Hawaz

Hawaz in this page give different education program and missionary lessons and holy learning

18/09/2022

መሞታችን አይቀርምና ከእነዚሁ ሁሉ እንራቅ

▪አትቅና እንደ ቃየል ወንድምህን
ትገላላህ። ዘፍጥረት 4÷1
ቃየል ወንድሙን የገደለው ስግብግብነት ነበር

▪ክፋ ባልንጅራን አትያዝ እንደ ሶምሶን በጠላት እጅ ትወድቃለህ። ፦ መጽሐፈ ምሳሌ 16÷ 15

▪ ዘፍጥረት 3÷1-8 በአባትህ አትሳቅ እንደ ካም ትረገማለህ። እንደ ሴምና ያፌት እንሁን ዘፍጥረት 9÷20 -21

አትመኝ፦እንደ አዳም የዲብሎስ ባሪያ ትሆናለህ።ዘፍጥረት 3÷1-8

እግዚአብሔር ለእኛ አንድ ነገር ሲሰጠን ወይም ሲያድርግልን እንደሚጠቅመን ያውቃል አወቆም ይሰጠናል

▪ እኛ ግን ያለን ትተን የሌለን እንመኛለን ከንቱነት

በሐሰት አትመስክር፦ እንደ ሐማ ባዘጋጀኸው ጉድጓድ ትገባለህ።
፦ መጽሐፈ አስቴር 7÷1

አትስከር አዕምሮ አሳጥቶ የማይገባ ሥራ ትሠራለህ። ዘፍጥረት 19÷30-38

አትዘሙት እንደ ሰሎሞን አምላክህን አስረስቶ ጣዖትን እንድታመልክ ያደርግሃል። ከዚህ ይሰውረን መጽሐፍ ነገሥት ካልዕ 1 11÷1-8

▪ ትዕቢተኛ አትሁን ፦እንደ ሰናክሬም ትወድቃለህ።መጽሐፈ ነገሥት
ካልዕ 2 19÷35

▪ ገንዘብን አትውደድ እንደ ይሁዳ ጌታህን ያስክድሃል። ማቴዎስ ወንጌል፦ 26÷14-16

ቀንድ ነገር ቢሆንም ገንዘብ በመውደድ ከስንት ነገር ርቀናል ከሃገራችን ከቤተሰባችን ከጓደኞቻችን ከልጆቻችን ሞልቶ በማይ ሞላ ሂወታችን......

ሥልጣንን አትውደድ፦እንደ አቤሴሎም በአባትህ ላይ ትነሣለህ፦ መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 2 15÷13-17

ዓለምን አትመልክት፦እንደ ሎጥ ሚስት የጨው ዐምድ ሆነህ ትቀራለህ፦ ዘፍጥረት 19÷ 22-23 1ኛ ቆ.ስ 2፥5

ማመናችሁ በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን።
1ኛ ቆ.ስ፦ 2፥15

‹‹. . . ሕይወት አዙሪት ናት፡፡ ረጅም ርቀት የተጓዝክ ቢመስልህም የምትጨርሰው ከጀመርክበት ነው፡፡ ራቁትክን ትወለዳለህ እርቃንህን ወደ መቃብር ትወርዳለህ፡፡

በጥርስ አልባው ድድህ እየጋጥክ ትጀምራለህ ፤ ጥርሱን ባረገፈው ድድህ እያልጎጠጎጥክ ትጨርሳለህ፡፡ ዘመንም ተምኔታዊ ነው፡፡ መስከረም ጥቅምት ብሎ ያስጀምርህና መስከረም ብሎ ያመጣብሀል፡፡

ሰኞ ማክሰኞ ብለህ ተጉዘህ እንደገና ሰኞ ትላለህ፡፡ ሕይወት አዙሪት ናት መጀመርያህ መጨረሻህ ነው፡፡ የጀመርክበት አትርሳ መጨረሻህ ነውና የጀመርክበትን አትናቀው፤ ትጨርስበታለህና፡፡

ተራ ሰው ሆነህ ትጀምራለህ ተምረህ ዕውቀት ብትጨምር ፣ ነግደህ ሀብት ብታገኝ ፣ ክቡረ ክቡራን ሆነህ የወርቅ ካባ ብትለብስ የምትጨርሰው እንደ ተራ ሰው አፈር ለብሰህ ነው፡፡››

‹‹ልብ በል! በማወቅ ትጀምራለህ በመዘንጋት ትጨርሳለህ፡፡ ዕውቀት አላመጣህምና ዕውቀት ይዘህ አትሔድም፡፡ በለቅሶ ትጀምራለህ በጭንቅ ትጨርሳለህ፡፡

በሰው እቅፍ ትጀምራለህ በሰው ሸክም ትጨርሳለህ፡፡ ልደትህ ከሞትህ በምን ይለያል? ሞትህስ ከልደትህ በምን ይከፋል?

