Am La Bi

Am La Bi “ከህሊናህ ጋር ተጨዋወት፤ተከራከር፤ተወዳጅ!

ሰውዬው በጉዞ ላይ እያለ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ይወድቃል። ጉድጓዱ አስፈሪና ያለ ሰው እርዳታ መውጣት የማይቻልበት ነበር። ሰውየው በከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆኖ "እባካችሁ እርዱኝ!" እያለ...
17/07/2026

ሰውዬው በጉዞ ላይ እያለ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ይወድቃል። ጉድጓዱ አስፈሪና ያለ ሰው እርዳታ መውጣት የማይቻልበት ነበር። ሰውየው በከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆኖ "እባካችሁ እርዱኝ!" እያለ መጮህ ጀመረ።..
የመጀመሪያው መንገደኛ መጣና ቁልቁል አየው። "እኔ ዶክተር ነኝ፣ ለአስቸኳይ ስራ እየተጣደፍኩ ነው። ስትወጣ ግን ነፃ ህክምና እሰጥሃለሁ" ብሎ አድራሻውን ወርውሮለት ሄደ።..
ሁለተኛው መንገደኛ መጣ። "እኔ ጠበቃ ነኝ፣ ፍርድ ቤት ቀጠሮ አለኝ። ከወጣህ ግን ነፃ ጥብቅና ቆሜ ይህንን ጉድጓድ የቆፈረውን አካል ከስሰን ካሳ እንድታገኝ እረዳሃለሁ" ብሎት አለፈ።..
እየመሸ መጣ፣ የሰውየውም ተስፋ እየጨለመ ሄደ። በድንገት ሶስተኛ መንገደኛ የእግር ኮቴ ተሰማ። ሰውየው አቅሙን አሰባስቦ ሲጮህ... መንገደኛው ቅንጣት ሳያቅማማ ራሱን ቁልቁል ወደ ጉድጓዱ ወረወረ!..
ጉድጓድ ውስጥ የነበረው ሰውዬ በድንጋጤ፡ "ምን አይነት ጅል ነህ? እኔን ልታወጣ ሲገባህ ራስህን አደጋ ላይ ጥለህ አብረኸኝ ትገባለህ?" ሲል ጠየቀው።
ሰውየውም ፈገግ ብሎ፡ "አይዞህ ወዳጄ! እኔም አንድ ቀን እዚህ ጉድጓድ ውስጥ ወድቄ ነበር፤ መውጫውን መንገድ ጠንቅቄ አውቀዋለሁ!" አለው።..
በተፈተንክበት መንገድ ቀድመው የተፈተኑ፣ በወደቅክበት ገደል የወደቁ ሰዎች የመውጫውን ቁልፍ በእጃቸው ይዘዋል። በህይወትህ ማንን እርዳታ መጠየቅ እንዳለብህ ጠንቅቀህ እወቅ።
የተፈተነ እና ያንተ ህመም የሚሰማው ወዳጅ ካለህ ካንተ በላይ እድለኛ የለም። አጥብቀህ ያዘው፣ "መውጫውን መንገድ አሳየኝ" በለው!

Amare Lucky

ስማርት ጫማ (Smart shoes for blind)የጃፓን ድርጅት ስማርት ጫማ ዘመናዊ ጫማዎች ለገበያ አቅርቧል።ጫማ ላይ የሚለጠፍ እንደ ሶል ያለ የሚንቀጠቀጥ (ቫይቭሬት)የሚያደርግ ማየት የተ...
13/05/2026

ስማርት ጫማ (Smart shoes for blind)
የጃፓን ድርጅት ስማርት ጫማ ዘመናዊ ጫማዎች ለገበያ አቅርቧል።

ጫማ ላይ የሚለጠፍ እንደ ሶል ያለ የሚንቀጠቀጥ (ቫይቭሬት)የሚያደርግ ማየት የተሳናቸው ሰዎች መምራት የሚችል ከአንድ ቦታ ወድ ለሌላ ቦታ መሄድ እንዲችሉ የሚያደርግ ቴክኖለጂ ነው።
አፕልኬሽኑ መስራት የሚችለው መሄድ ወድ የሚፈልጉት ቦታ ለአፑ ያስገባሉ ወይም ይነግሩታል። አንዴ የቦታውን ስም ካስገቡ አፑ ይጠቁማል። በጃፓን በስፍት እየተሸጠ ነው።
We Use Ai photo

ከመነቃቃት ባሻገር!!!ማንኛውንም አይነት አለም አቀፍ ጥናት ብትከታተሉ ከሚከተለው ቁጥር ብዙ ያልራቀ መረጃ ታገኛላችሁ፡፡⏭️ 92% የሚሆኑ ሰዎች ያወጡትን ግብ አይመቱም፡፡⏭️ ይህ ማለት 8%...
23/03/2026

ከመነቃቃት ባሻገር!!!

