Debre Berhan University

Debre Berhan University Debre Brehan University is one of the thirteen New Universities which was established in 1999 E.C

ማስታወቂያየ ኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት በሚሰጥባቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ  ደረጃ ት/ቤቶች የ9ኛና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። በመሆኑም በልዩ አዳ...
12/08/2026

ማስታወቂያ

የ ኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት በሚሰጥባቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የ9ኛና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። በመሆኑም በልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ተመዝግባችሁ ለመማር ፍላጎቱ ያላችሁና መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች በዚህ ሊንክ https://sbs.moe.gov.et/apply መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

✍️ ነጻ የትምህርት እድሉ የሚሰጣቸው ጥቅሞች
👉 ሙሉ የትምህርት ክፍያ ሽፋን
👉 የመኝታና የምግብ አገልግሎት
👉 የተሟላ እና ልዩ ሥርዓተ ትምህርት የሚከተል ጥራት ያለው ትምህርት
👉 ምቹ የመማሪያ አካባቢ
✍️ትምህርት የሚሰጥባቸው ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች
✍️ 9ኛ እና 10ኛ ክፍል
👉 ቡኢ ልዩ አዳሪ
👉 ጅግጅጋ ልዩ አዳሪ
👉 ጋምቤላ ልዩ አዳሪ
👉 ወሊሶ ልዩ አዳሪ
👉 ቦንጋ ልዩ አዳሪ
✍️ 9ኛ ክፍል ብቻ
👉 አርባ ምንጭ ልዩ አዳሪ
👉 ድሬዳዋ ልዩ አዳሪ
👉 አሶሳ ልዩ አዳሪ
👉 ባህር ዳር ልዩ አዳሪ
የመመዝገቢያ መስፈርቶች
✍️ ለ9ኛ ክፍል ተመዝጋቢዎች
👉 የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አማካይ ውጤት 85 በመቶ እና በላይ አማካኝ ውጤት ያለው/ያላት እንዲሁም በእንግሊዝኛና በሂሳብ ትምህርቶች 80 እና በላይ ያመጣ/ያመጣች ።
👉 ጥሩ ስነ -ምግባር ያለው/ያላት

✍️ ለ10ኛ ክፍል ተመዝጋቢዎች
👉በ2017 የትምህርት ዘመን በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 70 እና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች
👉በ9ኛ ክፍል ትራንስክሪብት 85 በመቶና በላይ አማካኝ ውጤት ያመጣ/ያመጣች እንዲሁም በእንግሊዝኛ እና ሂሳብ ትምህርት ዓይነት 80 በመቶና በላይ ያመጣ/ያመጣች።
✍️ የምዝገባ ሁኔታ
👉 ባሉበት በበየነ መረብ ( Online) ይመዝገቡ፡_ https://sbs.moe.gov.et/apply
✍️ መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች ምዝገባችሁን ባላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የመመዝገቢያ ፖርታል በኦንላይን መመዝገብ እና አስፈላጊ የተባሉ መረጃዎችን ማያያዝ ይጠበቅባችኋል
✍️ ምዝገባው እስከ ነሃሴ 15/2018 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል።
✍️ ለፈተና የሚቀርቡ ተማሪዎች ዝርዝር እና የፈተና ጊዜ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል
✍️ የመመልመያ መስፈርቱን አሟልተው ፈተናውን የሚያልፉ ተማሪዎች ባሉን ክፍት ቦታዎች በሚመደቡበት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ለመማር ፈቃደኛ የሆኑ መሆን አለባቸው።

Debre Berhan University Holds Strategic Consultative Meeting to Partner with Partners in Education Ethiopia ═══════ ❁✿❁ ...
11/08/2026

Debre Berhan University Holds Strategic Consultative Meeting to Partner with Partners in Education Ethiopia
═══════ ❁✿❁ ═══════

Debre Berhan (August 11, 2026) — Debre Berhan University (DBU), in collaboration with Partners in Education Ethiopia, has conducted a strategic consultative meeting aimed at jointly implementing multi-sectoral initiatives focused on quality education, health, and food security. The project targets students and parents at the selected pilot institution, Biruh Tesfa School.

Delivering the welcome address, Asmare Melese (Dr.), President of Debre Berhan University, recalled the pre-existing partnership between the university and the organization and expressed DBU's full support for the newly introduced development concept. Dr. Asmare affirmed that beyond providing material resources and technical expertise, the university is committed to co-designing and executing joint projects to achieve impactful and sustainable results.

