Debre Berhan Health Science College

Debre Berhan Health Science College Debre Berhan Health Science College is a college that trains ethical, qualified and competent middle

Debre Berhan Health Sciences College is one of the five health sciences colleges established in the Amhara region to address the shortage of health professionals in the region and in the country by training ethically trained and qualified middle level health professionals.
የደብረ ብርሃን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጤና ፖሊሲዉን ያማከለ በሙያዊ ስነምግባር ያታነፀ እና ብቃት ያላቸውን የመካከለኛ ደረጃ ጤና ባለሙያዎችን በማሰልጠን የክልሉን ብሎም በሃገሪቱ ያለውን የጤና ባለሙያ እጥረት ለመቅረፍ የሚሰራ በክልሉ ከተቋቋሙ 5 የጤና ሳይንስ ኮሌጆች አንዱ ሲሆን ይህንንም ለማሳካት በሙሉ አቅሙ እየሰራ ያለ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ነው፡፡

19/10/2025
የሃዘን መግለጫ የደብረ ብርሃን ጤና ሳይንስ ከዚህ በፊት በፋርማሲ ደፓርትመንት በመምህርነት ሲያስተምሩ የነበሩት መምህር እንግዳሸት ፈቃደ ባደረባቸው ህመም ምክንያት  በህክምና ሲረዱ ቆይተው ...
18/08/2025

የሃዘን መግለጫ

የደብረ ብርሃን ጤና ሳይንስ ከዚህ በፊት በፋርማሲ ደፓርትመንት በመምህርነት ሲያስተምሩ የነበሩት መምህር እንግዳሸት ፈቃደ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው በቀን 12/12/2017ዓ/ም ከዚህ አለም በድካም አርፈዋል።
መምህር እንግዳሸት ወደ ደብረ ብርሃን ዩንቨርስቲ እስከ ተዛወሩበት ግዜ ስራቸውን አክባሪ ጠንካራ መምህር ሰዉ አክባሪ ቅን ነበሩ የደብረ ብርሃን አስተዳደር ሰራተኞችና መምህራን ሰራተኞች ለቤተሰቡ ወዳጅ ዘመዶቹ በደረሰባችሁ መሪር ሃዘን መጽናናትን ይመኛል
የደ/ብ/ጤ/ሳ/"ኮሌጅ

የሃዘን መግሐጫ  የደ/ጤ/ሳ/ኮሎጅ የፋርማሲ መምህር የሆኑት አቶ ታደሰ ነጋሽ ባደረባቸዉ ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በቀን በ03/03/2015ዓ/ም ከዚህ አለም  በሞት ተለይተዋል ...
14/11/2022

የሃዘን መግሐጫ

የደ/ጤ/ሳ/ኮሎጅ የፋርማሲ መምህር የሆኑት አቶ ታደሰ ነጋሽ ባደረባቸዉ ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በቀን በ03/03/2015ዓ/ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል ።በመሆኑም የደ/ጤ/ሳ/ኮሎጅ መምህራን አስተዳደር ሠራተኞች የደረሰውን ህልፈት የተሠማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው ለጔዶኞቻቸው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን

የደ/ብ/ጤ/ሳ/ኮሎጅ

ደ/ብርሃን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በተለያየ ሙያ ለ21ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ፡፡ደ/ብርሃን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ሐምሌ 16/2014 ዓ.ም. የተማሪዎች የምረቃ በዓል አከናውኗል፡፡የኮ...
05/08/2022

