ወልደ_አብ

ወልደ_አብ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ወልደ_አብ, Education, adama, Debre Mark'os.

09/09/2022

ዜና ኦርቶዶክስ

ዲማና ደብረወርቅን አንድ ለማድረግ የተጠራ ሴራ ለበስ ጉባኤ ይበልጥ የሚያለያይ ሆኖ ተጠናቀቀ ።

ማህበረ ቅዱሳንና ዲማ ካህናት የመከፋፈል ሴራ ጠንስሰው ከመነሳታቸው በፊት የምስራቅ ጎጃም ኦርቶዶክሳውያን ካህናቱ ክህነት ከአንድ ጳጳስ ተሹመው፤ በአንድ ቤተ ክርስቲያን ቀድሰው፤ ሰው ሲሞትባቸው አብረው ፍትሐት ፈተው ፤ ሃይማኖታዊ በዓላትን አብረው አክብረው፤

ምእመናኑም በሃይማኖትም በሌላውም ማህበራዊ ኑሮ አብረው ኖረዋል ለነዚህ አባባሎች ትቂት ምስሌዎች እንጥቀስ

1ክህነት ከአንድ ጳጳስ መቀበል

አቡነ ዘካርያስ የምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነበሩጊዜ ህዳር 7 ቀን 1996 ዓ.ም በሞጣ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ዲቁና የሚሾሙ ወጣቶች ተሰባስበው ጳጳሱ ሹመቱን ሊሰጧቸው ሲሉ የተሰበሰቡትን ወጣቶች እስኪ ቅባት የሆናችሁ እጃችሁን አውጡ አሏቸው ወጣቶችም እጃቸውን ሲያወጡ ቅባት ነን ብለው እጃቸውን ያወጡት ካላወጡት በእጅጉ በለጡ ጳጳሱም ከዚህ በኋላ ምንም ተጨማሪ ቃል ሳይናገሩ ወጣቶችን ሾሟቸው።
አቡነ ዘካርያስ በኋላ ነው አቋማቸውን ቀይረው የከፋፋዩ ቡድን ፊት አውራሪ የሆኑ።
ወልደ አብ የተባለውን መጽሐፍ ራሳቸው ፈቅደው የገንዘብ ድጋፍ አድርገው ማሳተማቸው በተደጋጋሚ ተገልጿል መጽሐፉን ቀድመው ያወገዙም እርሳቸው ናቸው ።


2 በሀዘን እና በደስታ አንድ መሆን

የምስራቅ ጎዳም ኦርቶዶክሳውያን በሀዘን በደስታ አንተ ቅባት ነህ አንተ ካራ ነህ ተባብለው አይለያዩም በኀዘን በደስታ አብረው ይካፈላሉ። በዚህ ግንኙነታቸው ሊቃውንቱ በቅኔ እየተቀላለዱ የጥበብ ችሎታቸውን የሚያሳዩበት አጋጣሚም ብዙ ነው አንድ ምሳሌ እናንሳ
ቅባት ከሚባሉት ኦርቶዶክሳውያን የደብረ ወርቅ ሊቅ የተበሩ አለቃ ተሰማ የተባሉ ሊቅ ሞተው ካራ የሚባሉት የዲማ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንትም በፍትሐቱ ላይ ይገኛሉ በዚህን ጊዜ አንዱ የዲማ ሊቅ ቅኔ ሲቀኙ

እምልባ ኃዘነት ምድረ ደብረ ወርቅ ዘማ
አኮኑ ተሰብረ የቅቤ ቅሏ ተሰማ ።

አሉ የቅኔው ጥቅል ሀሳብ
"የቅቤ ቅሏ ተሰማ ስለተሰበረባት አመንዝራይቱ የደብረ ወርቅ ምድር ከልብ አዘነች" ማለት ነው።

የደብረ ወርቁ ሊቅ ሲመልሱ ደግሞ

ሐመደ እቶን ይመስል ገፀ ዘማዊት ዲማ፣
እስመ ኢረከበት ቅብዐ እምነ ባእል ተሰማ።

ብለው መለሱ ። የመልሱ ቅኔ ሀሳብ

"ከባለፀጋው ተሰማ ቅቤ ስላላገኘች ዘማዊት ዲማ ፊቷ አመድ ይመስላል" ማለት ነው።

በደስታም በሀዘንም አብሮነታቸውን የሚያሳይ አንድ ሌላ ምሳሌ እንጨምር በሞጣ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ ቦታ ሁለቱም ወገኖች ማለትም ቅባት ኦርቶዶክሶች እና ካራ ኦርቶዶክሶች

(ተዋህዶ ያላልናቸው ተዋህዶ የሚለው ጥንት ጸጋዎች የሚጠሩበት እንጅ የነርሱ ስም ስላልሆነ ነው)

አብረው የሚገለገሉበት አንድ ቤተክርስቲያን ነበር ከጊዜ በኋላ ግን የቅባት ተዋህዶ ወገኖች የብቻችን መስራት አለብን ብለው ሌላ ቤተ ክርስቲያን ይሰራሉ በኋላ የጥምቀት በዐል ሲያከብሩ ግን ሕዝቡ የመጀመሪያውን ቤተክርስቲያን ታቦት ተከትሎ ስለሄደ የአዲሱ ይቀዘቅዛል ይህ የሆነባቸው የአዲሱ ቤተክርስቲያን ሽማግሎች የመጀመሪያው ቤተክርስቲያን ታቦት እንደገባ ሕዝቡ ተመልሶ የአዲሱን ቤተክርስቲያን ታቦት እንዲያጅብ ሲለምኑት ሕዝቡ ተመልሶ አጅቦ አስገባው።

እነዚህን በመሰሉ እና ሌሎችም ጉዳዮች በአንዲት ቤተክርስቲያን ውስጥ አብሮ የሮረ ህዝብ ነው ሊቁ መላከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬም ሁለቱ ወገኖች እንደወንድማማች አብረው የሚኖሩ መሆናቸውን እንደሚከተለው ገልጸዋል ።


"ወንድማማቾች ከእናት ከአባታቸው ቤት ሲያድጉ ለጊዜው መምኑም በምኑም ቢጋጩ መልሰው ወንድሜ ወንድሜ ተባብለው እንደሚሳሳሙት …ያለ ነው እንጂ ከአያት ከቅድመ አያት የወረደ ጥንተ ባላጋራ ምክንያት አድርጎ ሊገባበትና ሊጠቀምበት የሚችል የበረታ ጠብ አይደለም የበረታ የሚያለያይ ጠብ ካለመሆኑም የተነሳ ሁሉም ወገኖች በእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ስር ይኖራሉ።

ሰው ሆይ(መድሎተ አሚን ) ገፅ 73-74

እንዲህ በክህነት ፣ በማህሌት በደስታ በሐዘን አብረው የኖሩ የምስራቅ ጎጃም ኦርቶዶክሳውያን ማህበረ ቅዱሳን እና የዲማ ካህናት ቅባቶች ከሆናችሁ ያላመናችሁ ስለሆናችሁ መጠመቅ አለባችሁ በማለት ይዘውት በተነሱ ከፋፋይ ተልኮ አንድ ሆነው የኖሩ ኦርቶዶክሳውያን ከሁለት እንደተከፈሉ ይታወሳል

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሲኖዶስ ደረጃ በተደጋጋሚ ተሞክሮ ያልተሳካውን የአንድነት ሙከራ አንድ እናደርጋለን የሚሉ ወገኖች አንድ እናደርጋለን በማለት አጋጣሚውን በመጠቀም የገንዘብ መዝረፊያ አድርገውታል።
ለዚህ ከተጠቀሙባቸው የተወሰኑትን እንጥቀስ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ አቡነ አብርሃም የደብረ ማርቆስ ከተማ ጳጳስ አቡነ ያሬድን ጋልበው ደብረወርቅ ከተማ መጥተው የደብረ ወርቅን ህዝብ ጥያቄ ለሲኖዶስ አቅርቤ ጥያቄው እንዲመለስ አድርጌ አንድነት እንዲፈጠር አደርጋለሁ ብለው ጥያቄዎችን የያዘውን ሰነድ ተረክበው ሄደው ራሳቸው እንዳይቀርብ አደረጉ ። በዚህም የደብረወርቅን ህዝብ አታለሉት ።

የደብረ ወርቅ ህዝብ ለሲኖዶስ ያቀረበውን ጥያቄ መረጃ ዘቤተክህነት በተሰኘው የዩቲብ ቻናላችን ያገኛሉ ።

ከዚያ በኋላ ደግሞ በማህበረ ቅዱሳን ቁጥጥር ስር ያለው የደብረ ማርቆስ ከተማ ሀገረ ስብከት ሰራተኞች ወደ መርጡለ ማርያም ሄደው የመርጡለ ማርያም ህዝብ በቆጋ አባቶች ላይ በጥላቻ እንዲነሳ ቅስቀሳ አድርገው አልሳካላቸው ሲል አንድ እንሁን በሚል ከመርጡለ ማርያም ከተማ ሽማግሌ መርጠው ወደ ጉንደወይን ህዝብ ላኩ የጉንደ ወይን ከተማ ህዝብና ካህናትም የሚመለከታቸውን ወገኖች ጠርተው ከተመካከሩ በኋላ የተላኩ ሽማግሎችን አክብረው ተቀብለው አንድነቱን አንጠላውም መጀመሪያም ተገፍተን ነው የተለየን አሁን ግን ጉዳዩ በሲኖዶስ ደረጃ የደረሶ እና ሲኖዶሱም ስላወገዘን ንግግረ ካስፈለገን በሲኖዶስ ደረጃ ነው መሆን ያለበት ብሎ መለሳቸው ።

አሁን ደግሞ የዲማና ደብረወርቅን ልዩነት እንፈታለን በሚል ስብሰባ ጠርተው ስብሰባው ይበልጥ በሚያለያይ ውሳኔ ተጠናቋል ።



ስብሰባው የተደረገው ፦ በ27/ 12 /2014

የስብሰባ ቦታ፦ ጠልማ ማርያም

ተሰብሳቢዎች፦

ከደብረቀርቅ

1, ደብረወርቅ ማርያም ገዳምን ወክለው የሔዱት የሰበካ ጉባኤ አባላት ፣ ካህናት ፣ ወጣቶችና የሀገር ሽማግሌዎች፣
2 የእናርጅ እናውጋ ወረዳ ቤተክህነት

ከዲማ

1, ዲማ ገዳም
ከቢቸና አጥቢያዎች የተውጣጡ ተወካዮች
2 እነማይ ወረዳ ቤተክህነት እና ስብሰባውን ያዘጋጀው ሀገረ ስብከቱ ናቸው

በዚህ ስብሰባ የተያዘው አጀንዳ
, የሁለቱ ገዳማትን ልዩነት መፍታት የሚል ሲሆን ልዩነቱን በማባባስ ተጠናቋል እንዲት ከተባለ ደግሞ

ከደብረ ወርቅ ተሰብሳቢዎች ዳግም ጥምቀት እያጠመቃችሁ ስለሆነ ይሔም በሲኖዶስ የተወገዘ ስለሆነ ይህ እንዲቆም ጠይቀዋል። ///////

