Debark University /ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ/official

Debark University /ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ/official Debark University, founded in 2015, is a public higher education institution in Ethiopia committed to quality education, research, and national development.

state established university

ጨረታ*****
17/09/2026

ጨረታ
*****

📢 CALL FOR RESEARCH PROPOSALSDebark University – Semien Mountain Research Institute (SMRI) is pleased to announce its In...
16/09/2026

📢 CALL FOR RESEARCH PROPOSALS

Debark University – Semien Mountain Research Institute (SMRI) is pleased to announce its Inaugural Call for Research Proposals for the 2019 E.C. funding year.

🏔️ Theme: Guarding the Roof of Africa Through Science and Action

SMRI invites researchers to submit focused, problem-oriented, and multidisciplinary research proposals addressing priority challenges of the Simien Mountains and surrounding communities.

🔬 Let science drive conservation, sustainable development, and community resilience.

📅 Submission Deadline: October 24, 2026
📌 Call Reference: SMRI/01/2019 E.C.

👉 For detailed information on the priority research areas, eligibility, submission requirements, and application process, please see the attached call document.
We invite researchers and research teams to seize this opportunity and contribute to shaping the future of the Simien highlands.

📢 ማስታወቂያ     **********ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የተማሪዎች ወደ ግቢ የመግቢያ፣ የምዝገባ እና የትምህርት መጀመሪያ ጊዜያትን እንደሚከተለው ያሳውቃል። 1.  2ኛ ዓመትና...
16/09/2026

📢 ማስታወቂያ
**********
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የተማሪዎች ወደ ግቢ የመግቢያ፣ የምዝገባ እና የትምህርት መጀመሪያ ጊዜያትን እንደሚከተለው ያሳውቃል።

1. 2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር የቅድመ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች:-

📝 የመመዝገቢያ ጊዜ፦ መስከረም 25–26/2019 ዓ.ም.
⚠️ በቅጣት የመመዝገቢያ ጊዜ፦ መስከረም 27/2019 ዓ.ም.
📚 ትምህርት የሚጀምረው፦ መስከረም 28/2019 ዓ.ም.

2. በ2018 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተምረው የማለፊያ ውጤት ያመጡ እና በ2019 ዓ.ም. በፍሬሽማን ፕሮግራም በት/ት ሚኒስቴር በኩል ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚመደቡ ተማሪዎች:-

📝 የመመዝገቢያ ጊዜ፦ መስከረም 28–29/2019 ዓ.ም.
⚠️ በቅጣት የመመዝገቢያ ጊዜ፦ መስከረም 30/2019 ዓ.ም.
📚 ትምህርት የሚጀምረው፦ ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም.

መስከረም 6/2019 ዓ.ም.
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ።

 #ማስታወቂያ :- ለኤክስቴንሽን ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
15/09/2026

#ማስታወቂያ :- ለኤክስቴንሽን ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ “ራስ ደጀን ንግድና ማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ” ተስፋ ሰጪ የንግድና የገቢ ማመንጨት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑ ታወቀ።የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ...
15/09/2026

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ “ራስ ደጀን ንግድና ማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ” ተስፋ ሰጪ የንግድና የገቢ ማመንጨት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑ ታወቀ።

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የገቢ ማስገኛ ኢንተርፕራይዞች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 650/2001 አንቀጽ 66 እና በኢንተርፕራይዞች ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 450/2012 መሠረት ያቋቋመው "ራስ ደጀን ንግድና ማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ" ከምስረታ ጊዜ ጀምሮ አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲያከናውን ቆይቶ በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ መግባቱ ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው የውስጥ ገቢ አቅሙን በማሳደግ የመማር–ማስተማርና የምርምር ተልዕኮዎቹን የበለጠ ለማስፈጸም፤ እንዲሁም በሂደት ተቋሙ ራስ ገዝ ለመሆን የሚያደርገውን ጉዞ ለማፋጠን ኢንተርፕራይዝ ማቋቋሙን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስማማው ዘገዬ ገልጸዋል ።በተጨማሪም የኢንተርፕራይዙ መመሰረትና ወደስራ መግባት በወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ እና በአካባቢው ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ዶ/ር አስማማው ጠቁመዋል።

የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አይቶልኝ ሙሌ በበኩላቸው፤ ተቋሙ በአሁኑ ወቅት አቅሙን አጠናክሮ በሦስት ዋና ዋና የሥራ ዘርፎች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጸዋል። በኮንስትራክሽን ዘርፍ በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭነት (GC Grade 4) የንግድ ፈቃድ በማውጣትና በኢ-ጂፒ (e-GP) በመመዝገብ ለጨረታዎች ብቁ የሆነ ሲሆን፤ በቅርቡም የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ያወጣውን የአጥር ግንባታ ጨረታ አሸንፎ ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጅቱን አጠናቋል። በተጨማሪም በወፍዳር ቀበሌ ድልድይ ፕሮጀክት ተረክቦ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየሠራ ይገኛል። የኮንስትራክሽን ዘርፉን ለማጠናከር ከቡና ባንክ ጋር በተደረገ የብድር ውል ሁለት የ2025 ምርት ዘመናዊ ሲኖትራኮች እና አንድ ሎደር ገዝቶ ወደ ሥራ በማስገባት በኪራይ አገልግሎት አበረታች ገቢ ማስገኘት ችሏል።

