19/03/2022
ተጠንቀቁ
👉 የሀያል ሀገራት መንግስታትና የዓለማችን ቢሊየነሮች ትኩረታቸው ወደ አንድ ቦታ ነው። ይኸውም ወደ ምድራዊቷ ገነት ኢትዮጵያ። የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ግልጽ ነው በሐይማኖት፣ በታሪክ፣ በራሷ በሆኑ ነገሮች ብቻ ለብዙ ሽህ ዘመናት በራሷ የታሪክ ምህዋር እየዞረች የነበረችና ያለች መሆኗ ኢትዮጵያን ለምንና እንዴት እንዳጠመዷት አንዱ ምስክር ነው።
ታዲያ ይህ ስራ ቀድሞ የጀመረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መልኩን እየቀየረ መጥቶ በ1990ዎቹ በምዕራባውያን አቆጣጠር የዓለም መንግስታት በተለይም ሃያላን የተባሉት ሃገራት ቬንዙዌላ ዉስጥ አንድ ለሰው ልጅ ደህንነት ስጋት የሆነ ሰነድ አጸደቁ። ይህ የሰው ልጅ የሞት ደብዳቤ አጀንዳ 21 ይሰኛል። በዚህ ድብቅ የሞት አጀንዳ ባነገበ አጀንዳ ላይ ትኩረት የተሰጠው ዋነኛ ግብ በ2030 ድህነትን ከምድር ማጥፋት ነው። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ 17 ዘለቄታዊ እቅድ ማምጫ ግቦች (sustainable development goals) እና 169 ትኩረት የተደረገባቸው ዘለቄታዊ እድገት ማምጫ ስራዎች (sustainable development targets) ተቀርጸዋል።
ምንም እንኳን የመንግስታቱ ሕብረት ድህነትን ለማጥፋት ይህን አጀንዳ ቀረጽኩ ቢልም እውነተኛው አጀንዳ ግን ጥንት ባቢሎናውያን እንደሞከሩት ሁሉ ዛሬም የመንግስታቱ ሕብረትን በሚመራው አካል የተቀረጸው ዓለምን በስማዝያ ሰይጣናዊ መንፈስ አንድ አድርጎ የመግዛት ስትራቴጂ ነው።
ድህነትን ከአለም ለመቀነስና አንድ መንግስት ለመመስረት የዓለም ሕዝብ ቁጥር መቀነስ እንዳለበት የዓለም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እምነት ነው። ይህንን እምነቱን ወደተግባር ለመቀየር አንድ ስትራቴጂ ነደፈ። በላብራቶሪ የተፈበረኩ በሽታዎችን ማሰራጨት። ይህንንም አፍሪካ ላይ ተገበሩት። ብዙ ሚሊየን ወንድም እህቶቻችን በኤች አይ ቪ፣ ኢቦላና መሰል በሽታዎች ረገፉ። ይህም ብቻ አልበቃቸውም የወሊድ ቁጥጥር በሚል ሰበብ የአፍሪካውያንን ዘር ማምከን ጂ ኤ ቪ አይ ግሎባል አሊያንስ ፎር ቫክሲን አንድ ኢሚዩናይዜሽን የተሰኘ ተቋምን መሰረቱ። ይህ ተቋም የመጀመሪያ ስብሰባውን በራሳቸው የቀን አቆጣጠር በ 2000 ዓ.ም ላይ ስዊዘርላንድ ውስጥ አደረገ። የዚህ ስብሰባ ዋነኛ ተካፋዮች አሁን ዶ/ር ተዎድሮስ የሚመሩት WHO እንዲሁም የማይክሮሶፍት መስራቹ ቢልጌትስ ከነቤተሰቡ፣ ሮክፌለር ፋውንዴሽንና ዎርልድ ባንክ ነበሩ። እነዚህ ተቋማት ዋነኛ የሚስጥር ማህበረሰቡ አካላት እንደሆኑ ልብ ያድርጉ። አጀንዳ 21 በተቃራኒው እየተተገበረ ያለው በምድር ላይ አንድ መንግስት፣ አንድ የኢኮኖሚ መዘውርና አንድ ሰይጣናዊ እምነት 666ን መመስረት ነው። ይህንን ለማድረግ የመንግስታቱ ሕብረት በፈበረካቸው አጀንዳዎች መሰረት የየሃገራቱን መንግስታት፣ መከላከያ ሰራዊት ኃይላቸውን እንዲሁም የፍትህ አካላትን፣ መገናኛ ብዙኃንን፣ ባንኮችና የሐይማኖት ተቋማትን በእጅ አዙር እየተቆጣተረ ይገኛል። ከምንም ነገር በላይ ግን የሕክምናውን ዘርፍ መቆጣጠር ዋነኛው ዓላማቸው ነው። አሁንም በስፋት እየተገበሩት ይገኛሉ። ለዚህም ትልቁን ሚና እየተጫወቱ ካሉ አጀንዳዎች መካከል አጀንዳ 21 ዋነኛው ነው።
የሚስጥር ማሕበሩ ወይንም ኃያላኑ በቅርቡ በጣም አሰቃቂ የሆነ አጀንዳ ቀርጸው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። ይህ እንቅስቃሴ እንግዲህ የጤናውን ዘርፍ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር በአንድ አሃዳዊ አገዛዝ የመጠቅለል ግብን ያነገበ ነው። ይህን አጀንዳ ለማሳካት አጠገባቸው ያሉትን ነገሮች ሁሉ በመጠቀም የተለያዩ ስልቶችን በመንደፍ ለአምስት ዓላማ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።
