Dabat Woreda Education Office-Dabat

Dabat Woreda Education Office-Dabat ​Let Dabat teach the awakened generation!
!

19/08/2026

ሁሉም ወላጅ ተማሪ ልጆቹን ከነገ ሐሙስ እስከ መጪው ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም ድረስ እንድታስመዘግቡ እያልን የዳባትና የወቅን ከተማ ትምህርት ቤቶች በሙሉ ነገ ነሐሴ 14 እና 15 ሙሉ በሙሉ እንዲመዘገቡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!

በ2019 የትምህርት ዘመን ከ355 ሺ በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ መታቀዱን የሰሜን ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ አስታወቀዳባት፡ ነሀሴ 13 /2018 ዓ.ም (ዳባት ኮሙዩኒኬሽን)"ትምህርት ከ...
19/08/2026

በ2019 የትምህርት ዘመን ከ355 ሺ በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ መታቀዱን የሰሜን ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ አስታወቀ

ዳባት፡ ነሀሴ 13 /2018 ዓ.ም (ዳባት ኮሙዩኒኬሽን)"ትምህርት ከፖለቲካ እና ከሀይማኖት ነጻ የሆነ ትውልድ የሚቀረጽበት ተቋም ነው " በሚል መሪ ቃል የተማሪ ምዝገባ ንቅናቄ በዳባት ከተማ ተካሂዷል።

በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የባከነውን የትምህርት ጊዜ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በተሟላ ሁኔታ ለማስጀመር ከትምህርት አመቻቾች፣ ከትምህርት አመራሩ፣ ከርዕሳነ መምህራን፣ከሱፐርቫይዘሮች፣ከሀይማኖት አባቶች፣ከሀገርሽማግሌዎች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላቶች ጋር ውይይት ተደርጓል።

በ2019 የትምህርት ዘመን ከ3 መቶ55 ሺ በላይ ተማሪችን ለመዝገብ ማቀዳቸውን የሰሜን ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ትምህርት ምሪያ ኃላፊ አቶ ክቡር አሰፋ ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ሶስት ዓመታት በትምህርት ተቋማቱ ላይ የትምህርት ስብራት የተከሰተበት መሆኑን የጠቆሙት አቶ ክቡር አሰፋ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን አንስተዋል ፡፡

በትምህርት ዘመኑ ሁሉም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመዘገቡ እና የተዘጉ ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ ለማስቻል በቁረጠኝነት አየሰሩ መሆናቸውን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

ዞኑ ካለው መልካም ምድራዊ አቀማመጡ፣ከሰሜኑ ጦርነትና በክልሉ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት በትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ ስብራት መድረሱን ገልጸዋል፡፡

ትምህርት ከፖለቲካና ከሃይማኖት ነጻ ሆኖ በ2019 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲቀጥል ለማስቻል ያለመ የንቅናቄ መድረክ መካሄዱን የዳባት ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አትርሳው ክንዴ አስረድተዋል፡፡

በ2017 ዓ.ም ከ90 ትምህርት ቤቶች መካከል 77 የትምህረት ተቋማት መዘጋታቸውን ያነሱት አቶ አትርሳው 35ሺ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

በ2018 ዓ.ም 36 አንደኛ ደረጃ እንዲሁም ሁለት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ተመላክቷል፡፡

የትምህርት ተቋማት መዘጋታቸው ያለእድሜ ጋብቻ፣ለቤት ሰራተኝነት አና ሴት ተማሪዎች ለጾታዊ ጥቃት መዳረጋቸው ተገልጿል፡፡

በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ የወደሙ የትምሀርት ተቋማቶችን ለመጠገን ህዝቡ፣መንግስት እና ባለድርሻ አከላቶች የድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል፡፡

የቀጣይ ዓመት የትምህርት ምዘገባ ከነሀሴ 14/2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 5 /2018 ዓ.ም ድረስ የተማሪዎች ምዝገባ እንደሚጠናቀቅ አቶ አትርሳው ክንዴ ገልጸዋል ፡፡

