02/09/2026
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የቅበላ ማስታወቂያ 🎓
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው የመግቢያ መስፈርት መሰረት በማታ (Extension) እና በርቀት (Distance) መርሃ ግብሮች በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በPGDT ተማሪዎችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል።
በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉና መማር የምትፈልጉ አመልካቾች ከነሀሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እያስታወቅን የምታመለክቱባቸውን የትምህርት መስኮች ዝርዝር ከታች መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
🎯 የማመልከቻ መስፈርት (በትምህርት ሚኒስቴር የመግቢያ መስፈርት መሰረት)፡
🔖 የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው በትምህርት ሚኒስቴር የወጣውን የየዘመኑን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ፤
🔖 ከዲፕሎማ ወይም ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ወደ ከፍተኛ ትምህርት ለመግባት የተቀመጠውን የመግቢያ መስፈርት ያሟሉ፤
🔖 በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአቅም ማሻሻያ (Remedial program) ተከታትለው የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ፤
🔖 ለበለጠ መረጃ የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ ይመልከቱ::
📑 ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶች/ማስረጃዎች፡
📝 የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ፎቶ ኮፒ፤
📝የብቃት ማረጋጫ (COC) (ለሚያስፈልጋቸው ብቻ)፤
📝ኦፊሻል ትራንስክርፒት (ለሚያስፈልጋቸው ብቻ)፤
📝ለማመልከቻ (Application fee) 300 ብር የተከፈለበት ኦሪጅናልና አንድ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
📍 የማመልከቻ ቦታ፡
🔖 ለማታ ትምህርት ፕሮግራሞች፡ በባህር ዳር ካምፓስ በየአካዳሚክ ክፍል ሬጅስትራሮች ሲሆን፤
🔖 ለርቀት ትምህርት ፕሮግራሞች፡ በርቀት ትምህርት ማዕከላት ማለትም በባህር ዳር፤ ጎንደር፤ ደሴ፤ ደብረ ብርሃን፤ አዲስ አበባ፤ ደብረ ማርቆስ፤ ፍኖተ ሰላም እና ሞጣ - እነሴ ማዕከላት ምዝገባ ይደረጋል::
⚠️ ተጨማሪ ማሳሰቢያዎች፡
🔖 የቀድሞው ትምህርት ፖሊሲ 12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃ ተቀባይነት የለውም፤
🔖 በዲፕሎማ የሚመዘገቡ አመልካቾች በምዝገባ ወቅት ኦፊሻል ትራንስክርፕት በፖስታ ሳጥን ቁጥር 79 ማስላክ አለባቸው፤
🔖 በሀገር አቀፍ ደረጃ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና ላልተዘጋጀላቸው የትምህርት ዘርፎች ዩኒቨርስቲው የሚያዘጋጀውን የመግቢያ ፈተና መውሰድ አለባቸው:: የፈተናው ቀን እና የቅበላ ውጤት ይፋ የሚደረግበትን ቀን በውስጥ ማስታወቂያ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et ወይም የፌስቡክ ገጽ ወደ ፊት ይገለፃል፤
🔖በቂ የተማሪ ቁጥር የማያመለክትባቸው የትምህርት መስኮች አይከፈቱም::
🔖ከዚህ በፊት ለመማር ተመዝግበው ባቋረጡት የት/ት መስክ በተመሳሳይ የቅበላ ዓይነት መመዝገብ አይቻልም::
💳 ክፍያ የሚፈጸምባቸው የባንክ አካውንቶች፡
የመመዝገቢያ ክፍያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሚከተሉት የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ገቢ የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች መክፈልና ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
📌 1000224663378 — ለቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ ማህበራው ሳይንስ፣ ሂውማኒቲስ፣ ለህግ፤ ትምህርት ኮሌጅ (PGDT)፣ግብርናና አካባቢ ሳይንስ እና ስፖርት አካዳሚ የትምህርት መስክ አመልካቾች ብቻ፤
📌 1000096185007 — ለኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት (EiTEX) የትምህርት መስክ አመልካቾች ብቻ፤
📌 1000013094563 — ለባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት (BiT) የትምህርት መስክ አመልካቾች ብቻ::
📚 የሚሰጡ የትምህርት መስኮች ዝርዝር (Programs Offered)
🔻 1. የርቀት ትምህርት ፕሮግራሞች (Distance Programs)
(የማመልከቻ ማዕከላት፡ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ደብረ ብርሃን፣ አዲስ አበባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ፍኖተ ሰላም እና ሞጣ-እነሴ)
* College of Business and Economics (BA Degree):
* Accounting and Finance
* Management
* Economics
* Marketing Management
* Logistics & Supply Chain Management
* Faculty of Humanities (BA Degree):
* English Language and Literature
* Ethiopian Language and Literature- Amharic
* Folklore / Culture Studies
* Ge’ez Language & Literature
* Journalism and Communications
* Faculty of Social Science (BA Degree):
* Civics and Ethical Studies
* Geography
* Sociology
* Political Science
* Social Work
* College of Education (PGDT Program):
* PGDT (Amharic; English; Geography; Civics; Mathematics; Chemistry; Biology; Physics; Sport Science; ICT; Economics; Business education)
🔻 2. የማታ ትምህርት ፕሮግራሞች (Extension Programs)
(የማመልከቻ ቦታ፡ በባህር ዳር ካምፓስ)
* College of Business and Economics (BA Degree):
* Accounting and Finance
* Economics
* Management
* Marketing Management
* Logistics & Supply Chain Management
* Tourism and Hotel Management
* School of Law (BA Degree):
* Law
* Governance and Developmental Studies
* Faculty of Social Science (BA Degree):
* Civics and Ethical Studies
* Geography
* Sociology
* Political Science
* Philosophy
* Social Work
* Faculty of Humanities (BA Degree):
* English Language and Literature
* Ethiopian Language and Literature- Amharic
* Folklore / Culture studies
* Ge’ez Language & Literature
* Journalism and Communications
* Cinema and Theatre Arts
* Sport Academy (BSc Degree):
* Physical Education
* Sport Science
* College of Agriculture and Environmental Science (BSc Degree):
* Veterinary Science
* Ethiopian Institute of Textile and Fashion Technology - EiTEX (BSc Degree):
* Fashion Design
* Garment Engineering
* Leather Product Engineering
* Textile and Apparel Merchandising
* Faculty of Computing (BSc Degree):
* Computer Science
* Software Engineering
* Cyber Security
* Information Systems
* School of Material Science and Engineering (BSc Degree):
* Material Science and Engineering
* Faculty of Civil & Water Resource Engineering (BSc Degree):
* Civil Engineering
* Hydraulic & Water Resource Engineering
* Water Resources & Irrigation Engineering
* Faculty of Electrical and Computer Engineering (BSc Degree):
* Electrical Engineering
* Computer Engineering
* Faculty of Chemical & Food Engineering (BSc Degree):
* Human Nutrition
* Faculty of Mechanical & Industrial Engineering (BSc Degree):
* Mechanical Engineering
* Automotive Engineering
* Electromechanical Engineering
* Industrial Engineering
🌐 የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ድረ-ገጽ፡
https://bdu.edu.et/registrar/
ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ መረጃውን ያካፍሉ! 🔄