ዲማዎች ነገሩን ሸፋፍነው ለማለፍ ሞክረዋል። " እኛ ከእስልምናና ከሌላ ሀይማኖት የመጣን አጥምቀናል እንጂ ሁለተኛ አላጠመቅንም" የሚል የማያዘልቅ መልስ ሰጡ የተሰጠው መልስ የመሸፋፈን መሆኑን የተረዱት ደብረ ወርቆች

ይሔንን ጉዳይ ግልጽ ሆኖ መነጋገር ስላስፈለገ እውነቱ መውጣት አለበት ከደብረወርቆች "አንገቱ ላይ ማተብ እያያችሁበት ያረገውን አየበጠሳችሁ ሌላ አላሰራችሁም ወይ? ለዚህ ራሳችን ምስክር ነንና አትክዱም" መካድ አትችሉም ብለው አፋጠዋቸዋል ። የዲማወችን ውሸት በማያፈናፍን ሁኔታ ያጋለጠባቸው እና ያልጠበቁት ሀፍረት ላይ የጣላቸው ደግሞ ራሳቸው ያሳተሙት መጽሐፍ ነበር መጽሐፉ ብርሃነ ሊቃውንት ዘዲማ የሚል ርእስ ያለው ሲሆን ሐምሌ 2014 ዐ . ም የታተመ ነው በዚህ መጽሐፍ ላይ የቅባት ትምህርት ተከታዮችን እና ደብረ ወርቅ ገዳምን የሚያክፋፉ እና ዲማዎች ቅባቶችን ማጥመቃቸውን የሚያረጋገጡ ጽሁፎች ይገኙበታል ከነዚህ ቃላት ።"በገጽ 25 ላይ የሚከተለው ሰፍሯል

" ብዙ የቅባትና ትቂት ደግሞ የእስልምና እምነት ተከታዮችን አስተምረው አጥምቀው መልሰዋል ካጠመቋቸው መካከል እግዚእኃረያ የተባለችው በዲማ ጊዮርጊስ ዘንድ ትታወቃለች "

እናም ዲማዎች ዳግም አላጠመቅንም ብለው ለማጭበርበር ሲሞክሩ ደብረ ወርቆች መጽሐፉን አውጥተው አንብበው አሳፍረዋቸዋል ።

ይህ መሸፋፈን የማያዋጣ መሆኑን የተረዱት የሚማው መምህር ግን

"ይሔንን ጥምቀት እኛ አልጀመርነውም ድሮ የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን ነው እየፈጸምን ያለነው ጥፋት ነው የሚለኝ ካለ ቀኖና እወስድበታለሁ ብለው ፍርጥ አድርገውታል ።

እኚሁ መምህር እማሳረጊያ ጸሎት ላይም ሲናገሩ " በቅብዐተ መንፈስ ቅዱስ ከበረ የሚለው ተወግዟል። የተወገዘ ደግሞ መጥፋት አለበት። ተዋህዶ ነን ካላችሁ አናጠምቃችሁም" በሚል ሀሳብ ደምድመውታል


የደብረ ወርቆች መልስ

ዳግም ጥምቀትን የማታቆሙ ከሆነ እኛም በገዳማችን ደብረ ወርቅ ህዝብ ፊት ቆመን ዲማ ሄዶ የቆረበ ፣ ክርስትና ያስነሳ ፣ የመነኮሰ ከቤተክርስቲያኗ ምንም አይነት መንፈሳዊ አገልግሎት እንደማያገኝና እንደምናወግዝ እወቁልን የሚል ሀሳብ ተናግረው ተለያይተዋል ። አንድ ለማድረግ የተጠራ ጉባኤ ይበልጥ በሚያለያይ ውሳኔ ተጠናቀቀ ። ማለት ይህ ነው ።

ይሄን ጉባኤ የተጠራ ዲማዎችም ደብረወርቆችም ፈልገውት አይደለም ማህበረ ቅዱሳን በተቆጣጠረው የደብረ ማርቆስ ከተማ ሀገረ ስብከት ስር አቡነ ያሬድ የሰላም ኮሚቴ ብለው በማህበረ ቅዱሳን አባላት ያቋቋሙት ቡድን የሚያደርገው የገንዘብ መዝረፊያ ስልት ነው ። ይህ ቡድን አንድ ለማድረግ ፣ ልዩነቶችን ለመፍታት እያለበየወረዳው እንደዚህ አይነት ስብሰባዎችን እየጠራ ገንዘብ ይዘርፋል ለዚህ ዘረፋው መሳሪያ ሆነው በወረዳዎች ለሚያስተባብሩለትም ገንዘብ ይከፍላል።

ለምሳሌ ደብረ ወርቅ ከተማ ውስጥ የዚህ ቡድን መሳሪያ ሆኖ የሚያገለግለው አለምነው አዘነ የተባለ ቄስ ነው ። ይህ የዘረፋ ስልት በሌሎች ወረዳዎችም እንደሚቀጥል ውስጥ አዋቲዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋ የደብረ ማርቆስ ካህናትና ህዝብ ይሄን ዘራፊ ቡድን በቃህ በማለት ዘረፋውን ሊያስቆም ይገባል ሰንሰለቱ ከወረዳ ቤተክህነት እስከ ጠቅላይ ቤተክህነት የተሳሰረ ነው።

በዩቲብ እንገኛለን መረጃ ዘቤተክህነት ብለው ይፈልጉን

24/01/2022

Yih new ewunetu

ከዲ/ን ትንሳኤ የfb ገጽ የተወሰደ ፤በድጋሚ ታነቡት ዘንድ ጋበዝኳችሁ ።የንታ ሄኖክ ለመሪጌታ ሐረገ ወይን አሻግሪ (ቄሰ ገበዝ - የቅኔ እና የሐዲስ መምሕር) ዘመርጡለ ማርያምከዛሬ 5 ዓመት...
02/08/2021

ከዲ/ን ትንሳኤ የfb ገጽ የተወሰደ ፤በድጋሚ ታነቡት ዘንድ ጋበዝኳችሁ ።
የንታ ሄኖክ ለመሪጌታ ሐረገ ወይን አሻግሪ (ቄሰ ገበዝ - የቅኔ እና የሐዲስ መምሕር) ዘመርጡለ ማርያም
ከዛሬ 5 ዓመት በፊት የላኩላቸው መልክት፤