ባለፉት ሦስት ዓመታት በክልሉ በተፈጠረው የሰላም ዕጦት ምክንያት የትምህርት ስርዓቱ እንዲጓደል መደረጉን የውይይቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡

አስተያየታቸውን የሰጡት ስንታየሁ አቡሃይ እና እሸቴ ሓምዛ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸው ለስደት፣ለጉልበት ብዝበዛ ና አልባሌ ቦታ እንዲውሉ መዳረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ችግሮችን በውይይት በመፈታት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ሁሉም አካል ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት አስተያየት ሰጭዎቹ ጠይቀዋል፡፡

በ2019 የትምህርት ዘመን በወረዳው 64ሺ ተማሪዎችን ለመመዝገብ መታቀዱን እና ትምህረት መሰከረም አምስት እንደሚጀምር ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የዳባት ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት    ከ 2ሺ 500 በላይ ተማሪዎች የክረምት   የማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጠ መሆኑን አስታወቀ ዳባት፡ ነሀሴ 12 /2018 ዓ.ም (ዳባት ኮሙዩኒኬሽን)  እንደ...
18/08/2026

የዳባት ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ከ 2ሺ 500 በላይ ተማሪዎች የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጠ መሆኑን አስታወቀ

ዳባት፡ ነሀሴ 12 /2018 ዓ.ም (ዳባት ኮሙዩኒኬሽን) እንደ ዳባት ወረዳ 3ሺ 7መቶ ተማሪዎችን የክረምት ወራት የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት ታቅዶ ለ2ሺ 6 መቶ ተማሪዎች መሰጠቱን የዳባት ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አምባው ሙሌ አስታውቀዋል፡፡

ተማሪዎችን ብቁና ተወዳዳሪ ለማድረግ ከመደበኛ የትምህርት ፕሮግራም በተጨማሪ በክረምት ወራት የማጠናከሪያ ትምህርት መሰጠቱ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡና አልባሌ ቦታ እንዳይውሉ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ምክትል ኃፊው አስረድተዋል፡፡

የማጠናከሪያ ትምህርቱ በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እየተሰጠ ነው ብለዋል አቶ አምባው ።

በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፉ የሚስተዋለውን የውጤት ማሽቆልቆል ከ20 ፐርሰንት ወደ 30 ፐርሰንት ከፍ ለማድረግ የክረምት ወራት የማጠናከሪያ ትምህርቱ አጋዥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማሳለጥና ዲጅታል ለማድረግ ክልል ትምህርት ቢሮ 1 መቶ 75 ኮምፒውተሮችን፣ 40 መጽሃፎችን ድጋፍ በማድረግ ቤተመጽሃፍቶች እንዲጠናከሩ ተደርጓል ብለዋል፡፡

የማጠናከሪያ ትምህርቱ ተማሪዎች መደበኛ ትምህርታቸውን ካጠቀናቁ ጀምሮ ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ፣ በስነ - ልቦና ፣ በክህሎትና በአመለካከት የተሻሉ እንዲሆኑ ይረዳል ያሉት የዳባት 01 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ተስፋሁን መብራት ናቸው፡፡


በትምህርት ቤቱ 12 የተሻለ እውቀት ባላቸው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና በሰባት መደበኛ መምህርራን ቅንጅት ከ700 በላይ ተማሪዎች በስድስት የትምህርት አይነቶች የማጠናከሪያ ትምህርቱ እየተሰጠ መሆኑን ርዕሰ መምህሩ ተናግረዋል፡፡

የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጡ ያገኘናቸው የደባርቅ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ አመት ተማሪ ሃና ግርማቸው በህብረተሰብና በእንግሊዘኛ የትምህርት አይነት እየሰጡ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

