20/08/2026
የላሊበላ ጥናት፣ ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ኩባንያ የዳይሬክተሮች ቦርድ የመጀመሪያ ጉባኤ በስኬት ተጠናቀቀ!
የላሊበላ ጥናት፣ ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ኩባንያ የዳይሬክተሮች ቦርድ የመጀመሪያ ጉባኤውን የቦርዱ ሰብሳቢና አባላት፣ እንዲሁም የኩባንያው ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበት በስኬት አካሂዶ አጠናቋል።
የጉባኤው ዋና ዋና ውሳኔዎች
✔️ የቦርድ አባላት ትውውቅ ተከናውኗል፣ የቦርዱ መደበኛ የመሰብሰቢያ ጊዜ ተወስኖ የቦርዱ የሥራ ሂደት ግልጽ እንዲሆን ተደርጓል።
✔️በጉባኤው የኩባንያውን የ2018 ዓ.ም. ግማሽ በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀምና የፋይናስ ሪፖርት በጥልቀት ገምግሞ አጽድቋል።
🎤 በግምገማውም የተመዘገቡ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ተነስተው ተመክሮባቸዋል።
✔️የ2019 ዓ.ም. የተዘጋጁት የበጀት፣ የፕሮጀክትና የካፒታል ማሳደጊያ ዕቅዶች በጥልቀት ተገምግመው የፀደቁ ሲሆን፣ የኩባንያውን የወደፊት ዕድገት፣ተወዳዳሪነትና ውጤታማነት ለማሳደግ በሚያስችሉ ስትራቴጅ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል።
✔️የቦርድ–ማኔጅመንት ትብብርን፣ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን በማጠናከር የኩባንያውን ተቋማዊ አቅም የበለጠ ለማሳደግ የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ የቦርድ አባላትና የኩባንያው ኃላፊዎች የኩባንያውን ዕድገት፣ ውጤታማነትና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት፣ በተቀናጀ አመራርና በትብብር ለመስራት የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል። በተለይም የኩባንያውን የገበያ ድርሻ ማሳደግ፣ ሙያዊ የአገልግሎት ጥራትን ማሻሻል፣ የደንበኞችን እምነት ማጠናከር እና የኩባንያውን ተወዳዳሪነት በቀጣይነት ማሳደግ የቀጣይ የስራ ዘመን ትኩረት እንዲሆኑ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ይህ የመጀመሪያው የዳይሬክተሮች ቦርድ ጉባኤ ኩባንያው ባለፉት ዓመታት ያስመዘገባቸውን መልካም ውጤቶች በማጠናከር፣ ያሉትን ዕድሎች በመጠቀም እና ለቀጣይ የስራ ዘመን የተሻለ ዕድገት የሚያስገኝ ጠንካራ የሥራ መሠረት በማስቀመጥ ረገድ ታሪካዊና ወሳኝ መድረክ ሆኖ በስኬት ተጠናቋል።