ደባርቅ ደ/ሳ/ቅ/ሚካኤል ቃለህይወት ሰ/ት/ቤት D/D/Sahle St.Michael QaleHiwot Sunday School

  • Home
  • Ethiopia
  • Debark'
  • ደባርቅ ደ/ሳ/ቅ/ሚካኤል ቃለህይወት ሰ/ት/ቤት D/D/Sahle St.Michael QaleHiwot Sunday School

ደባርቅ ደ/ሳ/ቅ/ሚካኤል ቃለህይወት ሰ/ት/ቤት D/D/Sahle St.Michael QaleHiwot Sunday School የደባርቅ ደ/ሳ/ቅ/ሚካኤል ቃለህይወት ሰ/ት/ቤት D/D/Sahle St.Michael QaleHiwot Sunday School

በዓሉ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልበኅዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡አምላካችን እግዚአብሔር ሳጥናኤል...
21/11/2025

በዓሉ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል
በኅዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡አምላካችን እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ አውርዶ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል፡፡

የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው፡፡ ይህም እንደሆነ እንድንረዳ በብሉይ ኪዳን የእግዚአብሔር ሕዝብ የተባለውን እስራኤል ዘሥጋን ሲራዳና ሲጠብቅ እንደነበረ ተጽፎልን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ በኢያሪኮ ምድረ በዳ እንደተገለጠለት ‹‹… ዐይኑን አንሥቶ ተመለከተ፤ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ የያዘ ሰው በፊቱ ቆመ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፤ “ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ? አለው፡፡ እርሱም “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቼአለሁ›› ይለናል፡፡ (ኢያ.፭፥፲፫)

እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ሹመቱ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይም በመሆኑ ስለ እነርሱ ዲያብሎስ ይዋጋው፣ በጸሎትም ረድቷቸዋል፡፡ ነገር ግን ኃጢአት ሠርተው ሲያገኛቸው ለእግዚአብሔር አድልቶ ኃጢአተኞችን ስለሚቀጣ እግዚአብሔር ሕዝቡን “በፊቱ ተጠንቀቁ! ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት” ብሎ አስጠንቅቋቸው ነበር፡፡ ይህም ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙን ያስረዳናል፡፡ ነገር ግን ከላይ የተጠቀሱት ጥቅሶች ሕዝበ እስራኤልን ይራዳቸው የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ አያረጋግጥም የሚል ካለ ‹መልአክ› የተባለው ቅዱስ ሚካኤል ስለመሆኑ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ነቢዩ ዳንኤል በተላከ ጊዜ ገልጦልን እናገኛለን፡- ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ቅዱስ ሚካኤል ስለመሾሙ ሲመሰክር ‹‹በእውነት በመጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር የሚረዳኝ ማንም የለም›› ብሏል፡፡ ስለዚህም ለኢያሱ የተገለጠውና እስራኤላውያንንም የመራው መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን እንረዳለን፡፡ (ዘፀ.፳፫፥፳፩፣ዳን.፲፥፳፩)

የቅዱስ ሚካኤል አለቅነት በሐዲስ ኪዳንም አንደሚቀጥል ይህ ነቢይ በትንቢቱ ‹‹በዚያ ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ ሚካኤል ይነሣል..›› በማለት ተናግሮለታል፡፡ ስለዚህም ቅዱስ ሚካኤል እኛን ከሰይጣን አሽክላና ወጥመድ ይጠብቀንና በጸሎቱ በእግዚአብሔር ፊት ይቆምልን ዘንድ በእኛም ላይ ሹም ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ የእግዚአብሔር ሕዝቦችና የርስቱ ወራሾች ነንና፡፡ (ዳን.፲፪፥፩)

