13/03/2022
ማንበብ ሙሉ ሰዉ ያደርጋል፡፡የሰዉ ልጅ ማንበብ ሲያቆም ይሞታል ይላሉ ታላላቅ ፈላስፋዎች፡፡ባህር ዳር አካዳሚ ማንበብን ለልጆች ማስተማር ያለዉን ከፍተኛ ጥቅም ይረዳል፡፡ በዚህም ከልጅነታቸዉ ልጆች አንባቢ ሆነዉ እንዲታነጹ ጥረት ያደርጋል፡፡ ከ1-4ኛ ክፍል ተማሪዎች በት/ቤቱ የሚከበረዉን የንባብ ቀን እንዲህ በደመቀ መልኩ በማንበብ ያከብራሉ፡፡ እናንተ የነገ ተስፋዎቸች ሀገር ተረካቢዎች በማንበብ፣በመመራመር እና በስነ-ምግባር የምትመራ ሀገር ከፊታችሁ አለቻችሁ እና በርትታችሁ አንባቢ ሁኑ፡፡