ዛቲ ጦማረ መልእክቱ ለሄኖክ መሲሐዊ ወገዳማዊ ወመነኮሥ ቤተ ደናግል ዘእምስካበ ቅዱሳን ቆጋ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳም ኅበ መ/ታ ሐረገ ወይን አሻግሬ ዘዮም መርጡለ ማርያም [ቄሰ ገበዝ]
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ ብሎ መጽሐፍ እንዲጀምር አካላዊ አብን ወላዲ ወአስራጺ፣ለባዊ ወአለባዊ፥ አካላዊ ቃልን ተወላዲ፥ነባቢ ወአንባቢ፤ አካላዊ መንፈስ ቅዱስን ሰራጺ፣ ህያው ወማህየዊ ብዬ አካላትን ሦስት ብል በባህርይ፣በህላዌ በመለኮት አንድ አምላክ ብዬ በማመን ነዋ እፅህፍ ጦማረ መልእክት ዘኦርቶዶክሳዊት ለፍቁር እሁየ ቄሰ ገበዝ መ/ታ ሐረገ ወይን አሻግሬ ከመ እኩን ሰማእተ በእንተ ርእትእት ሃይማኖት ዘተሀንጸት ዲበ ኮኵኅ ቅዱስ ዘይቤ “አንተ ውእቱ መሲሁ” ለእግዚአብሔር ፡(ሉቃ.9፣20)፡፡ ቃል ወልድ እኁየ ናሁ ውእቱ መጽአ፤ እንዘ ይቀንጽ ማእከለ አድባር(መኃ.2፣8) እንዲል ጥበበኛው፡፡
“ ቃለ-ወልድ እሁየ ናሁ ውእቱ መጽአ”፤ ስል ቅዱሳን የሆኑ የሃይማኖት አባቶቼን አንደበትና እምነት እንዲሁም ስለጻፉልኝ ኃይለ ቃል እኔም እንዲሁ እጽፍለዎታለሁ፡፡ነቢዩ ይህን ተናገረ፤እስመ ፈላሲ አነ ውስተ ምድር፤ ወነግድ ከመ ኩሉ አበውየ ፡፡ባይታወር ምንደኛ በምድር ሁሉ ስደተኛ እንደሆንኩ ማን አስተዋለኝ፡፡ ዓለምስ ማእበል እንደሚያማታው ግንድ እነደዚያ ለምን ታደርግብኛለች? ጸንኡ ጸርየ እለ ይረውዱኒ በአመፃ፤መዝ.68፡፡ አንድም በዝኁ እምስእርተ ርእስየ እለ ይጸልዑኒ በከንቱ እንዲል፡፡ አዎ በዩኒቨርሲቲዎቻቸው፣በጉባኤዎቸውና በአደባባዮቻቸው ሁሉ የስርዓታቸው አስጀማሪ እኔ ሁኛለሁ፡፡ወከደነኒ ኃፍረት ገጽየ፤ከመ ነኪር ኮንክዎሙ ለአኃውየ፤ወነግድ ለደቂቀ አቡየ ወእምየ ብሎ ዳዊት ራሱን እንደገለጸ፡፡ ይሁን እንጂ አንሰ ኢያረምም በእንተ ጽዮን ስለጽዮነ ዝም አልልም፤ ስለኢየሩሳሌምም ዝም አልልም፡፡(ኢሳ. 62፣1) ብሎ ኢሳይያስ እንደተናገረ አንደበቴ እስከተዘጋችበት፣ ምላሴ እስከአጠረችበት፣እጄ እስከታሰረችበት ወልድ ዋህድ ፈጣሪዬን ክርስቶስን “በመለኮቱ በተዋህዶ ክቡር፣ በሰውነቱ በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ኀየሰ፤ ወረሰ ፤ነግሰ፤ ኮነ እግዚአ፤ ኮነ ፈጣሬ መላእክት፤ ኮነ ወልደ ዘባሕርይ፡፡” ብዬ ምስክርነቴን አጮኻለሁ፡፡ተሠርዐ ወልደ እግዚአብሔር በኃይል ዝውእቱ ቅብዓ መንፈስ ቅዱስ፡፡ እነዳለ ተረፈ ቄርሎስ( ምቋም 😎 ጆሮ ያለው ይስማ፤ አእምሮ ያለውም ያስተውል፡፡ ይኸንም ምሥጢረ ሥላሴን በማስቀደም አንድነቱን ሦስትነቱን በመተንተን ሥጋዌውን በማስከተል “አማኑኤል”ና “ክርስቶስ” የተባለበትን መለኮታዊት ምሥጢር ለሆነች ሥርዓተ ተዋህዶ እንዲሁም መሥጢረ ቅብዓትን እንዲህ እናገራለሁ፡፡
ም ሥ ጢ ረ-ሥ ላሴ
የሥ ላሴ መ ዠ መ ሪያው አካል በህላዌ ው ህሊና ይባላል፤
ሁ ለተኛው አካል በህላዌ ው አእምሮ ይባላል፤
ሦ ስተኛው አካል በህላዌ ው ፈቃድ ይባላል፡፡
የሥ ላሴ መዠመሪያው አካል በባህርዩ ለባዊ ወአለባዊ ይባላል፤
ሁለተኛው አካል በባህርዩ ነባቢ ወአንባቢ ይባላል፤
ሦስተኛው አካል በባህርዩ ህያው ወ ማ ህያዊ ይባላል፡፡
የሥ ላሴ መ ዠ መ ሪያው አካል በመ ለኮቱ ጠ ባይእ ይባላል፤
ሁለተኛው አካል በመ ለኮቱ ጥ በብ ይባላል
ሦስተኛው አካል በመለኮቱ ኃይል ይባላል፡፡
ይኸውም አንድ እግዚአብሔር የሚባሉበት የይትዋሀዱ ርስት ነው፡፡ ሥላሴ በባሕርይ፣በህላዌ፣ በመለኮት አንድ ናቸው፡፡
ህላዌ ማ ለት አኗኗር፣ ባሕርይ ማ ለት መ ሥ ሪያ፣መ ንግስት ክብ ር፣ መ ለኮት ማ ለት መ ዋሀጃ፣ መ ንግስት፥ መ ሥ ሪያ፣ ክብር ነው፡፡
የአብ ም ባሕ ርይነት አካል ይባላል፡፡አካልም መ ለኮት ይባላል፡፡አካልም ማ ለት ሠ ሪ ማለት ነው ፡፡መ ለኮትም ማለት መ ሥ ሪያ፣መ ሥ ሪያም፣መ ንግሥ ትም፣ ክብ ርም ማለት ነው ፡፡አብም በራ ሡ ህልው ና ባሕ ርይ ይባላል፡፡ለወልድና ለመ ንፈስ ቅዱ ስ ሌ ላ ባሕ ርይ የላቸው ምና፡፡ ለባው ያንም መ ባላቸው በአብ ህላዌ ነው፡፡
የወልድም ቃልነት አካል ይባላል፡፡አካልም መለኮት ይባላል፡፡አካልም ማለት ሠሪ ማለት ነው ፡፡መለኮት ማለትም መሥሪያም ፣ መንግሥትም ፣ ክብርም ማለት ነው ፡፡ ወልድም በራሡ ህልውና ቃል ይባላል፡፡አብና መ ንፈስ ቅዱስም ነባብያን መባላቸው በወልድ ህላዌ ነው፡፡
የመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት አካል ይባላል፡፡አካልም መለኮት ይባላል፡፡አካልም ማለት ሠሪ ማለት ነው፡፡መለኮት ማለትም መሥሪያ ፣መንግሥትም ፣ክብርም ማለት ነው ፡፡ መንፈስ ቅዱስም በራሡ ህልውና ህይወት ይባላል፡፡አብና ወልድም ሕያዋን መባላቸው በመንፈስ ቅዱስ ሕላዌ ነው፡፡ወበከመ ነፍስከ ለሥጋከ ሕይወት ከማሁ ለአብ ወወልድ ህይወቶ ሙ መ ንፈስ ቅዱስ፡፡ ለስጋህ ነፍስህ ሕይወት እንድሆነች ሁሉ መንፈስ ቅዱስም ለአብና ለወልድ ሕይወታቸው ነው
የመለኮትንና የባሕርይን አንድነት ለማስረዳት አብን በመለኮቱ ጠባይእ ካልን አብ በወላዲነቱ በአስራጺነቱ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ አስገኛቸው ነውና ባነዲት ባህርይ አካል ሳይከፈል ፣አንደኛው ከሁለተኛው፣ ሁለተኛው ከሦስተኛው ሳይቀድም፤ ሁለተኛው ከአንደኛው፣ ሦስተኛው ከሁለተኛው ሳይከተል፤ ወልድን ወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን አሰረጸ፡፡ይህንም አንድነት ሊቁ አባት ቅዱስ ባስልዮስ ሲያስረዳ
“ነአምን በሃይማኖት ከመ ይትዋሀድ መለኮት በአብ እስመ እምአብ ተወልደ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስሂ ወጽአ እምኔሁ እንዘ ኢይቀድም ፩ዱ እምካልኡ ወካልኡ እምሳልሱ፡፡በአብ ወላዲነት አስራጺነት መለኮት አንድ እንዲሆን ሃይማኖትን እንመን፤ አብ ከወልድ ሳይቀድም ወልድም ከመንፈስ ቅዱስ ሳይቀድም ወልድ ከአብ ተወልዷልና መንፈስ ቅዱስም ከአብ ተገኝቷልና፡፡ ወበልደተ ወልድ ወበጸአተ መንፈስ ቅዱስ እምአብ ይትዋሀድ መለኮተ ሥላሴሁ ለአምላክነ፡፡ ወልድ ከአብ በመወለዱ መንፈስ ቅዱስም ከአብ በመስረጹ የፈጣሪያችን የሦስትነቱ መለኮት አንድ ይሆናል፡፡(ሃ.አ. ም.32፣ቁ. 6)” ብሏል፡፡
የፈጣሪዬን የሦስትነቱን ነገር እንዲህ እናገራለሁ፡፡ይህ አንድ አምላክ በስም በግብር በአካል ሦስትነት አለው ፡፡ለዚህም ምስክሬ ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት ይሁንብኝ፡፡ወአቃኒመ እግዚአብሔርሰ እሙንቱ አስማ ት፤ የእግዚአብሔር አቃኒም ስሞች ናቸው ፡፡ወአስማትኒ እሙንቱ አቃኒም ፤ ስሞችም አቃኒም ናቸው፡፡እስመ ትርጓሜሁ ለአቃኒም አካላት፣ ጽኑአን፣ ወቀዋምያን፣ ፍጹማነ ገጽ ወመልክእ፡፡ የአቃኒም ትርጓሜው በገጽ በመልክ ፍጹማን የሚሆኑ ባለመለወጥ ጸንተው የሚኖሩ አካላት ማለት ነው፡፡
የአካል ሦ ስትነት
አብ በተለየ አካሉ ወልድን ቢወልድ መንፈስ ቅዱስን ቢያሰርጽ አካል አካልን ወለደ አካልን አሰረጸ ማለት ነው፡፡ ወልድም በተለየ አካሉ ከአብ ቢወለድ አካል ከአካል ተወለደ ማለት ነው፡፡መንፈስ ቅዱስም በተለየ አካሉ ከአብ ቢሰርጽ አካል ከአካል ሰረጸ ማለት ነው፡፡
አብ በተለየ አካሉ ባህርየ ወልድ ወመንፈስቅዱስ ቢባልም በሀላዌ መለኮቱ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ ማሰብ (ህሊና) ማለት ነው፡፡ማሰብም መንግስትም ፣ክብርም ማለት ነው፡፡ ወልድ በተለየ አካሉ ቃለ አብ ወመንፈስ ቅዱስ ቢባል በህላዌ መለኮቱ የአብና የመንፈስ ቅዱስ አእምሮ ማለት ነው፡፡ እውቀትም መንግስትም ክብርም ማለት ነው፡፡መንፈስ ቅዱስም በተለየ አካሉ ሕይወተ አብ ወወልድ ቢባል በህላዌ መለኮቱ የአብና የወልድ ፈቃድ ማለት ነው፡፡ፈቃድም መንግስትም ክብርም ማለት ነው፡፡ፀአተ መንፈስ ቅዱስና ልደተ ወልድ ከአብ አካላቸው ከአብ አካል ሳይከፈል በብቻ አካላቸው መንፈስ ቅዱስ ሰረጸ፤ ወልድም ተወለደ ብለን እንመን፡፡ ፀአተ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እምአብ ተከፍሎተ አካል የለበትምና፡፡