ማንኛውንም አይነት አለም አቀፍ ጥናት ብትከታተሉ ከሚከተለው ቁጥር ብዙ ያልራቀ መረጃ ታገኛላችሁ፡፡

⏭️ 92% የሚሆኑ ሰዎች ያወጡትን ግብ አይመቱም፡፡

⏭️ ይህ ማለት 8% ሰዎች ብቻ ናቸው ግባቸውን የሚመቱት፡፡

⏭️ 3% የሚሆኑ ሰዎች ያወጡትን ግብ ይጀምሩና 30 ቀናት እንኳን ሳይቀጥሉት ያቆሙታል፡፡

ለዚህ ሁኔታ ከሚዳርጉ መንስኤች ዋና ዋናዎቹ

1. ግብን ሲያወጡ ግልጽ አድርጎ አለማውጣት

2. ግብን ካወጡ በኋላ ወደዚያ የሚያደርሳቸውን ስልት አለመዘርጋት

3. ባወጡት ግብና በሚከተሉት ስልት ላይ ተጠያቂነትን አለመፍጠርና ለብቻ መታገል

መመሪያዎች

1. በአንድ ሃሳብ ዙሪያ ከተነቃቃችሁ (Motivated ከሆናችሁ) በኋላ ግብን ማውጣታችሁን አትዘንጉ፡፡

2. ግብን ካወጣች በኋላ ከየት ተነስታች፣ ወደ የት እንደምትደርሱ፣ እንዴት እንደምትደርሱና መቼ ተከናውኖ ማየት እንደምትፈልጉ በግለጽ አስቀምጡ፡፡

3. በግልጽ ያወጣችሁትን ስልት በየቀኑ መከታተል፣ ስታቆሙ እንደገና መቀጠልና ከአቅም በላይ ሲሆን በሃላፊነት የሚጠይቃችሁና የሚያግዛችሁ ሰው አዘጋጁ፡፡

Dr. Eyob

09/03/2026

መጻጉዕ ሰው የለኝም እያለ ያለቅስ የነበረ፣ ሰው መሆኑን ረስቶ ሰው እንደሆነ ያስረዳለትን ጌታ እንዴት በጥፊ ይመተዋል።ወይ አለመታደል?

✍️መጻጉዕ ምን ሁኖ ነው?

አልጋህን ተሸክመህ ሂድ ሲለው ለመቆም ያበቃኝ ሳያንገላታ ደጅ ሳያስጠና እንዲሁ በነጻ ያለዋጋ በቅጽበት ያዳነኝ እርሱ ማነው? ብሎ ሳይጠይቅ?

ስድቤን ያራቀልኝ፣ መዋረዴን ያስወገደልኝ ይህን ሰው ከመሄዴ በፊት ልተዋወቀው አለማለቱ የመጻጉዕ በደል ከዚያ ይጀምራል፤ ምክንያቱም ከዚህ የበለጠም ውለታ የለምና::

ይህ ለመጻጉዕ እንደ አዲስ መፈጠር ነበር፣ ሊቁ እንዲህ እንዳለ “ኢያእመረ ዘአሕየዎ በዕለተ ሰንበት ብእሲ ዘአሕየወኒ ውእቱ ይቤለኒ ተንሥእ ንሣእ ዐራተከ ውእቱ ቤተከ፡ መጻጉዕ በዕለተ ሰንበት ያዳነውን አላወቀም! ያዳነኝ ያ ነው አልጋህን ተሸክመህ ተነሣ ወደ ቤትህም ሂድ አለኝ፡፡ በማለት ታሞ የተነሣ ፈጣሪውን ረሳ እንዲሉ መፃጉዕ መዳኑን ብቻ ነው ያየው፤ እንዴት እንደዳነ ማን እንዳዳነው መጠየቅም አልወደደም::