በዛሬው ቆይታችንም ይህንን ድብቁን የኃያላኑን ሴራ በጤናው ዘርፍ በዓለማችን ላይ ያሴሩትን ድንቅ ሴራ እንሆ አቅርቤላችኋለሁ። ምክንያቱም የህልመኞቹ ከንቱ ህልምና የእኩይ ሴራ ሙከራቸውን ማምከንና ማክሸፍ የሚቻለው እቅድና አላማቸውን ቀድሞ በማወቅ ነውና ለማወቅ መሞከር ነገሮችን በውን ለመረዳት መዘጋጀትም ያስፈልጋል። በርግጥም እንዲሁ ላይ በላይ ሲያዩት ተራ ገለጻና መሰረት የሌለው ግምት ቢመስልም ነገሩ ግን እሙን ነው። ሚስጥሩን እንካችሁ።
የ666 የሚስጥር ማሕበረሰብ የሕክምናውን ዘርፍ መቆጣጠር ላስቀመጡት ዓላማ በአንድ አኃዳዊ አገዛዝ የመጠቅለል ግብ ያለው አስተዋጽኦ በአምስት ዓላማዎች የተዋጀ ነው። እነኚህ ዓላማዎችም አንደኛ የዓለምን ሕዝብ አዕምሮ ማቀጨጭ ሁለተኛ የሕዝብ ቅነሳ ሦስተኛ ከፍተኛ የገንዘብ ትርፍ አራተኛ የሕዝብ ቁጥጥር አምስተኛ ሰውን ጀነቲካል ሪኢንጅነር ማድረግ። በቅደም ተከተላቸው መሰረት በዝርዝር እንመለከታለን።
አንደኛ የዓለምን ሕዝብ አዕምሮ ማቀጨጭ የሰዎችን አዕምሮ ማቀጨጭ ማለት የሰውን የማሰብ፣ የማገናዘብና የማስታወስ ችሎታ ማዳከም ማለት ነው። ሰዎች የማስታወስና የማገናዘብ ችሎታቸው በተዳከመ ቁጥር የተለያዩ የእለት ተእለት እንቅስቃሴዎችን የመመርመር አቅማቸው የደከመ ይሆናል። ይህን የሚስጥር ማህበረሰቡ ግቡን ለመምታት በሚያደርገው ዘርፈ ብዙ ጉዞ ላይ ተገዳዳሪና ተጠራጣሪ ሰዎች በብዙ እንዳይገጥማቸው በማድረግ ትልቅ አስተዋጻኦ ያበረክትላቸዋል። የማሰብና የማገናዘብ አቅም እየተዳከመ አዕምሮ በፊት በፊት እንኳን የሚያደርጉትን የሚስጥር ማህበረሰቡን ተግባራት ማሰላሰል ይሳነዋል። በዛም ላይ የማስታወስ አቅሙ እየተዳከመ አእምሮው ብዙ ነገሮችን አሁንም አሁንም ስለሚረሳ ማስታወስና ማገናዘብ የተሳነው ይሆናል። የሐይማኖት ትምሕርቶችና ስለሚስጥር ማሕበረሰቡ የሚናገሩ መረጃዎችን ቶሎ ቶሎ የሚረሳ አእምሮ በቀላሉ የሚስጥር ማሕበረሰቡ ተጠቂ ይሆናል። ይህንን ጠንቅቀው የተረዱት የሚስጥር ማህበራቱ አባላት በሕክምናው ዘርፍ እጃቸውን በማስገባት የተለያዩ መድሃኒቶችንና ክትባቶችን የሰውን አእምሮ የሚያዳክሙ ኬሚካሎች እንዲይዙ አድርገው በማምረት ትልቅ ስኬት እየተቀዳጁ ይገኛሉ። የሰውን ልጅ ከእንስሳ በወረደ መልኩ እንዲያስብ የሚያደርገው ኦቲዝምን ጨምሮ በሰፊው የዓለም ሕዝብ ላይ እየታየ እስካለው የመርሳት ችግር ድረስ በዋነኝነት የሚዳርጉት እኚህ የሚስጥር ማህበራቱ ፋርማሲዎች ቢግ ፋርም የሚያመርታቸው አደገኛ ክትባትና መድሃኒቶች ናቸው። ይህንን የጠለቀ የቢግ ፋርሞች ስልታዊ አሰራር ወደኋላ በስፋት እንመለከተዋለን። እንግዲህ የቢግ ፋርማ የህክምና ዘርፎች ቁጥጥር አደገኛ ዓላማ የሰዎችን አስተሳሰብ ማዳከም ነው።
በሁለተኝነት ደረጃ የሕዝብ ቅነሳ የሚስጥሩ ማህበራት ከመሪያቸው ሰይጣን ተቀበልነው ባሉት በአሜሪካ ጆርጂያ በሚገኘው ጆርጅ ጋይድስቶን በተባለው ዝርዝር መመሪያቸው ዉስጥ በግንባር ቀደምትነት የተቀመጠው መመሪያ የዓለምን ህዝብ ወደ ግማሽ ቢሊየን መቀነስ ነው። ይህ ማለት ዓለማችን ካሏት 7.8 ቢልየን ሕዝብ መካከል 7.2 ቢልየኑ መወገድ አለበት እንደማለት ነው። እንግዲህ ይህንን አላማቸውን ለማሳካት የህክምናው ዘርፍ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታልና እጃቸውን ካስገቡበት ዘመናት ተቆጥረዋል። የሕክምናው ዘርፍ ለዚህ ግባችን ያደርሰናል ያሉት በሚከተሉት ሦስት መንገዶች ነው። አንደኛ ወረርሺኝ ቫይረሶችንና በማምረትና በማሰራጨት የዓለምን ሕዝብ በከፍተኛ ቁጥር የመቀነስ ሂደት ነው። ሁለተኛ ስሎው ኪሊንግ በሚሉት ስልት ክትባትና መድሃኒቶች ዉስጥ ድብቅ በሽታዎችን በመጨመር ሰዎችን በዝግታ መግደል ነው። በዝግታ መግደል ማለት ሰዎች እኝህን መድሃኒቶችና ክትባቶች በተጠቀሙ ቁጥር እኚህ ድብቅ በሽታዎች በሰውነታቸው በማንሰራፋት ከ 10 እስከ 30 በሚደርሱ አመታት ዉስጥ በካንሰር ደምግፊትና መሰል
👇👇👇