የግብ ር ሦ ስትነት
አብ እምቅድመ አለም ወልድን ቢወልድ መንፈስ ቅዱስን ቢያሰርጽ ወላዲ ወአስራጺ መባልን ያንድነቱን ሦስትነት የሦስትነቱን አንድነት አልከለከሉትም፡፡እነዲሁ በደኃሪ ዘመንም ወልድን በሰውነቱ ግብር ቢቀባው ቀባዒ መባልን፤ በሰውነቱም ስልጣን ወልድን በድንግል ማህጸን ቢወልድ ወላዲ አብ መባልን ያንድነቱን ሦስትነት የሦስትነቱን አንድነት አልከለከሉትም፡፡
ወልድም ቅድመ አለም በመለኮቱ ከአብ ቢወለድ ወልድ ተወላዲ መባል ያንድነቱን ሦስትነት የሦስትነቱን አንድነት አልከለከሉትም፡፡እንዲሁ በደኃሪ ዘመንም ስለሥጋ እንግድነት (በሰውነቱ ሥልጣን) ከባህርይ አባቱ አካል ዘእምአካል፣ ባህርይ ዘእምባህርይ በድንግል ማህጸን ቢወለድ ተወላዲ ወልድ መባሉን፤ በሰውነቱም ሥልጣን ከአብ ዘንድ ቢቀባ፤ በሰውነቱም ግብር ተቀባኢ ነሣኢ፣ ተወካፊ መባልን፣ ያንድነቱን ሦስትነት የሦስትነቱን አንድነት አልከለከሉትም፡፡
መንፈስ ቅዱስም ቅድመ ዓለም በመለኮቱ ከአብ ቢሰርጽ ሰራጺ መንፈስ ቅዱስ መባሉን ያንድነቱን ሦስትነት የሦስትነቱን አንድነት አልከለከሉትም፡፡እንዲሁ በደኃሪ ዘመንም መንፈስ ቅዱስ ለወልድ በሰውነቱ ሥልጣን ህይወት መባሉን በሰውነቱም ግብር ቅብእ ተሰጪ ኃዳሪ መሆኑን ያንድነቱን ሦስትነት የሦስትነቱን አንድነት አልከለከሉትም፡፡
ባህርይም በራሡ ህልውና ለባዊ ወአለባዊ ሲሆን በቃልም ህልውና ነባቢ ሲሆን በህይወትም ህልውና ህያው ሲሆን ወልድን ወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን አሰረጸ፤ ማለት ነው፡፡ ስለዚሀ በህላዌው ህሊና ሲባል በባህርዩ ለባዊ ወአለባዊ ሲባል በመለኮቱ ጠባይእ ሲባል በተለየ አካሉ ባህርይ ሲባል በተለየ ግብሩ ወላዲ ወአስራጺ ሲባል በተለየ ስሙ አብ ሲባል አንድ ጊዜ ነው፡፡
ቃልም በራሡ ህልውና ነባቢ ወአንባቢ ሲሆን፣ በባህርይም ህልውና ለባዊ ሲሆን፣ በህይወትም ህልውና ህያው ሲባል አለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር አንድም፡- እንበለ ጊዜ ወሰዓት ይላል፤ ከአብ አካል ዘእምአካል ባህርይ ዘእምባህርይ ተወለደ ማለት ነው፡፡ ስለዚሀ በህላዌው አእምሮ ሲባል፣ በመለኮቱ ጥበብ ሲባል፣በባህርዩ ነባቢ ወአንባቢ ሲባል፣ በተለየ አካሉ ቃል ሲባል፣ በተለየ ግብሩ ተወላዲ ሲባል፣ በተለየ ስሙ ወልድ ሲባል አንድ ጊዜ ነው፡፡
መንፈስ ቅዱስም በራሡ ህልውና ህያው ወማህየዊ ሲሆን በባህርይም ህልውና ለባዊ ሲባል፣ በቃልም ህልውና ነባቢ ሲባል፣ አለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር ከአብ አካል ዘእምአካል ባህርይ ዘእምባህርይ ሰረጸ ማለት ነው፡፡ ስለዚሀ በህላዌው ፈቃድ ሲባል፣ በመለኮቱ ኃይል ሲባል፣በባህርዩ ሕያው ወማህየዊ ሲባል፣ በተለየ አካሉ ህይወት ሲባል፣ በተለየ ግብሩ ሰራጺ ሲባል፣ በተለየ ስሙ መንፈስ ቅዱስ ሲባል አንድ ጊዜ ነው፡፡ (ተጨማሪ ትርጓሜ ፊደላት ይመልከቱ)
የሦስትነቱን ያንድነቱን እንዲህ ባነሰች በጠበበች አገላለጽ ካየን አሁን ደግሞ እርስዎት ስለጻፉልኝ መልእክት፣የሐዋርያት እና የሊቃውንትን ስብከት በምናይበት ጊዜ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡ይህም ጽሑፍ መታሰቢያነቱ ብለው እንደተ ጨማሪ ጽሑፍ ገልጸውታል፡፡እነሆ ከመጀመሪያው ገጽ እነመልከት፡፡
ገጽ አንድ ላይ ሀ. መዝ.36፣6 የሦስትነት ምስክር፣
ለ. ሃ.አ. ም.10 ቁ. 12 ከአብ የወልድን መወለድ የመንፈስ ቅዱስን መስረጽ ይትነከር አላ ኢይትነገር መሆኑን፤
ሐ. ሃ.አ. ም.11 ቁ፣13 ወልድን በመለኮቱ ፍጡር ለሚሉ አርዮሳውያን ቅ. አገናጥዮስ የጻፈውን፣
መ ሃ.አመ ሃ. አ. ም.16፣ክ.1 ክርስቶስ በፈቃዱ ሥጋን እንደለበሰ ሰውም እንደሆነ ከኃጢአት በስተቀር ሥረዓተ
ሰብእን ሁሉ እንደፈጸመ ቅ. እለስክንድሮስ የጻፈውን፤
ለዚህ እጹብ ድንቅ ለሆነ የቸርነት ስራ እነዲህ ስል ተጨማሪ ምስክር እጽፍልዎታለሁ፡፡ኮነ በአርአያ ሰብእ እስከ ኮኑ ሰብእ ድልዋነ ይርአይዎ ለመለኮት::ሰወች መለኮትን ያዩት ዘንድ የበቁ እስኪሆኑ ድረስ በሰው ባሕርይ ተገለጠ። ብሎ ጎርጎርዮስ ገባሬ ታምራት ተናገረ።{ሃ.አ. ም.15፣ቁ. 11}
ሠ. ጸሎት ሃይማኖት ዘሠለስቱ ምእት፣
ረ . ሃ. አ. ም. 31 ቁ. 21 ቅ. አትናትዮስ ስለአካላዊ አብ ልብነት፣ስለአካላዊ ወልድ ቃልነት
ስለአካላዊ መንፈስ ቅዱስ ህይወትነት (እስትንፋስነት) የተናገረውን፣
ሰ. ሃ. አ. ም. 31. ቁ 29 ቅ. አትናቲዎስ ሥጋ ከመለኮት መለኮት ከሥጋ መዋሀዱንና መለወጥ
የሌለበት መሆኑን የተናገረውን በእኒህ ከ ሀ-ሸ በደብዳቤዎት ላይ የጠቀሷቸውን ኃይለ ቃላት፣ የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እምነታቸውን፣የነገሩንን፣ ያስተማሩንን በውነት እናምናለን፡፡በዚችም ሕግ በውነት ጸንተን እንኖራለን፡፡
በገጽ ሁለት(2) የተጻፉ ኃይለ ቃላት
ሀ. ሃ. አ. ም. 44፣ቁ 5 አዮክንድዮስ ክርስቶስ ቀዳማዊ ደኃራዊ መባሉን የመሰከረውን፣
ሃ. አ. ም. 45፣ቁ. 4 ከርስቶስ በሰውነቱ እንጅ በመለኮቱ ሕማም ሞት እነደሌለበት የተናገረውን፤
የማይቀበል፤ የማያምነውን፤ ከክርስቲያን ወገን ሁሉ የተለየ እንደሆነ እኒህ ቅዱሳን አባቶች በሥለጣነ መንፈስ ቂዱስ አወግዘዋል፡፡ነገር ግን በገጽ 148 ቁ.5 ያለውን ኃይለ ቃል “ለመለኮት ጥንት እንደሌለው ከትንሣኤው በውኃላ ለትእስብቱም እንዲሁ ፍጻሜ የለውም” ሲል ምን ማለቱ ነው?
በቃል ቅብእነት (በወልድ ቅብዕነት) ህያው ዘላለም ሁኖ ይሆን? ይህን ቅዱሳን መጻሕፍት መልስ ይሆኑን ዘንድ ልቡና ይስጣቹህ፡፡ እኛ ግን እንዲህ እንናገራለን፡፡ለትስብእቱ እንዲሁ ፍጻሜ የለውም ቢል ክርስቶስ በሰውነቱ የመንፈስ ቅዱስን ህይወትነት በንስአት በህድረት ተቀብሎ እንደባህርይ አባቱ እንደ አብ ህያው ወማህየዊ ሁኖበታልና ከእነአላዛር ትንሣኤ ሲለይ እስከ የሌለው ፍጻሜ አለ፡፡ ከትንሣኤውም በፊት በፈቃዱ ሞትን እነደቀመሰ በራሱ በሰባዊት ልሳን እንዲህ ሲል ተናገረ፡፡ወአልቦ ዘየሀይደኒያ አላ ለልየ እሜጥዋ በፈቃድየ እስመ ብውህ ሊተ አንብራሂ ወእሢማ ወብውህ ሊተ ካዕበ አንስኣ፤ ዘንተ ትእዛዘ ነሣእኩ እምኀበ አቡየ፡፡(ዮሐ.10፣18)
ለ. ሃ. አ. ም. 68. ቁ.13 ዮሐንስ አፈወርቅ ስለሥርዓተ ትእስብት አባቱን አምላኪዬ ብሎ እንደጠራው ይህም አንሰ ነሳእኩ ዘበአማን ትስብእተ፡፡ ወከመዝ ጸወዋእክዎ ለአምላኪየ ዘከመ ይደሉ ለሥርዓተ ትእስብት ዘረሰይክዎ አሀደ ምስሌየ ፡፡እርሱ እኔ ነፍስን ሥጋን በውነት ተዋሕጄአለሁና ከእኔ ጋር አንድ አካል አንድ ባሕርይ ላደረኩት ለስጋ ሥርዓት እንደሚገባ እንዲህ አባቴን አምላኪዬ ብዬ ጠራሁት ይላል፡፡ ያለውን የማይቀበለውን በዚህ ቅዱስ ሥልጣን ከክርስቲያን አንድነት የተለየ ይሁን፡፡
ሐ. በተራ ቁ. 2 ገጽ 272 ቁ.14 የቅዱስ ቄርሎስ አንደበት ጠቅሰውታል፡፡ይህም ኃይለ ቃል፡-
ነፋሕኩ በገጸ አርዳእየ አጠይቅ ከመ ፈጣሪ አነ ዘነፋሕኩ ውስተ ገጹ ለብእሲ ዘነበረ ውስተ ገነት ዘውእቱ አዳም ፡፡ በአዳም በንፍሐት መንፈስ ቅዱስን ያሳደርኩ ፈጣሪ እኔ መሆኔን አስረዳ ዘንድ በደቀ መዛሙረቴ ፊት እፍ ብዬ አሳደርኹ፤ አለ፡፡(ዮሐ.20፣22) ይላል፡፡ወልድ ዋህድ እንደአምላክነቱ ሕይወቱን መንፈስ ቅዱስን ቢሰጥ እነደሰውነቱ መንፈስ ቅዱስን በአካሉ ገንዘብ እንዳደረገ ለምእመናን ሁሉ ያስረዱልኝ፤እርስዎትም ይረዱለኝ፡፡ ይህ ቅዱስ አባት እንዲህ አለ፡-“ወካዕበ ነጽሩ ከመ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሶበ ነስአ መንፈሰ ቅዱሰ በትእስብቱ እንዘ ውእቱ ፍጹም ኀበ አቡሁ በመለኮቱ፤ ወእቱኒ ፈነወ መንፈሰ ቅዱሰ ኀበ ሰብእ እለ አምኑ ቦቱ፤ እንከሰ ገብረ ወልድ ግብረ አቡሁ እመ ወሀበ መንፈሶ ለእሊኣሁ ለሊሁ ነሥአ በትእስብቱ፡፡ ( ሃ.አ. ም.80፣ ቁ.1) እንኪያስ ወልድ ለወገኖቹ ለምእመናን መንፈስ ቅዱስን ከሰጠ ያባቱን ሥራ ሠራ፡፡ሰው በመሆኑ መንፈስ ቅዱስን ገንዘብ አደረገ”፡፡ ይላልና ዳግመኛም ሳዊሮስ ወበእንተ ዝንቱ ነሥአ መንፈሰ ዚያሁ ዘተነግረ በኢሳይያስ ነቢይ እንዘ ይብል መንፈሰ እግዚአብሔር ላዕሌየ በእንተ ዝንቱ ቀብአኒ ብሎ ተናገረ፡፡ ሃ.አ. ም 87 ቁ. 16.
