06/05/2023
የወር አበባ እያየሽ እርግዝና ሊፈጠር ይችላል?
አንድ ሴት በወር አበባ ዑደት አጋማሽ አካባቢ የመፀነስ ዕድሏ ከፍተኛ ነው። ይህ የዑደት ደረጃ የእርግዝና መስኮት (ፈርታይል ዊንዶ) (Fertile Windows) ይባላል።
[የእርግዝና መስኮት (ፈርታይል ዊንዶው) (Fertile Window)):- ማለት በወር አበባ ዑደትሽ ወቅት የመፀነስ እድልሽ ከፍተኛ የሚሆንበት ጊዜ ማለት ነው። ለአብዛኛዎቹ ሴቶች ይህ ጊዜ ኦቪውሌሽን ከመከናወኑ በፊት ያሉትን 5 ቀኖች፣ ኦቪውሌሽን የሚካሄድበትን ቀን እና ከኦቪውሌሽን ማግስት ያለውን አንድ ቀን ያጠቃልላል]።
ከእርግዝና መስኮት በፊት እና በኋላ የመፀነስ እድልሽ በጣም አነስተኛ ነው፤ ነገር ግን በእነዚህ ወቅቶች መጸነስ ትችያለሽ። በተጨማሪም ሊታሰብባቸው የሚገቡ በርካታ ምክንያቶች አሉ።
በዚህ ጽሑፍ የወር አበባ በምታይበት እና በወር አበባ ዑደት ወቅት ባሉ ሌሎች ጊዜዎች እርጉዝና የመፈጠር እድልን እንመለከታለን።
✅ በወር አበባዎ ወቅት እርጉዝ መሆን ይችላሉ?
አንድ ሴት በማንኛውም ጊዜ ማርገዝ ትችላለች። ይሁን እንጂ ብዙውን ጊዜ እርግዝና የሚፈጠረው እንቁላል በሚለቀቅበት (በኦቪውሌሽን) ጊዜ ነው።
አማካይ የወር አበባ ዑደት 28 ቀናት ነው።
[የወር አበባ ዑደት (Menstrual Cycle):- ማለት የአሁኑ የወር አበባሽ የመጣበት የመጀመሪያ ቀን እና የሚቀጥለው የወር አበባሽ የሚመጣበት የመጀመሪያ ቀን መካከል ያለው የጊዜ ልዩነት ነው።]
ኦቭዩሽን አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰተው የወር አበባሽ ካቆመ ከ12-14 ቀናት በኋላ ነው።
በኦቪውሌሽን ወቅት፤ እንቁላሉ የእንቁላል ከረጢትን (O***y) ትቶ የወንዱ የዘር ፍሬ ፈርቲላይዝ ማድረግ ወደሚችልበት ወደታች ወደ ማህፀን ቱቦ (Fallopian Tube) ጉዞውን ያደርጋል።
እንቁላሉ ከኦቪውሌሽን በኋላ ሊቆይ የሚችለው ለ 24 ሰዓታት ብቻ ነው። በዚህም ምክንያት፤ እርግዝና እንዲከሰት በእነዚህ 24 ሠዓት ውስጥ የወንድ የዘር ፍሬ (s***m cell) ጋር መገናኘት አለበት። ከዚያም እንቁላሉ ወደ ማህጸን ይጓዛል።
✅ በወር አበባ ዑደት ወቅት እርጉዝ የመሆን እድልሽ ምን ያህል ነው?