በጣም የሚገርመው ማንም ሊያደርግለት ያልቻለ የዘመናት እንቆቅልሹን የፈታለትን፤ ውሳጣዊ ጥማቱን ያረካለትን አምላክ መልኩን እንኳን በቅጡ ሳያይ “አመሰግናለሁም,, ሳይል አልጋውን ተሸክሞ ሄደ።

መፃጉዕ ያየው መዳኑን ብቻ ነበር፣ ስላዳነው ጌታ ማወቅ ጉዳዩም አይደለም፣ ዛሬም የእነርሱን መዳን መበልፀግ ብቻ የሚያስቡ አልጋቸውን ገንዘባቸውን ብቻ ይዘው የሚሄዱ፤ ማንጅራት ገትር እንደየዘው ሰው ዘወር ማለት የማይፈልጉ! የተነሡበትን ቦታ የሚረሱ እንደ መጻጉዕ ያሉ በዘመናችን እንዳሉና እንደሚኖሩ ማሳያ ነው::

✍️እግዚአብሔር ለሁላችንም ማስተዋሉን ይስጠን!!!

09/03/2026

ከአንዲት ቆንጅዬ ልጅ ጋ ነበርኩ። መኪና ውስጥ ነበርን ፒዛ እየጋበዝኳት አስተናጋጁ ሲያልፍ በእጄ ቢል እንዲያመጣልኝ ነገርኩት

ቢል ይዞ መጣ

እያየኝ ከፊት ከኃላ ኪሴ አውጣጥቼ ሂሳብ ከፈልኩ ...
ሄደ .... መልስ መጠበቅ ጀመርኩ አልመጣም ጠበኩት አልመጣም ተበሳጭቼ ክላክስ አስጮህኩ

(ሱሰኛ ይመስላል ፣ የቀረውን ገንዘብ ለማስቀረት አስቦ ነው ፣ ጉርሻ በፍቃደኝነት የሚሰጥ እንጂ በብልጠት የሚዘገን አይደለም ፣ ሲቆይብን ሰልችቶን እንድንሄድ ነው )

ያስጮኩትን ክላክስ ሰምቶ መጣ

"መልስ ስጠን እንጂ ጌታው "አልኩት

"የሰጠኸኝ ስድስት መቶ ነው ሂሳቡ ደሞ ስድስት መቶ ሰላሳ አምስት ብር ነው "አለኝ ( ስበረብር ስላየኝ የለው ይሆናል በማለት ተሳቆ ነው እንዳልገረጣ ይጎላል ያላለው )

ከሌለህ ብዬ ነው አይነት ፊት አሳየኝ ። አንዳንድ አድራጎት የሚያገዝፈው አደራረጉ ነው ።

ይቅርታ ቢሉን በደንብ ስላላስተዋልኩት ነበር።
በጣም አመሰግናለሁ አልኩት

እንደገና ኪሴን በርብሬ ድፍን ሁለት መቶ ብር ሰጠሁት እንዲመጣልኝ እንዳልቸኮልኩ እንዲሄድልኝ ቸኮልኩ
መልስ ሊያመጣልኝ ሄደ

ሳይነግሩን ለዋሉልን እየነገርን መዋል ነውር ነው አይደል ?
ሳይመጣብኝ ሄድኩኝ ።
Adhanom Mitiku

14/01/2026

---እልልታ---

>

የኮንዶሚኒየሙን ደረጃዎች ከልጇ ጋር እየወረደች ሳለ ህንጻው በእልልታ ድምፆች ደመቀ፡፡

በመጀመሪያ 'እልልልል' የሚል የአንዲት ሴት ቦግ ያለ ድምፅ ሽቅብ ተወርውሮ ጆሯቸው ገባ፡፡

ወዲያው የሴትየዋን ጥሪ የተቀበሉ ሌሎች ሴቶች እልልታ አንዱ በአንዱ ላይ እየተነባበረ ህንጻውን አጥለቀለቀው።

ደረጃዎቹን ጨርሰው ህንጻው መግቢያ ወለል ጋር ሲደርሱ አንዲት ነጭ የሌሊት ጋወን የለበሰች ሰፋ ያለችና እንደ ገመምተኛ የምትራመድ ሴት እና ሌላ አራስ ህጻን ሸፋፍነው ያቀፉ አዛውንት ሴት ገጠሟቸው።

