካከል 1247 (2.3%)

3. ተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 እና በላይ እንደ ሀገር 263 ተማሪዎች ያስመዘገቡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ
 አማራ………70 ተማሪዎች
 ኦሮሚያ…..…51 ተማሪዎች
 ደቡብ………..10 ተማሪዎች
 ሀረሪ…………1 ተማሪዎች
 አዲስ አበባ----117 ተማሪዎች
 ደሬደዋ-------- 2 ተማሪዎች
 ሲዳማ---------8 ተማሪዎች

4. ማህበራዊ ሳይንስ ከ500 እና በላይ እንደሀገር 10 ተማሪዎች ያስመዘገቡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ
 አማራ………1ተማሪ
 አዲስ አበባ----8 ተማሪዎች
 ደሬደዋ-------- 1 ተማሪ

5. ሁሉንም ተማሪዎች 100% ያሳለፉ ት/ቤቶች 7 ትምህርት ቤቶች ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ
 ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት
 ባሕር ዳር ስቲም ት/ቤት
 ጎንደር ኮሙኒቲ ስኩል
 ወላይታ ሶዶ ሊቃ ት/ ቤት
 አዳማ ኦዳ አዳሪ ት/ ቤት
ናቸው።

6. ከፍተኛ ውጤት (የዓመቱ ሰቃይ)
 ከአማራ ክልል ደሴ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ተማሪ ሚኪያስ አዳነ 666 አስመዝግቧል።

27/01/2023

የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ
በምስራቅ ጎጃም ዞን ትም/መምሪያ በ2015 የመጀመሪያዎቹ 6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ በአዋባል ወረዳ ተካሄዷል።
የዞኑ ትም/መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ የስራ ግምገማውን የመክፈቻ ንግግር በእንኳን ደህና መጣችሁ ያበሰሩ ሲሆን የግምገማውን አላማ አጠር አድርገው ገልፀዋል።
የወረዳ ት/ጽ/ቤት ኃላፊዎችን፣ የህዝብ ግንኙነት አስተባባሪዎችንና ሌሎች አጋር አካላትን ያካተተ ሲሆን የስራ ግምገማው ሞዳሊቲ የዞኑ ቡድን መሪዎች በስራቸው የተፈጸሙ ተግባራትን ያካተተ ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ ውይይት ተደርጎበታል።
በውይይቱ በርካታ ሀሳቦች የተነሱበትና የውድድር መንፈስ የተስተዋለበት ሲሆን በርካታ ተሞክሮ የሚቀመርባቸው ስራዎች የተንጸባረቁበትና ይህም በህዝብ ግንኙነት መታጀብ ቢችሉ ዞኑን ቀዳሚ እንደሚያደርገው ተገልጿል።
እያንዳንዱ ተግባር በህዝብ ግንኙነት ታጅቦ መረጃን ለህ/ሰቡ ማድረስ የቅድሚያ ስራችን መሆን አለበት በማለት አጽንኦት የሰጡት የመምሪያ ኃላፊው ፤ የየወረዳ ህዝብ ግንኙነት አስተባባሪዎች በዚህ የግምገማ ሂደት ማለፍ ለተቋማችን ትልቅ እድል እንደሆነ ገልጸዋል።
በመሆኑም የግምገማ ሀሣቡ የጋራ መግባባት ላይ የተደረሰበት ሲሆን የቀጣይ አቅጣጫዎች ተሰጥተው ውይይቱ ተፈጽሟል።

26/01/2023

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በዚህም ተፈታኞች ከዛሬ ሌሊቱ 5 ሰዓት ከ30 ጀምሮ በ በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/

በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም በቴሌግራም https://t.me/eaesbot ማየት የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ተፈታኞች ከተመሳሳይ እና የተዛባ መረጃ ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት እራሳቸውን እንዲጠብቁም አገልግሎቱ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

የትምህርት ስራዎች ግምገማ ተካሄደየምስ/ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ በደጀን ከተማ በትምህርት ስራዎች ላይ ግምገማ አካሄደ።የዞኑ ትምህርት ባለሙያዎችና አመራሮች በትምህርት ተቋማት ላይ የመማር...
06/12/2022