የማጠናከሪያ ትምህርቱ ለመደበኛ ትምህርታቸው እንደሚያግዛቸው ተማሪዋ አስገንዝባለች፡፡

ሌላኛው በጎ ፈቃደኛ የደባርቅ ዩኒቨርስቲ የአራተኛ አመት ተማሪ ሙሉቀን ተስፋሁን በግብረ ገብ የትምህርት አይነት እየሰጠ ሲሆን ተማሪዎች በስነ -ምግባራቸው የተሻሉና የተሻለ ውጤት እንደያስመዘግቡ ጠንክረው እያስተማሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ትውልድን መቅረጽ ሃገርን ማስቀጠል ነው ያሉት ተማሪ ሙሉቀን ተማሪዎች ካለቸው እውቀት በተጨማሪ አንብቦ የመረዳት ባህላቸውን ማጠናከር ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

በዳባት 03 አንደኛና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የማጠናከሪያ ትምህርት እየተከታተሉ ያገኘናቸው ተማሪ እስጢፋኖስ እና ሶስና ስላንተ የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት በ2019 የትምህርት ዘመን ለሚጀምሩት የክፍል ደረጃ የተሻለ እውቀት እንዲኖራቸው ለማስቻል ፋይዳው የጎላ መሆኑን አንስተዋል።

የማጠናከሪያ ትምህርት አሰጣጡ ይጠቅማሉ በሚሉ ይዘቶች በመሰጠቱ ደስተኛ መሆናቸውንም ተናግረዋል።




የዳባት ወረዳ ት/ት ጽ/ቤት 1ኛ ዙር በቅሬታ የተሰራ ዝውውር👇👇👇
16/08/2026

የዳባት ወረዳ ት/ት ጽ/ቤት 1ኛ ዙር በቅሬታ የተሰራ ዝውውር👇👇👇

የአብክመ ት/ት ቢሮ 2ኛ ዙር የዝውውር የቅሬታ መልስ👇👇👇
14/08/2026

የአብክመ ት/ት ቢሮ 2ኛ ዙር የዝውውር የቅሬታ መልስ👇👇👇

በጠለምት ወረዳ በተከሰተ ድርቅ ከ3,000 በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው ተነገረ​በድርቁ 14 ሺህ የቁም እንስሳት ሞተዋል ተብሏል​«ጉዳቱን የሚያጠና ግብረ ኃይል አቋቁመን ወደ አካባቢው ልከናል...
09/08/2026

በጠለምት ወረዳ በተከሰተ ድርቅ ከ3,000 በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው ተነገረ

​በድርቁ 14 ሺህ የቁም እንስሳት ሞተዋል ተብሏል

​«ጉዳቱን የሚያጠና ግብረ ኃይል አቋቁመን ወደ አካባቢው ልከናል» የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር

​በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ በሚገኙ አስር ቀበሌዎች በተከሰተ ድርቅ 3,386 ነዋሪዎች ወደ አጎራባች ወረዳዎች መፈናቀላቸውን የጠለምጥ ወረዳ አስታወቀ።

​ከሚያዝያ ወር 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በወረዳው በሚገኙ 24 ቀበሌዎች ውስጥ በአስሩ ዝናብ ባለመምጣቱ 3,386 ነዋሪዎች ቀያቸውን ለቀው መሰደዳቸውንና 14,089 የቁም እንስሳት መሞታቸውን፤ የጠለምጥ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳነ እሸቴ ለሪፖርተር ተናግረዋል።

​እርን፣ በተል፣ በስቅያ፣ መረው ብላ፣ መረው ገብርኤል፣ አገጣ፣ ደረባ፣ ከረዋ፣ ነጋዴ መሸገሪያና አተባ የተባሉ ቀበሌዎች፤ እስካሁን ምንም ዝናብ ያላገኙ መሆናቸውን የጠቀሱት አቶ አዳነ፤ ሌሎች ስድስት ቀበሌዎች ደግሞ ከሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ዝቅተኛ የዝናብ መጠን እያገኙ መሆናቸውንና ቀሪዎቹ ስምንት ወረዳዎች ዝናብ እያገኙ መሆናቸውን አስረድተዋል።