በተራ ቁጥር 3. የጠቀሱት “አንድ ክርስቶስን ከሁለት እነዳንከፍለው ከእግዚዘብሔር አብ የተወለደ ቃልን የክርስቶስ ገዥ ነው አንለውም” የሚለውን የቅ.ቄርሎስ አንደበት በዚህ እነታመናለን፡፡ ነገር ግን ቅድመ ዓለም ከእግዚአብሔር አብ የተወለደውን ለሥጋ ቅብእ ሆነው አንልም፤ በዚህም የሚያምኑ ስሁታን እነደሆኑ ገልጸን እንናገራለን፡፡ ለሥጋ አካለ ቃል ቅብዕ ከሆነ ክርስቶስ የተባለ ሥጋ ብቻ ነው ያስብላልና፡፡ ቃልንም ከመሲሕነት ያዋጣዋል፤አንድ ልጅ፣ አንድ መሲሕ፣አንድ ክርስቶስ አያሰብልምና፡፡ ወልድ ቅብዕ ብሎ ከመናገር ይልቅ የአካልና የባሕርይን ሁለትነት፣አካል ከባሕርይ ወይም ባሕርይ ከአካል ተለይቶ ቋሚ ሁኖ በራሱ ሊገኝ እንደሚችል ምሳሌ መስሎ፣ኃይለ ቃል ጠቅሶ ማስረዳት ይቀል ይመስለኛል፡፡
ሠ. በተራ ቁጥር 5 የጻፉት መለኮት ከሥጋ ሥጋ ከመለኮት ባለመቀላቀል እነደተዋሀደ ተናገረ እንጂ በተዋህዶ ከበረ አለን? ወይስ የቃል ቅብዕነት ለሥጋ ሆነ ብሎ ተናገረን? በተዋህዶ አንድ አካል አንድ ባህርይ ይባል ዘንድ በሚገባ አስረዳ፡፡
ረ. በተራ ቁ. 7 የጠቀሱት ኃይለ ቃል "ወእምነተ ተዋህዶሰ ኢይብልዎ ዘእንበለ ዳእሙ በምክረ እከይ” (ሃ.አ.ም.78፣69)፡
“አደረበት ይላሉ እንጂ የተዋህዶን እምነት አያምኑበትም"፤ ይላል ፡፡እኛስ አካለ ቃል በአካለ ሥጋ አደረበት አንልም፡፡መለኮት ከሥጋ ሥጋ ከመለኮት ያለቱሣሄ ያለተጋውሮ፣ ያለተላጽቆ ተዋህዶ አንድ ልጅ በምትል ሃይማኖት እናምናለን፤እናሳምናለን፡፡ምናልባት እምነተ ተዋህዶ ሲል ክርስቶስ በሰውነቱ በተዋህዶ የከበረ አምላክ ያለ መስለዎት ይሆን? መጻሕፍት ተዋህዶ ዕያሉ ሢያገኙ በተወህዶ ከበረ ያለ እየመሰለወት ነው መሰለኝ ተዋህዶ ያለበት ጥቅስ አልቀረም፡፡ መጀመሪያ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ፍቅር ካለወት ተዋህዶ ማለት ምን ማለት ነው? “ተቀብዐን”ና “ተዋሀደን” ትርጓሜቸውን ለይቶ ከተረዱ በወኋላ ምሥጢረ ሥጋዌው ሁሉ ግለፅ ይሆናል፡፡ አውጣይኬ ትስብእትንና መለኮትን እንደቀላቀለ ወልድ ቅብእ የሚሉ ሊቃውንትም እኒህን ሁለት የተለያዩ ትርጉም ያላቸውን ቃላት ቀላቅለው ያለስልቱ ያለትርጉሙ መጻሕፍትን እንመልሳለን እያሉ መጻሕፍትን ሲቆነጽሉ ምሥጢራትን ሲያፋልሱ ራሳቸው ስተው ሰውን ሲያስቱ ይኖራሉ፡፡
መ. ሃ. አ. ም.82፣ቁ.20 የጠቀሡት ኃይለ ቃል እንዲህ ይላል “አላ ይቤ ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር፡ አንድ አድርጎ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ እንጂ፡፡አኮ ዘከመ ትስብእቱ ፡ ፡ ልጄ ማለቱም ሰው እንደመሆኑ አይደለም፡፡ አላ ዘከመ መለኮቱ፤ አምላክ እንደመሆኑ ነው እንጅ፡፡ “ልጄ ማለቱ ሰው እንደመሆኑ አይደለም” ብለው ሲናገሩ ክህደት አይሆንብዎትምን? “በሰውነቱ የእግዚአብሔር ልጅ፣ በመለኮቱ የማርያም ልጅ አይደለም” እንደማለት ያለ ነውና፡፡በመንፈስ ቅዱስ ጠቋሚነት በዮሐንስ ምስክርነት “ዝነቱ ወእቱ ወልድየ” ያለው እኮ ይህ በሰባዊት አካል የሚታይን ልጅ ነው፡፡ ይህም ልጁ ሰው በመሆኑ የባሕርይ አባቱ በልጁ ቃልነት “ልጄ ይህ ነው ብሎ” እንደመሰከረ መጻፍት ይናገራሉ፡፡ ቃልንማ በ5500 ዓመተ ዓለም ውስጥ ይሁን ቀድሞ ዓለም ሳይፈጠር “ዝንቱ ውእቱ ወልድየ” አላለውም፤ ይለውም ዘንድ አይገባ፡፡ ስለዚህ “ዝንቱ ውእቱ ወልድየ” ብሎ የተናገረ ሰው በመሆኑ ነው፡፡ መጥምቁም ያየው እኮ በሰውነት አካል ነው፤ “ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር” ያለውም በሰባዊት አካል የታየውን ልጅ ነው፡፡ አባቱም “ዝንቱ ውእቱ ወልድየ” ያለው በሰውነት አካል ለመጥምቁ እየታየ ነው፤ በደብረ ታቦር ለነጴጥሮስ፣ ዮሐንሰ ያዕቆብም እንዲሁ፡፡ ከላይ የጠቀሱት ኃይለ ቃል የአማረኛ ልሳኑ የአተረጓጎም ህጸፅ አለበት፡፡ይኸንስ እንዲህ ሲሉ ይተረጉማሉ፡፡ አላ ይቤ ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር አኮ ዘከመ ትስብእቱ፤ አላ ዘከመ መለኮቱ ፡፡አንድ አድርጎ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ እንጂ፡፡ ልጄ ማለቱም በሥጋ ነቱ ወልዶት አይደለም፤ አብ በመለኮቱ ቢወልደው ነው እንጂ፡፡ ቃል ከሥጋ ሥጋ ከቃል ጋር ሲዋሀድ ከእግዚአብሔር አብ የተገኘ ቃልን ድንግል እናት በእርሷ ባሕርይ ጸነሰችው፤ ከድንግል የተከፈለ ሥጋንም እግዚአብሔር አብ ባንዲት ባሕርይ በመለኮቱ ወለደው፡፡ ወዮ! ለዚች መለኮታዊት ምሥጢር አንክሮ ተደሞ ይወስናት ይሆን? ምንት ውእቱ ሰብእ ከመትስክሮ ተብሎ በነቢዩ እንደተነገረ፡፡ ስለዚህ በመለኮቱ የማረያም ልጅ በሰውነቱ የእግዚአብሔር አብ ልጅ አይደልም ተብሎ ይነገር ዘንድ ጽኑ ክህደት ነው፡፡ እርሷ ድንግል ከእርሷ ባህርይ ያልሆነውን መለኮትን ለእርሷ በሚገባ ሥጋዌ የእርሷ በሆነ ባህርይ በማይነገር በማይመረመር ምሥጢር በህቱም ድንግልና ወለደችው፡፡የድንግል ሥጋዌ የአዳም ሥጋዌ አይደለምን? የአዳም ስጋዌስ በነባቢት በህያዊት ነፍስ የምትገለጥ አይደለችምን? ዝኒ ከማሁ ልደተ ወልድ በሥጋ እምእግዚአብሔር አብ፡፡ እግዚአብሔር አብም ከድንግል የተገኘውን ሥጋ አንድም ከእርሱ ባህርይ ያልተገኘውን የአዳምን ባህርይ ከእርሱ በተገኘ ህይወቱ በሆነ በመንፈስ ቅዱስ አካል ዘእምአካል ባህርይ ዘእምባሕርይ በድንግል ማህጸን ወለደው፡፡ እነዲህ እንመን እነዲህ እናስተምር፡፡ንስጥሮሳውያንን፣ልዮናውያንን በቃል እየነቀፉ የእምነት ተባባሪ ሁነው እንዳይገኙ የሊቃውንትን ትርጓሜ ያሰተውሉ ዘንድ እለምነዎታለሁ፡፡
ኢትዮጵያዊዉ ሊቅ አባ ዘጊዮረጊስ ይህንን በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው እንዲህ ሲሉ ተናገሩት ፡-
እመድኅረ ሥጋዌሁሰ ኢንቤሎ ለወልድ ወልደ እግዚአብሔር በመለኮቱ ወወልደ ዕጓለመሕያው በትስብእቱ፡፡ድንግልኒ ወለደት ዘኢዚያሃ መለኮተ በዘዚያሃ ሥጋ ዘምስለ ዘዚያሃ ሥጋዌ፡፡ አብኒ ወለደ ዘኢዚያሁ ሥጋ በዘዚያሁ መለኮት ምስለ ዘዚያሁ ኃይል ዘህሉና አምላክ፡፡
ሰው ከሆነ በውኋላ በመለኮቱ የእግዚአብሔር ልጅ በሰውነቱ የሰው ልጅ ልንለው አይገባም፡፡ድንግልም ለእርሷ በተገባ ሥጋዌ የእርሷ በሆነ ሥጋ የእርሷ ያልሆነውን መለኮትን ወለደችው፡፡አብም የባሕርዩ ያልሆነውን ሥጋ የባሕርዩ ከሆነ የህሉና አምላክ ኃይል ጋር የእርሱ በሆነ መለኮት ወለደው፡፡(መጽሐፈ ምሥጢር ገጽ 34 ቁ46 ይመልከቱ)
ሠ .ሃ. አ. ገጽ 413 ቁ.9 ብለው የጠቀሱት ኃይለቃል “በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቍአቸው” እንዳለ የምናምንባት ሃይማኖት ይች ናት፡፡ብሎ አባ ገብርኤል ተናግሮታል፡፡ እናንተ ባንደበታቹህ እንዲህ ተጽፏል ትላላቹህ፡፡ነገር ግን ክርስቲያኖች በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠምቀው ሁለተኛ ታጠምቃላቹህ፡፡በውነት ከርስቶስ መሲህ ያለ ሁለተኛ ይጠመቅን?
ረ. ሃ.አ. ገጽ 422 ቁ.17 የጠቀሱት ኃይለ ቃል ተዋህዶ መንታንትን አጠፋ አለ እንጂ፤ የሁለትነትን ፍርድ ይለውጣል አለ እንጂ መቼ በተዋህዶ ከበረ አለ፡፡