እግዚአብሔር ነቢዩ ሙሴን የሕዝቡ መሪ አድርጎ መሾሙ እጅግ ትሑትና ስለመንጎቹን ነፍሱን እንኳ አሳልፎ እስከመስጠት ደርሶ ስለሚወዳቸው ነበር፡፡ (ዘኁ.፲፪፥፫፣ዘፀ.፴፪፥፴፪) በሕዝቡም ላይ እርሱን መሾሙ እንዲሠለጥንባቸው ወይም እንዲገዛቸው ሳይሆን በትምህርቱና በጸሎቱ እነርሱን እንዲቤዣቸው ነው፡፡ እንዲህም ስለሆነ ቅዱስ እስጢፋኖስ ስለሙሴ ሲመሰክር ‹‹እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው›› አለ፡፡ (የሐዋ.፯፥፴፭) እንዲሁ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል እጅግ ትሑትና ለሠራዊቱ ተቆርቋሪ የሆነ መልአክ በመሆኑ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ተሾመ፡፡ በመላእክትና በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ መሾሙ ልክ እንደ ሙሴ በእነርሱ ላይ ሊሠለጥንባቸው ወይም ሊገዛቸው ሳይሆን መላእክትን ሊመራ፣ እኛን ደግሞ ከሰይጣን ጥቃት ሊጠብቀንና በጸሎቱ ሊራዳን ነው፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን መላእክት እኛን እንደሚጠብቁና እንደሚራዱ እንዲሁም ስለእኛ በፊቱ አንደሚቆሙ ሲያስተምረን ‹‹ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ስንኳ እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ሁል ጊዜ በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁ›› ብሎናል፡፡ (ማቴ.፲፰፥፲) እኛን ይጠብቁ ዘንድ የተሰጡን ቅዱሳን መላእክት ስለእኛ እንዲህ የሚቆረቆሩና ስለመዳናችን የሚተጉ ከሆነ በቅድስናው ልቆ የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመው ቅዱስ ሚካኤል እንዴት ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ይበልጥ አይቆም? (ሉቃ.፲፫፥፮-፱) እንዴትስ በተሰጠው ሥልጣንና ኃይል አይረዳን? (መዝ.፴፫፥፪) እርሱ ‹‹ስለሕዝብህ ልጆች የሚቆመው›› መባሉም እኛን በጸሎቱና በተራዳኢነቱ የጽድቅ ሕይወታችንን በሚገባ እንድናከናውን እንደሚራዳን የሚያሳይ ኃይለ ቃል ነው፡፡

የመልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ጸሎቱና በረከቱ በእኛ ላይ ለዘለዓለሙ ይደርብን፤ አሜን፡፡

 ሚካኤል የሚለው ስም አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ በተሰኘው መዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ሲገልጹ ቃሉ የዕብራይስጥ ሲሆን፤ ሚ ማለት “መኑ” ፥ ካ ማለት ...
21/11/2025


ሚካኤል የሚለው ስም አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ በተሰኘው መዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ሲገልጹ ቃሉ የዕብራይስጥ ሲሆን፤ ሚ ማለት “መኑ” ፥ ካ ማለት “ከመ” ማለት ሲሆን፥ ኤል ማለት ደግሞ “አምላክ” ማለት ነው። በዚህም መሠረት ቅዱስ ሚካኤል የስሙ ትርጓሜ “መኑ ከመ አምላክ፥ ማን እንደ እግዚአብሔር” ማለት ነው።

በሥነ ፍጥረት ትምህርት እግዚአብሔር ሳጥናኤልን ቅሩበ እግዚአብሔር፣ ለእግዚአብሔር የቀረበ አድርጎ እንደ ሾመው ቅዱሳት መጻሕፍት ይመሰክራሉ፡፡ ነገር ግን ሳጥናኤል ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ክብር ትቶ አምላክነትን በመሻቱ በትዕቢቱ ምክንያት ሥልጣኑ ተገፍፎ ወደ ምድር ጥሎታል፡፡ በቦታውም ቅዱስ ሚካኤልን ሾሞታል፡፡ የቅዱስ ሚካልን ሲመት ምክንያት በማድረግም ዕለቱን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅዳር ፲፪ ቀን በየዓመቱ በድምቀት ታከብረዋለች፡፡ (መጽሐፈ አክሲማሮስ)