​የሰሜን ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ክቡር አሰፋ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ከፍተኛ የዝናብ እጥረት መኖሩን ገልጸዋል።

​በጠለምጥ ወረዳ ብቻ ሳይሆን በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ድርቅ ያጋጠመ ቢሆንም፤ ከሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. በኋላ አንዳንድ ወረዳዎች ዝናብ መጣሉ መጀመሩን አቶ ክቡር አክለዋል።

​በድርቁ ምክንያት በጠለምት ወረዳ ደረሰ የተባለውን ጉዳት አጣርቶ መረጃ የሚያቀርብ ግብረ ኃይል ተዋቅሮ ወደ ወረዳው መላኩን የገለጹት አቶ ክቡር፤ እስካሁን በወረዳው ስለሞቱ እንስሳትም ሆነ ስለተፈናቀሉ ሰዎች የደረሳቸው መረጃ እንደሌለና የተጠና ነገር ባለመኖሩም የጉዳቱን መጠን ከመናገር ተቆጥበዋል።

​በሰዎችና በእንስሳት ላይ የደረሰ ጉዳት መኖሩ በጥናት ከተረጋገጠ፤ መረጃውን መሠረት በማድረግ ከመንግሥትና ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች እርዳታ ሊጠየቅ እንደሚችል አስታውቀዋል።

​የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ ይህንን ይበሉ እንጂ፤ የወረዳው ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳነ ግን፤ በአካባቢው ለረጅም ጊዜ አጥጋቢ ዝናብ ባለመምጣቱ በየወቅቱ የእንስሳት ሞትና የነዋሪዎች ስደት እንደሚያጋጥም ተናግረዋል።

​አሁንም በርካታ እንስሳት በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኙ የተናገሩት አቶ አዳነ፤ ከወረዳው በተገኘ የሁለት ሚሊዮን ብር የእንስሳት መድኃኒት መገዛቱን ጠቅሰዋል። በአካባቢው ማሽላና ጤፍ በብዛት እንደሚመረት የተናገሩት አቶ አዳነ፤ አርሶ አደሮች በሚያዝያ ወር የተለያዩ ሰብሎችን ዘርተው እንደነበር አስታውሰው፤ ነገር ግን ዝናቡ ወቅቱን ጠብቆ ባለመምጣቱ 9,088 ሄክታር መሬት ሰብል ማብቀል ሳይችል በመቅረቱ ለከሰራ መዳረጋቸውን ጠቅሰዋል።

​በአሁኑ ወቅት ወረዳው ዜጎችን ከድርቅ ለመታደግ አስፈላጊውን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ነገር ግን ከመንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አቶ አዳነ ጥሪ አቅርበዋል።

 ለዞናችን የ8ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ዘጠነኛ ክፍል በዚህ ዓመት በከፍተኛ ውጤት የተዛወራችሁ መስፈርቱን የምታሟሉ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የሠጠው የነፃ የትምህርት ዕድል ተጠቀሙ👇
09/08/2026


ለዞናችን የ8ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ዘጠነኛ ክፍል በዚህ ዓመት በከፍተኛ ውጤት የተዛወራችሁ መስፈርቱን የምታሟሉ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የሠጠው የነፃ የትምህርት ዕድል ተጠቀሙ👇

  ምክንያት በጊዜአዊነት ተመድባችሁ የነበራችሁ መምህራኖች  #በጊዜአዊነት ዝውውር ባለመሠራቱ ምክንያት ከ2016 እስከ 2018 ዓ.ም ድረስ የተመድባችሁ በመመሪያው መሠረት ወደ  #መደበኛ ት/...
07/08/2026