እ.ኤ.አ. በ 2018 በተደረገ ጥናት አንድ ሴት በወር አበባ ዑደቷ ከ8 ኛው እስከ 13 ኛው ቀን መካከል የመፀነስ እድሏ ከፍተኛ ነው። ይህ ማለት አንድ ሴት የወር አበባ በምታይበት ወቅት የመፀነስ እድሏ ዝቅተኛ ነው።
ይሁን እንጂ በእነዚህ ሶስት ዋና ዋና ምክንያቶች የተነሳ ይህን ያህል ቀላል አይደለም:-
1️⃣ የአንድ ሴት የወር አበባ ዑደት ርዝመት (Cycle Length)
2️⃣ በእያንዳንዱ ወር ኦቪውሌሽን የሚከሰትበት የጊዜ ልዩነቶች
3️⃣ የወንድ የዘር ፍሬ (ስፐርም) በሰውነት ውስጥ ለምን ያህል ጊዜ በሕይወት ይቆያል የሚሉት ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው።
💎 የወር አበባ ዑደት ርዝመት
የወር አበባ በየ 21-35 ቀናት የሚመጣ ከሆነ አሁንም "መደበኛ" ዑደት ነው ሊባል ይችላል። ስለዚህ የዑደት ርዝመት በተለያዩ ሴቶች መካከል በእጅጉ ይለያያል።
አጭር የወር አበባ ዑደት ያላቸው ሴቶች ረዘም ያለ ዑደት ካላቸው ሴቶች ይልቅ ለወር አበባ መምጫ ጊዜያቸው ተጠግተው ኦቪውሌት ያደርጋሉ (እንቁላል ይለቃሉ)።
💎 የኦቪውሌሽን ጊዜ
በመጀመሪያ ኦቪውሌሽን ለሚለው ቃል የአማርኛ ትርጓሜ እንስጠው።
[ኦቪውሌሽን (Ovulation):- ማለት በሴቶች የወር አበባ ዑደት ደረጃ ውስጥ ከአንዱ የእንቁላል ከረጢት (One of the ovaries) እንቁላል የሚለቀቅበት (የሚወጣበት) ሂደት ነው። በአጠቃላይ፤ ይህ ሂደት የሚቀጥለው የወር አበባ ከመምጣቱ ከሁለት ሳምንት በፊት ይከሰታል።]
የወር አበባ ዑደት ርዝማኔ እና የኦቪውሌሽን ትክክለኛ ጊዜ ባላቸው ሰፊ ልዩነት ምክንያት አንድን ሴት የማርገዝ እድሏ ከፍተኛ የሆነበት ጊዜ (Fertile Period) ላይ ነች ብሎ ለመናገር ይከብዳል።
አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት፤ እንቁላል ከመለቀቁ በፊት ባለው ቀን የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸም እና ወሩን ሙሉ (በወር አበባ ሙሉ ዑደት ውስጥ) በተደጋጋሚ በዘፈቀደ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ፤ ተመሳሳይ የመፀነስ እድል እንዳላቸው አሳይተዋል።
💎 የወንድ የዘር ፍሬ ሚና
የወንድ የዘር ፍሬ (ስፐርም) በሰውነት ውስጥ ከ3-5 ቀናት በህይወት ሊኖሩ ይችላሉ። ይህም ማለት አንድ ሴት እንቁላል ከመልቀቋ 5 ቀናት በፊት የግብረ ሥጋ ግንኙነት ብታደርግም ልታረግዝ ትችላለች።
ስለዚህ በወር አበባ ወቅት እርግዝና ሊፈጠር ይችላል፤ ነገር ግን ያለመሆን እድሉ በጣም ከፍተኛ ነው። (It's possible to become pregnant during the period, it is unlikely).
✅ ከወር አበባዎ በፊት ወይም በኋላ ወዲያው ማርገዝ ይቻላል?
ብዙውን ጊዜ የእርግዝና መስኮት (ፈርታይል ዊንዶው) (Fertile Window) በአንድ ሴት የወር አበባ ዑደት አጋማሽ ላይ ይከሰታል።
ይህ መስኮት እንቁላል ከመውጣቱ (ከመለቀቁ) ጥቂት ቀናት በፊት የሚቆይ ሲሆን እንቁላል ከተለቀቀ (ከወጣ) ከአንድ ቀን በኋላ ያበቃል። በዚህ ወቅት ሴቶች የመፀነስ እድላቸው ከፍተኛ ነው።
በዚህም ምክንያት ሴቶች የወር አበባቸው ከመጀመሩ በፊት ባሉት ቀናት የመፀነስ እድላቸው አነስተኛ ነው። ነገር ግን ይህ ትክክል የሚሆነው የወር አበባቸው መደበኛ ለሆነ እና የ28 ቀን የወር አበባ ዑደት ርዝማኔ ላላቸው ሴቶች ነው።
ይሁን እንጂ አንድ ሴት ከወር አበባዋ በኋላ ወዲያውኑ ልታረግዝ ትችላለች። ይህ የሚሆንበት ምክንያት፤ የወንድ የዘር ፍሬ ከግብረ ሥጋ ግንኙነት በኋላ እስከ 7 ቀናት ድረስ እንቁላል ማዳበር (ፈርቲላይዝ ማድረግ) ስለሚችል ነው።