በሽታዎች የመግደልና የሕዝብ ቁጥርን የመቀነስ አካሄድ ነው። ሦስተኛው ስልታቸው ደግሞ እኚህ የሚያመርቷቸው ክትባቶች ዉስጥ የሰውን የመራባት አቅም የሚያዳክሙ ኬሚካሎችን በመጨመር የሰው ልጅ የመዋለድ አቅምን ማዳከም ነው። ይህ ስልት ከተቀነባበሩ ምግቦችና የምግብ ኬሚካሎች ጋር በመሆን በሰሜን አመሪካና አውሮፓ የ50 በመቶ የወንድ የዘር መቀነስን አስከትሎአል።
ሌላው የማህበሩ ዓላማ ሦስተኛው ከፍተኛ የገንዘብ ትርፍ ማካበት ነው። በ2014 ብቻ ቢግ ፋርማዎች የአንድ ትሪልየን ዶላር ግብይት ፈጽመዋል። እኚህ የህክምናውን ዘርፍ የተቆጣጠሩ የቢግ ፋርማ ከበርቴዎች አንድ አባባል አላቸው። ይህም a patient cured is a customer lost! የሚል ሲሆን በግርድፍ ትርጉሙ በሽተኛውን መፈወስ ደንበኛን ማጣት ነው እንደማለት ነው። በዚህ አቋማቸው በሽተኞችን ከህመማቸው የሚፈውሱ መድሃኒቶችን ከማምረት ይልቅ በጊዜያዊነት የሚያስታግሱ ብቻ አድርገው በማምረት የመድሃኒት ቋሚ ደንበኛ ህሙማንን በመፍጠር ተዝቆ የማያልቅ ረብጣ ዶላሮችን ወደ ካዝናቸው ማስገባት ነው። ከዚህም ባለፈ መድሃኒቶች የጎንዮሽ ተጨማሪ በሽታ የሚያመጡ አድርገው በማምረት በተደራራቢ በሽታዎች የሚጠቁ ሰዎችን በመፍጠር በየዓመቱ የሽያጭ መጠናቸውን እያሳደጉ ይገኛሉ።
በአራተኝነት ደረጃ የህዝብ ቁጥጥር የሚስጥር ማህበሩ ግብ የዓለምን ሕዝብ ሁሉ በአንድ የኢኮኖሚ፣ የትምህርት፣ የሃይማኖትና የባህል ብሎም በአንድ የመንግስት ስርዓት መጠቅለል እንደመሆኑ የህክምናውን ዘርፍ በመጠቀም በነሱ መድሃኒቶች ጥገኛ የሆኑ፣ በቁጥጥራቸው ስር የሆኑ ሕዝብን በመፍጠር እየተጠቀሙበት ይገኛሉ። አንድ በተደራራቢ በሽታዎች የተጠቃና ለቢግ ፋርማ መድሃኒቶች ጥገኛ የሆነ ግለሰብ እነኚህን መድሃኒቶች ለማገኘት የግድ የቢግ ፋርማን ትእዛዝና መመሪያዎች ለመከተል ይገደዳል። ያ ደግሞ በተዘዋዋሪ ለሚስጥር ማህበሩ ህጎች መገዛት ማለት ነው። ለምሳሌ እነኚህን መድሃኒቶች የምንሸጠው በእጁ ወይንም በግንባሩ የ666ትን ምልክት የታተመበትን ችፕ ለተቀበለ ብቻ ነው የሚል ህግ ቢያረቁ በሽተኞች ወይ መሞት ወይም ደግሞ አርማውን መቀበል ብቸኛ አማራጫቸው ይሆናል። ይህ ነው እንግዲህ የህዝብ ቁጥጥር ማለት። ይህ ነው ሰዎችን በፊት ለፊት ሳይሆን በእጅ አዙር ማስገደድና ለራሳቸው ዓላማ ማሰለፍ ማለት።
አምስተኛው ሰውን ጀነቲካል ሪኢንጅነር ማድረግ ይህ ሂውማን ሪኢንጅነሪንግ በመባል የሚታወቀው የሚስጥር ማህበሩ እንቅስቃሴ ሲሆን ባዮሎጂ ቴክኖሎጂና የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም የሰው ልጆችን ወደ ሰውን ያለፈ ከተፈጥሮ በላይ ወደሆነ ደረጃ የማድረስ ሂደት ነው። በዚህም በዘረመላቸው የበለጸጉ(gine reach) ሰዎችን በመፍጠር የሚስጥር ማህበሩ ለሚያደርገው እንቅስቃሴዎች አጋዥ እንዲሆኑ አልሞ ተነስቶአል። ይህንንም ለማሳካት ስውርና ግልጽ በሆነ መልኩ ቢግ ፋርማዎች ከቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር በመተባበር እየሰሩ ይገኛሉ። የፕሪስተር ዩንቨርስቲው ሊ ሲልቨር እንደሚገምተው ከሆነ በዚህኛው ክፍለ ዘመን ላይ የኢኮኖሚ፣ የሚድያ፣ የመዝናኛ፣ ኢንዱስትሪና የእውቀት ኢንዱስትሪው ሁሉ ገጽታቸው በዘረመላቸው በበለጸጉ መደቦች ቁጥጥር ስር ይውላል። ከዛ ዉጪ ሆነው በተፈጥሯዊ ብቻ ሆነው የሚቀሩ ደግሞ በዝቅተኛ ክፍል ተመድበው አገልግሎት ሰጭዎች ወይም ላብ አደሮች ይሆናሉ ሲል ተንብዮአል። እነዚህ የተመለከትናቸው የህክምናውን ዘርፍ ለምን ተቆጣጠሩ የሚሉ ምክንያቶችን ሲሆኑ በጣም የሚደንቀው ግን ይህንን ዓላማቸውን ለማሳካት የሚጠቀሙባቸው ስልቶች ጉዳዩ አንገብጋቢና ለሚስጥር ማሕበረሰቡ የሕክምናው ዘርፍ የሚያበረክተውን አወንታዊ አስተዋጽኦ ምን ያህል እንደሆነ ነው። ይህን ለማሳካት 11 ስልቶችን የሚጠቀሙ ሲሆን ስልቶቹንም እንደሚከተለው እናነሳቸዋለን።
በቅድሚያ በንግግሬ ዉስጥ የጠቀስኩት ቢግ ፋርማ የሚለው ቃል በሕክምናው ኢንዱስትሪ የተሰማሩ ትልልቅ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን የሚወክል መሆኑን ላስታውሳችሁ።
