Kilto construction and industrial college

Kilto construction and industrial college We have avision to civilize our community

በብቃትና በጥራት የተደራጀ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶችን በማፍራት ሥራ አጥነትን መቀነስ ይገባል ተባለ።               ሚያዚያ 23/2015 ዓ.ም =============================...
02/05/2023

በብቃትና በጥራት የተደራጀ ሥራ ፈጣሪ ወጣቶችን በማፍራት ሥራ አጥነትን መቀነስ ይገባል ተባለ።

ሚያዚያ 23/2015 ዓ.ም
================================
የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን
================================

የቂልጦ ኮንስትራክሽን እና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2015 በጀት አመት ውስጥ ባለፉት 9 ወራቶች የተከናወኑ ተግባራትንና የቀጣይ የተማሪ ቅበላንና በሌሎች አጀንዳዎኝ ሁሉም የቦርዱ አባላት በተገኙበት ዝርዝር ውይይት ተደርጓል።

በአሁኑ ወቅት የሚስተዋለውን የስራ አጥ ቁጥር ከመቀነስ በዘለለ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂን በመቅዳት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ወጣቶችን ማፍራት እንደሚገባ ተገለፀ።

በ2015 በጀት አመት በ9 ወሩ ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትንና የኮሌጁን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በዝርዝር ለቦርዱ ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በቦርድ ስብሰባው ላይ የስልጤ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፈድሉ ከድር እንዲሁም ሁሉም የቦርዱ አባላት ተሳትፈዋል፡፡

በዋናነትም ኮሌጁ በቀጣይ ግዜያት ከሌሎች ባለድርሻ ሴክተር መስሪያቤቶችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የሚያከናውናቸው ተግባራትንና የቅንጅት ስራዎች ላይ አፅንኦት ተሰጥቶበታል፡፡

የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ መህዲያ ቡሴር እንደገለፁት የቂልጦ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከልና የምርምር ማዕከል እንዲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ተገቢውን የድጋፍና ክትትል ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡

አስተዳዳሪዋ አክለውም በኮሌጁ የሚሰለጥኑ ሰልጣኞች ብቁና በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ስራ ፈላጊ ሳይሆን ተፈላጊ እንዲሆኑ ቦርዱና የኮሌጁ ማህበረሰብ ሀላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ በትኩረት እየሰሩ እንደሆነ ገልፀዋል።

ወ/ሮ መህዲያ አክለውም የቂልጦ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ እያገጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመሻገር ብሎም ኮሌጁ የሚፈለግበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ የቦርድ አባላትና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት አለበቸው ብለዋል፡፡

የስልጤ ዞን ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፈድሉ ከድር በመድረኩ እንዳሉት የቦርድ አባላቱና ኮሌጁ በተናበበና በተቀናጀ መልኩ በመስራት በመደበኛና በአጫጭር ግዜ ስልጠናዎችን ለመውሰድ ወደ ተቋማት የሚገቡ ሰልጣኞች ቅበላን በተሻለ መልኩ መፈፀም ይገባል ሲሉ አሳስቧ፡፡

አቶ ፈድሉ ከድር አክለው እንዳነሱት ኮሌጁን አሁን ላይ ካለበት አንድ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ተማሪዎች ተገኝተው ትምህርታቸውን በአግባቡ ሲወስዱ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

ተማሪዎችን ወደ ኮሌጁ ገብተው የተለያዩ የትምህርት አይነትና ሙያ እንዲወስዱ እንዲሁም ኮሌጁን
ደረጃውን ከፍ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት በየ ቀበሌው በመግባት ለተማሪዎች ግንዛቤ በመፍጠርና በማስተባበሩ ረገድ ወሰኝ ሚና እንዳላቸውም ጠቁመዋል፡፡

የቂልጦ ኮንስትራክሽንና እንዱስትሪያል ኮሌጅ ዲን አቶ ከድር ቀጀላ በበኩላቸው የቂልጦ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ ሰልጣኞችን ለማፍራትና ኮሌጁ የሚፈለግበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ የቦርድ አባላትና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው ገልጿል፡፡

አቶ ከድር ቀጀላ አክለውም በበቂ ዕውቀትና ክህሎት የዳበሩ ኢንተርፕራይዞችን በብዛትና በጥራት በማፍራት ረገድ የሚስተዋሉ ጉድለቶችን በማረም የዘርፉን ውጤታማነት በተ

02/05/2023
የቂልጦ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ከክልል የተበረከተለትን 02 የmetal manufacturing department ማሽኖች ተረክቧል ።ማሽኖቹ 1·HYDRAULIC PIPE BENDING ...
08/04/2023

የቂልጦ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ከክልል የተበረከተለትን 02 የmetal manufacturing department ማሽኖች ተረክቧል ።ማሽኖቹ 1·HYDRAULIC PIPE BENDING MACHINE.
2.METAL CUTTING MACHINE ነቸው።

07/04/2023
የቂልጦ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ የCOC ምዘና ሰጠ።መጋቢት 29/07/2015የቂልጦ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን የመደበኛ ሰልጠኞች በተለያዩ ተቋማዊ ምዘናዎች...
07/04/2023