For his part, Mr. Yihalem Abebe, General Manager of Partners in Education Ethiopia, explained that the organization is a Canada-based charity founded by Ethiopians. He noted that while the foundation currently operates across various zones in the Amhara Region, it plans to expand its operational footprint to other regions across the country in the future.

Mr. Yihalem further highlighted that the primary objective of the initiative is to build and empower educational institutions by leveraging local capacities surrounding schools. Explaining why Biruh Tesfa School was selected as a demonstration site, he stated that DBU will actively participate across all phases—from infrastructural development to academic research, training, and technical assistance—to establish an exemplary model for other institutions.

During the session, Mr. Feredi Merha-Tsidik, Director at Partners in Education Ethiopia, presented a working document outlining the joint action plans and respective institutional roles of both parties. The presentation was followed by an interactive discussion where participant questions and feedback were addressed by the General Manager, Mr. Yihalem Abebe.

In his closing remarks, President Asmare Melese (Dr.) highlighted that the project has already commenced healthcare interventions in collaboration with the Asrat Woldeyes Health Sciences Campus, specifically launching eye screening services. He concluded by reassuring stakeholders that planned initiatives in other focus areas will be rolled out progressively, with both organizations working in close coordination to address operational challenges as they arise.

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከ“Partners in Education Ethiopia” ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ምክክር  አካሄደ═══════ ❁✿❁ ═══════ደብረ ብርሃን ነሐሴ 05 ቀን ...
11/08/2026

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከ“Partners in Education Ethiopia” ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ምክክር አካሄደ
═══════ ❁✿❁ ═══════

ደብረ ብርሃን ነሐሴ 05 ቀን 2018 ዓ.ም- ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከ “Partners in Education Ethiopia” ጋር በመተባበር፣ ለማሳያነት (pilot program) ከተመረጠው የብሩህ ተስፋ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና ወላጆችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የትምህርት ጥራት፣ የጤና እና የምግብ ዋስትና ማረጋገጫ ፕሮጀክቶችን በጋራ ለመተግበር የሚያስችል የስትራቴጂክ ውይይት አካሂዷል።

በመድረኩ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስማረ መለሰ (ዶ/ር) የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው፤ ዩኒቨርሲቲው ከድርጅቱ ጋር አስቀድሞ የነበረውን አጋርነት በማስታወስ፣ አሁን ይዞት የመጣውን አዲስ የልማት ፅንሰ-ሐሳብ ተቋሙ ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍ ገልጸዋል። አክለውም ዩኒቨርሲቲው በቁሳቁስና በባለሙያ የቴክኒክ እውቀት ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር፣ በቀጣይም የጋራ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽና በማስፈጸም ውጤታማ ስራ ለማከናወን በትጋት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

ሌላው ንግግር ያደረጉት የ “Partners in Education Ethiopia” ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ይህዓለም አበበ በበኩላቸው፤ ድርጅቱ መቀመጫውን ካናዳ አድርጎ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተመሰረተ የበጎ አድራጎት ተቋም መሆኑን አብራርተዋል። በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል በሚገኙ ልዩ ልዩ ዞኖች እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝና በቀጣይም ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች አገልግሎቱን የማስፋፋት ዕቅድ እንዳለው ጠቁመዋል።
አቶ ይህዓለም አክለው እንደገለጹት፤ የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ በትምህርት ቤቶች ዙሪያ ያሉ አካባቢያዊ አቅሞችን በመጠቀም የትምህርት ተቋማትን አቅም ማጎልበት ነው። ይህንንም ለማሳየት የብሩህ ተስፋ ትምህርት ቤት በተሞክሮነት መመረጡን ገልጸው፤ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ቤቱ መሠረተ-ልማት ግንባታ ጀምሮ የመማር-ማስተማር ሂደቱን በሚደግፉ የምርምር፣ የስልጠና እና የቴክኒክ እገዛዎች ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ለሌሎች አርአያ የሚሆን ተቋማዊ ሥራ በጋራ እንደሚከናወን ተናግረዋል።

በውይይት መድረኩ የ“Partners in Education Ethiopia” ዳይሬክተር አቶ ፈረዲ መርሃ-ፅድቅ፤ በሁለቱ ተቋማት መካከል የሚከናወኑ የጋራ ተግባራትንና የእንቅስቃሴ ድርሻዎችን የሚዘረዝር የሥራ ሰነድ አቅርበዋል። በቀረበው ሰነድ ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በአቶ ይህዓለም አበበ አማካይነት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