የመጀመሪያው ስልት አንደኛ የተፈጥሮ ወይም ባህላዊ ህክምናን ማዳከም የሰው ልጅ በተፈጥሮው በሽታን የመከላከል ኢሚዩን ሲስተም የተባለ ራሱን ባራሱ የመፈወስ ጸጋ የተሰጠው ፍጡር ነው። ከሰው የሚጠበቀው ይህ በሽታውን በራሱ የመከላከል አቅም እንዳይስተጓጎልና እንዳይዳከም ማድረግ ብቻ ነው። በተለያዩ ምክኛቶች መዳከም ከገጠመውም የተፈጥሮ ጸጋ የሆነውን የተለያዩ እጽዋቶችን በመጠቀም መፈወስ ይቻላል። ይህ የህክምና ስራዓት በሰው ልጅ ታሪክ ለረጅም አመታት ከዘለቁና እጅጉንም ፍቱን ከሆኑ ስልቶች መካከል አንዱ ነው። ሆኖም የሰው ልጅን ለመቆጣጠር አቋራጭ መንገዶችን መንደፍ የጀመሩት የ666 የሚስጥር ማህበራት እጃቸውን በሕክምናው ማስገባት ከጀመሩ አንድ መቶ አመታት ተቆጥረዋል። የሚስጥር ማህነሩ የሕክምናውን ዘርፍ ለዘመናት በህክምናው ዘርፍ ዘመናዊ ቁጥጥር ማድረግ የጀመረው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1910 ዓ.ም ነው። የተፈጥሮ ህክምናን በማሳደግ ነበር ጆን ዲ ሮክፌለር የተባለው የሚስጥር ማህበሩ አባልና የነዳጅ ከበርቴ ፊቱን በሰፊው ወደ ህክምናው ዘርፍ በማዞር በ1910 ዓ.ም በአሜሪካ የተፈጥሮ መድሃኒቶች ሳይንስ ያላመነባቸው በማስባል የሚያሳግዳቸው ህግ በኮንግረሱ እንዲጸድቅ አስደረገ። በዚህም መንግስት ለተፈጥሮ መድሃኒቶች ፓተንት መስጠት በማቆሙ ሮክ ፌለርና አጋሮቹ ቢግ ፋርማ እነኚህን የተፈጥሮ መድሃኒቶችን በመስረቅ አንድ አትክልት በሽታን የሚፈውሰው በየትኛው ኬሚካሉ መሆኑን በመለየት ያቺን ፈዋሽ ኬሚካል በላብራቶሪ በመስራት ፓተንት በራሳቸው ተቋም መያዝ ተግባራቸው አደረጉት። በዚህም ሳይንሳዊ የመድሃኒቶች ምርት ሂደት ቅድም የጠቀስናቸውን ዓላማዎች የሚያሳኩባቸውን ኬሚካሎች አብረው የመቀመም ስራቸውን በስፋት ገፉበት። በዚህ አይነት የተጀመረው የቢግ ፋርማ ጉዞ ዛሬ ከ አንድ መቶ አመታት በኋላ በመላው ዓለም የተፈጥሮ ወይም የባህል መድሃኒቶችን በስፋት አስጥሎና በሳይንስ ተገኙ በተባሉ የፋርማሲ ምርቶች መተካት ችሏል።
የ666 ሚስጥር ማህበረሰብ ተልእኮ ፈጻሚ የሆኑት የቢግ ፋርማ ተቋማት የመኖርና የህልውና ጉዳይ የተመሰረተው የተፈጥሮ መድሃኒቶችን በማጥፋት ላይ እንደሆነ በተለያዩ ስልቶች የተፈጥሮ ወይም የባህላዊ መድሃኒቶችን ማገድና ማጥፋት በመላው ዓለም ተያይዘውታል።
ሁለተኛው ስልታቸው የትምህርት ስርዓትን መቆጣጠር ነው። ቢግ ፋርማ የተፈጥሮ መድሃኒቶችን ከማሳገድ በመቀጠል የተጓዘው የህክምና ትምህርት ቤቶች ወደ መደገፍና ሰው ሰራሽ ህክምና ከተፈጥሮ የላቁ እንደሆኑ በተማሪዎች አእምሮ እንዲቀረጽ ወደማድረግ ነገር። በረጅም ሂደትም ለቢግ ፋርማ ሰው ሰራሽ መድሃኒቶች ቅድሚያ የሚሰጡ በርከት ያሉ የህክምና ባለሙያዎችን የሚያፈሩ የትምህርት ተቋማት በመላው ዓለም መብዛት ቻሉ። አሁን ላይ በመላው ዓለም ያሉ የመንግስትና የግል የህክምና ትምህርት ቤቶች በሚስጥር ማህበሩ የተቀረጸውን የትምህርት ካሪኩለም የሚተገብሩና በቢግ ፋርማ ድጋፍ የሚንቀሳቀሱ ሆነዋል። በዚህ አይነት ስልታዊ አካሄድ ቢግ ፋርማዎች ለነሱ ምቹ የሆኑ ባለሙያዎችን በማፍራት ቁጥጥራቸውን በማስፋት ላይ ናቸው።
ሌላኛው መንገድ ወይም ሦስተኛው መንገዳቸው የህክምናው ዘርፍ ላይ ያሉ ተቋማትና ባለሙያዎችን በጥቅም መያዝ ነው። የቢግ ፋርማ ሦስተኛው ስልት ጥቅማ ጥቅም እንደ መደለያ በመጠቀም ሰዎችን መያዝ ነው።
👇👇👇
