ደባርቅ ባህረል ኑር መድረሳ/Haji Edris Mussa Debark

ደባርቅ ባህረል ኑር መድረሳ/Haji Edris Mussa Debark Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ደባርቅ ባህረል ኑር መድረሳ/Haji Edris Mussa Debark, Religious school, Debark, Debark'.

በደባርቅ ከተማ የሚገኙ የባሕረኑር ደረሶች ረቢዒን በመድረሳችን በማለት " ሙሀመድ የእውነተኛው መንገድ ብርሃን"    " ኑሩል ሂዳያህ" በሚል መሪ ቃል  ዛሬ ሐሙስ መስከረም 8 / 2018ረቢ...
18/09/2025

በደባርቅ ከተማ የሚገኙ የባሕረኑር ደረሶች ረቢዒን በመድረሳችን በማለት
" ሙሀመድ የእውነተኛው መንገድ ብርሃን"
" ኑሩል ሂዳያህ" በሚል መሪ ቃል ዛሬ ሐሙስ መስከረም 8 / 2018
ረቢዑል አወል 26 /1447 ሂ. በድምቀት ተከብሮ ውሏል ይህ መውሊድ እንዲሳካ በጉልበት፣ በዱዓ፣በገንዘብ እና በተለያዩ ነገሮች ድጋፍ ያደረጋችሁ ደረሶች፣ሙሂቦች እና የኢትዮጵያ ኢስላማዊ አስተምህሮ ማህበር/ መርከዝ ምስጋናችን የላቀ ነው ጀዛከሏሁ ፊኩም

በደባርቅ ከተማ የሚገኙ የባሕረኑር ደረሶች ረቢዒን በመድረሳችን በማለት " ሙሀመድ የእውነተኛው መንገድ ብርሃን"    " ኑሩል ሂዳያህ" በሚል መሪ ቃል  ዛሬ ሐሙስ መስከረም 8 / 2018ረቢ...
18/09/2025

በደባርቅ ከተማ የሚገኙ የባሕረኑር ደረሶች ረቢዒን በመድረሳችን በማለት
" ሙሀመድ የእውነተኛው መንገድ ብርሃን"
" ኑሩል ሂዳያህ" በሚል መሪ ቃል ዛሬ ሐሙስ መስከረም 8 / 2018
ረቢዑል አወል 26 /1447 ሂ. በድምቀት ተከብሮ ውሏል ይህ መውሊድ እንዲሳካ በጉልበት፣ በዱዓ፣በገንዘብ እና በተለያዩ ነገሮች ድጋፍ ያደረጋችሁ ደረሶች እና ሙሂቦች ምስጋናችን የላቀ ነው ጀዛከሏሁ ፊኩም

17/12/2024

" መዲና ከተማ ካሏት ብዙ ስያሜዎች ውስጥ አንዱ "المحبوبة" (ተወዳጇ) የሚለው ስሟ ነው :: በዛም የተሰየመችው ሰይዳችን صلى الله عليه وسلم ስለሚወዷት፣ አሏህም ለሚወዳቸው ነብይ صلى الله عليه وسلم መኖርያም ማረፊያም አድርጎ መርጦ ስለወደዳት ነው ::
አሏህም ጋር መልክተኛው صلى الله عليه وسلم ጋር ልክ እንደዛውም አጠቃላይ ሙዕሚኖችም ጋር ተወዳጅ ናት :: በትውስታዋ ብቻ ውስጥ የሚረካው፣ ውስጧ በያዘችው ሚስጥርም ልብ የሚዋልለው ለዚህ ነው .."

📗 አል ኢማም አስ'ሰምሁዲ'ይ
"ወፋኡል ወፋእ ቢአኽባሪ ዳሪል ሙስጦፋ" ከተስኘው ኪታባቸው
https://t.me/mededulhabib

አሏህ የወዳጆቹ ወዳጅም ተወዳጅም ያድርገን☺️

ደባርቅ ባህረኑር መድረሳ መውሊደ ረሱል ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም መውሊድ  ኻዲሞቻችንን ዘይረን ሞቅ ደመቅ ወዳለው ኻድራ ገብተናል
01/10/2024

ደባርቅ ባህረኑር መድረሳ መውሊደ ረሱል ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም መውሊድ ኻዲሞቻችንን ዘይረን ሞቅ ደመቅ ወዳለው ኻድራ ገብተናል