ሁለቱን የከበቡት ከስምንት የማያንሱ ሴቶች ከአንድ ገላ እንደተሰሩ ሁሉ እኩል እየተነንቀሳቀሱ እልልታቸውን ቀጥለዋል፡፡

ልጇን ወደ ራሷ ሳብ አድርጋ መንገዱን አሰፋችላቸው፡፡

“እማዬ፣ ለምንድነው የሚጮሁት?” ብሎ ጠየቃት ልጇ ሴቶቹ በአጀብ አልፈው ደረጃውን መውጣት ሲጀምሩ፡፡

‹‹እየጮሁ አይደለም እኮ ልጄ… እልል እያሉ ነው››

መለሰችለት፡፡

‹‹ እሺ ለምንድነው እልል የሚሉት?›› መልሶ ጠየቃት፡፡
‹‹ደስ ስላላቸው ነዋ››
‹‹ለምንድነው ደስ ያላቸው?››

ልጇ ጥያቄዎችን አከታትሎ ሲተኩስባት ፈገግ አለችና በእንሂድ ሁኔታ ቀደም ብላ እጁን ይዛ እየጎተተች፣

‹‹ልጅ ስለተወለደላቸው ነው ደስ ያላቸው›› አለችው፡፡

‹‹አላየኃቸውም እንዴ? …ትልቋ ሴትዮ እኮ ህጻን ልጅ አቅፈዋል››

‹‹አይቻቸዋለሁ›› አለ ልጁ፡፡

የግቢው የውጪ በር ጋር ደረሱ።

“ማሚ” አለ ልጇ በሰው የተሞላው አውራ ጎዳናን ሲቀላቀሉ፡፡

“ወዬ?”

“እኔ ስወለድ አንቺና አክስቶቼ..አያቴ… እንደዚህ ደስ ብሏችሁ ነበር እንዴ?”

“እንዴት ደስ አይለንም ልጄ? ..በጣም ነው ደስ ያለን እንጂ”

“እልል ብላችሁ ነበር?”

“አዎ፣ በደንብ ብለናል”

"ሁላችሁም?"

"ሁላችንም"

“አባቴም? ››

ደነገጠች፡፡

ዞር ብላ ቁልቁል አየችው፡፡

‹‹አባትህ ምን? ›› በፍርሃት ጠየቀችው፡፡

‹‹እሱም ስወለድ እልል ብሎ ነበር?”

ከየት መጣ ያለችው ጭንቀት ወረሳት፡፡ መልስ ከመስጠትዋ በፊት ትንሽ አመነታች፡፡

“አባትህ?”
‹‹አዎ››
“አይ ልጄ… ወንዶች እኮ እልል አይሉም”

በመልሷ እንደረካ ሁሉ ጭንቅላቱን በስምምነት ነቀነቀ፡፡

በዝምታ ጥቂት እርምጃዎችን ከተጓዙ በኋላ ግን፣

“ማሚ›› አላት፡፡
‹‹ወ--ዬ››
‹‹ቅድም ወንዶች እልል አይሉም ነው ያልሽኝ አይደል?”
‹‹አዎ አይሉም›› አስረግጣ መለሰች፡፡
“እሺ… ግን አባቴ እኔ ስለተወለድኩ ደስ ብሎት ነበር ?”

በረጅሙ ተነፈሰች፡፡

“ይሄውልህ ልጄ” አለች ቃላቶቿን በጥንቃቄ እንደምትመርጥ እያሳበቀባት ረጋ ብላ፣

“ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ ነግሬህ የለ? … እኔ አንተን የወለድኩ ቀን አባትህ አብሮኝ አልነበረም። ስለዚህ ደስታውን በምን ይግለጽ አላውቅም። ግን ደስ ብሎት እንደነበር እርግጠኛ ነኝ።”

“ካላየሽው እንዴት እርግጠኛ መሆን ትችያለሽ?”

ዝም አለችው፡፡

“ስወለድ አልመጣ። በዚያ ላይ አሁንም በስንት አመት ነው የሚያገኘኝ። አሁን እንኳን ለልደቴ መች መጣ?”