ይህም ብቻ አይደለም፤ እስራኤላውያን በግብፅ በባርነት ቀንበር ተይዘው ለ፪፲፭ በስቃይ ሲኖሩ ያለቀሱት ዕንባ መንበረ ጸባዖት ደርሶ ከግብፅ ወደ ምድረ ርስት ይገቡ ዘንድ እግዚአብሔር ሊቀ ነቢያት ሙሴን አሥነስቶ ባሕረ ኤርትራን ከፍሎ አሻግሮ፣ ለዐርባ ዘመናት ሲጓዙ ቀን በደመና ሌሊቱን በብርሃን እየመራ ያደረሳቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ይህንን ቀን መታሰቢያ አድርጋ የምታከብርበት ዕለት ነው፡፡

ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ ወልደ ነዌ በሰው አምሳል ተገልጦ “የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ ‘ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ?’ አለው፡፡ እርሱም ‘እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ፤ አሁንም ወደ አንተ መጥቻለሁ’ አለ፡፡ ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደ” በማለት እግዚአብሔር የቅዱስ ሚካኤልን ክብር ገልጧል፡፡ (ኢያ. ፭፥፲፫-፲፬)

የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይ ጭምር ነው፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል፣ ለእኛ ለሰዎች አማላጅ ሲሆን ለቅዱሳን፣ ፃድቃን ሰማዕታት ደግሞ አጋዣቸው ነው፤ በሕይወታቸውና በተጋድሏቸውም እስከ መጨረሻው ይረዳቸዋል፡፡

ይህንንም በቤተ ክርስቲያናችን በመጽሐፈ ስንክሳር እና ድርሳነ ሚካኤል ኅዳር ፲፪ ቀን እንደተጻፈው መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ዱራታዎስንና ሚስቱ ቴዎብስታን ከዲያብሎስ ፈተና የታደገበት ዕለት ነው፡፡

ዱራታዎስና ቴዎብስታ ሁልጊዜ ያለማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ነበር፡፡ ነገር ግን በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ፡፡ ለቅዱስ ሚካኤልም ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉትን እስኪያጡ ድረስ ቸገራቸው፡፡ ዱራታዎስም የእርሱንና የሚስቱን ልብስ ሸጦ ለመልአኩ በዓል መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ ይዞ ወጥቶ ሄደ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም በታላቅ መኮንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለትና ወደ ባለ ጸጎች ሄዶ በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ፣ ሁለተኛም ወደ ባለ ስንዴ ዘንድ ሄዶ በእርሱ ዋስትና ስንዴን እንዲወስድ፣ ዳግመኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ዘንድ ሄዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ፣ ነገር ግን ወደ ቤቱ ሳይርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ አዘዘው፡፡ ዱራታዎስም እንደታዘዘው አደረገ፡፡ ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ ቤቱ ሁሉ በበረከት ተመልቶ አገኘው፡፡ እርሱም እጅግ ተደስቶ የዚህን የክቡር መልአክ የመታሰቢያውን በዓል አደረገ፡፡ ጦም አዳሪዎችንና ድኆችንም ጠርቶ አጠገባቸው፡፡

ከዚህም በኋላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቴዎብስታ ቅዱስ ሚካኤል ለሁለተኛ ጊዜ ተገለጠላቸው፡፡ ዱራታዎስንም የዓሣውን ሆድ እንዲሰነጥቅ አዘዘው፡፡ በሰነጠቀውም ጊዜ ፫፻ (ሦስት መቶ) የወርቅ ዲናር በዓሣው ሆድ ውስጥ ተገኘ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ዱራታዎስንና ሚስቱን ቴዎብስታን እንዲህ አላቸው፡- “ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ፣ ለባለ ዓሣውና ለባለ ስንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ፡፡ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ እግዚአብሔር አስቧችኋልና በጎ ሥራችሁን፣ መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን አስቦ በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ፣ በኋለኛውም መንግሥተ ሰማያትን አዘጋጅቶላችኋል” አላቸው፡፡

