Bonga University

Call Directions Website

Bonga University Bonga University is one of the Public Higher Educational Institution in Ethiopia.
(1)

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ግብ ተኮር ስርዓተ ትምህርት (OBE)  ግምገማ እያካሄደ ነው።‎‎*******ጥቅምት 02/2019 ዓ.ም ******‎ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ግብ ተኮር ሥርዓተ- ትምህርት (Outcom...
12/10/2026

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ግብ ተኮር ስርዓተ ትምህርት (OBE) ግምገማ እያካሄደ ነው።
‎
‎*******ጥቅምት 02/2019 ዓ.ም ******

‎ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ግብ ተኮር ሥርዓተ- ትምህርት (Outcome Based Education /OBE) Curriculum ውጫዊ ግምገማ (External Validation workshop እያካሄደ ይገኛል።
‎
‎በግምገማ መድረኩ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚ/ር የመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች አቶ አድነው ኤርበሎ እና አቶ መኮንን ታደስን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት
‎ከአቻ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተጋቡዙ እንግዶች
‎የዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

‎መድረኩን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የመማ/ማስ/ምር/ቴክ/ሸግ/ም/ፕ/ ከለለው አዲሱ (ዶ/ር) አስጀምረዋል።

ክቡር ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው እንደገለፁት የስርዓተ-ትምህርት ዝግጅት በቀላሉ የሚታይ ሳይሆን ዘርፈ ብዙ ክህሎት እና እውቀት የሚያስጨብጥ እስትራቴጂያዊ ሂደት ነው በማለት ገልጸዋል።

‎አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው ብቁና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ምሩቃንን ማፊራት ላይ ትኩረት አድርጎ እየስራ መሆኑንም አውስተዋል።

‎የዛሬውም መድረክ ግብ ተኮር ሥርዐተ ትምህርት ግምገማ እንደመሆኑ የሚሰጡ ሙያዊ አስተያየቶች ጉድለቶችን ለማረም አስፈላጊነታቸው የጎላ እንደሆነ በአጽንኦት ገልጸዋል።
‎
‎መድረኩ የዛሬውን ጨምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት እንደሚካሄድ ከወጣው መርሀ-ግብር መረዳት ይቻላል።

‎በጋራ እንችላለን!
‎
‎

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ክቡር ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ ዳግም በመሾማቸው የተሰማውን ደስታ ገለፀ።         ==============ክቡር ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ  የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ...
08/10/2026

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ክቡር ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ ዳግም በመሾማቸው የተሰማውን ደስታ ገለፀ።

==============

ክቡር ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው በድጋሚ በመሾማቸው ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተሰማውን ደስታ ይገልፃል።

ክቡር ሚኒስትር ዩኒቨርሲቲያችን መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንልዎትም ይመኛል።

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ!

በጋራ እንችላለን!

07/10/2026
‎የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ለ"ኢሬቻ" በዓል መልካም ምኞታቸውን ገለጹ።‎‎          ======== መስከረም 23/2019 ዓ.ም==============‎‎የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ...
03/10/2026

‎የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ለ"ኢሬቻ" በዓል መልካም ምኞታቸውን ገለጹ።
‎
‎ ======== መስከረም 23/2019 ዓ.ም==============
‎
‎የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) እንኳን ለ"ኢሬቻ" በዓል በሰላም አደራሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
‎
"‎ኢሬቻ" ከአስቸጋሪው የዝናብ ወቅት በኋላ የሚከበር የምስጋና በዓል መሆኑን የጠቀሱት ክቡር ፕሬዝዳንቱ ኢትዮጵያችን ከምትኮራባቸው የባህል ትውፊቶች እና የአደባባይ በዓላት አንዱ ነው ብለዋል።
‎
‎የገዳ ስርዓት አካል የሆነው " ኢሬቻ " ዓመቱን በሰላም ላሻገረ ፈጣሪ ምስጋና የሚቀርብበት እና የመጪውን ዘመን በፀሎት እና በምስጋና በአባ ገዳዎች እና ሀደ ስንቄዎች ምርቃት የምንቀቀልበት ነው።
‎
‎ዴሞክራሲን በተግባር በገዳ ስርዓቱ ቀድሞ የተገበረው ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ ለሀገራችን የኩራት ምንጭ መሆኑ አያጠራጥርም።
‎
‎ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሀ-ሕዝብ ፣ ታሪክና ባህል ማሳያ የሆነው "ኢሬቻ" ከሀገር ኩራትነቱ ባሻገር ግዙፍ የሆነ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን የመፍጠር አቅሙ ከፍተኛ ነው።
‎
በመሆኑም ‎ከወንድም የኦሮሞ ህዝብ ጋር "ኢሬቻ" በዓል ስናከብር ታላቅ ኩራት እየተሰማን ነው።
‎
‎በድጋሚ መልካም የ"ኢሬቻ" በዓል እንዲሆን እመኛለሁ።
‎
‎ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት!!
‎
‎በጋራ እንችላለን!