ምክንያት በጊዜአዊነት ተመድባችሁ የነበራችሁ መምህራኖች #በጊዜአዊነት ዝውውር ባለመሠራቱ ምክንያት ከ2016 እስከ 2018 ዓ.ም ድረስ የተመድባችሁ በመመሪያው መሠረት ወደ #መደበኛ ት/ቤታችሁ እንድትመለሱ እያሳስብን ት/ቤቶች በመደበኛ ዝውውር የተሠራላቸውን መምህራን ብቻ እንድታስተናግዱ እያልን ቋሚ መምህራኖቻችሁ ተከታትላች እንድታሰሩ እያልን ወደ መደበኛ ት/ቤታቸው ያልተመለሱ መምህራንን ተከታትሎ ሪፖርት ያላደረገ ተጠያቂ ይሆናል።ከመደበኛው ዝውውር ውጪ መምህራንን ተቀብሎ ያስተናገደ በአሰራሩ መሠረት ተጠያቂ ይሆናል።
ማሳሰቢያ:-ችግሩ ያልተፈታ ከሆነ ከፍትህና ከፖሊስ #የታደሠ ማስረጃ በማምጣት በመመሪያው መሠረት የምዕራቡ ወደ ምስራቅ የምስራቁን ወደ ምዕራብ በተመሳሳይ ርቀት ከነበሩበት ት/ት ቤት ተመጣጣኝ ሊሆን ወደ ሚችል ት/ቤቶች ክፍት ወደሆኑት ት/ቤቶች በዝውውር ኮሚቴው ምደባ ይሰጣል።

02/08/2026

በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት በቴክኖሎጅ ታርሞ ይፋ የተደረገ ሲሆን በክልሉ 173699 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው ይታወቃል። ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከልም 135003(77.72%)ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል። ይህ ውጤት ከ2017ዓ.ም ከተመዘገበው ውጤት ጋር ሲነፃፀር የ20% ጭማሪ(እድገት) ተመዝግቧል።

ተማሪዎችም ውጤታቸውን በሁለት አማራጮች ማየት የሚችሉ ሲሆን:-
➊ በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application ) ላይ
1) ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara.ministry.et/ #/result የሚለውን አድራሻ በመፃፍ
2) በሚመጣው ቅጽ (form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) እና ስም በአማርኛ በማስገባት
3) ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡

❷ በተጨማሪም በሚለው የቴሌግራም ቦት ላይ በመግባት ተማሪዎች ውጤታቸውን መመልከት የሚችሉ ሲሆን መጀመሪያ
1) start የሚለውን ይጫኑ!
2) በመቀጠልም ክፍልዎን ይምረጡ
3) ከዚያም ክልልዎን ይምረጡ
4) በመቀጠል የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምን በማስገባት ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

ተማሪዎች ማንኛውም ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ይችላሉ። ቅሬታቸውንም ለማቅረብ
➌ በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ላይ ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application ) ላይ
1) ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara.ministry.et/ #/complaint የሚለውን አድራሻ በመፃፍ
2) በሚመጣው ቅጽ(form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) እና የተማሪውን የመጀመሪያ ስም (First Name)በማስገባት
3) የትምህርት ዓይነት አሳይ(Fetch course) የሚለውን ቁልፍ በመጫን
4) ቅሬታ ማቅረብ የሚፈልጉበትን ይምረጡ
5) በመጨረሻም ሪፖርት (Add Complaint) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ።

ማስታወሻ ፡ በቅድሚያ ቪፒኤን ማጥፋት ይኖርባችኋል፡፡

👉 2018ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል።

Responsive admin theme build on top of Bootstrap 4

02/08/2026

🇪🇹 የደግነት ምላሽ ለአዲሱ የትምህርት ዘመን! 🙏
!
​ለተማሪዎቻችን ብሩህ ተስፋ በመሆን በድጋፍ ላይ ለተሳተፋችሁ ወገኖቻችን በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን። እስካሁን የተደረገው አጠቃላይ ድጋፍ፡