ቢግ ፋርማዎች ከመጨረሻዎቹ የህክምና የትምህርት ዓመታት ጀምሮ ተማሪዎች የተለያዩ የገንዘብ፣ የከፍተኛ ትምህርት፣ የጉዞና የመሳሰሉትን ጥቅማ ጥቅሞች እንዲያገኙ በማድረግ ተማሪዎችን በማማለል ስልታዊ አሰራርን ይጠቀማሉ። ተከታታይነትና ቀጣይነት ባለው በዚህ ስልት ለቢግ ፋርማ ታማኝ የሆኑ የነሱን መድሃኒቶች በገፍ የሚያዙ ባለሙያዎች በመላው ዓለም ማፍራት ችለዋል። ለምሳሌ በአሜሪካ ከአስራሁለት ዶክተሮች አንዱ በፋርማሲ ድርጅቶች መድሃኒት ለበሽተኛው በደንብ እንዲያዝ ይከፈለዋል። ይህ ክፍያ ቀጥተኛ ብቻ ሳይሆን በምግብ መልክ፣ በማማከር፣ የጉዞ ክፍያና ለቢግ ፋርማ የሚደረጉ የማሳመን ንግግሮችን በመጠቀም የሚደረጉ ናቸው። የምግብና የመጠጥ ክፍያዎች የተለመደው አይነት እንደሆኑ አሜሪካን ጆርናል በ2016 ዓመት እትሙ ላይ አስነብቦ ነበር። በሌላ ጥናት እንደተረጋገጠው አንድ ምግብ ስፖንሰር ያገኘ ዶክተር የተጋባዡን የመድሃኒት ምርት ወይም ብራንድ ለታካሚው የማዘዝ ነገሩ በሰፊው እንደሚጨምር ያሳያል። ፖሊሲ የሚያረቁ የመንግስት ሰዎችም ለዶክተሮች የሚሰጠው ጥቅማ ጥቅም በማበረታታት ነገሩን አባብሰውታል። ይህን በጥቅማጥቅም የህክምና ባለሙያ የማጥመድ ስልት ዋን ሞር ገርል በተሰኘው የዶክተር ፒተር ሮስት ስራ ላይ በሁለት መንገድ መሆኑን እንደሚከተለው አስቀምጠውታል። አንደኛው ስልት በተለያዩ የህክምና ተቋማት ገንዘብ ለጥናት ወይም ሪሰርች በመመደብ አብረው በጋራ ጥናቱን በመስራት ነው። በዚህ ረዘም ያለ የጥናት ሂደት ብዙ ጓደኛዎች ያፈራሉ። የነሱ ጥገኛ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ። በቀጣይም በተዘዋዋሪ ጥናቱ እነሱ እንደሚፈልጉት እንዲሆን የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋሉ። በዚህ አካሄድ የነሱ ምርቶች (Drugs) በዩንቨርስቲዎችም ሆነ ዶክተሮች ትልቅ ድጋፍ እንዲያገኝ ያደርገዋል።
ሁለተኛው ስልታቸው ደግሞ በህክምናው ላሉ ሴክተር ተቋማት የመንግስት ይሁንታን እንዲያገኙ የማድረግ ስልት ነው። ይህ የመንግስት ሰዎችን የመግዛት የቢግ ፋርማዎች ስልት በመላው ዓለም ባሉ ሀገራት እየተፈጸመ ያለ ሲሆን በውጤቱም የቢግ ፋርማ ምርቶች የመንግስት አፕሩቫል ወይም ማህተም ያረፈባቸው እንዲሆኑ እያስቻለ ይገኛል። በዚህም እነኚህ የቢግ ፋርማ አደገኛ መድሐኒቶችና ክትባቶች በሕዝቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳትና ሞት እያስከተሉ ይገኛሉ። እንደ ፌኒፔን ዲክስስ ዞሀይድሮ እና ሴሊ ብሬክስ ያሉ መድሐኒቶች ብዙ ሰዎችን ከገደሉ በኋላ ነበረ በኤፍ ዲ ኤ (FDA) የተሰጣቸውን በዝግታ የሚገድሉና የሰውን አዕምሮ የሚያቀጭጩ በኤፍ ዲ ኤ የተሰጣቸውን ፍቃድ የተነጠቁት። እንግዲህ እነኚህ በፊትለፊት ገዳይ የሆኑ መድሐኒቶች ህጋዊነትን አግኝተው ብዙ ከፈጁ በኋላ የሚከለከሉ ከሆነ በዝግታ የሚገድሉና የሰውን አዕምሮ የሚያቀጭጩ ስውሮቹ መድሐኒቶችና ክትባቶች ምን ያህል መንሰራፋት እንደሚችሉ መገመት አይከብድም።
ይህ የመንግስት ሰዎችን በጥቅም የመያዝ ሂደት ለቢግ ፋርማ አመቺ የሆኑ ህግጋቶችን ለማጸደቅ እየረዳ ይገኛል። በአሁን ጊዜ በበርካታ ሀገራት ልጆችን ማስከተብ የውዴታ ግዴታ ህግ ሆኖ እየጸደቀ ነው። በዚህም ሰዎችን ከልጅነታቸው ጀምሮ በማጥቃት አስተሳሰባቸው የቀጨጨ በሽታን የመከላከል ተፈጥሯዊ አቅማቸው ወይም ኢሚዩን ሲስተም የወረደና ለመድሐኒት ጥገኛ የሆነ ትውልድ በመፍጠር ላይ ናቸው። ከዚህም ባለፈ እነኚህን የህክምና ትሪትመንቶች ዋጋውን በየጊዜው በመጨመር ቢግ ፋርማዎች ረብጣ ዶላር እያተረፉበት ይገኛሉ። በቅርቡ እንኳን በአሜሪካ ሁለት ጥንዶች የስድስት ወር ልጃቸውን ውድ የሆነ የጤና ምርመራ ወይም ቴስት አናስደርግም በማለታቸው በቁጥጥር ስር ውለው በሰላሳ ሽህ ዶላር መቀጮ ተለቀዋል። አሁን አሁን በሀገራችንም ሰፊ የሆነ አስገዳጅ የልጆች ክትባትና ጤና ተኮር ህጎች እየወጡ ይገኛሉ።
ሌላኛው በአምስተኛ ደረጃ የተቀመጠው አደገኛ መድሐኒትና ክትባቶችን ማምረት ነው ቢግ ፋርማዎች የተፈጥሮ መድሐኒቶችን ከማጥፋትና ማሳገድ፣ የትምህርት ስርዓትን መቆጣጠር፣ ባለሙያዎችና ባለስልጣኖችን በጥቅም በመደለል ያገኙትን ምቹ ድል በመጠቀም ዓላማውን ማለትም ሕዘብ ቅነሳውን፣ አዕምሮ ማቀጨጩን፣ ገንዘብ ማካበትና ሕዝብ ቁጥጥሩን ለማሳካት የሚረዷቸውን የመድሐኒትና ክትባት ምርቶችን ማምረትን ተያይዘውታል።