እነርሱም ይህን ነገር ሲሰሙ ደነገጡ፤ የከበረ ገናናው መልአክም “ከመከራችሁ ሁሉ ያዳንኳችሁ የመላእክት አለቃ እኔ ሚካኤል ነኝ፤ መሥዋዕታችሁንና ምጽዋታችሁን ወደ እግዚአብሔር ፊት ያሳረግሁ እኔ ነኝ፡፡ አሁንም በዚህ ዓለም ከበጎ ነገር እንድታጡ አላደርጋችሁም” አላቸው፡፡ ይህንንም ከነገራቸው በኋላ ወደ ሰማያት ወጣ፤ እነርሱም በፍርሃትና በክብር ሰገዱለት፡፡”

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከበዓሉ በረከት ረድኤት ይክፈለን፤ ጥበቃውና አማላጅነቱ አይለየን፡፡ አሜን፡፡

ምንጭ፡– ድርሳነ ቅዱስ ሚካኤል፣ ስንክሳር ዘወርኃ ኅዳር፣ መጽሐፈ አክሲማሮስ፣ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ

“አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት።”   መዝሙር 132፥8 በአንዱ በአዳም ሞት ወደ ዓለም ገብቷልና ለሰው ሁሉ ሞት የተገባ ሆነ ። ምንም እንኳ ከፍጥረቱ ተለይታ የመለኮ...
21/08/2025

“አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት።” መዝሙር 132፥8

በአንዱ በአዳም ሞት ወደ ዓለም ገብቷልና ለሰው ሁሉ ሞት የተገባ ሆነ ። ምንም እንኳ ከፍጥረቱ ተለይታ የመለኮት ማደርያ ዙፋኑ ብትሆን ፣ የሕይወት ውኃ ከማኅጸኗ ቢፈልቅ ፣ የትንሣኤያቻን በኩር ጌታችን ኢየሱስ የሆዷ ፍሬ ቢሆንም ሕይወትን የወለደችው ማርያም ሞትን ቀምሳለች። ነገር ግን ለመነሳት (ለትንሣኤ) የልጇን መምጣት ፣ የመላእክትን የመለከት ድምጽ መስማት አላስፈለጋትም #በሥልጣኑ የተነሳው ልጇ #በሥልጣኑ አስነስቷታል። ልዑል ማደርያውን በመቃብር ትኖር ዘንድ አልተዋትም ከመቃብር ቀሰቀሳት አስነሳት እንጂ።

ለክርስቲያን የእመቤታችን ትንሣኤ አያስደንቀውም እንኳ እሷ እኛም እንነሳለን እንኳን እኛ የማያምኑ አሕዛብም ይነሳሉ (ለአሳር)። የእመቤታችን ወደ ሰማይ መውጣት አያስደንቀንም እሷ ራሷ ዳግሚት ሰማይ ናት ፤ ሰማይ አልተሸከመውም እሷ ግን ተሸክመዋለች ፣ ሰማያት እንኳ በፊቱ ንጹሕ አይደሉም የእሷ ንጽሕና ግን በአብ ዘንድ የተወደደ ነው። እሷ ሰማይ የሚቀናባት ሰማይ ፣ የምትናገር ገነት ናት።

አባቷ ደዊት በሃብተ ትንቢቱ የመነሳቷን ነገር “አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት" ብሎ ዘምሮላታል። ሊቃውንት ልጆቿም የአባቷን የዳዊት መዝሙር አብራርተውለታል። ይህም "ዕረፍት" የተባለችው መንግሥተ ሰማያት ናት አንዲል ቅዱስ ጳውሎስ (ዕብ 4፥3) ። አንተ የተባለው ብቻውን አምላክ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ እንደሆነ እሙን ነው ፤ መቅደስ የተባለውም የጌታችን ሰውነቱ መሆኑን ወንጌላዊው እንዲህ በማለት ይነግረናል “ኢየሱስም መልሶ፦ ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው።....እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር።”ዮሐንስ 2፥19-21። ታቦት የተባለችው ደግሞ አማናዊት ታቦት ፤ በሰው እጅ ያልተሰራችው ታቦት ድንግል ማርያም ናት። ታቦት ማለት ማደርያ ማለት ነው ታድያ መቅደስ ለተባለ ለጌታችን ሰውነት ማደርያ (ታቦት) የሆነች ከእመቤታችን በቀር ማን አለ? አካላዊ ቃል ያደረባት ሴትስ ከማርያም በቀር ማን ናት??

