East Gojjam Zone Education Department/ምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Debre Mark'os
  • East Gojjam Zone Education Department/ምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ

East Gojjam Zone Education Department/ምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ East Gojjam zone education department
ICT Development work process

15/03/2026
15/03/2026

በአማራ ክልል 308 ደረጃቸውን የጠበቁ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሊገነቡ ነው።

ባሕር ዳር፡ የካቲት 26/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር 308 ደረጃቸውን የጠበቁ ቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶች እንደሚገነቡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ጥላሁን ወርቅነህ ተናግረዋል።

የትምህርት ጥራት ችግርን በዘላቂነት በመፍታትና ብቁ እና ተወዳዳሪ ዜጎች ለመፍጠር መንግሥት በወሰደው ቁርጠኛ አቋም ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ማስፋፋትና ማጠናከር ላይ በትኩረት እንደሚሠራ ቢሮ ኀላፊው አብራርተዋል።

"ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የትምህርት መሠረቶች ናቸው" ያሉት ኀላፊው ቀጣዩ ትውልድ የተሻለ ነገን እንዲያልም ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ላይ በትኩረት ይሠራል ብለዋል።

በክልሉ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለማስፋፋትና ራሳቸውን ለማስቻል ከሚደረገው ጥረት በተጨማሪ 154 ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በትምህርት ሚኒስቴር የጀት ድጋፍ ግንባታቸው ይካሄዳል። 154 ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ደግሞ በወረዳና በኅብረተሰብ ተሳትፎ ይገነባሉ ብለዋል።

በአጠቃላይ 308 ደረጃቸውን የጠበቁ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚገነቡ ይኾናል።

ለዚህም የተቋራጭ ልየታ ሥራ እየተካሄደ እንደሆነና በሚቀጥሉት 6 ወራት ሁሉም ተጠናቅቀው ለ2019 የትምህርት ዘመን መማር ማስተማር እንደሚጀምሩ አቶ ጥላሁን አስታውቀዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

04/03/2026

21.2K likes, 276 comments. “ #አድዋ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ”

01/03/2026

"የትምህርት ዘመኑን በውጤት ለማጠናቀቅ ሁሉም አካል ርብርብ ሊያደርግ ይገባል።"

አቶ ጥላሁን ወርቅነህ
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ

26/02/2026

የተማሪዎች ማጠናከሪያ ትምህርት መመሪያ

1. ዓላማ

የመማር ክፍተቶችን መለየትና መሙላት

የተማሪዎች ውጤት ማሻሻል

እርምጃ የሚወስዱ የመማር ስልቶችን ማስገባት

ተማሪወችን ከመደበኛው ክፍለ ጊዜ በተጨማሪ መደገፍና መርዳት ነው፡፡

2. የተማሪ መለያ መንገዶች

የቀድሞ ፈተና ውጤቶች

የመምህር ምልክቶች (Observation)

አጭር የመለኪያ ፈተና (Diagnostic Test)

የወላጅ እና የተማሪ ግብረመልስ

3. የትምህርት ዝግጅት

የትምህርት ዓላማ ግልፅ ማድረግ

የቀላል እና የተመራ እንቅስቃሴዎች

ተማሪ-ተማሪ ስራ (Peer learning)

አነስተኛ ቡድን ስራ

ተደጋጋሚ ልምምድ

4. የማስተማር ስልቶች

በቀላል ቃላት ማብራሪያ

ምሳሌ በመጠቀም ማብራሪያ

ጥያቄ-መልስ ዘዴ

ተግባራዊ ስራዎች

ተደጋጋሚ ግምገማ (Continuous assessment)

5. የጊዜ እቅድ

በሳምንት 2–3 ጊዜ ከመደበኛ ክፍል ጊዜ በኋላ

40–60 ደቂቃ ክፍለ ጊዜ

እቅድ ማቀድ (እንደ ችግር መጠን)

6. ግምገማ እና ክትትል

ቅድመ ፈተና (Pre-test)

መካከለኛ ግምገማ

የመጨረሻ ፈተና (Post-test)

የውጤት ማሻሻያ ሪፖርት

7. የወላጅ ተሳትፎ

የወላጅ ስብሰባና ውይይት

የቤት ስራ ክትትል

የልጅ ውሎና እድገት መረጃ መስጠት

8. አስፈላጊ ሰነዶች

የተማሪ መከታተያ ፎርም

የእቅድ ማቀናበሪያ ቅፅ

የግምገማ መዝገብ

24/02/2026
20/02/2026

አንተ ከሌለህ ሥራው ይቆማል? እንግዲያውስ ገና መሪ አልሆንክም!