06/09/2024
17/08/2022

©የአላህ ሠላም በውዱ ረሡላችን ሰ.ዐ.ወ ይስፈን

ዑመር ረዐ ድንገት ረሱል ሰዐወ ወደተኙበት ደሳሳ ጎጆ ሲገባ ህመሙን ሚያብስበት ትዕይንት ተመልከተ።

እዝያች ደሳሳ ጎጆ ውስጥ በተነጠፈች ብጣሽ የግመል ቆዳ ላይ ረሱል ሰዐወ በሳር የተሰራ ትራስ ተንተርሰው ተኝተዋል።

የተኙባት ቆዳ አርጅታ ጫፍ ጫፏ ተበላልቷል። የቆዳው ድርቀት መላ ሰውነታቸው ላይ ሰንበር አውጥቶ ገላቸው ተጎድቷል።

ከተኙበት ክፍል ቁና እማትሞላ ገብስ በስልቻ ተደርጎ ጥግ ላይ ተቀምጧል። የድህነት መገለጫዎችን በሙሉ ዑመር ከረሱል ሰዐወ ቤት ሲመለከት ስሜቱ አስገድዶት እንባውን ያፈስ ጀመር።

ነቢ እንባውን ተመለከቱት፦‹‹ዑመር ምን ሁነኃል? ለምን ታለቅሳለህ?›› አሉትም።
ዑመር ረዐ ሲቃ ከሚተናነቀው ድምፅ ጋር ግብግብ እየፈጠረ፦‹‹ነቢዋ! ገላዎት ባለቀ የቆዳ ንጣፍ ሰንበር አውጥቶ እያየሁ እንዴት አላልቅስ?! ከርስዎ ክፍል ይህችን ምታክል ገብስስ እየተመለከትኩ እንዴት አላልቅስ?!

የሮም እና የፐርሺያ ንጉሳን በወርቅ እና በአልማዝ ባሸበረቁ አልጋዎች ላይ የሀር ጨርቅ አንጥፈው በፍራፍሬዎች እልፍኝ ተደላድለው ሲኖሩ እርሶ የአላህ ነቢይ እና ውድ ሁነው እንዴት?! ›› ብሎ የቁጭት ለቅሶውን ቀጠለ።

ነቢ ፈገግታ ከፊታቸው እያስነበቡት እንዲህ አሉት፦‹‹ዑመር! እነሱ እኮ ድሎታቸው የፈጠነላቸው ሰዎች ሲሆኑ በቅርቡ ከድሎት ይቋረጣሉ።

እኛ ደግሞ ፀጋዎቻችን ወደ ጀነት የተሸጋገረላቸው ህዝቦች ነን፤ ታድያ ዱንያ ለነሱ ሁና አኪራ ለኛ እንድትሆን አትፈልግም እንዴ? ››

ዑመር ንግግራቸው ቢያሳምነውም ምቾት አልሰጠውም፦‹‹ነቢዋ! ታድያ ሌላው እንኳ ቢቀር ለምን ከዚህ ለስለስ ባለ ምንጣፍ ላይ አይተኙም? ›› አላቸው በስስት እየተመለከተ።

ነቢ ጉዳዩን ግልፅ ሊያደርጉለት ፈለጉና ጠንከር አሉ፦‹‹ዱንያ እና እኔን ምን አገናኘን?! እኔ እና ዱንያ ማለት እኮ ልክ የበረኃ ተጓዥ በአንዲት ጥላ ተጠልሎ ፀሀይዋ ስትበርድ ጉዞውን እንደሚቀጥለው ነው እኮ (ጥላዋ ስር እድሜ ልኩን አይኖርም)››