የትምህርት ስራዎች ግምገማ ተካሄደ
የምስ/ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ በደጀን ከተማ በትምህርት ስራዎች ላይ ግምገማ አካሄደ።
የዞኑ ትምህርት ባለሙያዎችና አመራሮች በትምህርት ተቋማት ላይ የመማር ማስተማሩን ስራ በመፈተሽ የተገኘውን የድጋፍ ውጤት ሪፖርት የዞንና ወረዳ ኮር አመራሮች፣ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት ተደርጓል።
በዞን ኮር አመራርና ትምህርት መምሪያ ኃላፊ የተመራው ይኧው መድረክ የቀረበውን የመስክ ድጋፍ ሪፖርት መሰረት በማድረግ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ግብዓት ማሟላት፣ የመማር ስራ፣ የተለያዩ አደረጃጀቶች ወደ ስራ አለመግባታቸውና ውጤታማ አለመሆናቸውን የሚፈትሽ የግምገማ ስርዓት ነበር።
በውይይቱ ዝቅተኛ አፈጻጸም ያላቸው ከፍተኛ አፈፃፀም ካላቸው የአሰራር ልምድ የቀሰሙበት፤ አንዱ ከሌላው ጥንካሬዎችንና እንከኖችን ያየበት ሲሆን የሚመሯቸውን ተቋማት ለመለወጥ የዞን ኮር አመራሩ አጽእኖት ሰጥቶ ያደማደመ ሲሆን ተወያዩ በቃልኪዳን የተሳሰሩበት እና ለራሳቸው ህሊና ቃል የገቡበት መድረክ ነበር።

የተፋጠነ የትምህርት ፕሮግራም ውይይት ተካሄደበምስ/ጎጃም ዞን የተፋጠነ የትምህርት ፕሮግራም (Speed School) በ10 ወረዳዎች 20 ት/ቤቶችን ያቀፈ የት/ጽቤት ኃላፊዎች፣ ቡድን መሪዎች፣...
28/11/2022

የተፋጠነ የትምህርት ፕሮግራም ውይይት ተካሄደ
በምስ/ጎጃም ዞን የተፋጠነ የትምህርት ፕሮግራም (Speed School) በ10 ወረዳዎች 20 ት/ቤቶችን ያቀፈ የት/ጽቤት ኃላፊዎች፣ ቡድን መሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ ር/መምህራንና መምህራን በተገኙበት ውይይት ተካሄደ።
የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ ውይይቱን የመሩ ሲሆን
1ኛ. የነበረውን የግንኙነት አግባብ የተፋጠነ ለማድረግ
2ኛ. በየተቋሙ ያለውን አፈፃፀም ተቀራራቢ ለማድረግ
3ኛ. መሰረታዊ የሆኑ እውቀቶችንና ክህሎቶችን ለመመጋገብ እንዲያስችል የተቃኘ አላማ ያለው የውይይት መንፈስ እንደሆነ አጽእኖት ሰጥተውበታል።
ፕሮግራሙ በመደበኛ የትምህርት ስርዓት የመማር እድል ያላገኙ እድሜያቸው ከ9-14 ዓመት የሆኑ ህፃናት የሚሳተፉበት ሲሆን ለ10 ወራት ተምረው የእድሜ እኩዮቻቸው የደረሱበት 4ኛ ክፍል ላይ እንዲሆኑ የተመቻቸ ፕሮግራም ነው። እጅግ የሚወደድ፣ አዋጭ እና በየደረጃው ያለው ባለድርሻ አካላትን ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ነው። በዞናችን 600 ተማሪዎች የሚከታተሉት መርሃግብር ሲሆን በየደረጃው ፈተና እየተዘጋጀ ብቃታቸው ተረጋግጦ ወደሚቀጥለው ክፍል የሚዛወሩበት እንደሆነም ተገልጿል።
ውይይቱ ትልቅ ተሞክሮ የቀረበበት አንዱ ከሌላው የተማረበትና ውጤታማ አሰራሮች የተንጸባረቁበት ነበር።

08/11/2022

Access Google Forms with a personal Google account or Google Workspace account (for business use).

28/10/2022

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውይይት ተካሄደ

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ፈተና አፈፃፀምና የ1ኛው ሩብ አመት ግምገማ ተካሄደ።

የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከምስራቅ ጎጃም ዞን ትም/መምሪያ ጋር በመተባበር ውይይቱ ጥቅምት 18/2015 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን የክልል፣ የዞን እና የወረዳ አመራሮች የትም/ባለሙያዎች፣ የ2ኛ ደረጃ አመራሮችና መምህራን የተሳተፉበት መድረክ ነበር።
መድረኩ ቁጭትን የፈጠረና ግንቦት ላይ ለሚሰጠው የ2015 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞችን በስነምግባር እና በፈተና ዝግጅት እንዲደረግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ አጽእኖት የተሰጠበት መድረክ ነበር።

Address

Debre Mark'os
20

Telephone

+251587712297

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when East Gojjam Zone Education Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to East Gojjam Zone Education Department:

Shortcuts

Share

Category