ሰዎች መሪነትን የሚለኩት "ያለ እኔ ምንም አይሠራም" በሚል ጥገኝነት ነው፤ እውነተኛ መሪ ግን የሚለካው "እኔ በሌለሁበት ሥራው እንዴት ይሄዳል?" በሚለው ነው። ሰዎችን ማብቃት (Empowerment) ማለት ሥልጣንን አጥብቆ ከመያዝ ይልቅ፣ ሥልጣኑን ለሌሎች በማካፈል መሪው ራሱን "አላስፈላጊ" (Redundant) የሚያደርግበት የልዕልና ጥበብ ነው።
የዚህን ጥበብ ምሰሶዎች እንመልከት፦

የ"እኔነት" ፍርሃትን መስበር
ሰዎችን ማብቃት እንዳይቻል የሚያደርገው ትልቁ እንቅፋት "ተተኪዬ ከእኔ ቢበልጥስ?" የሚለው የውስጥ ስጋት ነው። ደካማ መሪዎች በዙሪያቸው "እሺ ባይ" ሰዎችን ይሰበስባሉ። ጠንካራ መሪ ግን ከእርሱ የሚበልጡና የሚሻሉ ሰዎችን ያበቅላል። ሥልጣንን ማጋራት ማለት ቦታህን ማጣት ሳይሆን፣ ተፅዕኖህን ማባዛት (Multiplying your Influence) ነው።

መሪነት ተከታዮችን ማፍራት ሳይሆን፣ መሪዎችን ማብቃት ነው።

ሥልጣንን የማጋራት ጥበብ (Delegation)

ማብቃት ማለት ሥራን ማዘዝ ብቻ ሳይሆን፣ ውሳኔ የመወሰን ኃይልን መስጠት ነው። ብዙ መሪዎች ሥራውን ይሰጡና ውሳኔውን ግን እጃቸው ላይ ያስቀራሉ። እውነተኛ ማብቃት ማለት ሠራተኛው ስህተት እንዲሠራና ከስህተቱ እንዲማር መፍቀድ፣ በራሱ እንዲወስን ድጋፍ መስጠት ነው።

ሠራተኞችህ ውሳኔ ለመወሰን አንተን ማማከር ግድ ይላቸዋል ወይስ በራዕዩ መመራት ይችላሉ?

የመውጫ ስልት፦ ተተኪ ማፍራት

ተተኪ ያላፈራ መሪ፣ ምንም ያህል ድንቅ ሥራ ቢሠራ፣ ሥራው ከእርሱ ጋር አብሮ ይሞታል። አንድ መሪ ለሥልጣኑ የሚሰጠው ትልቁ ክብር፣ ሥልጣኑን ለሚመጥነው ሰው በክብር ማስረከብ መቻሉ ነው። ማብቃት ማለት የአንተን ራዕይ የሚረከብና ካቆምክበት የሚቀጥል ትውልድ መፍጠር ነው።

ዛሬ እነዚህን ሦስት ነገሮች አከናውን፦

1. ኃላፊነትን ማስተላለፍ፦ ዛሬ ቢያንስ አንድ የምትወደውንና አንተ ብቻ የምትወስነውን ሥራ ለሌላ ሰው ሙሉ ኃላፊነት ሰጥተህ እንዲሠራው አድርግ። (በሂደቱ ጣልቃ አትግባ!)
2. አቅምን መለየት፦ በቡድንህ ውስጥ "ተተኪዬ ሊሆን ይችላል" የምትለውን አንድ ሰው ለይተህ ዛሬ ልዩ ምክር (Mentorship) ስጠው።
3. ራስን መገምገም፦ "ዛሬ እኔ ባልኖር ይህ ቡድን ለምን ያህል ጊዜ ሊቀጥል ይችላል?" ብለህ ራስህን ጠይቅ።

"እውነተኛ መሪ ስኬቱን የሚለካው ባፈራቸው መሪዎች ብዛት ነው።"

ሰዎችን በማብቃት ረገድ ያጋጠመህ ትልቁ ፈተና ምንድነው?
ተተኪ ማፍራት ለምን ይከብደናል?

ዛዲግ አብርሃ
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት

Address

Debre Markos Ethiopian
Debre Mark'os
20

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when East Gojjam Zone Education Department/ምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to East Gojjam Zone Education Department/ምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ:

Shortcuts

Share

Category