ደ/ብርሃን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በተለያየ ሙያ ለ21ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ፡፡
ደ/ብርሃን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ሐምሌ 16/2014 ዓ.ም. የተማሪዎች የምረቃ በዓል አከናውኗል፡፡የኮሌጁ መመህራንና ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች እና የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት ነው የምርቃት ስነስርአቱ የተካሄደው፡፡ የኮሌጁ ምክትል ዲን መምህር ሔኖክ ዲታ ባደረጉት ንግግር በመከላከል ላይ የተመሠረተውን የሀገራችን የጤና ፖሊሲ ከመተግበር አንጻር ኮሌጁ ለሀገራችን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን መሆኑን ገልጸዋል።
ኮሌጁ በ2014 ዓ.ም በነርሲንግ ፣ በፋርማሲ ፣ በሚድዋይፍ ፣ በላብራቶሪ ፣ በኢንቫይሮመንታል ኸልዝ ፣ በጀነሪክና አፕግሬድ ጤና ኤክስቴንሽን እና በአንስቴዥያ ሙያ በመደበኛ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 726 የጤና ባለሙያዎች አስመርቋል።
ከነዚህ ተመራቂዎች ውስጥ 90 በመቶ ሴቶች መሆናቸውንና የዛሬዎቹን ሳይጨምር ከዚህ በፊት በተለያዩ ዙሮች 5 ሺህ 728 ተማሪዎች በማሰለጠን ለሥራ አሰማርቷል ሲሉ የኮሌጁ ምክትል ዲን መምህር ሔኖክ ዲታ ተናግረዋል።
የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል ጤና መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ፀዳለ ሰሙንጉሥ እንደተናገሩት የጤናው ሴክተር መከላከልን መሠረት ያደረገ ፓኬጅ በመተግበር ሞዴል የሆኑ የጤና ተቋማትና በመገንባትና የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን በማሰማራት ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ በዚህም እናቶች ከቅድመ ወሊድ ጀምሮ በጤና ተቋማት እንድወልዱ በማድረግ በወሊድና ተያያዥ ምክንያቶች እንዳይሞቱ በማድረግ የእናቶችንና ሕጻናትን ሞት በመቀነስ የድርሻውን እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን የዛሬ ተመራቂዎችም ለጤናው ዘርፍ ተጨማሪ አቅም ናችሁ ሲሉ የክብር እንግዳዋ ተናግረዋል።
ተመራቂዎች ከኮሌጁ በትምህርት ያገኛችሁትን ዕውቀት ከምርቃት በኋላ በተከበረው የጤና ሙያ ወደሥራ ስትሰማሩ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ዘር ፣ ብሔርና ቀለም ሳትለዩ ርኅራኄና ትህትና የተሞላበት አገልግሎት በመስጠት የገባችሁትን ቃለ መሐላ ተግባራዊ ማድረግ አለባችሁ በማለት ወይዘሮ ፀዳለ አሳስበዋል።

የደ/ብርሃን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ግንቦት 15/2013 ዓ.ም. የኮሌጁ መመህራንና ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች እና የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት የተማሪዎች የምርቃት ስነስርአ...
03/06/2021

የደ/ብርሃን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ግንቦት 15/2013 ዓ.ም. የኮሌጁ መመህራንና ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች እና የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት የተማሪዎች የምርቃት ስነስርአት አካሂዷል፡፡
የኮሌጁ ዲን አቶ ማሙዬ መንገሻ ባደረጉት ንግግር ትምህርት የአንድ ሀገር ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ እድገት ለማምጣት የሚረዳ ቁልፍ መሣሪያ በመሆኑ ኮሌጃችንም ይህንን በመረዳት ጥራት ያለው፣ደረጃውን የጠበቀና ውጤት ሊያመጣ የሚችል ሥልጠና በመስጠት ብቃት ያላቸው ህብረተሰቡን በቅንነትና በታማኝነት የሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎችን ለማፋራት አላማዬ ብሎ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡
ኮሌጁ በ2013 ዓ.ም በተለያየ ጊዜ 47 የፋርማሲ፣47 የነርስ፣47 የሚድዋይፍሪይ እና 39 የጤና መረጃ ባለሙያዎችን ያስመረቀ ሲሆን በዛሬው ዕለት ለ3 ተከታታይ ዓመታት ያሰለጠናቸውን 242 የደረጃ 4 ጤና ኤክስቴንሽን እና 94 የኣካባቢጤና አጠባበቅ ወይም የኢንቫይሮሜንታል ባለሙዎችን በድምሩ 336 የጤና ባለሙያዎችን የሚያስመርቅ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 81 ፐርሰንት የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡
በምረቃ ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማት የተሰጠ ሲሆን በመጨረሻም ውድ ተመሪቂዎች በኮሌጁ ቆይታችው ባገኙትት እውቀት ላይ የራሣችውን ጥረት በማከል ከሁሉም በላይ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ለመንከባከብና የጤና ችግሮችን ለመቅረፍ ደከመኝ ሰለቸኝ ሣይሉ ሙያችው በሚፈቅድላችው ሁሉ በቅንነት፣በታማኝነት እንዲያገለግሉ የቃለ-መሃላ ስነ ስርዓት የተካሄደ ከመሆኑ በተጨማሪ የእለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት የሰ/ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፀዳለ ሰሙንጉስ ይህንኑ ለተመራቂዎች በአደራ ጭምር አሳሰበው መጪው ዘመን ጥሩ የሥራ ጊዜ እንዲሆንላችሁ ተመኝተዋል፡፡
በአጠቃላይ የመማር ማስተማር ሂደቱን ከግቡ እንዲደርስ ድጋፍ ላደረጉልን መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ኮሌጁ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል፡፡

Address

Debre Berhan
Debre Birhan

Opening Hours

Monday 02:00 - 17:00
Tuesday 02:00 - 05:00
Wednesday 02:00 - 05:00
Thursday 02:00 - 17:00
Friday 02:00 - 17:00

Telephone

+251116815190

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debre Berhan Health Science College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Debre Berhan Health Science College:

Shortcuts

Share