ሕይወት መጀመርያና መጨረሻዋ አንድ ነው፡፡ ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም፡፡ ልብ በል የዓለም ከንቱነት ግን ውበቷ ነው፡፡

20/01/2022

አንዲት አማናዊት ጥምቀት"
" አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤"
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:5)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖት ምዕመን መሆን ማለት ምስጢረ ጥምቀት መዳናችን የሚፈጸምበት ፥ ረቂቁን መንፈሳዊ ልደት ተወልደን መንግስተ ሰማያትን ገንዘብ የምናደርግበት ምስጢር መሆኑን ማመን መታመን ማለት ነው፡፡

ምስጢረ ጥምቀት ከአምስቱ አዕማደ ምስጢራት መካከል አንዱ ነው፡፡ ምስጢረ ጥምቀትን በተመለከተ የዘላለም ህይወት የሚገኝበትን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ቅድስት ቤተክርስቲያን በፍጹም ጥንቃቄ ለልጆቿ ታስተምራለች፡፡

ምስጢረ ጥምቀትን የመሠረተልን ለሥም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ አምላካችን በጥምቀቱ ፦

፩.በተግባር በመጠመቅ ጥምቀት ለፍጥረታዊው ሰው አስፈላጊ መሆኑን

፪.በውኃ በመጠመቅ ማያት [ ውሆች ] ዳግመኛ የምንወለድባቸው ማኅፀኖች ይሆኑ ዘንድ ኃይልን ሰጣቸው

፫.ጌታችን መጠመቅ ሳይኖርበት ስለ እኛ ሲጠመቅ ምስጢረ ሥላሴ ተገልጦ የባህርይ አባቱ አብ ልጅነቱን እንደመሰከረለት እኛም ስንጠመቅ ከእርሱ ዳግመኛ መወለዳችንና የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን ይመሠክርልናል፡፡

፬.እርሱ ሲጠመቅ "ሰማያት ተከፈቱ" እንደተባለ በጥምቀቱ አገራችን በሰማይ መሆኑን የአገራችንን በር ከፍቶ አሳየን ፤ የምንጠመቀው ያንን ሰማያዊ ሀገር ለመውረስ የሚያበቃ ልጅነት ለማግኘት መሆኑን በተግባር አሳየን፡፡

በመሆኑም በአማናዊቷ ጥምቀት የሚገኘው ፦

፩.ሥርየተ ኃጢአት [ መዳን ]

ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ለማዳን ከፅንሠቱ ጀምሮ እስከ ዕርገቱ ድረስ ያደረገው ነገርና የሰጠው ጸጋ ፣ እንዲሁም በዕለ ዓርብ በመስቀል ላይ የቆረሰው ሥጋውና ያፈሰሰው ደሙ ፣ ሞትን ድል አድርጎ መነሣቱ ሁሉ ለእያንዳንዳችን የሚደርሰን በጥምቀት አማካኝነት ነው፡፡

በመስቀል ላይ ሳለም ሐራዊ ጎኑን በጦር በወጋው ጊዜ ከቅዱስ ገቦው [ጎኑ] ውኃና ደም እንዲወጣ የፈቀደው ለዚህ ነበር ፣ ከጎኑ በተገኘው በውኃና በደሙ ልጅነትንና ሥርየተ ኃጢአትን እንድናገኝ ነው፡፡ በማየ ገቦዎ እንጠመቃለን ፣ ደሙን ደግሞ በምሥጢረ ቁርባን እንቀበለዋለን፡፡ ጥምቀት የኃጢአት ሥርየት እንደሚያሰጥ ቅዱስ መጽሐፍ ፦
"ንስሐ ግቡ ፣ ኃጢአታችሁም ይሠረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፡፡" (ሐዋ.፪፥፴፰)

፪.የእግዚአብሔርን ልጅነት ማግኘት ዳግም ልደት

"ኢየሱስም መልሶ። እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።..
ኢየሱስም መለሰ ፥ እንዲህ ሲል። እውነት እውነት እልሃለሁ ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።

ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው ፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።" [ዮሐ.፫፥፫] በማለት በጥምቀት ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት የማይችል መሆኑን በአምላካዊ ቃሉ አስተምሮናል፡፡

፫.መንግሥተ ሰማያትን መውረስ

በጥምቀት በምናገኘው የእግዚአብሔር የልጅነት ጸጋ የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ የምንችል ባለ ተስፋዎች እንድንሆን ያደርገናል፡፡ እግዚአብሔር የሰጠንን ጸጋ ለመቀበል በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጆች ሆነን ካልተወለድን በስተቀር ከእናት ከአባት በተወለድነው ተፈጥሯዊና ሥጋዊ ልደት መንፈሳዊና ሰማያዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ አንችልም፡፡ (ዮሐ.፫፥፫)

፬.ከክርስቶስጋር አንድ መሆን ፣ በሞቱና በትንሣኤው መተባበር

ጥምቀት የጌታችንን ሞቱንና ትንሣኤውን ማመናችንን በተግባር

10/12/2021

Address

Street
Debre Birhan
2242

Telephone

+251901225774

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hawaz posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Hawaz:

Shortcuts

Share