21/08/2026
ለሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ከየተቋማቱ ለተውጣጡ የህዝብ ግንኙነት ፎካል ፐርሰን አባላት በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ወ/ሪት ኤፍራታ ሸንቁጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዙሪያ ያለብንን የቴክኖሎጂ እውቀት በማዳበር በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆን ይጠበቅብናል፤በተቋማችን የሚሰጠውን ስልጠና በተገቢው መከታተል ያስፈልጋል ብለዋል።
ስልጠናው በጽህፈት ቤቱ የአይ ሲቲ ባለሙያ አቶ ዘላለም ተስፋዬ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)ዙሪያ በተግባር የተደገፈ ስልጠና ሰጥቷል።
የስልጠናው ተሳታፊዎችም በበኩላቸው የሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI) ግንዛቤ ማስጨበጡና ከዘመኑ ጋር አብሮ እንድንዘምን ከማድረጉ ባለፈ ስራን የማቅለል ትልቅ አስተዋፅኦ ያለው ነዉ፤ አጠቃቀማችንን በማስተካከል የተሻለ ስራ ለመስራት የሚጠቅም ቢሆንም ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንዳያመዝን መጠንቀቅ ይገባል ብለዋል።