ሰ. ሃ. አ. ገጽ 451 ቁ. 13-14 ፤በገጽ 456 ቁ15፤ገጽ465 ቁ. 9፤ገጽ 474 ቁ. 10-11፤ ገጽ 475 ቁ15- 16፤ የጠቀሷቸው ቃላት ተዋህዶን የማይቀበሉ፣ወልድ ዋህድን ሁለት ባህርያት ባንድ አካል የሚሉ ልዮናውያንን፣ ሁለት አካል ሁለት ባህርይ የሚሉ ንስጥሮሳውያንን፣ አላውያንን፣ ከሀድያንን የሚገስጽ የሚናገር ነው እንጂ፤ ሥጋና መለኮት ባንድነት ተዋህደው ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባህርይ አንድ ባህርይ ከሁለት ግብር አንድ ግብር መሆኑን፣ ወልድ ቃለ እግዚአብሔር ኅያው ወልደ አብ ወልደ ማርያም መባሉን የሚመሰክሩ እንጂ ወልድ ቅብእ ያለ መሰለዎትን? ይህ የሚያሳዝን ነገር ነው፡፡የራስን እምነት ዐውቆ ኃይለ ቃላትን ጠንቅቆ መናገር በራሡ ብልህነት ነው፡፡ “ወእሙንቱሰ ኢያምጽኡ ስምዐ እምነ መጻሕፍት አሐተ ቃለ አላ ይዜከሩ እምኀበ ርእሶሙ ወይትቃወሙ በዘይነብቡ ወይብሉ ከመ ክርስቶስ ፪ቱ ህላውያት፡፡እነዚያ ግን ከመጻሕፍት አንዲት ቃልስ ስንኳ ምስክር አላመጡም፤ከርሳቸው አንቅተው ይናገራሉ፤በዚያውም ሁለት ባሕርይ ነው እያሉ ይከራከራሉ፡፡” ብሎ የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳሳት ንጹህ አባት አባ ዮሐንስ እንደተናገረ፡፡(ሃ.አ. መ.102፣ ቁ. 13) “ወልድ ቅብዕ፤ በተዋህዶ ከበረ” እያላቹህ በነቢያት ያልተነገረ በሓዋርያት ያልተሰበከ በሊቃውንት ያልታየ ያልተተረጎመ ከኅሊናቹህ አንቅታቹህ ትናገራላቹህና፤በከንቱም ትከራከራላቹህ፤ መጽሓፍ ነሥአ ተወክፈ ቢል ንስአቱን ህድረቱን ዘኢይረብእ አላችሁት፡፡ እንግዲህ ወዲህ ከዚህ በላይ (ግብረ መንፈስ ቅዱስን ከመካድ በቀር) ምን ክደት አለ፡፡ አያይዞም “ወእሙንቱሰ ኢተመይጡ እንዘ እሙንቱ ቦቱ ወኢሰሙ ቃለ መጻሕፍት እነዚያ ግን ካሉበት ክህደት አልተመለሱም፤ መጻሕፍት የተናገሩትንም አልሰሙም፡፡”አለ፡፡ (ሃ.አ. ም. 102 ቁ፣15)
ወዘሰ ሀደረ ለእሌሁ መንፈስ ቅዱስ በእንተ ሥርዓተ ትስብእት፡፡ መንፈስ ቅዱስ በእረሱ ላይ አደረ መባሉ ቃል ሰው ስለሆነ ነው ብሎ ይነግራቹሀልና፡፡(ሃ.አ. ም.87፣18) ይኸን ዘኢይረብእ አላችሁት፤ በአዳም ላይ የሥጋን ህይወት እፍ ብሎ ያሳደረን አምላክ ከባህርይ ህይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ለያችሁት፤ ስለነሳው ሥጋ በመንፈስ ቅዱስ ከበረ ብላቹህ አታምኑም፤በዚህም የመንፈስ ቅዱስን ግብር ካዳቹህ፡፡
በገጽ 4 የጻፏቸው ኃይለ ቃላት
ሸ ሃ አ. ም. 105ቁ. 10-13 እና ቁ.15-16 የጠቀሱትን የአባ ፊላታወስ አንደበት ራሱ እንደጻፈልን ሃይማኖታችን፣ እምነታችን ይህ ነው አንድ ልጅንም ወደሁለትነት የሚከፍሉትን የምንረታበት ምላሽ የምናሳጣበት ኃይላችን ነው፡፡ “ወናርህቅ እማእከሌነ ኩሎ ዘይክህድ ሃይማኖተ ኦረቶዶክሳዊተ (ሃ. አ. ም105 ቁ16) ኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖትን የሚክደውን ሁሉ ከመካከላችን እናርቅ” እንዳለ አባ ፊላታዎስ
ቀ ሃ. አ. ም 114 ቁ5 የጠቀሱትን ኃይለ ቃል ስናይ" ወዓዲ ንብል አብ ህይወት፣ ወልድ ህይወት መንፈስ ቅዱስ ህይወት እንዘ አሐዱ ህይወት በህላዌ መለኮቱ፡፡ዳግመኛ በመለኮት በባሕርይ አንድ ሕወት ሲሆን አብ ሕይወት ነው ወልድ ሕይወት ነው መንፈስ ቅዱስ ህይወት ነው እንላለን፡፡" ይላል፡፡ ዕንዲህ ሲል ምን ማለቱ ነው? አብ ልብነቱን ለቆ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ ሕይወታቸው ሆነ ማለት ይሆን? ወይስ ወልድ ቃልነቱን ለቆ ለአብ ና ለመንፈስ ቅዱስ ህይወት ሆነ ማለት ይሆን ? “ወዘንተ ሶበ ንቤ ንሜስል ከመ አይሁድ እለ ይሰልብዎ ንባቦ ወህይወቶ እለ አልቦሙ አምላክ ንሜስል፡፡ ይህንን ብንናገርስ አምላክ ያላደረባቸውን ቃሉን እስትንፋሱን ያሳጡጥትን አይሁድን መምሰላችን ነው፡፡”ይላል ቅዱሱ አባት የስክንድርያና የግብጽ ሊቀ ጰጳሳት አባ ስኑትዩ፡፡ (ሃ.አ. ም.110 ቁ.11)
እኛስ የአብን ህይወትነት፣ የወልድን ህይወትነት የመንፈስ ቅዱስን ህይወትነት እንዲህ እንናገራለን፤ እንዲህም እናስተምራለን፡፡ አብ ህይወት ቢል የባህርይ ሲሆን የወልድና የመመንፈስ ቅዱስ አካላዊ የልብነት ህይወታቸው ነው፡፡ወልድ ህይወት ቢል ለአብና ለመንፈስ ቅዱስ አካላዊ የቃልነት ሕይወታቸው ነው፡፡መንፈስ ቅዱስ ህይወት ቢል የባህርይ ሲሆን ለአብና ለወልድ አካላዊ የደህንነት (የእስትንፋስነት) ህይወታቸው ነው፡፡እግዚአብሔር ሕያው ዘላለም የሚባልም በመንፈስ ቅዱስ ህይወትነት ነው፡፡ የጸጋ ከሆነ ግን የሥሉስ ሀይወትነት ለመላእክትና በስሙ በክርስቶስ አምነው ተጠምቀው በህገ ነፍስ ጸንተው ለሚኖሩ ምእመናን የሚሰጥ ክብራቸው፣ ጸጋቸው፣ ሁሉን በጸጋ የሚገዙበት፣ የሚይዙበት ነው፡፡ስለዚህ ሊቃውንት አብ ህይወት ወልድ ህይወት መንፈስ ቅዱስ ሀይወት እያሉ በጸጋ እግዚአብሔር ደረሱት፡፡
ንሥአተ መንፈስ ቅዱስ ኅድረተ መንፈስ ቅዱስ የባሕርይ እንጅ እንደ መላእክት ነቢያት፣ ሐዋርያት ፣ጻድቃን፣ ሰማእታት የጸጋ እንዳይደለ ሊቃውነተ ቤተ ክርስቲያን ተናግረዋል፡፡ ሀደረ የባህርይ ሲሆን ኤፍሬም ሶርያዊ “ዘየሀድር ውስተ ብርሃን ኀበ አልቦ ዘይቀርቦ” ብሏል፡፡ ወንጌላዊም ቃል ሥጋ ኮነ ወሀደረ ላዕሌነ ብሏል፡፡ ቃል ከሥጋ ጋር መዋሀዱ የባሕርይ ነውና፡፡
ነሥአ የባሕርይ ሲሆን “ወነሥአ ሥጋ ዚያነ” ይላል፡፡
ጥያቄ 1 ተቀብዐ ተዋሀደ ተብሎ የሚተረጎምበት ከሊቃውንት አንደበት ከሰማኒያ አሐዱ መጻሕፍት ይላኩልኝ፡
2 ወልድ ቅብዕ ክርስቶስ ሰውነቱን በቃል ዘይትነት አከበረው የሚል ከሊቃውንት አንደበት ከሰማኒያ አሐዱ መጻህፍት ፈልገው ፈልገው በአምላክ እናት ይላኩልኝ፡፡ ወሮታ ከፋይ ነኝ፡፡
3 ወልድ “በተዋህዶ ከበረ፡፡” የሚለው በሰውነቱ ነውን ወይስ ባምላክነቱ? ይህስ ክብር የስልጣን ነው ወይሰ የግብር? “አክባሪው፣ ከባሪውና ክብሩ ማነው” ይላሉ? አካላዊ ነው ይላሉ ወይስ ዝርው? መቸም ቢሆን ዝርው ነው እንደማይሉ ይታወቃል፡፡ አከላዊ ነው ሲባል እንዴት ነው? አካል የተባለውስ ማነው? ሥጋ ወይስ ቃል ነው?
4 ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በሦስተኛው ድርሳን የነቢዩን ትንቢት የሐዋርያውን ስብከት ሲተረጉም “ዝነቱ መንበርከ መትልው ቀብዐከ “ አለ፡፡ ወዲህም ወበእንተ ወልዱሰ ይቤ መንበርከ እግዚኦ ለዓለመ ዓለም ስለወ ልድ መ ንበርከ እግዚኦ ለዓለመ ዓለም አለ፡፡
ወ ዝ ንቱ ያሌቡ ዕንበይነ መ ንግስት፡፡ “መ ንበርከ” ያለው መ ንግስቱን ያስረዳል፡፡ካለ በውኋላ አየይዞም ወ አስተማ ሰሎ በእለ ይ ወ ርሱ ወ እለ ይነሥኡ ክብረ ወ መ ንግስተ፡፡ አለ፡፡ወዲህም
ወ እም ዝ አትለዎ ወይቤ በእነተ ሥ ጋ ዌ ሁ አፍቀርከ ርትዐ ወ አ መ ፃ ጸላእከ በእንተዝ ቀብ ዐከ እግዚአብ ሔ ር አም ላክከ ቅ ብ ዐ ት ፍ ሕ ሥ ት ዘይኄ ይስ እም እለ ከማ ከ:፡መንበርከ እግዚኦ አንድም በትረ መንግስትከ ካለ በውኃላ ስለሰውነቱ ብእንተዝ ቀብዐከ እግዚአብሔር አምላክከ አለ፡፡
ዘንተኒ ይቤ በፍኖተ ክላህ ይህን አሁን የተናገረውን በትንቢት በምሳሌ ፣ባገባብ፣፤ ተናገረ፤
1ኛ ትንቢት፡- ትንቢት የሚመጣውን አውቆ መናገር ነው፡፡
2ኛ ምሳሌ ቀብዐከ ብሎ በትረ መንግስትከ በትረ ጽድቅ ማለት ነው
3ኛ አገባብ በሰውነቱ ተቀባ ማለት ነው፡፡
አንድም በጩኸት በድፍረት ተናገረ፡፡አነድም ጩኾ ደፍሮ ተናገረ፡፡
4ኛ ድፍረት አምላክ ከበረ ማለት ነው፡፡ አነድም ድፍረት አምላክከ ማለት ነው፡፡
እንዲህ ሲል ተረጎመው፡፡ይህንም ከተናገረ በውኋላ በ15ኛው ድርሳኑ
ወኵሉ ምግባረ መንፈስ ኅዱር ውስተ ሥጋሁ፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ሥራው ሁሉ በለበሰው ሥጋ ገንዘቡ ነውና ፡፡ በዚህ ጊዜ እሰመ ቦአ ወኅዱር ውስተ ሥጋሁ ብሎ ይገጥሟል፡፡ አንድም ደብተራ ውስተ ሥጋሁ አንድ ወገን በዚህ ጊዜ ፍጽምት ወህዱር ብሎ ይገጥሟል፡፡
እስመ አኮ በመስፈርት ዘወሀቦ እግዚአብሔር መንፈሰ፡፡እግዚአብቤር አብ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስን በልክ በመጠን የሰጠው አይደለምና፡፡የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ሁሉ ገንዘቡ ነው፡፡ እያለ የወነጌላዊው ዮሐንስን አንደበት ተረጎመው፡፡ ይህ ከሆነ የሊቃውንት አንደበት ነስአ ተወክፈ ቢል እንደጥምቀቱ፣እንደግርፋቱ
