08/10/2022
በሰው ቂም አትያዝ
በሰው ቂም አትያዝ በሰው ላይ ያለውን ቂም በልቡናው የሚያሳድር ሰው ጸሎቱ ቅድመእግዚአብሔር አትደርስምና ከመናፍቃን ጋር አትጸልይ ከአሕዛብ ጋርም ቢሆን ሃይ አበ 20፥17
ተቆጡ ነገር አትበድሉ በመኝታችሁ ሳላችሁ በልባችሁ የምታስቡት ይታወቃችሁ መዝ 4፥4
የዋሀን ብፁአን ናቸው እነርሱ ምድንን ይወርሳሉና...በሚሰድቧችሁና በሚያሳድዷችሁ ጊዜ ስለእኔም እየዋሹ ክፉውን ሁሉ በሚናገሩባችሁ ጊዜ ብፁዓን ናችሁ ማቴ5፥5-12
ወንድሞቻችን ራሳችሁ አትበቀሉ ቁጣን አሳልፏት እኔ እበቀላለሁ...ጠላትህ ቢራብ አብላው ቢጠማም አጠጣው ይህንን ብታደርግ የእሳት ፍህም በራሱ ላይ ትክምራለህ ሮሜ 12፥19-21
ተቆጡ አትበድሉም ፀሐይ ሳይጠልቅም ቁጣችሁን አብርዱ ለሰይጣንም መንገድ አትስጡ ኤፌ4፥26-27
ሕፀፅ እንደሚያመጣብህ የምታውቀውን አትሥራ ሰውን ሁሉ ውደድ ሰዎች ሁሉ በአንተ ዘንድ ከራስህ ይልቅ የከበሩ ይሁኑ ከሰው ሁሉ ጋር ሰላማዊ ሁን ሃይ አበ 21፥5
አሁንም በክርስቶስ ደስታ ወይም በፍቅር የልብ መጽናናት ወይም የመንፈስ አንድነት ወይም ማዘንና መራራትም በእናንተ ዘንድ ካለ እርሱን ብቻ ታስቡ ዘንድ አንድ ልብና አንድ ምክርም ሆናችሁ ትህትናን በያዘ ልቡና ከራሳችሁ ይልቅ ባልንጀራችሁን አክብሩ እንጂ አትታበዩ ፊልጵ 2፥1-5