የመዝሙረኛውን ቃል ከነ ትርጓሜው ደግመን ስናነበው እንዲህ ይላል “አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ (መንግሥተ ሰማያት )ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ(የሰውነትህ) ታቦት (ማደርያ ፣ማርያም)።”


በአማን ማርያም ተነስታለች
በአማን ማርያም አርጋለች።

 ከእመቤታችን 33ቱ ዓበይት በዓላት መካከል የሆነው ከግንቦት 21-25 እመቤታችን በደብረ ምጥማቅ ለ5 ተከታታይ ቀናት በአካል ትገለጥበት የነበረው በዓል መታሰቢያ ነው። መልካም በዓል!
29/05/2025



ከእመቤታችን 33ቱ ዓበይት በዓላት መካከል የሆነው ከግንቦት 21-25 እመቤታችን በደብረ ምጥማቅ ለ5 ተከታታይ ቀናት በአካል ትገለጥበት የነበረው በዓል መታሰቢያ ነው።

መልካም በዓል!

[ግንቦት 11 የቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ በዓል]✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ♥♥ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አባቱ አብዩድ (ይሥሐቅ) እናቱ ክርስቲና (ታውክልያ) ሲባሉ የተወለደውም በ፭፻...
19/05/2025

[ግንቦት 11 የቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ በዓል]
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
♥♥ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አባቱ አብዩድ (ይሥሐቅ) እናቱ ክርስቲና (ታውክልያ) ሲባሉ የተወለደውም በ፭፻፭ ዓ.ም. በአክሱም ነው፡፡ ሰባት ዓመት ሲመላው አባቱ ስላረፈ፤ እናቱ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እንዲያስተምረው ለአባ ጌዴዎን ሰጠችው፡፡ ነገር ግን ማጥናት ስላልቻለ አባ ጌዴዎን ይቈጣው ነበርና ሸሽቶ ከዱር ውስጥ ገባ፤ ከዐዘኑም ብዛት የተነሣ በዛፍ ሥር ተጠልሎ ሳለ አንዲት ታናሽ ትል ከዛፍ እኩሌታ ደርሶ ሲወድቅ ሲነሣ በመጨረሻም በጭንቅ ከዛፉ ላይ ሲወጣ በማየቱ እግዚአብሔር በዚኽች ታናሽ ፍጥረት እንዳስተማረው በመረዳት ይቅርታ ጠይቆ ወደ መምህሩ ተመልሷል፡፡

♥ “ወእምዝ ሶበ ሰአለ ኀበ እግዚአብሔር በብካይ ብዙኅ ተርኅወ ልቡናሁ ወተምህረ በሐጺር ዕለት መጻሕፍተ ብሉይ ወሐዲስ” ይላል ከዚኽ በኋላ ቅዱስ ያሬድ ወደ እግዚአብሔር በለመነ ጊዜ ልቡናው ብሩህ ኾኖለት በዐጭር ጊዜ ውስጥ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን ተምሮ በመጨረስ ዲቁናን ተሾመ፤ እስከ ርሱ ዘመን በማነብነብ እንጂ በከፍተኛ ድምፅ የመዝሙር ማሕሌት አልነበረም፤ እግዚአብሔርም ለዚኽ አባት የመላእክትን ዝማሬ ሊያሳየው ስለወደደ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ሦስተኛው ሰማይ እንደተነጠቀ ኹሉ ሊቁም ተነጥቆ የኻያ አራቱ ካህናተ ሰማይን የምስጋና ዝማሬ ሰምቶ ተመለሰ፡፡

♥ ቅዱስ ያሬድ ከአርያም ወርዶ ወደ ምድር እንደ ደረሰ ወደ አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ገብቶ፡- “ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ” (ለአብ ምስጋና ይገባል፣ ለወልድም ምስጋና ይገባል፣ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፡፡ ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ ዳግመኛም ለሙሴ የድንኳኑን ሥራ እንዴት እንደሚሠራ አሳየው) ሲል ዘምሮ ይቺኑ መዝሙር ከሰማይ መላእክት አገኘኹት፣ በማለት አርያም በሚል ሥያሜ ጠርቷታል፡፡

