Solutions for a problem

Solutions for a problem Problems can be changed to blessings! understand them and solve them positively. Answerd prayers!

ክብር ለሰው ልጆች ሁሉ በመላው ዓለም
02/03/2026

ክብር ለሰው ልጆች ሁሉ በመላው ዓለም

02/03/2026

ቀን 22/06/2018 ዓ.ም

የአልጎሪዝም ወጥመድ !

በኢትዮጵያችን አንገብጋቢ አጀንዳዎቻችን ፖለቲካ፣ ሰብዓዊ መብት፣ በህይወት የመኖር ደህንነት፣ የኑሮ ውድነት፣ ኢኮኖሚ፣ ሰላም እና ሌሎች... ጉዳዮች ናቸው።

እውነት ነው እነዚህ ወሳኝ ጉዳዮች መሆናቸው አይካድም።

ነገር ግን ከነዚህ እኩል ሀገርን እና ትውልድን ከውስጥ እየበላ ስላለውና ትልቅ አደጋ ስለደቀነው የማህበራዊ ሚዲያ (በተለይም ቲክቶክ) ሱስ መነጋገር ይበጃል።

1. ትምህርት የሀገር ግንባታ ዋናው መሰረት ነው። ዛሬ ዛሬ ላይ የማህበራዊ ሚዲያው /ቲክቶክ " ሳይማሩ መታወቅን " እና " ሳይለፉ መክበርን " እንደ ስልጣኔ እያቀረበ ታዳጊዎቻችንን ከመጽሐፍ እያራቃቸው ነው። አንዳንዱ የትውልዱ አካል ማንበብን እንደ ኋላ ቀርነት፣ ስክሪን ላይ ፈዞ መዋል ደግሞ እንደ "ፈታ ማለት " እያየው ነው።

2. በተለይም ከማህበራዊ ሚዲያዎች መካከል ቲክቶክ አእምሮን በቀላሉና ያለ ድካም በሚገኝ ደስታ እንዲለምድ እያደረገው ነው። ትምህርት ደግሞ ትዕግስት፣ ጥረትና ትኩረት ይጠይቃል። በዚህ ምክንያት ልጆቻችን መጽሐፍ ማንበብ " አሰልቺ "፣ ቲክቶክ ማየት ግን " አስደሳች " እየሆነባቸው ነው።

3. ጠንክሮ ሰርቶ፤ ተመራምሮ ፤ አጥንቶ ሀገርን መለወጥ ቀርቶ በስክሪን ፊት ቆሞ በመሰዳደብ፣ ለረጅም ሰዓት ቁጭ ብሎ በማውራት ፣ የቤተሰብን የግልን የሰዎችን ገመና አደባባይ በማስጣት ፣ ሲበሉ ሲጠጡ ሲዞሩ በመዋል ፣ በመጨፈር ወይም ሰውን በመሳደብ የሚገኝ " ቀላል ገንዘብ " የልጆቻችን ህልም ሆኗል። ይህ ለሀገር አደጋ ነው።

4. የኛ ማህበረሰብ የሚታወቅበት ጨዋነት፣ መከባበርና እሴት በ"ቪው" እና "ላይክ" እየተቸረቸረ ነው። ዝና ለማግኘት የማይደረግ ነውር የለም።

5. የነገ ሀገር ተረካቢ ልጆቻችን በዲጂታል ሱስ አእምሯቸው እየታወረ ነው።

6. ልጆቻችን ስልክ ውስጥ ጠፍተዋል። ከቤት ሳይወጡ ግን ከእኛ ርቀዋል። ቲክቶክ የልጆቻችንን ስነ-ልቦና እና የትምህርት ፍላጎት እየገደለ ነው። የወደፊት ተስፋቸው በ60 ሰከንድ ቪዲዮ እየተቀበረ ነው።

7. ልጆቻችን " ለመክበር፣ ገንዘብ ለማግኘት ፣ ለመታወቅ፣ ጥሩ ህይወት ለመኖር ምንም መማር አያስፈልግም " የሚል የተሳሳተ መልዕክት እየተጋቱ ነው። ሳይማሩና ሳይለፉ በቲክቶክ ብቻ ገንዘብና ዝና ያገኙ ሰዎችን እንደ አርአያ (Role Model) ማየት ጀምረዋል።

8. መጽሐፍ ገልጦ ለማንበብ የሚሰለቻቸው ልጆች ለሰዓታት ስክሪን ላይ አይናቸው ሳይዝል መቆየት ይችላሉ። ይህ በትምህርታቸው ላይ ትልቅ ቀውስ እየፈጠረ ነው።

9. ልጆቻችን ስልክ ሲነኩባቸው የሚቆጡ፣ ስልክ ሲቀሙ የሚበሳጩና በትንሽ ነገር የሚጨቃጨቁ እየሆኑብን ነው።

10. ልጆቻችን የወላጆችን ጨዋነትና ስነ-ምግባር ሳይሆን የማህበራዊ ሚዲያ ዝነኞችን ጩኸትና ነውር ፣ ስድብ ፣ ጋጠወጥነት እንደ ስልጣኔ እየቆጠሩት ነው።

የሚመለከተው አካል ሁሉ ለተማሪ ወላጆች እንድደርስ ቢያደርግ እና ከወላጆች ጋር ውይይት እንድደረግ ቢደረግ መልካም ነው።

( ከዘርፉ ባለሞያዎች የተወሰደ)
( ላዕከ ኄራን ነኝ)

01/03/2026
26/02/2026
እድሉን ተጠቀሙበት አልፋ ለስኬታችን ጉልህ ድርሻ !
26/02/2026

እድሉን ተጠቀሙበት

አልፋ ለስኬታችን ጉልህ ድርሻ !

24/07/2024
30/10/2022

ሰው በመሆን ውስጥ ድንቅ ምሥጢር አለ!
ማስተዋሉን ይስጠን

08/12/2021

የጽናት ውጤት
አቤት ሲጥም!

16/10/2021

ታገሱ

በትዕግስት የማይሸነፍ የለም

Address

Addis Ababa
Bole Sub City

Telephone

+251911290201

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Solutions for a problem posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Solutions for a problem:

Shortcuts

Share

Category