የቂልጦ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ የCOC ምዘና ሰጠ።

መጋቢት 29/07/2015

የቂልጦ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን የመደበኛ ሰልጠኞች በተለያዩ ተቋማዊ ምዘናዎችንና ትሬኒንጎችን እየሰጠ ቆይቶ ዘሬ መጋቢት 27/07/2015 ዕውቅና በገኛበቸው በተለያዩ ዲፐርትመንቶች ለሰልጠኞች ምዘና ሰጥቷል።ምዘናውንም በ
1·mechanics /metal manufacturing
2·Garment technology
3·structural construction
4·Furniture making
5·Food preparation/Trade
በምዘናው ከተቀመጡት ሰልጠኞች፣ኢንተርፕራይዞች እና የመንግስት ሰራተኞች መከከል 96% ቱ ምዘናውን በብቃት አልፈወል።

የቂልጦ/ኮ/ኢ/ኮሌጅ የቅድመ ምዘና ትሬኒንግ ዘሬ አጠናቀቀ  ።መጋቢት 28/07/2015 የቂልጦ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ለመደበኛ ሰልጠኞች፣ለኢንተርፕራይዞች እና ለመንግስት ሰራተኞ...
06/04/2023

የቂልጦ/ኮ/ኢ/ኮሌጅ የቅድመ ምዘና ትሬኒንግ ዘሬ አጠናቀቀ ።
መጋቢት 28/07/2015

የቂልጦ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ለመደበኛ ሰልጠኞች፣ለኢንተርፕራይዞች እና ለመንግስት ሰራተኞች ሲሰጥ የቆየውን የcoc የምዘና ትሬኒንግ ዘሬ አጠናቀቀ።
ኮሌጁ ነገ አርብ የcoc ምዘና በተለያዩ ዘርፎች ምዘና ይሰጠል።

የሁልበረግ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ከቂልጦ ኮ/ኢ/ኮ የልምድ ልውውጥ አከሄደ።
30/03/2023

የሁልበረግ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ከቂልጦ ኮ/ኢ/ኮ የልምድ ልውውጥ አከሄደ።

የቂ/ኮ/ኢ ኮሌጅ በአሰልጠኞች የተሰሩ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ለኢንተርፕራይዞች አሸጋገራ።የተሸጋገሩ ቴክኖሎጂዎች የማህበረሰቡን ችግር ሊፈቱ ይችለሉ ተብሎ የተሰቡና ኢንተርፕራይዙ አበዝቶ ወደ ህ...
28/03/2023

የቂ/ኮ/ኢ ኮሌጅ በአሰልጠኞች የተሰሩ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ለኢንተርፕራይዞች አሸጋገራ።የተሸጋገሩ ቴክኖሎጂዎች የማህበረሰቡን ችግር ሊፈቱ ይችለሉ ተብሎ የተሰቡና ኢንተርፕራይዙ አበዝቶ ወደ ህብረተሰቡ ተጠቀሚ እንዲሆን የሚያደርጉበትና ራሰቸውም ተጠቀሚ የሚሆኑበት ነው።የተሰሩ ቴክኖሎጂዎች በነፍስወከፍ ለተለያዩ ኢንተርፕራይዞች የተሰጡ ሲሆን
1· ቴራዞ መምረቻ ማሽን ለሙሀጅር ኮንስትራክሽን
2· ሶለር ፐኔል ቲልቲንግ/ትራኪንግ ማሽን ለብልጽግና(መሀመድ)
3· በቆሎ መፈልፈያ ማሽን ለሰኢድ
4·ሁለት አገልግሎት የሚሰጥ አከፈ ሲፈለግ አከፈ ለሌለ አገልግሎት ሲፈለግ ዘፒያ ሊሆንየሚችል ቴክኖሎጂ ለሶጀት ብረተብረት
5 ·ደብል ፌስ የበህል ልብስ እና የመሰሰሉት ነቹው በዝህም ፕሮግራም የኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት ሀለፊ የተገኙ ሲሆን ቴክኖሎጂዎቹ ወደ ህ/ሰቡ ወርደው ችግር ፈቺ መሆን አለበቸው ብለወል በሌለ በኩል የኮሌጁ ዲን አቶ ከዲር ከጄለ ቴክኖሎጂዎችን በመብዘት የማህበረሰቡን ትንሽም ችግር ቢሆን መፍተት አለበት የሉ ሲሆን ለቀጠይም ከኢ/ዞች ተበብረን እንሰራለን ብለወል።በተጫማሪም ከአሰልጠኞችና ከማኔጅመንት አበለት የተለያዩ ገንቢ ሀሰቦች ተነስተወል።

ረመዳን ሙባረክ!የታላቁ የመረዳን ፆም የፊታችን ሀሙስ መጋቢት 14 አንድ ብሎ እንሚጀመር ተገለፀእንኳን ለታላቁ የረመዳን ወር በሰላም አደረሰን‼️
21/03/2023

ረመዳን ሙባረክ!
የታላቁ የመረዳን ፆም የፊታችን ሀሙስ መጋቢት 14 አንድ ብሎ እንሚጀመር ተገለፀ
እንኳን ለታላቁ የረመዳን ወር በሰላም አደረሰን‼️

21/03/2023

Address

Kilto
Ciro

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kilto construction and industrial college posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Kilto construction and industrial college:

Shortcuts

Share

Category