በመጨረሻም የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አስማረ መለሰ (ዶ/ር)፤ ፕሮጀክቱ በጤናው ዘርፍ ከአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ጋር በመተባበር የዓይን ሕክምና ምርመራ ሥራዎችን መጀመሩን ጠቅሰው፤ በቀጣይም በሌሎች የተለዩ ዘርፎች የታቀዱ የጋራ ስራዎች ወደ ትግበራ እንዲገቡ እንደሚደረግና በሂደት የሚያጋጥሙ ተደራራቢ ችግሮችንም በጋራ ለመቅረፍ ቅንጅት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ  የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሄደ═══════ ❁✿❁ ═══════ደብረ ብርሃን (ነሐሴ 05 ቀን 2018 ዓ.ም) — ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች...
11/08/2026

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሄደ
═══════ ❁✿❁ ═══════

ደብረ ብርሃን (ነሐሴ 05 ቀን 2018 ዓ.ም) — ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች፣ የካምፓስ ማህበረሰብ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት፣ በምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት አዘጋጅነት የተካሄደውን አህጉራዊ እና ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ አካል የሆነ ተቋማዊ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በዋናው ግቢ በይፋ አካሂዷል።

በዚሁ መርሃ-ግብር ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስማረ መለሰ (ዶ/ር)፤ ተቋሙ ለአካባቢ ጥበቃ እና ለሥነ-ምህዳር መረጋገጥ የሚሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት አብራርተዋል። ፕሬዚዳንቱ አክለውም፣ ዩኒቨርሲቲው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብርን በተደራጀና በተቀናጀ አሰራር በአንኮበር እና በሸዋሮቢት የምርምር ማዕከላት ለበርካታ ዓመታት ሲተገብር መቆየቱን አስታውሰው፤ ባለፈው ዓመት በተነደፈው ስልታዊ ዕቅድ መሠረት ደግሞ በመሐል ሜዳ ካምፓስ የችግኝ ተከላና ተከታታይ የእንክብካቤ ተግባራት በስፋት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ዶክተር አስማረ አጽንኦት ሰጥተው እንደተናገሩት፣ በቀጣይም ተቋሙ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት (Integrated Watershed Management) አቀራረብን በመከተል የላቀ አካባቢያዊና አካዳሚያዊ ውጤት ለማስመዝገብ ይሰራል። ይህ ተቋማዊ እንቅስቃሴ ለግብርና ኮሌጅ የመማር-ማስተማር፣ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎች ምቹ የተፈጥሮ ላቦራቶሪ ከመፍጠሩ ባሻገር፣ ለሌሎች ሀገራዊ ተቋማትም በምሳሌነት የሚጠቀስ ሊሆን እንደሚችል አስረድተዋል።

በሌላ በኩል የመርሃ-ግብሩ አስተባባሪ የሆኑት የማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መቅደስ ጌራወርቅ (ረዳት ፕሮፌሰር)፤ ደብረ ብርሃን ከተማ ፈጣን የኢንዱስትሪ ማዕከል እየሆነች ከመምጣቷ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ስነ-ምህዳራዊ ጫናዎችንና የአካባቢ ብክለትን ለመቋቋም ከተማ አቀፍ ተቋማዊ ቅንጅትና የተክሎች እንክብካቤ ወሳኝ መሆኑን አሳስበዋል። በዚህም መሠረት ዩኒቨርሲቲው በመሐል ሜዳ፣ በአስራት ወልደየስ ካምፓሶች እና በአንኮበር ቦታኒካል ጋርደን የታቀዱ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን በስኬት ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል።

ረዳት ፕሮፌሰር መቅደስ አክለውም፣ ቀደም ሲል ለተከላ የሚሆኑ ችግኞች ከውጭ አካላት በግዥ የሚቀርቡ እንደነበር አስታውሰው፤ ዘንድሮ ግን ተቋማዊ ራስ-ችሎታን በመገንባት በምርምር፣ ህትመትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት 3 ዓይነት እንዲሁም በግቢ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 2 ዓይነት በጠቅላላው 5 የስነ-ምህዳር ተስማሚ የችግኝ ዝርያዎች በከፍተኛ መጠን በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢና በመሐል ሜዳ ችግኝ ጣቢያዎች እንዲዘጋጁ መደረጉን አብራርተዋል።
በዚሁ ዕለት በተካሄደው መርሃ-ግብርም የስነ-ምህዳር ጥገናንና ውበትን ታሳቢ ያደረጉ የሀበሻ ጽድ፣ የፈረንጅ ጽድ፣ የፈረንጅ ግራር፣ ግራቪሊያ እና ፓይንስፑላ የተሰኙ የችግኝ ዝርያዎች በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ተተክለዋል።