​ደብተር ገዝተው ያስረከቡ፦ 16 ደርዘን ደብተር

​በአካውንት ገቢ ያደረጉ፦ 11,150 ብር
አካውንት👉 አባይ ባንክ 27811131934680

​ቃል የተገበ፦ 38 ደርዘን ደብተር እና 1 ፓኮ እስክርቢቶ

​የተሳታፊዎች ዝርዝር፦

​1. ደብተር ገዝተው ያስረከቡ

​አቶ ሙሌ አንዳርጌ፣ አቶ ጋሻው ስዩም፣ ወ/ሮ አስችላ አማረ፣ ወ/ሪት አድና ሰይፉ፣ ወ/ሮ ታድላ ካሴ፣ አቶ አበጀ ገብሬ (እያንዳንዳቸው 1 ደርዘን / 600 ብር)

​አቶ ነጋሽ ምስጋናው፣ ወንድም ጌትነት ዱቤ (እያንዳንዳቸው 2 ደርዘን / 1,200 ብር)

​አቶ ደስታው አለባቸው፣ ወንድም ሰለሞን ሞላ (እያንዳንዳቸው 3 ደርዘን / 1,800 ብር)

​2. ገቢ ያደረጉ

​አቶ ክፍሌ አቡሃይ (650 ብር)

​አቶ ደጀን ምትኩ፣ ወገኔ አማረ፣ አትርሳው ክንዴ (እያንዳንዳቸው 1,200 ብር)

​ወ/ሮ አፀደ ማሞ (1,500 ብር)

​አቶ ሙሉቀን ፀጋነህ፣ አቶ ሀይለማርያም አባይነህ፣ አቶ አግኝቼ ጌጡ፣ አቶ ዳኘው ሙሃባው፣ አቶ ውቤ ዘውዱ፣ ስሙ ያልተነበበ ወንድም፣ አቶ አይቶልኝ ሙሉየ፣ አቶ ሞገስ አቡሃይ፣ ወንዴ በላይ (እያንዳንዳቸው 600 ብር)

​3. ቃል የገቡ👇

👉​አቶ አወቀ አደራጀው (4 ደርዘን)
👉ፋሲካ መረሳ፣ አቶ መኳንንት ጥጋቡ፣ አቶ አምባው ሙሌ (እያንዳንዳቸው 2 ደርዘን)
👉​አቶ ደጀን አስምሮ፣ አቶ አድሴ አለምነህ፣ አቶ አብዱ አድሴ፣ ወ/ሮ አዲስ አካሉ፣ አቶ አድኖ ገላው፣ አቶ እሸቱ ሲሳይ፣ አቶ ሙሉጌታ በውቀት፣ አቶ ሞገስ አቡሃይ፣ መልሰው ካሴ፣ አቶ አበበ ፈንቴ፣ አቶ በለጠ ደሴ፣ አቶ በለጠ ወረታ፣ አቶ ብርሃኑ ቤዛኩሉ፣ አቶ ጋሻው ስዩም፣ አቶ እንዳልክ አማረ፣ አቶ መሰለ አበበ፣ ወ/ሮ ዘርፌ ምህረት፣ አቶ ተቀባ ፈንታሁን፣ አቶ ደስይላል እንየው፣ አቶ ማንደፍሮ ታደሰ፣ ር/መ/ር ወርቅነህ ሰጠኝ፣ አቶ በሬ በየነ፣ ር/መ/ር ምስጋናው በለጠ፣ አቶ አደራጀው ጌታቸው፣ አቶ ይርጋ አለሙ፣ አቶ ሃብታሙ ሙሉ (እያንዳንዳቸው 1 ደርዘን)

​ቃል የገባችሁ ወገኖች ድጋፋችሁን ገቢ እንድታደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን።

Address

የጀግኖቹ ከተማ ዳባት
Dabat

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dabat Woreda Education Office-Dabat posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category