♥ይኽነኑ ድርሳነ ዜማ የጻድቁ ካሌብ ልጅ ንጉሥ ገብረ መስቀል በሰማ ጊዜ ጫማውን ሳይጫማ ንግሥቲቱም ደንገጡሮቿን አጃቢዎቿን ሳታስከትል መኳንንቱ፣ ካህናቱና መምህራኑ እነሱን ተከትለው እየተጣደፉ ወደ ዐደባባዩ በመኼድ በተመስጦ ሲሰሙት ውለዋል፡፡

♥ ቅዱስ ያሬድ ዐምስት የዜማ መጻሕፍትን የደረሰ ሲኾን እነርሱም
፩ኛ) ድጓ
፪ኛ) ጾመ ድጓ
፫ኛ) ምዕራፍ
፬ኛ) ዝማሬ
፭ኛ)መዋሥዕት ናቸው፡፡

♥ እነዚኽንም ታላላቅ ድርሰቶቹን በሦስት የዜማ ስልቶች ማለት በግእዝ፣ በዕዝል፣ በአራራይ አዘጋጅቷቸዋል፡፡ “ወአሐተ ዕለተ እንዘ ይዜምር ያሬድ ቀዊሞ ታሕተ እገሪሁ ለንጉሥ ገብረ መስቀል ወእንዘ ያጸምዕ ንጉሥ ቃሎ ለያሬድ ተከለ በትረ ኀጺን ውስተ መከየደ እግሩ ለያሬድ” ይላል፤ ከዕለታት ባንዳቸው ቅዱስ ያሬድ በተመስጦ ልዑል እግዚብሔርን በዝማሬ ሲያመሰግን ንጉሥ ገብረ መስቀል ሳያውቁት ልባቸው በጣዕመ ዜማው በመመሰጡ የብረት ዘንጉን በቅዱስ ያሬድ እግር ላይ ተክለውታል፤ ከእግሩም ብዙ ደም ቢፈስስም ቅዱስ ያሬድ ግን ማሕሌቱን እስከሚፈጽም ድረስ ምንም አልሰማውም ነበር፡፡

♥ንጉሡም የደሙን መፍሰስ አይቶ ደንግጦ ቅዱስ ያሬድን “የደምኽ ዋጋ የፈለግኸውን ንገረኝ” አለው፤ ቅዱስ ያሬድም ተምኔቱ ወደ ገዳም መኼድ እንደኾነ ነገረው፤ ያን ጊዜ ንጉሡ እያዘነ አሰናብቶታል፡፡

♥ “ወእምዝ ቦአ ያሬድ ውስተ ቤተ ክርስቲያን ወቆመ ቅድመ ታቦተ ጽዮን” ይላል ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በታቦተ ጽዮን ፊት በመቆም የአንቀጸ ብርሃንን ምስጋና ከመዠመሪያው እስከ መጨረሻው በተናገረ ጊዜ በእግዚአብሔር ኀይል ክንድ ያኽል ከምድር ከፍ ከፍ አለ፤ ከዚኽ በኋላ ወደ ሰሜን ተራራዎች ወደ ገዳም ሲኼድ የአኲስም ጽዮን ካህናት እስከ ተከዜ ወንዝ ድረስ ሸኙት ርሱም እጅግ ባማረ ጣዕመ ዜማ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ሰላም እግዚአብሔር ኲሉ ባቲ ተሃሉ ወትረ ምስለ ኲልክሙ” (በኹሉ ላይ ጸንታ የምትኖር የእግዚአብሔር ሰላም ዘወትር ከኹላችኊ ጋር ትኑር) ብሎ የስንብት መዝሙርን ዘመረ፤ ካህናቱም ይኽነን ቃል ሰምተው መሪር እንባን አለቀሱና ተሰነባበቱ፡፡