አቶ አይቶልኝ አክለው እንደገለጹት፤ ኢንተርፕራይዙ በሌሎች የሥራ ዘርፎችም የላቀ አገልግሎት ለመስጠት የተዘጋጀ ሲሆን፣ በሕትመት ሥራ ዘርፍ ዘመኑ ያፈራቸውን ማሽኖች በመትከልና የሙከራ ሥራዎችን በማጠናቀቅ የማንኛውንም ዓይነት የሕትመት ትዕዛዞች ለመቀበል ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ሆኗል። በተመሳሳይ መልኩ በእንጨትና ብረታብረት ውጤቶች ዘርፍ ዘመናዊ ማሽኖችን በመጠቀም ጥራት ያላቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለደንበኞች ማቅረብ ጀምሯል።

በቀጣይም ኢንተርፕራይዙ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት የማማከር ሥራዎችን፣ የሳሙናና ጽዳት ዕቃዎች ማኑፋክቸሪንግን፣ የእንስሳት መኖ ማቀነባበርና ማድለብን፣ የቱሪዝምና የጉዞ ውክልና አገልግሎትን፣ የሞዴል ፋርማሲና መድኃኒት አቅርቦትን፣ የእርሻ መካናይዜሽንን እንዲሁም የመምህራንና ሰራተኞች የካፌና መዝናኛ አገልግሎቶችን ለማስጀመር በትጋት እየሠራ ይገኛል።

መስከረም 5/2019 ዓ.ም
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
For the latest updates:
🌐 Website: http://www.dku.edu.et
📘 Facebook: https://www.facebook.com/Debarkuniversityandcollegeofficial
🐦 Twitter: https://twitter.com/DebarkUniETH
📲 Telegram: https://t.me/+Ed4_Lp3bywo4MzI0
📹 YouTube: https://www.youtube.com

ለመላው የዩኒቨርሲቲያችን መምህራን፣ አስተዳደር ሰራተኞች ፣ ተማሪዎችና የቀድሞ ምሩቃን እንዲሁም የአካባቢያችን ማህበረሰብ እና አጋር አካላት ፤ እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አ...
10/09/2026

ለመላው የዩኒቨርሲቲያችን መምህራን፣ አስተዳደር ሰራተኞች ፣ ተማሪዎችና የቀድሞ ምሩቃን እንዲሁም የአካባቢያችን ማህበረሰብ እና አጋር አካላት ፤ እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የደስታና የስኬት ዘመን እንዲሆን እንመኛለን ።

ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ፤
ጳጉሜ 5/2018 ዓ/ም።

🎓 የስኬት ጉዟችሁን በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ይጀምሩ!የ2018 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ወስዳችሁ የመግቢያ ነጥብ ያሟላችሁ ውድ ተማሪዎች፣ የአካዳሚክና የሙያ ጉዟችሁን በጥራት ለመጀመ...
05/09/2026

🎓 የስኬት ጉዟችሁን በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ይጀምሩ!

የ2018 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ወስዳችሁ የመግቢያ ነጥብ ያሟላችሁ ውድ ተማሪዎች፣ የአካዳሚክና የሙያ ጉዟችሁን በጥራት ለመጀመር ደባርቅ ዩኒቨርሲቲን ይምረጡ!

🏔️ ዩኒቨርሲቲያችን በፈጣን የለውጥ ጉዞ ላይ የሚገኝ ተቋም ሲሆን፤ ተማሪን ማዕከል ያደረገ የመማርና የማስተማር ሥርዓት ለመገንባት በሰፊው እየሰራ ይገኛል።

በመሆኑም በሚከተሉት ኮሌጆች በመቀላቀል ፤ ህልምዎን እውን ያድርጉ !

🌱 ግብርናና አካባቢ ሳይንስ
💼 ንግድና ኢኮኖሚክስ
💻 ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ
👥 ማኅበራዊ ሳይንስ
🏥 ጤና ሳይንስ
⚖️ ሕግ

📌 ዝርዝር ትምህርት ክፍሎችና ፕሮግራሞች በዩኒቨርሲቲው ድረ-ገጽ ወይም እዚህ በተያያዘው ባነር ላይ ይገኛል።

🌟 የዛሬ ምርጫዎ የነገ ስኬትዎን ይገነባል! ደባርቅ ዩኒቨርሲቲን ይምረጡ!