11/08/2026
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
08/08/2026

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ 10 ሺህ ችግኞችን ለአካባቢው ማህበረሰብ አከፋፈለ።‎═══════ ❁✿❁ ═══════‎ደብረ ብርሃን ​ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም (ደብዩ) -ተቋሙ ከመማር ማስተማር እና ...
03/08/2026

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ 10 ሺህ ችግኞችን ለአካባቢው ማህበረሰብ አከፋፈለ።
‎═══════ ❁✿❁ ═══════

‎ደብረ ብርሃን ​ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም (ደብዩ) -ተቋሙ ከመማር ማስተማር እና ምርምር ስራው ጎን ለጎን ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ተልዕኮውን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በዛሬው ዕለት ያሰራጫቸው ችግኞች በዩኒቨርሲቲው የግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ሳይንስ ኮሌጅ ተመራማሪዎች የተዘጋጁና በማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት በኩል ለተለያዩ አካላት ተደራሽ የተደረጉ ናቸው።

‎የችግኝ ዝግጅቱና ስርጭቱ በመሀል ሜዳ ግብርና ካምፓስ፣ በአንኮበር ቦታኒካል ጋርደን እና በሸዋሮቢት ግብርና ምርምር ማዕከላት የተዘጋጁ መሆኑ ተገልጿል።

‎​በዛሬው እለት የተሰራጩት እነዚህ ችግኞች የአካባቢውን የአየር ንብረት በቀላሉ የሚቋቋሙ መሆናቸውን የተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ በላይነሽ ሲሳይ ገልጸዋል። በዝርያ ሽፋን ካላቸው መካከል Grevillea robusta (ግራቪሊያ ሮቡስታ)፣ Acacia decurrens (የፈርጂ ግራር)፣ Acacia melanoxylon (ኦሜዲላ)፣ Callistemon (ቦትል ብራሽ) እና ባህር ዛፍ መሆናቸውን ተናግረዋል።

‎እነዚህ ችግኞች ከአግሮ-ኢኮሎጂው ጋር የሚስማሙ፣ የአፈር ለምነትን የሚጨምሩ፣ ለአካባቢ ውበት፣ ለንብ እርባታ እና ለአግሮ-ፎረስተሪ ልማት ከፍተኛ ተመራጭነት ያላቸው መሆናቸውን ተመላክተዋል።

‎ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ አገር በቀል ዛፎች ላይ በማተኮር ከግብርናው ጋር አብረው ሊሄዱ የሚችሉ አማራጮችን በስፋት ለማስተዋወቅ አቅዷል።

‎​የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ግንኙነትና የአረንጓዴ ልማት ኦፊሰር አድማሱ ላቀው (ዶ/ር) በበኩላቸው ችግኞቹ ከመሰራጨታቸው በፊት በትምህርት ቤቶች፣ በቀበሌዎች፣ በኮንዶሚኒየሞች እና ጥብቅ ቦታዎች ውስጥ በቂ የጉድጓድ ዝግጅት መደረጉን ተረጋግጧል። ከተመረጡ 10 ተቋማት ጋርም በትብብር መሰራቱን አንስተው ዩኒቨርሲቲው በዘንድሮው የክረምት ወቅት አጠቃላይ 15 ሺህ ችግኞችን ለማሰራጨት አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

‎በዘንድሮው ዓመት የተጀመረውን የልማት ስራ በቀጣይ ዓመት በማጠናከር ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን ጭምር ለአካባቢው ማህበረሰብ የማድረስ እቅድ መያዙንም ገልጸዋል።

‎​መሳለሚያ አስተዳደር ጽህፈት ቤትን ወክለው የተገኙት ወ/ሮ ትእግስት አለማየሁ በበኩላቸው ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ 6,500 ችግኞችን በቀበሌ አስተዳደር ደረጃ መረከባቸውን ገልጸዋል።

‎እነዚህ ችግኞች ለአካባቢ ውበት ግንባታ የሚውሉ ሲሆን በነገው ዕለት ለተለያዩ ተቋማትና ድርጅቶች ተሰራጭተው የተከላ መርሃ ግብር እንደሚካሄድባቸው አስታውቀዋል።

‎​ይህ በዩኒቨርሲቲውና በአካባቢው አስተዳደር መካከል የተከናወነው የጋራ አረንጓዴ ልማት ስራ የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ-ተኮር ተልዕኮ ከፍ አድርጎ የሚያሳይና የነገዋን አረንጓዴ እና ውብ ከተማ እውን ለማድረግ የሚያስችል ጠንካራ ርምጃ መሆኑ ተመላክቷል።

Address

Debre Berhan

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debre Berhan University posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share