♥ በትርጓሜ ቅዳሴ ማርያም መቅድም ላይ እንደምናነብበው ቅዱስ ያሬድ ማይ ኪራህ በተባለው ቦታ ተሰውሮ ጸዋትወ ዜማን ሲያስተምር እመቤታችን ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምን የብህንሳውን አባ ሕርያቆስን በአካለ ነፍስ እንዲመጡ አድርጋ ኤፍሬም ውዳሴዬን፤ ሕርያቆስ ቅዳሴዬን ነግራችኹት ቅዱስ ያሬድ በዜማ ይድረስልኝ ብላ ነግረውት በዜማ ደርሶታል፤ ይኽም ሊታወቅ ሥረይ በቅዳሴ ማርያም ይበዛል፡፡

♥ ርሱም ጸዋትወ ዜማን ለደቀ መዛሙርቱ እያስተማረ መላእክት ዘወትር እየጐበኙት በጾም በጸሎት ተወስኖ በተጋድሎ ለኻያ ኹለት ዓመት ጸንቶ ኖረ፤ በመጨረሻም ጌታችንም ለቅዱስ ያሬድ ተገልጾለት “ኦ ፍቁርየ ቀዳሚኒ በከመ ሰመርኩ ትርአይ ሥርዐተ ስብሐተ መላእክት ዘበሰማያት ወአስተኀለፍከ ዘንተ ማሕሌተ ዲበ ምድር... ” (ወዳጄ ሆይ ቀድሞ በሰማይ ያለ የመላእክትን ሥርዐተ ማሕሌት እንድታይና ወደ ምድርም አስተላልፈኽ ይኽነኑ ዜማ እንድትመሠርት እንደ ወደድኊ ኹሉ እኔ ዳግም ተመልሼ በምመጣበት ጊዜ ከካህናተ ሰማይና ሄሮድስ ደማቸውን ካፈሰሰው ሕፃናት ጋር በደብረ ጽዮን ትዘምር ዘንድ ሰማያዊ የክብር አክሊልና የብርሃን ልብስ ተዘጋጅቶልኻል” ብሎት ቃል ኪዳንን ሰጥቶት በክብር ዐረገ፡፡ የቅዱስ ያሬድ መታሰቢያውም ግንቦት ዐሥራ አንድ ነው፡፡

♥ ሊቁ አርከ ሥሉስም የቅዱስ ያሬድን ነገር በአርኬው ላይ፦
“ሰላም ለያሬድ ስብሐተ መላእክት ለሕዋጼ
እንተ አዕረገ በልቡ ኅሊና መንፈስ ረዋጼ
ለትምህርተ መጽሐፍ ገብአ እምኀበ ኮነ ነፋጼ
በብዙኅ ጻማ ዘአልቦ ሑጻጼ
መልዕልተ ጒንደ ዖም ነጺሮ እንዘ የዐርግ ዕጼ”
(የመላእክትን ምስጋና ለመጐብኘት ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጥ ፈጣን ዐሳብን ወደ ልቡናው ያሳረገ ለኾነ፤ ጒድለት በሌለበት በብዙ ድካምም ወደ ዛፍ ግንድ ጫፍ ላይ ትል ሲወጣ ተመልክቶ፤ ኰብልሎ ከኼደበት መጻሕፍትን ለመማር የተመለሰ ለኾነ ለያሬድ ሰላምታ ይገባል) በማለት ሊቁ ማሕሌታይን አመስግኖታል፡፡

♥ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ ማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን ሊቁ ቅዱስ ያሬድን ሲያወድስ፡-
“ሰላም ለያሬድ ቀሲስ ዘጽጉብ እክለ መንፈስ ቅዱስ፤
ዘአስተጋብአ ምድራሳተ እምኲሎሙ መጻሕፍት
ወአሰርገዋ በሐዋዝ ስብሐት ወበጥዑም ማሕሌት
ለብሔረ ኢትዮጵያ በስብሐት ሃሌ ሉያ
ዘከዐወ ቃለ መለኮት ዲቤሃ
ከመ አስራበ ወርቅ ንጹሐ”፡፡
(የመንፈስ ቅዱስን ምግብን የጠገበ፤ ከመጻሕፍት ኹሉ ትርጓሜያተ ድርሰትን ያሰባሰበ፤ ሃሌ ሉያ በሚል ምስጋና የኢትዮጵያ ሀገርን በጥዑም ማሕሌትና በሚያምር ምስጋና ያስጌጠ፤ የመለኮት ቃልን በላይዋ ላይ እንደ ንጹሕ የወርቅ ሻሻቴ ያፈሰሰ ለኾነ ለካህኑ ያሬድ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡

[የጽሑፉ ምንጭ፡- አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የደረሰው ተአምኆ ቅዱሳን ንባቡና ትርጓሜው በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ የተጻፈ፤ ከገጽ 232-235]፡፡
የቅዱስ ያሬድ በረከት ይደርብን፤ እናንተም ይኽነን ሊቅ አወድሱት

"እነሆ ለህዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምስራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት  እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኃል"(ሊቃ ፪÷፲-፲
07/01/2025

"እነሆ ለህዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምስራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኃል"(ሊቃ ፪÷፲-፲

ሐዲስ ሐዋርያ ዘኢትዮጵያ   እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ የልደታቸው መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን !!!" ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወ...
02/01/2025

ሐዲስ ሐዋርያ ዘኢትዮጵያ

እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ የልደታቸው መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን !!!

" ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል።"
ማቴ. ፲፥፵፩ /10፥41/

✝️ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከአባታቸው ከካህኑ ፀጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀሪያ በታህሣሥ ፳፬ /24/ ቀን ተወለዱ

✝️ አባታችን በመላው ሀገራችን በመዘዋወር ወንጌልን የሰበኩ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያን ሥጋን ድውያን ነፍስን የፈወሱ አባት ናቸው

✝️ ተክለ ሃይማኖት የስማቸው ትርጓሜ ፍሬያማ ዛፍ፣ የእግዚአብሔር ተክል" ማለት ነው

✝️ በጻድቃን መኖር ሀገር ከጥፋት ትድናለች

✝️ የጻድቃንን ስም ጠርቶ እግዚአብሔርን በመለመን በረከትና ረድኤት ይገኛል

✝️ ጻድቃንን ማሰብ ሥራቸውን መዘከር ክርስቲያናዊ ሕይወታችንን ያጎለምሰዋል

✝️ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ደግሞ ከእነዚህ ጻድቃን መካከል ዋንኛው ናቸው

እግዚአብሔር አምላካችን የጻድቃን ቅዱሳኑን ጸሎት ሰምቶ ካለንበት መከራ ያውጣን። የአባታችን የጻድቁ ተክለ ሃይማኖት በረከትና ምልጃ አይለየን።




#ቅዱሳን
#ድንግል
#ተዋህዶ

#ኢትዮጵያ

                                        መዝ 23፥6💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
27/12/2024


መዝ 23፥6
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

 እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል አደሰን፣አደረሳችሁ!!!
12/12/2024


እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ዓመታዊ በዓል አደሰን፣አደረሳችሁ!!!

30/11/2024

የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች

ቴሌግራም፡- http://t.me/mkpublicrelation

የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት፡- http://www.facebook.com/eotcmkidusan/

የማኅበረ ቅዱሳን ሕዝብ ግንኙነት:-https://www.facebook.com/mahiberekidusan.mkusa/

ኢንስታግራም፡- http://www.instagram.com/pr.deputy/

ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org

ትዊተር፡- http://www.twitter.com//

ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK

30/11/2024

MK TV || ዕለታዊ መረጃዎች || በሸርካ ወረዳ 11 ኦርቶዶክሳውያን ተገደሉ
https://youtu.be/qsqgp15tpaQ

Address

St. Mikael
Debark'

Telephone

+251988231626

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደባርቅ ደ/ሳ/ቅ/ሚካኤል ቃለህይወት ሰ/ት/ቤት D/D/Sahle St.Michael QaleHiwot Sunday School posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to ደባርቅ ደ/ሳ/ቅ/ሚካኤል ቃለህይወት ሰ/ት/ቤት D/D/Sahle St.Michael QaleHiwot Sunday School:

Shortcuts

Share