በድንገት ቀርፋፋ እርምጃዋን ገታችና ቆመች።

መንገዱን ሞልቶ ከሚተመው እግረኛ ለመሸሽ ልጇን ወደ አንዱ ግንብ ጥግ ወስዳ አቆመችውና፣

“ምክንያቱም አንተን የማይወድህ ሰው የለማ” ብላ ጀመረች፡፡

ሁሌም ሰበብ ፈልጎ አባቱን ሲያነሳ እንደምትሆነው ከእንባዋ ጋር ግብ ግብ ገጥማለች፡፡

“ሁሉም ሰው ይወድሃል። እንኳን አባትህ ገና ዛሬ ያገኘህ ሰው እንኳን ስለተወለድክ በጣም ደስ ነው የሚለው..አባትህም ቢሆን አልሆንለት ብሎ ነው እንጂ----- ”

ሳትጨርስ አቋረጣት፡፡

‹‹ማሚ በቃ ተይው››
‹‹ለምን?››
‹‹እንድታለቅሺ አልፈልግም››

በግራ እጇ መፍሰስ የጀመረ እንባዋን ጠርጋ የግዷን ፈገግ አለችና በቀኝ እጇ እጁን አጥብቃ ይዛው የእግር ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡

የወጡበትን ሙዝና ብርቱካን የሚገዙበት አትክልት ቤት ሊደረሱ ሲሉ ግን ያልጠበቀችውን ነገር አድርጎ አስደነገጣት፡፡

ልጇ በሚቆራረጥና በሚንቀጠቀጥ ድምጹ ጮክ ብሎ

"እልልልልልል !" አለ፡፡

‹‹እንዴ ማኪዬ… ምንድነው?›› አለች እየሳቀች፡፡

በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ትኩረታቸው ልጇ ላይ ነው፡፡

‹‹እልል ማለት እየተለማመድኩ ነው ማሚ›› በኩራት መለሰላት፡፡

‹‹ለም…ን…?›› ግራ በመጋባት ጠየቀችው፡፡

‹‹እህቴን ወይ ወንድሜን ስትወልጂልኝ ስለተወለዱ ደስ እንዳለኝ እልል ብዬ ላሳያቸው እፈልጋለሁ…›› አለ የገፋ ሆዷን በትንሽ አመልካች ጣቱ እየጠቆመ፡፡

የምትለው ነገር ጠፍቷት በድንዛዜ ታየው ጀመረች፡፡

‹‹ምነው ማሚ..ወንድ እልል አይልም ስላልሽኝ ደበረሽ እንዴ?…›› አለ ሽቅብ እያያት፡፡

‹‹አይደለም ልጄ…ጥሩ ነው…ተለማመድ…ጥሩ ነው›› አለች አሁንም ያለ እቅድ የፈሰሰ እንባዋን በአንገት ልብሷ እየጠረገች፡፡

♾♾♾♾♾♾♾♾

✍️ሕይወት እምሻው

14/01/2026

🧘 #ግዴለሽ ሁን፦ የውስጥ ሰላምህን የምታገኝበት ጥበብ! ✨

"ለሁሉም ነገር ግድ የሚሰጥህ ከሆነ፣ ለሰላምህ የሚሆን ቦታ አይኖርህም!"

ዛሬ የምነግራችሁ ስለ "ግዴለሽነት" ነው። ግዴለሽነት ሲባል ዝም ብሎ መዝረክረክ ሳይሆን፣ አላስፈላጊ ጫጫታዎችን ችላ የማለት ብቃት ነው። ብዙዎቻችን የምንደክመው በሥራ ብዛት ሳይሆን፣ ለማይገባቸው ነገሮች በምንሰጠው ከልክ ያለፈ "ግድ" (Concern) ነው።

እውነተኛ ነፃነት እንዲሰማህ በነዚህ 3 ነገሮች ላይ ግዴለሽ መሆን ጀምር፦

1. ለሰዎች አሉታዊ አስተያየት ግዴለሽ ሁን! 🗣️

ሰዎች ስለ አንተ የሚናገሩት ነገር የእነርሱ ማንነት እንጂ የአንተ ዕውነት አይደለም። የሁሉንም ሰው ምላሽ ለማስተካከል ከሞከርክ የራስህን ጉዞ ትረሳለህ። እነርሱ ይበሉ፤ አንተ ግን መንገድህን ቀጥል።

2. በማትቆጣጠራቸው ነገሮች ላይ ግዴለሽ ሁን! 🌦️

የሰዎች ጠባይ፣ የአገሪቱ ሁኔታ፣ ወይም ትላንት የሆነው ስህተት በአንተ ቁጥጥር ስር አይደሉም። በማትቆጣጠረው ነገር ላይ መጨነቅ ኃይልህን በከንቱ መበተን ነው። ትኩረትህን በአንተ እጅ ባለው "ዛሬ" ላይ ብቻ አድርግ።