፣እንደስቅለቱ፤እነደሞቱ ሁሉ ንሥአተ መንፈስቅዱስ ህድረተ መንፈስ ቅዱስ አልጠቀመውም ሲባል ምን ማለት ነው? ዘኢይረብእ ከሆነ ለምን “እስመ አኮ በመስፈርት ዘወሀቦ” አለ?
እኔ ግን ስለመንፈስ ቅዱስ ዘይትነት፣ ስለመንፈስ ቅዱስ ቅብዕነት ልጽፍልዎት ብወድ የቀረችው መላ ዘመኔ ባልበቃችኝ ነበር፡፡ነገር ግን ከነቢያት ከሐዋርያት ከሊቃውንት አንዳንድ እነዲህ እጠቅስለዎታሁ፡፡
ከነቢያት በትር ትወጽእ እምስርወ እሴይ ፤ ወየዐርግ ጽጌ እምጉንዱ፤ ወየሐድር ላእሌሁ መንፈሰ እግዚአብሔር .....(ኢሳ.11፣1-4) ትርጓሜውን ሃ.አ. ዘሳዊሮስ ም.87 ክፍል 9 ይመልከቱት
ከወንጌል በከመ ቦቱ ለአብ ሕይወት ከማሁ ለወልድኒ ወሀቦ ሕይወተ ከመይኩን ሕይወት በኀቤሁ (የሐ.5፣25)
ከሊቃውንት፡- ወባሕቱ ንሕነሰ መሲሓውያን ንብል በሃይማኖት ርትዕት ወጽድቅት ወንጽት ከመ እሉ ነኪራን እምኔሁ እለ ይብሉ ከመ ዝ፡፡ እኛ ክርስቲያን ግን በቀናች በተረዳች ሃይማኖት ጸንተን እንዲህ የሚሉ ከሱ የተለዩ እነደሆኑ እንናገራለን፡፡ አው ተብህለ በእንቲያሁ ከመ ቅቡዕ ውእቱ ወተሰምየ ወልደ አምላክ፡፡የተቀባ ክርስቶስ እንደሆነ ቢነገር የአምላክ ልጅም ቢባል
ኢንኀፍር ንህነ እምስርአተ መድኅን፤ መድኅን ክርስቶስ በፈጸመው ሥርዓት እኛ አናፍርም፡፡
ወሶበ ኮነ ሰብአ ተሰምየ ሓዋርያ ወተቀብዐ ምስሌነ ከመ ሥርዓተ ትስብእት እንደእኛ የለ ሰው ቢሆን ሐዋርያ ተባለ፤ ለሰውነትም እንደሚገባ እንደኛ መሲሕ ተባለ፡፡(አነቀጹ ተቀብዐን መሲሕ ብሎ ተረጎመው ትንሽ ሸሸሁ መስሎት) ትርጉሙስ ይህ ነው ሰው ሲሆን ሐዋርያ ተባለ፤ ሰው እንደመሆኑም ከበረ ተብሎ ይተረጎማል፡፡ (ሃ. አ. ም.121፣ ቁ.12)
ወከመዝ ነአምሮ ከመ ለሊሁ ተቀብዐ ከመ ሥርአተ ትእስብት እንደሰው ሥርዐት እነደተቀባ እናውቀዋለን
ወዳእሙ ለሊሁ ውእቱ ዘይቀብዕ ረእሶ በመንፈሱ ባሕቲቱ፡፡ ጥንተ ሕይወቱ በሆነ በመንፈስ ቅዱስ ራሱን የሚያከብር እርሱ ነው እንጂ፡፡
ከመ አንትሙ ትብዓሉ በንዴተ ዚያኣሁ፣ በእርሱ ዜግነት እላንት ባለጸጋ እንድትሆኑ፣
ከመ ተቀብዐ ሕይወቶ መንፈሰ ቅዱሰ፣ ሕይወቱ የሆነ መንፈስ ቀወዱስን እንደተቀባ፣ እንዘ ለሊሁ ይቀብዕ ርእሶ፣ ለተቀባኢ አካሉ ራሱ ቀባኢ ሲሆን በከመ ስምዐ ኮነ ለሊሁ እንዘ ይብል ፣ እርሱም እንዲህ ሲል ምስክር እንደሆ በእንቲኣሆሙ አነ እቄድስ ርእስየ፤ ስለአርሳቸው እራሴን አከብራለሁ ሲል ምስክር እንደሆነ
ከመሰ ተቀብዐ ቃል ለርእሱ ይትአመር እመንገለ ስሙ፡፡እስመ ክርስቶስ ብሂል ቅቡዕ ውእቱ ወኢተሰምየ በካልእ ግብር ፡፡ዘኢኮነ ሎቱ፡፡ ዓዲ እስመ ክርስቶስ ይመርህ ኀበ ሠለስቱ አስማት ዘውእቶሙ አብ ቀባዒ ወወልድ ተቀባዒ ወመንፈስ ቅዱስኒ ቅብዕ፡፡ (ድርሳነ ቄረሎስ ይመልከቱ) በውነት ይህ የቅዱሱና የሊቁ ኃይለ ቃል እንዲህ በሕያውነት እያለ ልብ በወለደው የክህደት ሰንሰለት ስንቱ ተጠፈረ፡፡
ልብ ሊሉት የሚገባ ነገር ተረፈ ቄርሎስ እና ድርሳነ ቄርሎስ ሁለት የተለያዩ መጻሕፍት እንደሆኑ መገንዘብ አለበዎት፡፡ ከተረፈ ቄርሎስ ጰላድዮሱ ላይ “ክርስቶስ ሰምይ ቅብዐተ ይሰመይ ዘውእቱ ብሂል መሲሕ” ይላል፡፡ እዚህ ላይ “ቅብዓተ” ቢል መቀባትንና መቅባትን ይነግረናል “ዘውእቱ ብሂል መሲህ” ሲል ግን በሰውነቱ መቀባቱን ይነግረናል፤ ያስረዳናል እንጂ ወልድ ቅብዕ አይልም፡፡ ነገር ግን “ቅብዓተ” ሲል ወልድ ቅብዕ ለማለት ነው መስሏቸው ልባቸውን ነፍተው ደረታቸውን አስፍተው የሚናገሩ እንደአሉ ይነገራል፡፡በዚህ መጽሐፍ ላይ ከፍ ብሎ የተጠቀሰውን ኃይለ ቃል በምናይበት ጊዜ እንዲህ ይላል፤ “ክርስቶስ ይሰመይ በእንተ ቅብዓት ዘተቀብዐ በመንፈስ” ፡፡ በውነት ወልድ ቅብእ ቢባል ኑሮ ““ክርስቶስ ይሰመይ በእንተ ቅብዓት ዘተቀብዐ በቃል” ባለ ነበር፡፡ በውነት የደስታ ዘይትን ተቀባ እየተባለ ስለመነገሩ ደቂቀ አዳም ጸሐፍት ውቅያኖሶቹ ሁሉ ቀለማት ቢሆኑ ተጽፎ ባለቀም ነበር፤ምስጢሩስ ምን ይረቅ ምን ይደንቅ፤ በውነት ተቀባ ካላልን ሞተስ ማለት እንዴት እንችላለን ?
በሦስተኛው ድርሳን “ወለመንክዮንሂ አግሀደ ሎቱ ከመ መለኮት ኢይትቀብዐ አላ በእንተ ትስብእተ ሥጋሁ” ብሎ ሥጋውን ምትሀት የሚሉ መንክዮናውያንን ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በተቀብዐ አንቀጽ የረታቸው አየደለምን? “ተቀብዐንም” የምትክዱ ከሆነ ሥጋውን ምትኃት የምትሉ አይሆንባቹሀምን? “ተወሀደ” ማለት ነው የመትሉትም ከሆነ “ከመ መለኮት ኢይትቀብዐ” ሲል ምን ታደርጉት ይሆን? አዎ! ሊቃውንት ጠፍተውላቹሀል፤ መጻሕፍትም አእምሮ በሌላቸው ስሑታን ተቆንጽለዋል፤እንግዲህ ወዲህስ የባለቤቱን መምጣት እንጠብቃለን እንጂ ከእናንተ ጋር በእምነት አንድነት አይኖረንም፡፡
ሌላው ልነግረዎት የምፈልገው ሃይማኖት እና እምነት ልዩነታቸውን ያውቁ ዘንድ ይገባል፡፡ተዋህዶና ቅብዓት ሓይማኖት አይደሉም፡፡ እምነት ናቸው እንጂ፡፡ባንዲት ኦርቶዶኣዊት እምነት ውስጥ ሥርዓተ ተዋህዶንና ምሥጢረ ቅብዓትን እንናገራለን እናስተምራለን፡፡
ማሳሰቢያ ብለው የጻፉት በኬልቄዶን ጉባኤ (በውሾች ጉባኤ) የልዮን ክታብ ባንድ አካል ሁለት ባሕርያት የምትል ካቶሊካዊት ዶግማ ተወሠነች፡፡ቅዱሱና ንጹሁ አባት አባ ዲዮስቆሮስ ስድስት ኤጲስ ቆጶሳትን ጨምሮ ራሱን ከጉባዔው ቢለይ በደሴተ ጋግራን እንዲጋዝ ተደረገ፡፡ከዚህ ውጭ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በዚህ ጉባዔ ተወሰነ ብለው በውነት ከንፈር የማይነካው ውሸት ለምን ይዋሻሉ? መረጃ ምንጭ ለምን አልጠቀሱም፤ በቄልቄዶን ጉባኤ መወሰኑን የሚናገርስ መጻሕፍ ምን መጻፍ ነው? ይልቅስ ቅዱስ ቄርሎስ ተዋህዶ የምትለዋን ቃል ህድረት የምትለዋን ክፉ ጥፉ ከሐዲ የሚሆን የንስጥሮስን የክህደት አንደበት የዘጋበት፤ በኤፌሶን ጉባኤ ይችን ክህደት አጥፍታ የቃልንና የሥጋን ፍጹም አንድነት ኅብረት ለማስተማር፣ በውነት አምላክ ወሰብእ፤ ወልድ ዋህድ ተብሎ ይታመን ዘንድ የተወሰነች የሃይማኖት እምነት ናት፡፡ በዚችም እምነት እኛ መሲሓውያን ጸንተን እንኖራለን፡፡
ይልቅስ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዶግማ የተወሰነው በዓጼ ዮሐንስ አራተኛ የጸጎችን ምላስ ከቆረጠ በኋላ ነው፡፡ ዓመተ ምህረቱም በ1878 ዓ.ም ነው፡፡ የተዋህዶ ዶግማ መንግስታዊ ሃይማኖት ተደረጎ ተወሰደ፡፡ሌሎች ሃይማኖቶች ግን ከባድ የተባለ ሓይማኖታዊ ቅጣት ደረሰባቸው ይላል፡፡(ምንጭ የኢትዮጵያ ታሪክ) ሌላው የዓጼ ቴዎድሮስ ግፍ በነተክለ ጻድቅ መኩሪያ የታሪክ መጻሕት ሰፋ ብሎ ተዘርዝሯል ያነን ማስተዋል በራሱ ብልህነት ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡ የምንቀበለው ሥጋና ደም መለኮት የተዋሀደው፣ ደማዊት ነፍስ ያልተለየችው፣ነባቢት ሕያዊት ለባዊት ነፍስ
የተለየችው ነው፡፡ ይህ ሥጋና ደም በንሥኣተ መንፈስቅዱስ፣ በህድረተ መንፈስ ቅዱስ፣ በመንፈስ ቅዱስ ቅብዕነት
የከበረ መሆኑን ለምእመናን ሁሉ ያስረዱልኝ፤እርስዎትም ይረዱልኝ
ኃይለ ቃል ሲጠቀስ የመጽሐፍ ገጽ ባይጠቀስ መልካም ነው፡፡ ምዕራፍና ቁጥር እንጂ፤ መጻሕፍት ከይዘታቸው አንጻር በገጽ ይለያያሉና፡፡
ይህ አጭር ጽሑፍ መታሰቢያነቱ ለአስተማሩኝ፣ በሃይማኖት ላጸኑኝ
ደናግላን አባቶቼ መምሕር ሰውአገኘሁ የአራቱ ጉባያት ሊቅ (ዘደብረ ወርቅ)
መሪጌታ ዘገየ (ዘቀዳች ኢየሱስ)
መምሕር ይኄይስ ወርቄ የአራቱ ጉባያት መምሕር (ዘደብረ ወርቅ)
መሪጌታ ፈንታ ገብሬ የድጓና የዜማ መምህር (ዘመርጡለ ማርያም)
መሪጌታ ፈንቴ ውቤ የድጓና የዜማ (ዘመርጡለ ማርያም)
መሪጌታ ወልዴ ውሂብ የቅኔ፤ አገባብና የአራቱ ጉባያት መምሕር(እነዘባ ማርያም)
ማስተዋሻነቱ ለውድ ልጄ ትንሣኤ ሄኖከ ፈንታ
ዲያቆን አበበ ቢያዝን
ጸሃፊውን እና አስተማሪዎችን አመሰኛለሁ ክብር ይስጥልኝ
አንድ ቀን ዕጠቀመዋለሁ በድጋሚ አመሰኛለሁ ይቀመጥ

