Debay tilat gin werda education office

Debay tilat gin werda education office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Debay tilat gin werda education office, Education, Debre Mark'os.

29/10/2021
28/10/2021

1ሺህ 2 መቶ ተፈታኝ ተማሪዎችን ሀገር አቀፍ ፈተና ለማስፈተን የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ገለጸ ፡፡
በምስራቅ ጎጃም ዞን ደባይ ጥላት ግን ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክንዴ አያል ለወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በሰጡት መረጃ እንደገለጹት በ2013 የትምህርት ዘመን በመማር ላይ የነበሩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን እና የግል ተፈታኞችን ከጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው ሀገራዊ ፈተና ለማስፈተን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡ አቶ ክንዴ እንዳሉትም በዚህ ሀገራዊ ፈተና በማህበራዊ ሳይንስ 8 መቶ 16 ፤ በተፈጥሮ ሳይንስ ደግሞ 173 መደበኛ ተፈታኞች መኖራቸውን ገልጸው በግል ደግሞ በማህበራዊ ሳንስ 1መቶ 12 እና በተፈጥሮ ሳይንስ 176 በአጠቃላይ በመደበኛ እና የግል ተፈታኞች 1ሺህ 2 መቶ 77 ተማሪዎች መሆናቸውን ተናግረዋል ፡፡
በዚህ ሀገራዊ ፈተና ላይ ተማሪዎችን እንደ ሀገር ተወዳዳሪ ለማድረግ መምህራን ያልተሸፈኑ ትምህርቶችን እያከካሱ ፣የጥያቄ ወረቀቶችን እሰሩና ቤተ መጽሀፍት ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ክፍት በማድረግ ተማሪዎች አገልግሎት እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት አቶ ክንዴ ከዚህ በተጨማሪም ተማሪዎች በስነ ልቦና ዝግጁ እንዲሆኑ በሳይኮሎጂ መምህር የምክር አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
ፈተናው እንደ ወረዳ በ2 መፈተኛ ጣቢዎች ማለትም መደበኛ ተማሪዎች በቁይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የግል ተፈታኞች ደግሞ በቁይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይሰጣል ብለው የመፈተኛ ክፍሎች ፣ወንበሮች ዝግጁ እየተደረጉ ነው ከዚህም ባለፈ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን መከላከል የሚስችሉ ቁሳቁስ ዝግጁ እየተደረጉ ነው ብለዋል
አቶ ክንዴ አክለውም በባለፈው አመት ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የማለፍ ምጣኔው ዝቅተኛ የነበር ቢሆንም አንዳንድ ተማሪዎች ግን ከፍተኛ ውጤት አስመዝግበው ከሌሎች ጋር ተወዳዳሪ ለመሆን በቅተዋል ብለዋል ፡፡በዘንድሮው አመትም ተማሪዎች እራሳቸውን ለፈተናው አዘጋጅተው በመግባትና ወላጆች እና የትምህርት ባለድርሻዎች ደግሞ መኮራረጅ ሌብነት መሆኑን በማሳወቅ ደርሻ እንዳለባቸው አቶ ክንዴ አሳስበዋል ፡፡

17/09/2021

ለ2014 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤታቸው በመሄድ እንዲመዘገቡ የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ጥሪ አቀረበ፡፡
የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክንዴ አያል በመጀመሪያ እንኳን ለ2014 የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ በማለት የዘንድሮው የትህርት ዘመን አሸባሪው የህዋህት ቡድን በከፈተብን ጦርነት መካከል ሆነን የምንጀምረው ይሆናል ብለዋል፡፡
የትምርት ተቋማትም መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የትምህርት ስራዎችን አጠናክረን መስራት አለብን በማለት ከመምህር፣ከሱፐርቫይዘሮች እና ከርዕሰነ መምህራን ጋር በመሆን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ተናረዋል፡፡ አቶ ክንዴ እደተናገሩት በ2014 የትምህርት ዘመን 4 ሽኅ 951 ንጥር ቅበላ ፤30 ሺህ 720 ከ1 እስከ 8ኛ ክፍል በጥቅል ተሳትፎ እና ከ9ኛ እስከ 12 ኛ ክፍል ደግሞ 7ሺ 765ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ ለማምጣት በእቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው ብለዋል ፡፡
ምዝገበው መስከረም 3 ቀን 2014 ዓ.ም እንደተጀመረ የተናገሩት አቶ ክንዴ እስከ መስከረም 14/2014 ዓ/ም እንደሚካሄድም ገልጸዋል ፡፡ አቶ ክንዴ እንዳሉት እስከአሁን የተመዘገቡት ተማሪዎች ዝቅተኛ በመሆናቸው ተማሪዎች እና ሌሎች የትምህርት ባለድርሻ አካላት በወቅቱ ተማሪዎች እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አቶ ክንዴ አክለውም በተመደቡበት ትምህርት ቤት ላይ ያልተገኙ መምህራን ከወዲሁ በመግባት የተማሪዎችን ምዝገባ በወቅቱ ማካሄድ እንዳለባቸው እና ወላጆችም ለልጆቻቸው የጽህፈት መሳሪዎችን በማዘጋጀት ለትምህርት ምዝገባ መላክ እንዳለባቸው አሳስበው መደበኛ የ2014 ትምህርት በወረዳችን መስከረም 21 ቀን 2014 ዓ.ም ይጀምራል ብለዋል ፡፡

Address

Debre Mark'os
20

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debay tilat gin werda education office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category