3. ለጊዜያዊ መሰናክሎች ግዴለሽ ሁን! 🚧

ትልቅ ራዕይ ያለው ሰው መንገድ ላይ ለሚጮሁ ውሾች ሁሉ ድንጋይ አይወረውርም። ትናንሽ እንቅፋቶች ሲገጥሙህ እንደ ትልቅ ተራራ አትመልከታቸው። "ይህም ያልፋል" በማለት በፈገግታ እለፋቸው።

‎ #የሚወዳቹን ነፍስ ችላ አትበሉ!‎‎እኛ ሰዎች እንግዳ የሆነ ልማድ አለን ግራ ለሚያጋቡን፣ የሚርቁንን እና ዓለምን ፈገግ ብለን ለማየት ብቻ እድል ለሚሰጡን ሰዎች ትኩረት እንሰጣለን። ምናል...
02/11/2025

‎ #የሚወዳቹን ነፍስ ችላ አትበሉ!

‎እኛ ሰዎች እንግዳ የሆነ ልማድ አለን ግራ ለሚያጋቡን፣ የሚርቁንን እና ዓለምን ፈገግ ብለን ለማየት ብቻ እድል ለሚሰጡን ሰዎች ትኩረት እንሰጣለን። ምናልባት ኩራት ሊሆን ይችላል። ምናልባት ፍርሃት ሊሆን ይችላል።

‎ጀርባችንን ብንሰጥም እንኳ ፍቅር ቦታ ባልሰጠናቸው ሰዎች ዘንድ ሁልጊዜ እንደሚቆይ እምነት ሊሆን ይችላል። አንድ ሰው በእውነት ሲወደን፣ የራሱን ክፍሎች ይሰጠናል። ጊዜ፣ ጉልበት፣ ትዕግስት፣ ታማኝነትን ለኛ ያስገዛል። ስማችንን በልቡ ውስጥ በደማቅ ቀለም ይጽፋል። ጉድለቶቻችንን ያያል እናም ሽፍን አድርጎ ይቆያል። ዓለም ሲያጨበጭብልን ብቻ ሳይሆን ስንደክም፣ ስንጠፋ፣ ራሳችንን ስንጠራጠር ወይም ዋጋ ቢስነት ሲሰማን አብሮን ነው።

‎እንዲህ አይነትን ነፍስ ችላ ማለት አንድን ሰው ማጣት ብቻ አይደለም በህይወት ውስጥ አንድ ጊዜ የሚመጣን ቅንነት ማጣት ነው።

‎እውነተኛ ፍቅር ብርቅ መሆኑን የምንገነዘብበት ጊዜ ይመጣል። ምናልባት ብዙ ሰዎች ባሉበት አለም በዝምታ፣ ምናልባትም ባዶ ክፍል ውስጥ ስንገኝ እውነተኛ ፍቅር ብርቅ መሆኑን እገነዘባለን። ዓለም በፈጣን ግንኙነቶች፣ ጊዜያዊ ሰዎች እና ጥልቀት በሌላቸው አባሪዎች የተሞላች ናት። ፍቅር ሁሉም ሰው አይሰጠውም፣ ሁሉም ሰው በጥልቅ አይሰማውም።

‎በእውነት የሚወድ ሰው፡ እርሱ በማዕበል ውስጥ መልህቅ፣ ቀናት ግራጫ ሲሆኑ ብርሃን፣ እንደ ተራ ሰው ተደብቆ ግን ጸጥ ያለ ተአምር ነው።

‎ዝምታው ከመኖሩ በላይ እስኪሰማ ድረስ አትጠብቁ።
‎መኖሩ ታማኝነቱን ሊያሳያቹ የሞከረውን ያህል እስኪያስተምራቹ ድረስ አትጠብቁ። የእውነት የሚወደን ሰው ፍቅሩ ስለማያልቅ አይሄድም ስለማናየው ግን ይሄዳል።

‎በእውነት የሚያስብላቹ ሰው በማግኘታቹ እድለኛ ከሆናቹ አዳምጡት፣ አድንቁት፣ ምላሽ ስጡት፣ ዋጋ ስጡት። ለእነሱ ዕዳ ስላለባቹ አይደለም ፍቅር እውቅና ሊሰጠው ስለሚገባ፣ ልቦች ማለቂያ በሌለው ቸልተኝነት ለመጽናት የተገነቡ ስላይደሉ።