ዛሬ መስከረም 21/2019 ዓ.ም በፈረንጆቹ October 1,2026 ዓለም ዓቀፍ የቡና ቀን እየተከበረ ይገኛል።ቦንጋ ዩኒቨርሲቲም የሀገራችንን የቡና ዘርፍ ለማጎልበት "የቡና ሳይንስ ትም/ት ...
01/10/2026

ዛሬ መስከረም 21/2019 ዓ.ም በፈረንጆቹ October 1,2026 ዓለም ዓቀፍ የቡና ቀን እየተከበረ ይገኛል።

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲም የሀገራችንን የቡና ዘርፍ ለማጎልበት "የቡና ሳይንስ ትም/ት ክፍልን በመክፈት እስከ ሶስተኛ ዲግሪ ድረስ እየሰጠ ይገኛል።

በድጋሚ እንኳን ለዓለም ዓቀፉ የቡና ቀን አደረሳችሁ አደረሰን።

Bunoo uyone! 🌿🌿

በጋራ እንችላለን!

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውን አስተላለፉ።   ======== መስከረም 16/2019 ዓ.ም========የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ(ዶ/ር)...
26/09/2026

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውን አስተላለፉ።

======== መስከረም 16/2019 ዓ.ም========

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ(ዶ/ር) ለደመራ እና ለመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ ሲሉ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ለመላው ኢትዮጵያውያን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ክቡር ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው ኢትዮጵያ ሀገራችን በዓለም ዓቀፉ የትም/ት የባህል እና ሳይንስ ተቋም "ዩኔስኮ" በማይዳሱ የዓለም ቅርስነት ካስመዘገበቻቸው በርካታ የአደባባይ ክብረ-በዓላት አንዱ የሆነው የመስቀል ደመራ በዓል ለኛ ለኢትዮጵያውያን ትርጉሙ ቡዙ ነው።

የመተባበር እና የአንድነት ምልክት የሆነው የደመራ በዓል የመደመር እሴት ቀድሞ የተገለፀበት የተምሳሌታዊ ልዩ ህብር መገለጫ ነው።

ኢትዮጵያውን ሁሌም አንድ ስንሆን ሀይል አለን ውበትም እንዲሁ።

የመስቀል በዓልን ስናከብርም ሁሌም ሊታወሰን የሚገባው ከመስቀሉ ሀይል ባሻገር የመተባበርን ፣ የመተጋገዝን እንዲሁም ለአንድ ዓላማ አብሮ የመቆምን ትርጉም ሊሆን ይገባል።

የ2018ቱን ሀገራዊ ምርጫ እንዲሁም ግዙፉን ሀገራዊ ምክክር ባሳካንበት ማግስት እንዲሁም የቀጣዩን አምስት ዓመታት የሚያገለግሉ እንደራሴዎች በሚሰየሙበት ዋዜማ ላይ ሆነን በዓሉን ማክበራችን ሌላው የበዓሉ ልዩ ድምቀት ነው።

በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር እንዲሁም የጤና እንዲሆን እየተመኘሁ እንደተለመደው በዓሉን ስናከብር ያለንን በማካፈል በኢትዮጵያዊ ለጋስነት እና መተባበር እንድናከብር ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

መልካም የደመራ እና የመስቀል በዓል ይሁንልን!!

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት!

በጋራ እንችላለን!

Bonga University Hosts Public Lecture on History and Territoriality       :::::::::::::: September 25, 2026:::::::::::::...
25/09/2026

Bonga University Hosts Public Lecture on History and Territoriality

:::::::::::::: September 25, 2026::::::::::::::

Bonga University hosted a public lecture titled "History and Territoriality: Inquiring Cultural and Political Practices of Territory," delivered by renowned ethnohistorian Professor Wolbert G.C. Smidt.

Opening the event, Dr. Kellelew Adissu, Academic Vice President of Bonga University, delivered welcoming remarks emphasizing the vital role of historical analysis in addressing complex contemporary challenges.

Professor Wolbert Smidt, a distinguished scholar specializing in the history and anthropology of Northeast Africa and Ancient Arabia, delivered an engaging presentation on the history of the Kafa kingdom and region, drawing on historical maps to illustrate how historical and cultural practices have shaped territorial identity over time.

The session brought together key members of the university leadership and academic community, including the Head of the President's Office, the Academic Affairs Director, College Deans, Department Heads, faculty members, and representatives of the Kafa intelligentsia.

Following the lecture, participants engaged in a Q&A session.

In his closing remarks, Dr. Yared Ayalew, Director of International Partnerships, expressed gratitude to Professor Wolbert G.C. Smidt and co-organizer Dr. Zegeye W/Mariam for coordinating the program, highlighting the ongoing importance of researching and preserving the region's historical heritage.

Together We Can!