12/04/2021

በምስራቅ ጎጃም ኦርቶዶክሳዊ ህዝብ ላይ የተሸረበ ሴራ እና መዘዙ

የአማራ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በምስራቅ ጎጃም ህዝብ ሃይማኖታዊ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት አቡነ ማርቆስን አስመልክቶ ለሲኖዶስ የጻፈውን ደብዳቤ ተከትሎ በምስራቅ ጎጃም ኦርቶዶክሳዊ ህዝብ ላይ ሌላ ሴራ ታቅዷል ።

ሴራውን ያቀዱት በማህበረ ቅዱሳን አገልጋይነታቸው እና የምስራቅ ጎጃም ህዝብ ጠላትነታቸው የታወቁት በዋናነት አቡነ ዲዮስቆሮስ ፣አቡነ ኤርምያስ እና የሲኖዶሱ ፀሐፊ አቡነ ዮሴፍ ናቸው። እነዚህ ጳጳሳት ¡ በምስራቅ ጎጃም ህዝብ ላይ የሸረቡትን ሴራ ወደ ፍጻሚ ለማድረስ ያላቸውን ፍላጎት ይፋ ያደረጉት ተረኛ የቋሚ ሲኖዶስ አባልነታቸውን አጋጣሚ ተጠቅመው መጋቢት 17/2013 ዓ.ም ባደረጉት የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ በወሰኑት ውሳኔ ላይ ነው ። በእለቱ ከተደረገው የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ እና ውሳኔ መረዳት እንደሚቻለው አቡነ ማርቆስ ተነስተው በምትካቸው የአካባቢው ተወላጅ ያልሆነ ጳጳስ እንዲመደብ ህዝቡን የመናቅ ሃሳብ ቀርቧል። ይህን ሀሳባቸውን ለግንቦት ሲኖዶስ አቅርበው እስኪያስወስኑ ድረስ ደግሞ አቡነ ማርቆስ ሀገረ ስብከታቸውን ለቀው በጠቅላይ ቤተክህነት እንዲቀመጡ እና ሀገረ ስብከቱን በጉልበት በማሸግ ለሁለት ወራት ስራ ያስፈቱ፣ የጳጳሱን መኖሪያ ቤት አጥር ሰብረው ገብተው ጳጳሱን ለመግደል ሙከራ ሲያደርጉ በፀጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ ተይዞ ያሉ ከስራ የታገዱ ነውጠኛ ሰራተኞች ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ወስነዋል። ማህበረ ቅዱሳን ሰሞኑን በቴሌብዥኑ ሲያደርገው የሰነበተው የጥላቻ ቅስቀሳ እና የሀሰት ፕሮፓጋንዳም የዚሁ የሴራው አካል ነው ። ይህ በምስራቅ ጎጃም ህዝብ ላይ የተሸረበ ሴራ በዋናነት ከሦስት ወገን የመነጨ ነው።

አንደኛው የምስራ ጎጃምን ህዝብ ዳግም መጠመቅ አለበት የሚል አቋም ይዞ ሲያጠምቅ የኖረው ዋነኛው ማህበረ ቅዱሳን ነው። ይህም ሰሞኑን ሲያደርገው ከሰነበተው የቴሌብዥን ፕሮግራሙ መረዳት ይቻላል።

ሁለተኛው የክልሉን ርእሰ መስተዳደር ጨምሮ በክልሉ መንግስት ባለስልጣን የሆኑ የማህበረ ቅዱሳን አባላት እና ደጋፊዎች ናቸው።
ሦስተኛ የዚሁ ማህበር አገልጋይ የሆኑ ጳጳሳት ናቸው።
የዚህ ሁሉ ውጤት ደግሞ ከዚህ በፊት ሲደረግ እንደነበረው የምስራቅ ጎጃምን ህዝብ በማፈን መናፍቅ ነህ ዳግም ተጠመቅ እያሉ ለማጥመቅ እና ይመሩኛል ብሎ የመረጣቸውን በቆጋ ገዳም ያሉ አባቶቹን ለማስወገዝ ነው።

በዚህ ሁሉ ሴራ ላይ ግን የምስራቅ ጎጃም ህዝብ የራሱን አቋም ይዟል
ይሄውም
አንደኛ ሰሞኑን ማህበረ ቅዱሳን በቴሌብዥኑ ሲያደርገው የሰነበተውን የጥላቻ እና የመከፋፈል የውሸት ፕሮፓጋንዳ ሲኖዶሱ መርምሮ እርምጃ የማይወስድ ከሆነ

ሁለተኛ አቡነ ማርቆስ ከምስራቅ ጎጃም የሚነሱ ከሆነ፣

ሶስተኛ በፈፀሙት ወንጀል የተባረሩ የሀገረ ስብከቱ ሰራተኞች ወደ ስራቸው ከተመለሱ የምስራቅ ጎጃም ህዝብ ከቤተክርስቲያኒቱ ተገንጥሎ የራሱን አስተዳደር እንደሚመሰርት ወደ አዲስ አበባ በመሄድ ለፓትርያሪክ ጽህፈት ቤት ለማሳወቅ ሰፊ ውይይት እያደረገ ነው።

ሌላው የክልሉ መንግስት አመራሮች በሃይማኖት ጣልቃ እየገቡ ለሚፈጽሙበት በደል ደግሞ በምርጫ ካርዱ ለመቅጣት ሀሳብ እየተንሸራሸረ ነው ።
አጋጣሚው ደግሞ በተሸረበው ሲራ መሠረት ሲኖዶሱ አቡነ ማርቆስን የሚያነሳ ከሆነ ምርጫው ከግንቦቱ ሲኖስ በኀላ ስለሆነ ክልሉን የሚመራው ፓርቲ በምስራቅ ጎጃም አብዛኞቹ ወረዳዎች የሚያጋጥመው ሽንፈት ከባድ ይሆናል ። የዚህ ሁሉ ውጤት ደግሞ ከግንቦት ሲኖዶስ ጋር የተያያዘ ነው። በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ደግሞ በተለይም ሲኖዶሱ አቡነ ማርቆስን አንስቶ የተባረሩ ሰራተኞችን ከመለሰ የምስራቅ ጎጃም ህዝብ ከቤተክርስቲያቲቱ እንደሚገነጠል አያጠራጥርም።

05/04/2021

የምስራቅ ጎጃም ኦርቶዶክሳዊ ህዝብ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ አቋሙን ያሳውቁለት ዘንድ ከየወረዳው ተወካዮችን መምረጡ ተገለፀ።

ተወካዮች ሲኖዶሱ ሰሞኑን ማህበረ ቅዱሳን በቴሌብዥን ዝግጅቱ በምስራቅ ጎጃም ህዝብ እና ሀገረ ስብከት ላይ ሲያሰራጨው የሰነበተውን የጥላቻ ፣ የስም ማጥፋት እና የመከፋፈል ተግባር በመመልከት በማህበሩ ላይ እርምጃ የማይወስድ ከሆነ እና አቡነ ማርቆስን ከምስራቅ ጎጃም የሚያነሳ ከሆነ የምስራቅ ጎጃም ህዝብ ከቤተክርስቲያኒቱ ተገንጥሎ የራሱን አስተዳደር እንደሚመሰርት ለሲኖዶሱ ለማሳወቅ ነው ።
ጉዞው የሚደረገው በ29 /08/13 ነው።
በጉዞው መሳተፍ ለምትፈልጉ 0922426375 ደውላችሁ መነጋገር ትችላላችሁ። ብለዋል አስተባባሪዎች።

05/04/2021

ታላቅ የህዝባዊ ንቅናቄ ጥሪ

ሰሞኑን ማህበረ ቅዱሳን በቴሌብዥን ፕሮግራሙ የምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን እና ህዝብ አስመልክቶ ሲያሰራጭ የሰነበተውን የውሸት ፣የጥላቻ እና የመከፋፈል ተግባር በማስመልከት እዲሁም ሲኖዶሱ በአቡነ ማርቆስ ላይ የያዘውን የመወላወል አቋም በመቃወም የምስራቅ ጎጃም ህዝብ ሕዝባዊ ንቅናቄ በማድረግ አቋሙን ለማሳወቅ መዘጋጀቱን በየወረዳው ያሉ አስተባባሪዎች አሳወቁ።
በዚህም መሠረት በ29/08/2013 ዓ.ም ከየወረዳው የተውጣጣ ህዝብ ወደ አዲስ አበባ በማምራት ለጠቅላይ ቤተክህነቱ አቋሙን ለማሳወቅ መርሐግብር መያዙን አስተባባሪዎች ገልፀዋል።

Address

Adama
Debre Mark'os
1212

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወልደ_አብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to ወልደ_አብ:

Shortcuts

Share

Category