‎የሚወዳቹን ነፍስ ችላ አትበሉ!
‎ችላ ያላቹትን ፍቅር ምትራቡበት ቀን ይመጣልና።

‎©️ሶሪት

Follow me Amare Lucky

ሁለት አይነት እረፍቶችአንደኛው የአካል እረፍት ሲሆን፣ ሁለተኛው የአእምሮ እረፍት ነው፡፡የአካል እረፍት ማለት ከአንዳንድ ስራዎች በመታቀብ፣ በመተኛት ወይም ቁጭ በማለት ማረፍ ማለት ነው፡፡ ...
02/11/2025

ሁለት አይነት እረፍቶች

አንደኛው የአካል እረፍት ሲሆን፣ ሁለተኛው የአእምሮ እረፍት ነው፡፡

የአካል እረፍት ማለት ከአንዳንድ ስራዎች በመታቀብ፣ በመተኛት ወይም ቁጭ በማለት ማረፍ ማለት ነው፡፡ ይህንን ማድረጋችን ሰውነታችን ራስን በመጠገን እንደገና ጉልበትን ለማግኘት እንዲችል ያግዘዋል፡፡

የአእምሮ እረፍት ማለት አእምሯችንን ከባባድ ሃሳቦችን ከሚጠይቅ ስራ ማሳረፍ፣ በማሕበራዊ ሚዲያዎች ከሚጎርፉ ሃሳቦች መጠበቅና አሉታዊና አስጨናቂ ሃሳቦችን በመግታት ማሳረፍ ማለት ነው፡፡ ይህንን በማድረጋችን በቂ እንቅልፍ ማግኘት፣ ትኩረትን ማደስና መረጋጋት ይሆንልናል፡፡

ከእዚህ ከሁለቱ የእረፍት አይነቶች አንዱ ሲጓደል ራሳችንን ለዝለት አናጋልጣለን፡፡

ዛሬ ምንም እንኳን ስራ ስለሌላችሁ አካላችሁ ቢያርፍም፣ አእምሯችሁ ካላረፈ ከዝለት አታመልጡም፡፡

ይህንን ሁኔታ በቶሎ ካላረማችሁት ደግሞ፣ ማታ በቶሎ መተኛት አለቻል፣ ሌሊት በድንገት መንቃትና እንደገና ለመተኛት መታገል፣ የመኖርና የመስራት ፍላጎትን ማጣት፣ ቀድሞ የሚያስደስታችሁን ነገር አለመፈለግና መሰል ሁኔታዎች ምልክቶቹ ናቸው፡፡

የመፍትሄ ጉዞ ለመጀመር

1. ጸሎት ማድረግና በፈጣሪ መደገፍ

2. መቆጣጠር በምንችላቸውና በማንችላቸው ሁታዎች መለየት

3. መቆጣጠር በምንችላቸው ነገሮች ላይ አቅምን ያገናዘበ እቅድ ማውጣት

4. መቆጣጠር የማንችላቸውን ነገሮች ሆን ብሎ መልቀቅ

5. የምናያቸውንና የምናነባቸውን ነገሮች በመምረጥ ጥሩ ጥሩ ነገሮች ላይ ማተኮር፡፡

መልካም የእረፍት ቀን ይሁንላችሁ፡፡

Dr. Eyob

Follow me Amare Lucky

አይፋታሽም!⚠️⚠️💎💎ረጅም ርቀት ሸክም ተሸክሞ የሚጓዝ ሰው ላይደክመ አይችልም። መወገድ የሚኖርበት አላስፈላጊ እቃ ቤት ቢቀመጥ ቦታ መያዙ አይቀርም። በውስጥሽ የሚመላለሰው ያልፈፀምሽው ሃሳብ...
01/11/2025

