16/09/2026
የባህርዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሰራተኞች ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ
=========
መስከረም 06/2019 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) — የባህርዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሰራተኞች በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ እንዳይርቁ በማሰብ 1,800 ደብተሮችና 500 እስክርቢቶዎችን ድጋፍ አደረጉ።
ድጋፉ የተደረገው ከኮሌጁ ሰራተኞች በተሰበሰበ ገንዘብ ሲሆን፣ የትምህርት ቁሳቁሶቹም ለአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስረክበዋል።
ድጋፉን የተቀበሉት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ መኳንት አደመ፣ የኮሌጁ ሰራተኞች በራሳቸው ተነሳሽነት ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። ተማሪዎች በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ሳቢያ ከትምህርት ገበታ እንዳይርቁ የሚደረጉ ተግባራት ትልቅ ማህበራዊ አስተዋፅኦ እንዳላቸውም ገልጸዋል።
ድጋፉን ያስረከቡት የባህርዳር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ ሙሉቀን አሰፋ በበኩላቸው፣ የኮሌጁ ሰራተኞች በየዓመቱ ተመሳሳይ የበጎ አድራጎት ተግባራትን ማከናወናቸውን ገልጸዋል።
በዚህ ዓመትም አንድም ተማሪ በትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ከትምህርት እንዳይርቅ በማሰብ ሰራተኞቹ በጋራ ድጋፍ ማድረጋቸውን የገለጹት ዲኑ ለሰራተኞች የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።
በቀጣይም ተመሳሳይ የበጎ አድራጎትና የትምህርት ድጋፍ ተግባራትን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አቶ ሙሉቀን ገልጸዋል።
በአማራ ክልል አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ መርሃ ግብር በርካታ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ድርጅቶች፣ግለሰቦችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በስፋት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
5. በቲክቶክ ገፃችን bureau
KEMBANGTOTO memelopori enterprise situs toto 4D tertata rapi poling togel mudah akses melalui penyusun antarmuka terstruktur yang mempermudah pemantauan pilihan angka secara intuitif.