ሰላሏሁ አላ ነቢዪና ሙሐመድ

15/08/2022

# ኢትዮጵያ_ማናት ?
የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሶለም 3ተኛ ኸሊፋ
ሰይዲና ዑስማን ኢብኑ አፋን ሁለቴ የጎበኟት፣
የረሱለሏህ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ልጅ (ሩቂያ) በልታ ጠጥታ አድራ ውላ
ያደረችባት፣
ረምላ ቢንት አቡ ሱፊያን ከነቢዩ ጋር ጋብቻ ፈፅማ የተደገሰባት፣
ሙስዓብ ኢብኑ ዑሜይር ለይል እየቆመ ቁርዐን የቀራባት፣
አምር ኢብኑ ዓስ የሰለመባት፣
አብድረህማን ኢብኑ ዓዉፍ ዘዴ የተማረባት፣
ጀህፈሩል ጠያር ኢልም ያስተማረባት፣
ሶሓቦች የተወለዱባት እና የተቀበሩባት…
" መሰረተ ጠንካራ ናት ማንምየማይጥላት "
በአሉባልታ ሳይሆን በተግባር የሞከሯት
ተዋርደው ፣ አንሰው ፣ ተንኳሰው
የተመለሱባት ታላቅ ሀገር ነች!!!
ስትነቃነቅ የምትወድቅ እንዳይመስልክ!
መነቃነቋ እውነተኛውን ከውሸታሙ ለማበጠር ነው’ንጂ
እሷ መቼም አትወድቅም ትጥላለች እንጂ
እንደ፧፦ አባይ ወንዝ መሬት ላይ ብትመለከታትም ?
እወቅ!!! ወንድሜ ልንገርህ እንደ አባይ ወንዝም መሰረቷ ከላይ ነው።
የእነ ሰይዱና ነጃሺ ፣ የሰይዱና ቢላል ፣ የሉቅማነል ሐኪም
" የብዙ ሳዳቶች ሀገር ናት!!! "
ሰይዱል አሪፊን ሼኽ ኑር ሁሴን አህለል በይቲ ረሱለሏህ ፣ ሰይድ አህመደል
በደዊ ፣ እነ ጀዲ ዑስማን የፋጢማ ዘሮች……
ያለፉባት እና የተቀበሩባት ሀገር ነች!!!
ረሱሉ ( ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም )
ሐበሻን አትንኩ!!! ሐበሻን የነካ ወዮለት ያሉት ለሶሓቦች ነበር እንደሌላ ሀገር
እንዳትመስላቸው ። የዚህን የማስጠንቀቂያ ምስጥሩ ምን ይሆን ? እስቲ
ኡለሞች ጋር ቀርበህ ጠይቅ!!!
ሐበሻ ምንድን ናት ብለህ ።
ሐበሻ የእውነት ሀገር ፣ ፍትሃዊ ንጉስ ያለባት ሀገር ናት ። ረሱሉ ( ሰለሏሁ
ዐለይሂ ወሰለም ) ሐበሻን አሏህ ይባርካት ያሉት ንግግራቸው የጀሊሉ ስለመሆኑ
አትጠራጠር!!!
ህዝብ ፊት ሌላ መልክ ፣ ጓሮ ጓሮ ሌላ ፊት የሚቀይር ሰው ነገ ሁለት የእሳት
ምላስ ይገጠምለታል ብለዋል!
ረሱሉ ( ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም )!!!
ከረሱላችን ( ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ) ጋር ከነበሩ ከመካም ከመዲናም ሰዎች
መካከል ሙናፊቆች ነበሩ። ግን ከሐበሻዎች ውስጥ የመሀባ ባህር ውስጥ
ሰምጠው ራሳቸውን የረሱ አንጂ አስመሳይ ሙናፊቆች አልተገኙባትም!!
የኃላው ከሌለ የለም የፊቱ ።
አሏህም ለሰይዳችን ( ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ) ከሳቸው በፊት የነበሩትን
የቀዲሞችን መናቂብ ይነግራቸው ነበር ሰምተው እንዲከተሉ ያ ሐቢቢ ያ
ሙሐመድ የአባትህን የኢብራሂምን መንገድ ተከተል ነበር ያላቸው።
ወንድሜ በሲልሲላ ወደ ኃላ ስንመለስ ፧፦
ዑለሞችን ፣ መሻዒኾችን ፣ ወሊዮችን ፣ ሷሊሂዎችን ፣ ሰለፎችን ፣ ታቢኢኖችን ፣
ሶሃቦችንና ረሱላችን ( ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ) እናገኛለን!!!
ወንድሜ እህቴ ?!!
የመሻይኾቻችንን ድልድይ መጠበቅ ፣
ማስቀጠል እና ማስፋፋት ሓላፊነታችን ነው!!!

[የአሏህ መልእክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም መዲና በገቡ ጊዜ ሁሉ ነገሯ አበራ]                       🌴اللهم صل على سيدنا محمد وعلى ءاله وصحبه وسلم🌴
04/08/2022

[የአሏህ መልእክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም መዲና በገቡ ጊዜ ሁሉ ነገሯ አበራ]
🌴اللهم صل على سيدنا محمد وعلى ءاله وصحبه وسلم🌴

31/07/2022

አሰላሙ ዓለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ
የሸኾቹ የመጀመሪያ ልጅ የሆነችው ጣህራ እድሪስ በገጠማት ድንገተኛ ህመም ወደ አኺራ ሂዳለች። ለሸኾቹ እና ለመላው ቤተሰባቸው አሏህ ሶብሩን ይስጣቸው እሷንም ጀነተል ፊርደውስ አሏህ ይወፍቃት!!
በያለንበት ፋቲሃ እንቅራ ዱዓ እናድርግላቸው

Address

Debark
Debark'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደባርቅ ባህረል ኑር መድረሳ/Haji Edris Mussa Debark posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share