🌐 www.dku.edu.et
✉️ [email protected]
📍 ደባርቅ ከተማ፣ ሰሜን ጎንደር

📅 ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም.
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ።

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና ማዕከልን (CPD Center) እናስተዋውቃችሁ ።የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና ...
03/09/2026

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና ማዕከልን (CPD Center) እናስተዋውቃችሁ ።

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ስልጠና ማዕከል (CPD Center) ዋና ዓላማ የጤና ባለሙያዎችን ክሊኒካዊ ክህሎት እና ዘመናዊ የሕክምና እውቀት በየጊዜው በማጎልበት የማህበረሰባችን የጤና አገልግሎት ጥራት ማሳደግ ነው። ማዕከሉ "የጤና ባለሙያዎችን ማብቃት፤ የህክምና አገልግሎትን ማሳደግ" የሚለውን ራዕይ በመሰነቅ በስራ ላይ ያሉ ባለሙያዎች የንድፈ-ሀሳብ እውቀታቸውን ከተግባራዊ ልምምድ ጋር የሚያስተሳስሩበትን ምቹ የስልጠና ድጋፍ ይዘረጋል። ይህ ዓላማ ባለሙያዎችን ብቁ ከማድረግ ባለፈ፤ በጤናው ዘርፍ የሚታዩ ክፍተቶችን በዕውቀትና በጥራት ለመሙላት ታስቦ የተነደፈ ነው።

ይህንን ዓላማ ለማሳካት ማዕከሉ አራት ዋና ዋና አገልግሎቶችን በግንባር ቀደምትነት ያከናውናል። የመጀመሪያው በአካልና በኦንላይን የሚሰጡ ዘመናዊ የሙያ ስልጠናዎች ሲሆኑ፣ እነዚህም በክህሎት ላብራቶሪዎች (Simulation Labs) የተደገፉ ናቸው። ሁለተኛው የጤና ምርምሮችን ማካሄድ እና ማሰራጨት ሲሆን፣ ሦስተኛው ደግሞ የቨርቹዋል ዌብናሮችን እና ራስን በራስ የማስተማሪያ የዲጂታል ሞጁሎችን (iHRIS Integration) በስፋት መተግበር ነው። አራተኛው እና ወሳኙ ተግባር ደግሞ ባለሙያዎች የሚያገኟቸውን የCPD የትምህርት ነጥቦች (CEUs) በቀጥታ ከሙያ ፍቃድ እድሳት ሲስተም ጋር በማገናኘት የመያ ፈቃድ እድሳትን ማቀላጠፍ ነው።

በተጨማሪም የማዕከሉ የሥራ እንቅስቃሴዎች ሁለንተናዊ የብቃት ማሻሻያ ላይ ያተኮሩ ሲሆን ከምርምርና ስልጠና ባሻገር ክሊኒካዊ ውይይቶች፣ የሕክምና ጥራት ማሻሻያ ፕሮጀክቶች፣ የማህበረሰብ ተሳትፎ ስራዎች፣ ሙያዊ የምክር ድጋፎች (Mentorship) እና የጤና አመራር ስልጠናዎች በማዕከሉ ውስጥ ይሰጣሉ። ማዕከሉ እነዚህን ስልታዊ ስራዎች በማቀናጀት ጥራት ያለው ትምህርት፣ የሙያ ልቀትን እና የተሻለ የጤና ውጤትን በተግባር ያረጋግጣል።

ነሃሴ 28/2018 ዓ.ም
የህዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
For the latest updates:
🌐 Website: http://www.dku.edu.et
📘 Facebook: https://www.facebook.com/Debarkuniversityandcollegeofficial
🐦 Twitter: https://twitter.com/DebarkUniETH
📲 Telegram: https://t.me/+Ed4_Lp3bywo4MzI0
📹 YouTube: https://www.youtube.com

 #ማስታወቂያ ለሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
01/09/2026

#ማስታወቂያ ለሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የሐዘን መግለጫ!ደባርቅ ዩኒቨርስቲ  የአካባቢያችን የሀገር ሽማግሌና የሰባት ከዘራ አባል  በነበሩት በተከበሩ   አቶ ሙሉጌታ ደርሶ  ህልፈተ ሕይዎት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ፣ ለቤተሰቦቻቸው...
29/08/2026

የሐዘን መግለጫ!

ደባርቅ ዩኒቨርስቲ የአካባቢያችን የሀገር ሽማግሌና የሰባት ከዘራ አባል በነበሩት በተከበሩ አቶ ሙሉጌታ ደርሶ ህልፈተ ሕይዎት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ፣ ለቤተሰቦቻቸው ፣ ወዳጆቻቸው እና ለመላው የአካባቢያችን ማህበረሰብ መጽናናትን ይመኛል ፡፡

አቶ ሙሉጌታ ደርሶ የአካባቢ ልማት ኮሚቴ አባል በመሆን ለማህበረሰባችን ለሰጡት አገልግሎት፣ እንዲሁም የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ለመመስረት በተደረጉ ጥረቶች ላበረከቱት የማይረሳ አስተዋጽኦ ሁሌም በክብር ይታወሳሉ ።

ደባርቅ ዩኒቨርስቲ ።
ነሃሴ 23/2018 ዓ/ም

Address

Debark
Debark'
90

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debark University /ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ/official posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Debark University /ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ/official:

Shortcuts

Share