በጣም በጥቂቱ የነዚሀን መድሐኒቶችና ክትባቶች ጉዳይ እንይ፥ ለእናቶችና ህጻናት አየተሰጡ ያሉ ክትባቶች በአብዛኛው ሜርኩሪ የተባለ ኒውሮ ቶክሲን ንጥረነገር ያዘለ በመሆኑ ልጆች ለኦቲዝም ወይም የአዕምሮ ነርቭ ውድመት እየተጋለጡ መሆኑን ብዙ ጥናቶች እያሳዩ ነው። ሌላኛው ለዘመናት የዘለቁ የፍሉ ክትባቶችም ምንም ጥቅም የሌላቸውና የማይቀለበስ ውድመት የሚያመጡ መሆናቸው እየተረጋገጠ ነው። በ2017 ፕ/ት ትራምፕ ፍሉ ሹት ኢዝ ኤ ግሬተስት ስካም ኢን ሜዲካል ሂስትሪ በማለት ቢግ ፋርማዎች ላይ ውጊያቸውን ጀምረዋል። ሌላው ሂሮኮሞርዮ የተባለ የክትባት አጥኚ ህጻናት ተገቢ ያልሆነ ክትባት እየተሰጣቸው በመሆኑ ተፈጥሯዊ በሽታን የመከላከል አቅም እያጡ ነው። ክትባቶች ለሚያስፈልጋቸው ብቻ መሰጠት ሲገባው ቀድሞ በሽታን መከላከል በሚል ስም ለሁሉም መሰጠቱ ትልቅ ጥፋት መሆኑን አስቀምጧል። ለዚህም ይመስላል ሕንድ በ2015 ቢልጌትና ቢግ ፋርማን በነፍስ በላነት እከሳለሁ ህንዳውያንን በተለይ ህጻናትን በግሎባል መድሐኒቶችና ክትባቶች ጎድቶብኛል ገድሎብኛል ብላ የከሰሰችው። ሌላኛው ሰከንድ ካንሰር ኢን አዶልት በተባለ መዝገብ መሠረት የተለያዩ ህክምናዎችና መድሐኒቶች ተጨማሪ በሽታዎችን ያመጣሉ ይላል። እንደ ራድዮቴራፒና ኪዮሞቴራፒ ያሉ ህክምናዎች የካንሰር ምንጭ እንደሆኑ ያስቀምጣሉ። ከዚህ በተጨማሪ በዕለትተዕለት መገልገያ በሆኑት የፕላስቲክ ማሸጊያዎች፣ ሳሙናዎች፣ የትንኝ መከላከያ ፔስቲሳይዶች ወዘተ... የሚገኘው ካይሲኖጀኒክ ፔትሮኬሚካል ለካንሰር መንስኤ እንደሆነ ይህ መዝገብ ያትታል። የዚህ አይነት ሴራዎች እየተፈጸሙ ያሉት የካንሰር ኢንዱስትሪ የዓለም ትርፋማ ቢዝነስ ስለሆነ ነው። በ2019 አንድ መቶ ሃያ አምስት ቢልዬን ዶላር ያመነጨ ቢዝነስ ነበርና። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የተባለው ዝነኛው የቢግ ፋርማ ተቋም ለገበያ የሚያውለውን የፓወደር ምርቱን ለካንሰር አጋላጭ መሆኑን በመሸሸግ የ4.7 ቢልዮን ካሳ እንዲከፍል መታዘዙን ኒዮርክ ታይምስ በ2018 ዘግቦ ነበር። ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ይህንን ሚስጥሩን ለዘመናት እንዳይወጣ ብዙ ሰርቶ ነበር። በሂብሩ ዩንቨርስቲ ኦፍ ጀሩሳሌም ጥናት መሰረት በአሜሪካና አውሮፓ ያሉ ወንዶች በ2060 መሐን ይሆናሉ ይላል። በሰሜን አሜሪካ አውሮፓና አውስትራሊያ ያሉ ወንዶች በአርባ አመታት ውስጥ ሃምሳ በመቶ የወንድ የዘር መቀነስ ተስተውሎባቸዋል። በተቃራኒው ለቢግ ፋርማ ጂ ኤም ኦና የተቀነባበሩ ምግቦች ብዙም ተጋላጭ ያልሆኑት አፍሪካ፣ ደቡብ አሜሪካና ኤስያ ምንም አይነት የስፐርም ካውንት ቅነሳ አልታየባቸውም። የዚህ አይነት ሴራዎች የሚስጥር ማህበሩ የሕዝብ ቅነሳ አጀንዳዎቹን የሚጠቁሙ ናቸው።
ስድስተኛ የመድሐኒት ደንበኞችን ማፍራት የቢግ ፋርማ የምንጊዜም አባባልና መርህ ኤ ፔሸንት ኪዩርድ ኢዝ ኤ ከስተመር ሎስት በሽተኛውን መፈወስ ደንበኛ ማራቅ ነው የሚል ሲሆን በዚህ መርሀቸው መሠረት በፍብሪካዎቻቸው የሚያመርቷቸውን መድሐኒቶች በሽታን ለጊዜው ብቻ የሚፈውሱ ብሎም የጎንዮሽ ጉዳት የሚያመጡ አድርገው ነው የሚያመርቷቸው። ይህ ማለት ለምሳሌ አንድ ለጨጓራ የሚሰጥ መድሐኒት ጉበትን የሚነካና ድካም የሚፈጥር እንዲሆን አድርገው ያመርቱታል። በመሆኑም ያ የጨጓራ መድሐኒት
👇👇👇
የታዘዘለት ታካሚ ደግሞ ጉበቱን ለመከላከል ሲል ሌላ የጉበት መከላከያ መድሐኒት እንዲታዘዝለት ግድ ይሆናል። ከዛም ባለፈ መድሐኒቱ የሚያመጣውን ድካሞች ለመከላከል ሲባል ደግሞ አንቲ ፔይን ይታዘዝለታል። አራት መድሐኒቶች ይሸጣሉ ማለት ነው። በአሜሪካ የታዘዘ መድሐኒት የሚወስድ ግለሰብ በአማካይ በተጨማሪ አራት መድሐኒቶችን እንደሚወስድ ጥናቶች ይጠቁማሉ። እነኚህ በገፍ የሚወሰዱ መድሐኒቶች ሌላ ተጨማሪ በሽታዎችን በመውለድ ለሌላ ህመምና መድሐኒት እያጋለጡ መሆናቸው በግልጽ አየታየ ነው።