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የስርዓተ-ትም/ት ውስጣዊ ግምገማ መርሀ-ግብር አካሄደ።           ========= መስከረም 13/2019 ዓ.ም========ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የአዲሱ ትም/ት ፖሊሲ ማሻሻያ...
23/09/2026

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የስርዓተ-ትም/ት ውስጣዊ ግምገማ መርሀ-ግብር አካሄደ።

========= መስከረም 13/2019 ዓ.ም========

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የአዲሱ ትም/ት ፖሊሲ ማሻሻያ ትግበራ አካል የሆነዉን ግብ-ተኮር ሥርዓተ-ትምህርት (Outcome Based Education (OBE) Curriculum) የዉስጣዊ ግምገማ የሆነው መርሀ-ግብር ዛሬ ተጀምሯል።

በዚሁ መርሀ ግብር የዩኒቨርሲቲው መማ/ማስ/ምር/ቴክ/ስር/ማ/አገ/ት ምክትል ፕሬዝዳንት ከለለው አዲሱ (ዶ/ር) እንደገለፁት የትም/ት ጥራት ትልቁ መለኪያ በምሩቃን ላይ የሚታየው የተወዳዳሪነት ብቁ መሆን ሲቻል እንደሆነ አስገንዝበዋል።
አክለዉም ምክ/ፕሬዚዳንቱ ጊዜው የሚጠይቀውን ብቁ እና ተወዳዳሪ ምሩቃንን ለማፍራት በየወቅቱ የሚደረግ የሥርዓተ-ትምህርት ግምገማና ማሻሻያ አስፈላጊነታቸው ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ሁሉም ፕሮግራሞቻችን ተገምግመው ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ዕውቅና ለማግኘት በትኩረት ከሚሠሩ ተግባራት መካከል አንዱ ግብ-ተኮር ሥርዓተ-ትምህርት (Outcome Based Education (OBE) Curriculum) መሆኑን ገልፀው በተለይ የዛሬው መድረክ በዋናነት፡ -

• የፕሮግራም ውጤታማነት/Program Outcome/ እና
• የኮርስ ውጤታማነት/Course Outcome/
• የመማር ማስተማር ስልት (Teaching Methodologies)እንዲሁም
• የግምገማ ስርዓት (Assessment Strategies) ከዩኒቨርሲቲው የትኩረት መስክ ልየታ እና ራዕይ ጋር የተሳሰረ ሥርዓተ-ትም/ት እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን በማሳሰብ መርሀ-ግብሩን በይፋ አስጀምረዋል።

የአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር መ/ር አጥናፉ አስፋው በበኩላቸው ስለ ግምገማው (Validation) ወሳኝነት በመጥቀስ መምህራን ለውጤታማነቱ ሙያዊ ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል። አክለውም ስለአሰራር ሂደቱ ደረጃ በደረጃ የሚኖሩ ተግባራትን አብራርተዋል።

በመቀጠል ስድስቱም ኮሌጆች የተመረጡ ትም/ት ክፍሎቻቸውን በመያዝ ያዘጋጁትን ሰነድ በየግል እንዲገመግሙ የተደረገ ሲሆን በቀጣዩ ለሚኖረዉ ውጫዊ ግምገማ (External Validation) እንዲዘጋጁ የሚያስችል ነው።

መርሀ-ግብሩን በዋናነት የዩኒቨርሲቲው የትም/ት ጥራት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ሲያስተባብር የሚቆይ ሲሆን በነገው ዕለት እንደሚጠናቀቅ ከወጣው መርሀ-ግብር መረዳት ይቻላል።

በጋራ እንችላለን!

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች እና የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች በተለየ ድባብ የ2019 ዓ.ም. "ማሽቃሮን" በቦንጊ ሸምበቶ እያከበሩ ይገኛሉ!!! :::::::::::መስከረም 12/2019 ዓ....
22/09/2026

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች እና የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች በተለየ ድባብ የ2019 ዓ.ም. "ማሽቃሮን" በቦንጊ ሸምበቶ እያከበሩ ይገኛሉ!!!

:::::::::::መስከረም 12/2019 ዓ.ም:::::::::::::

ታዋቂ ቲክቶከሮች ጆን ዳንኤልና ታኩር እንዲሁም የካፋው ክስተት ዮሀንስ ምስክር /ንቃተ ህሊና/ ማሽቃሮን ለዓለም አጉልቶ ለማሳየት ወደ ለምለሚቷ ካፋ በመምጣታችሁ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተሰማውን አድናቆት ይገልፃል።

"ማሽቃሮን" በዩኔስኮ የማስመዝገቡን ሂደት ከማፋጠኑም ባሻገር ብዙዎች ይሄንን ልዩ የበዓል አከባበር በስፋት እንዲያዩት ያደርጋል።

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ በማዋል እንደዚህ ዓይነት ተምሳሌታዊ ወጣቶችን እንዲያበዛልን ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ምኞቱን እየገለፀ በድጋሚ መልካም "የማሽቃሮ" በዓል እንዲሆንልን ምኞቱን ይገልፃል።

Waama diggoona kafecooch yemene shaddiyee mashiqare baarooch shagitoote!!!

በጋራ እንችላለን!

Address

Bonga
334

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bonga University posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share