አይፋታሽም!
⚠️⚠️💎💎
ረጅም ርቀት ሸክም ተሸክሞ የሚጓዝ ሰው ላይደክመ አይችልም። መወገድ የሚኖርበት አላስፈላጊ እቃ ቤት ቢቀመጥ ቦታ መያዙ አይቀርም። በውስጥሽ የሚመላለሰው ያልፈፀምሽው ሃሳብም ላያስጨንቅሽ አይችልም። ያልተናገርሽው ብሶት እየበላሽ ይቀመጣል፤ ያልገፅሽው ፍላጎት በሔድሽበት እየተከተለ ያስጨንቅሻል፤ ያልወሰንሽው ውሳኔ ዋጋ እያስከፈለሽ ይቀጥላል። አንድን ነገር ወስነሽ እስካላደረግሽው፣ እርምጃ እስካልወሰድሽበት ድረስ ሸክምነቱን ማስቀረት አትችይም። መስተካካል የሚችሉ ብዙ ችጎግሮች ቢኖሩበሽ ለማስተካከል ምንም የማታደርጊ ከሆነ ሃሳባቸው ብቻውን ሌላ ችግር ይሆንብሻል። እራስ ምታት ላይ ሌላ እራስ ምታት የሚጨምረው እራሱ ባለቤቱ ነው። የሰው ልጅ በአንዴ ስለአንድ ጉዳይ ሁለት በተለያዩ ሁኔታ ውስጥ ተገኝቶ ሊጨነቅ አይችልም። ነገር ግን አንድ ሃሳብ ተሸክሞ ሃሳቡን ባለመኖሩ በሚያጣው ነገርና ስለሃሳቡ አለመተግበር ደጋግሞ በመጨነቁ በአንድ ጉዳይ ሁለቴ ይጎዳል።

አዎ! ጀግኒት..! አይፋታሽም! ፍቅርሽን ካልገለፅሽ ከጭንቅላትሽ አይወጣም፤ ችግርሽን በድፍረት ካልተጋፈጥሽ የዘወትር ጭንቀትሽ መሆኑ አይቀርም፤ መራመድ አስበሽ ካልተራመድሽ ወኔሽ እየወረደ፣ ብርታት እያጣሽ ትመጪያለሽ። ብርታት የሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ በርታ በይ፤ ድፍረት በሚያስፈልጋቸው ነገሮች ላይ ደፋር ሁኚ። ጥንካሬሽን ስትፈልጊው አትጪው፤ ጥበብና ማስተዋል፣ ብለሃትና ብስለት ወሳኝ በሆኑበት ስፍራ በሚገባ ከመጠቀም ወደኋላ አትበይ። ደፋርና ጪስ መውጫ አያጣምና የሚያሳስብሽን ጉዳይ በድፍረት ለመከወን ተዘጋጂ። ዛሬ ነገ በማለት የሚተርፍሽ የሃሳብ ሸክምና ጭንቀት እንደሆነ አስተውይ። ቆረጥ ያለ ውሳኔ፤ በግልፅ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ፣ በየዘርፉ የሚወሰዱ እርምጃዎች ያስፈልጉሻል። ሃሳቦችሽ አልፋታ ቢሉሽ አንቺ እርምጃ ወስደሽባቸው፣ በዙሪያቸው ተንቀሳቅሰሽ እርምጃ ወሰደሽ ተፋቺያቸው።

አዎ! ጀግናዬ..! አንድ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ የምታስበውና ውስጥህ የተቀበለውን ነገር እስካላደረከው ድረስ የእንቅልፍህ ጠላት መሆኑ አይቀሬ ነው። አስገራሚ ሃሳብ ያለው ሳይሆን ሃሳቡን የሚኖር ሰው በጠፋበት ዘመን ጨክኖ ሃሳቡን ለመኖር፣ ሸክሙን ለማራገፍ፣ ወደፊት ለመጓዝ፣ ከግቡ ለመድረስ የሚፍጨረጨር ሰው እራሱንም ሆነ ሃሳቡን ነፃ ያወጣል፤ የተረጋጋ ህይወትን ይጎናፀፋል፤ በህልሙ አለም ታሪኩን ይፅፋል። ከሃሳብ ድገግሞሽ በላይ የተወሰነ ተግባር እፎይታን ይሰጣል፤ ወደ ሰላም ይመራል፤ ለውጤት ያበቃል። ሚዛን ለደፉ፣ ፋታ ለነሱህ፣ ሸክም ለሆኑብህ ጠቃሚ ሃሳቦች ቅድመተከተል ስጥ፤ በየደረጃው ወደተግባር እያስጠጋህ፣ ለክንውን እያበቃህ ከመፋታትም በላይ አትርፍባቸው፣ ከመገላገልም በተሻለ ተጠቀምባቸው።

✍️ (Epha A.)

Follow me Amare Lucky

for better tomorrow! | ለተሻለ ነገ! Vision: Creating a better environment and life understanding for others. Content Genre: Inspiring thoughts, counsel, motivational speech's, life reflections by Ephrem Aschalew. Check back for my videos that are posted on the topics of motivation, wisdom, r...

Address

At Home
Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Am La Bi posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category