ሌላው አሁን አሁን በመላው ዓለም አየተለመዱ ያሉ መድሐኒቶች ወይም አኛ ፔይን ኪለር የምንላቸው ህመም ማስታገሻዎች ናቸው። አነኚህ ፔይን ኪለሮች ሰውነትንም ሆነ ጭንቅላትን ሱስ የሚያሲዙ ናቸው። ለጭንቀት፣ ለስቃይ፣ ለእንቅልፍና ለድካም ወዘተ እየተባሉ የሚወሰዱ እነኚህ ፔይን ኪለሮች ከፍተኛ የጤና መቃወስን በዘላቂነት የሚያመጡ ናቸው። በዚህ ስልታዊ አካሄድ ለመድሐኒት ጥገኛ የሆኑ በቢልዬን የሚቆጠሩ ደንበኞችን በመላው ዓለም በማፍራት ቢግ ፋርማዎች ከፍተኛ ትርፍን እያካበቱና ሰዎችን የመቆጣጠር ዓላማቸውን እያሳኩ ይገኛሉ።
ሰባተኛ ስልታቸው ሳቢ ማስታወቂያዎች ቢግ ፍርም ኢንዱስትሪ በማስታወቂያው ረገድ ከፍተኛ የተባለ ገንዘብ ያወጣል። በዚህም በርካታ ተጠቃሚዎችን መሳብ ችሏል። በአሜሪካ ከየትኛውም ኢንዱስትሪ በላይ ለማስታወቂያ በጀት የሚያወጣ ሲሆን በስፋት ማስታወቂያዎቻቸው ደስታ፣ ሰላምን፣ ከስቃይ መላቀቅን በቀላሉ በመድሐኒቶች ማግኘት እንደሚቻል የሚያሳዩ ናቸው። ይህም ተጠቃሚዎችን ለማማለል ያለ ዶክተር ትዕዛዝ ከፋርማሲ መድሐኒቶችን የመሸመት ባህል እያጧጧፈው ይገኛል። ከዚያም አልፎ ዶክተሮችን ሁሉ ይህንን መድሐኒት እዘዝልን የሚሉ ታካሚዎች አንዲበራከቱም እያደረገ ይገኛል። እነኚህ ማስታወቂያዎች ጭንቅላትን መስለብ የሚችሉ ሳቢ በሆኑ የቪድዮና የድምጽ ቅንብሮችና በአማላይ ፓኬጆች የተዋቡ ነቸው። በዚህ ረገድ የብዙ ዓመት ልምድ ያላትና በፋርማሲ የሽያጭ ስራ የተካነችው ጎን ኤልሰን እንዲህ ብላለች ሴፍ(Safe) ወይም ጉዳት አልባ መድሐኒት የለም። እኛ ግን የተካንን ወሬኞች ስለሆን መድሐኒቶች ምንም ጉዳት እንደሌላቸው ማሳመንን ተክነንበታል ብላለች። ከዚህ በተጨማሪ ትልቅ ክብር የሚሰጣቸው ዶክተር ሪቻርድ ሆርተን አብዛኛው እነሱ አነሰ ቢባል ግማሽ በመድሐኒቶች ዙሪያ የሚነገሩ ዘገባዎች ሐሰት ናቸው። ሲሉ ተናግረዋል። በነገራችን ላይ ቢግ ፋርማዎች ከመድሐኒት ባለፈ ከጤና ዘይት እስከ ህጻናት ወተት ድረስ ቁጥጥራቸውን አስፍተውታል። በሀገራችንም አሁን አሁን በስፋት እያደገ ያለው የህጻናት ወተትና የዘይት ማስታወቂያዎች በማን የሚዘወሩ ይሆኑ? ይህን ለራሳችሁ ያዙትና ወደ ስምንተኛው አንለፍና
ስምንተኛው ሪፒቲንግ ነው ሪፒቲንግ ማለት አንድ መድሐኒት በተለያዩ ምክንያቶች ከገበያ ሲወጣ ወይም ሲወገድ ስምና አስተሻሸጉን በመቀየር በድጋሚ ወደ ገበያ የማምጣት ስልት ነው። ለምሳሌ ፕሮዛክ የተባለው መድሐኒት በአሜሪካ እጅግ ብዙ ተጠቃሚ የነበረው ሲሆን ራስን ለማጥፋት እንደሚገፋፋ ከታወቀ በኋላ ግን ገበያው ቀንሶ ነበር። ይህንን ተከትሎ በአዲስ ማሸጊያና በአዲስ ስም የቀድሞው መድሐኒት ይዞታውን ሳይቀይር ሳራፊም የሚል በዋጋ ጭማሪ የሴቶች የወር አበባ ማስታገሻነት በሚል ለመመለስ ችሏል። በዚህ አይነት ስልት በርካታ መድሐኒቶች ወደ ገበያ እየተመለሱ ይገኛሉ።
ዘጠነኛ በሽታዎችና ቫይረሶችን ማምረት ይህ ስልት ሰፋ ያለ የህዝብ ቅነሳና ዳጎስ ያለ ገንዘብ ለማግኘት የሚያስችል ነው። በዚህ ረገድ በአሁኑ ሰዓት የተከሰተውን ኮሮና ቫይረስን በቂ ምሳሌ አድርገን ማንሳት ይቻላል። ኮሮና ቫይረስ እስካሁን ብቻ ብዙ ሰዎችን የቀጠፈ ሁነኛ ሕዝብ መቀነሻ መሳሪያ ሆኗል። ከዛ በተጨማሪ ለኮሮና ቅድመ መከላከያና ህክምና የሚወጣው ወጪ ለቢግ ፋርማዎች ቢልዬን ዶላሮችን ወደ ካዝናቸው እያስገባላቸው ይገኛል። በቀጣይ የሚመጡ ክትባቶችና መድሐኒቶች የበለጠ እንደሚያተርፏቸው ይጠበቃል። በአሁን ሰዓት የተከሰተውን ኮሮናን አነሳን እንጂ ኢቦላ፣ ዚካ፣ ኤች አይ ቪ ኤድስና የመሳሰሉት ቫይረሶች በሚስጥር ማህበሩ ቢግ ፋርማ የተመሰረቱ እንደሆነ ብዙ ማስረጃዎች ያጋልጣሉ።
አስረኛው የህክምና ሪከርድን መሠብሰብ የሰዎች የህክምና ሪከርድ በዶክተሩና በታካሚው መካከል ብቻ የሚጠበቅ ሚስጥር ነው። ይህ ሪከርድ በሌሎች ሰዎች እጅ በገባ መጠን የታካሚው ደህንነት ስጋት ውስጥ ይገባል። የህክምና ዳታው የሚታወቅ ግለሰብ ወይም ሕዝብን በቀላሉ ማጥቃት ይቻላል። ይህን የተረዱት ቢግ ፋርማዎች በተለያዩ ስልቶች የህክምና ዳታን ይሰበሰባሉ። በ2018 ፌስቡክ የተጠቃሚዎቼን ደህንነትና ጤና ለመመዝገብ እንዲረዳኝ የህክምና ሪከርዳቸውን አንዲሰጠው መጠየቁ ይታወሳል። በዚህ አይነት ስልቶች ቢግ ፋርማዎች የግለሰቦችና የህዝብ ሪከርድ ሲሰበስቡ ይስተዋላሉ።