አጭር የወር አበባ ዑደት ያላት ሴት ከወር አበባዋ በኋላ ወዲያው የግብረ ሥጋ ግንኙነት ብትፈጽም እና እንቁላል ቀደም ብሎ የተለቀቀ ከሆነ፤ እንቁላል ከወንድ የዘር ፍሬ ጋር እንዲገናኝ ሴቷ በፍጥነት እንቁላል ልትለቅ ትችላለች (Ovulate Quickly)።
✅ ስለ ኦቭዩሽን ተጨማሪ መረጃ
ብዙ ሴቶች የወር አበባ ማየት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ እስከ ማረጥ (እርጂና) ድረስ በመደበኛነት እንቁላል ይለቃሉ (በመደበኛነት ኦቪውሌት ያደርጋሉ)፤ ነገር ግን ይህ ሁልጊዜ አይደለም።
የአንድ ሴት የወር አበባ ዑደት ርዝማኔ እና መደበኛነት በህይወት ዘመኗ ሙሉ ሊለያይ ይችላል። እናም በእያንዳንዱ የወር አበባ ዑደቷ ኦቪውሌት የምታደርግበት ጊዜ (እንቁላል የምትለቅበት ጊዜ) እንዲሁ የተለያየ ሊሆን ይችላል።
በተጨማሪም ኦቭዩሽን (የእንቁላል መለቀቅ) ከማረጥ (Perimenopause) በፊት መደበኛ ያልሆነ መሆኑ የተለመደ ነው። ይህ ከማረጥ በፊት ያለው ጊዜ ነው።
✅ የሚከተሉት ምክንያቶች መደበኛ ያልሆነ የኦቪውሌሽን ጊዜ እና የወር አበባ ላይ ተጽዕኖ ያደርጋሉ:-
🔸ማጨስ
🔸ከመጠን ያለፈ ውፍረት
🔸በሽታዎች (ህመሞች)
🔸ጭንቀት
🔸በእንቅልፍ ሠዓት እና በሥራ ፕሮግራሞች ላይ ለውጦችን ማድረግ።
👉 የሚከተሉትን ዘዴዎችና መሳሪያዎች በመጠቀም የኦቪውሌሽን ቀንዎን መከታተል ይችላሉ።
🔹የእርግዝና ሰንጠረዦችን መጠቀም (Free Fertility Charts)
🔹በየቀኑ በእረፍት ጊዜ የሰውነታቸውን የሙቀት መጠን መለካት እና እንቁላል መለቀቁን (Ovulation) የሚጠቁሙ ለውጦችን መፈለግ
🔹የእርግዝና መቆጣጠሪያዎችን በመጠቀም የሉቲናይዚንግ ሆርሞን (Luteinizing Hormone) መጨመርን ለማረጋገጥ መሞከር
🔹የስማርት ስልክ አፕሊኬሽኖችን በመጠቀም ሳይንሳዊ ግምገማዎችን በማድረግ መከታተል ይቻላል።
✅ የወሊድ መከላከያዎች ተጽእኖ
የእርግዝና መስኮት (Fertile window) ተለዋዋጭ ባህሪን ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ እርጉዝ መሆን የማይፈልጉ ሴቶች የወሊድ መከላከያዎችን መጠቀም አለባቸው።
ጥምር የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒኖች የእንቁላል መለቀቅን (ኦቪውሌሽን) እና እርግዝና እንዲቆም (እንዳይኖር) ያደርጋሉ።
አንዳንድ የእርግዝና መከላከያ መድሃኒቶች የአንድን ሴት የወር አበባ ኡደት እንዲዛባ ወይም ከነጭራሹ እንዲቆም ያደርጋሉ።
✅ ማጠቃለያ
በወር አበባ ወቅት አንድ ሴት ማርገዝ ትችላለች፤ ነገር ግን የመሆን እድሉ እጂግ በጣም አነስተኛ ነው። (ምንም እንኳን በወር አበባዋ ወቅት የመከሰት ዕድሉ በጣም ያነሰ ቢሆንም፤ አንድ ሴት በወር አበባ ዑደቷ ወቅት በማንኛውም ጊዜ ልታረግዝ ትችላለች።)
በወር አበባ ጊዜ ወይም ከወር አበባ በኋላ የመፀነስ እድል የሚወሰነው:-
▪️የግብረ ሥጋ ግንኙነት በመፈጸም
▪️የወር አበባሽ ርዝመት እና
▪️በወር አበባ ዑደት ውስጥ እንቁላል የሚለቀቅበት ትክክለኛ ቀን (Exact Ovulation Day)።
እነዚህ ሶስት ምክንያቶች የእግዝና መስኮትን (Fertility Window) ትክክለኛ ጊዜ እና ቆይታ ለመተንበይ አስቸጋሪ ያደርጉታል።
መልካም ጤንነት!!
ምንጭ:- Medical news today
ለበለጠ የጤና መረጃ:
የ YouTube ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ:
https://youtube.com/
የፌስቡክ ገጻችንን ላይክና ሸር ያድርጉ:
https://www.facebook.com/EthioTena