አስራ አንደኛውና የመጨረሻው የቢግ ፋርማ ተቃዋሚ ባለሙያዎችን ማጥቃት ቢግ ፋርማዎች በተለያዩ ስልቶች የነሱን መረጃዎች ለሕዝብ የሚያጋልጡ ሰዎችና ተቋማት ላይ የጥቃት በትራቸውን በመወርወር ላይ ይገኛሉ። የተወሰኑ ጥቃቶቻቸውን ለማሳያ ብንመለከት በቅርብ ጊዜ በጥይት ህይወቱን ያጣው ታዋቂው ራፐር ኒፕሲ ሁስል ተጠቃሽ ነው። ራፐሩ በዶክተር ሳቢ ዙሪያ ዶክመንተሪ እያዘጋጀ ነበረ። ዶክተር ሳቢ ኤድስና ካንሰርን ለመሰሉ በሽታዎች የተፈጥሮ መድሐኒቶችን ያገኙና ብዙዎችን የፈወሱ በ1980ዎቹ የነበሩ ሰው ናቸው። እኚህ ዶክተር በቢግ ፋርማ በተቀነባበሩ ክሶች በ1988 ዓ.ም ኤፍ ዲ ኤ ያላጸደቀውን መድሐኒት በህዝብ ላይ ተጠቅመሀል በሚል ቢከሱትም 77 ከኤድስ የፈወሷቸውን ታካሚዎች ምስክርነት ፍርድ ቤት በማቅረብ ነጻ መውጣት ችለው ነበር። በኋላ ላይ ግን በአውሮፕላን ጉዞ በሚያደርጉበት ወቅት ከተፈቀደው በላይ ገንዘብ ይዘዋል በሚል የተቀነባበረ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ክስ ተከሰው እስር ቤት የገቡ ሲሆን በዛው እስር ቤት ውስጥ ባሉበት ወቅት በአንድ እስረኛ ተገድለው ህይወታቸው በቢግ ፋርማዎች የተነጠቁ የክፍለ ዘመኑ ድንቅ ዶክተር ነበሩ። ሌላኛው ሴራቸውን ስንመለከት በኦቲዝምና በሌሎች የቢግ ፋርማ ክትባቶች ዙሪያ አንሉኪንግ ኦቲዝም የተባለ ጽሁፎችን በማዘጋጀት ቢግ ፋርማዎችን እያጋለጠች የነበረችው ጃማ ቢክ ባልታወቀ በተባለ ምክንያት ሞታ ተገኝታለች። የዚህ ፕሮጀክት ኤዲተር የነበረውና በድፍረቱ የሚታወቀው ጥልቁን የኦቲዝም ኢንቨስቲጌሽን ያደረገው ዳን ኦልማስተርድ እሱም ሞቶ ተገኝቷል። ሌላኛው ካናዳውያኑ ቢልዬነር ጥንዶች የ3.5 ቢልዬን ዶላር ባለቤት የሆኑት ባሪ ሸርማንና ባለቤታቸው ቢግ ፋርማን ተቃርነው በመስራታቸው በ2016 ተገድለው ተገኝተዋል። ሌላው ኪዮሞ ቴራፒ ለካንሰር አጋላጭ መሆኑን በትጋት ይገልጹና ይሰሩ የነበሩ ፎር ባንክስና አን የተባሉ ጥንዶች እስከ ሁለት ልጆቻቸው በአሪዞና ተገድለው ተገኝተዋል። ሌላ በተፈጥሮ መድሐኒቶች አቀንቃኝነቷ የምትታወቀው የቢግ ፋርማዋ ተጻራሪና ተቺ አና ቦሪች በሎሳንጀለስ ሞታ ተገኝታለች። ሄሊንግ መልቲፕልስኬለርስ እና ዘካንዲዳ ኬር የተሰኙና ሌሎች መጽሐፍትን የጻፈች ትጉህ ሴትም ነበረች። በአጠቃላይ በአሜሪካ ብቻ በአስራ ስምንት ወራት ውስጥ ከስልሳ በላይ ዶክተሮችና ሪሰርቸሮች ተገድለው ተገኝተዋል። ሙሉ የሞቱትን ሰዎች ዝርዝር ለማግኘት ከፈለጋችሁ pharmamurders.com ላይ መመልከት ይቻላል።
👇👇👇
ይህ የተደራጀ አፈናና ግድያ በአሜሪካ በስፋት ይዘገብ እንጂ በመላው ዓለም ላይ የተዘረጋ እንደሆነ መገመት አይከብድም።
እንግዲህ በአስራአንድ ከፍለን የተመለከትናቸው የቢግ ፋርማ ስውርና ግልጽ የሆኑ የጥቃት ስልቶች ይህንን ይመስላሉ። ታዲያ በመጨረሻም ሁላችንም ልንነቃ ይገባል። ዙሪያችን በሰይጣናዊ መንፈስ ተከቧል። ኃያላኑ አለምን በአንድ መንግሥት ብለው የወጠኑት ሀሳብ እንዳይሳካላቸው ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማድረግ ይገባናል። ከላይ መጀመሪያ በስዕሉ ላይ ያያችኋቸውን መጽሐፍት በዋቢነት ተጠቅሜአቸዋለሁ።
አመሰግናለሁ።
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
https://t.me/mengste_semayat/209
The FDA and the MHRA, the regulator of pharmaceutical companies in the USA and Britain, are both controlled by the big pharmaceutical corporations. The FDA and MHRA have big pharma directors on their boards, and so big pharma control their own regulation. The result is pharmaceutical drugs kill a mi...